ዛሬ ከኢፌዴሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ ያስሚን ወሀብረቢ ጋር በምክር ቤታችንና በሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው መካከል ያለውን ተቋማዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርና የጋራ የትብብር መስኮችን ለማስፋት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ የትውውቅና የትብብር ውይይት አካሂደናል። በዚህ አጋጣሚም ለነበረን ገንቢና ፍሬያማ ውይይት በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትና በራሴ ስም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ከዚህ በተጨማሪም፣ በውይይቱ ላይ ለተገኙት ሚኒስትር ዴኤታዎችና የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አመራሮች ላደረጉት ንቁ ተሳትፎ፣ ላቀረቡት ገንቢ ምክረ ሐሳቦችና ከእኛ ጋር ላደረጉት ግልጽና ወዳጃዊ ውይይት ልዩ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። የዛሬው ውይይታችን በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር፣ ተቋማዊ የጋራ ግንዛቤን ለማስፋትና በትብብር ልንሠራባቸው የሚገቡ የጋራ የሥራ መስኮችን ለመለየት ያስቻለ አስፈላጊና ጠቃሚ መድረክ ነበር። በውይይታችን የተለዩትንና በቀጣይ በጋራ ለመፈጸም የተስማማንባቸውን አበይት የሥራ ጉዳዮች በተግባር ለማሳካት፣ ምክር ቤታችን ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር በቅርበትና በቅንጅት ለመሥራት ያለውን ጽኑ ፍላጎት በዚህ አጋጣሚ እንደገና ማረጋገጥ እፈልጋለሁ። ይህንንም ለማሳካት በተቀናጀ የአሠራር ሥርዓት፣ በቀጣይነት በሚደረግ የተቋማቱ የሥራ ግንኙነትና በጋራ ክትትል በመታገዝ በውይይታችን የተነሱትን ጉዳዮች ወደ ተጨባጭ ውጤት ለማሸጋገር እንደምንሠራ አረጋግጣለሁ። በተጨማሪም፣ በውይይታችን የተነሱትን ሐሳቦች፣ የተለዩትን የትብብር አቅጣጫዎችና የተጋራናቸውን የጋራ ግንዛቤዎች ወደ ተግባር ለመቀየር የምክር ቤታችን መላው አመራርና ባለሙያዎች ዝግጁ መሆናቸውንም በዚሁ አጋጣሚ አረጋግጣለሁ። በመጨረሻም፣ ለነበረን ጥሩና ፍሬያማ ውይይት፣ እንዲሁም ለተደረገልን ሞቅ ያለ አቀባበል፣ ለክብርት ሚኒስትሯና ለሁሉም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አመራሮችና ኃላፊዎች በድጋሚ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። የተከበሩ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ❇️❇️❇️❇️ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ስልክ፡ +251115514005 ፋክስ፡ + 251115517699 P. O. Box 517, ኢ.ሜይል: [email protected] ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber X- https://x.com/EthiopiaChamber ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber Youtube:https://www.youtube.com/@ethiopianchamber Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 2 h | 364 |
| 6 h | 560 |
| 9 h | 588 |
- After 6 hours560
- Total to date588








