Posts of የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች
( ያመስግን - ሰይጣን ) ኤልያስ ሽታኹን ሰው ሆኖ አያውቅምና የያዘው ሁሉ አልወደቀምና - እንደደመና ክብሩን ቢያጣ በትዕቢቱ ቢጣል : ወደኑሮ አልተወረወረምና እግዜርን ያመስግን ሰይጣን ! ሰው የሚሉት ፍጡር ስንቱን ቻለ? እንደደንገጡር መሰበረን ያስናቀ መሰበር ተሰብሮ ሞት ያስናቀ ቀብር ተቀብሮ : (ስንቱን ችሎ ኖሮ) ሰውነት ጥልቅ ሰውነት ብርቅ መቆም መሄድ መገኘት ወይ መቅረት ግራ ነው ሰውነት - ቀኝ ነው ሰውነት መሐል ነው ሰውነት ! በቅጽበት የሚለዋወጥ በሞት የታጀለ ሰው መሆንም ውስጥ - ሰው አለመሆን አለ ውል የለው - ወይም ደርዝ : መኖር ነው መድኃኒት መኖር ለሚባል መርዝ። ሩቅ ነው ሰውነት ቅርብ ነው ሰውነት : ማይደረሰበት - የሚደረሰበት! መቻሉ አጀብ ነው ምን ቢደክም ግና : ከነግሳንግሱ የሰው ልጅ ነው ግሩም - የሰው ልጅ ነው ጀግና ! ይሳነዋል መዳህ - አይችል ከራስ መብረር ሰይጣን ሰው ቢሆን ኖሮ - ራሱን ባጠፋ ነበር!
Open in Telegram"መርሻዬ" ዕድለኛ ሆነህ ጌታህን አጊንተህ : " ምን ላርግልህ? " ቢልህ አደራ እንዳትስት ብዙ ነገር ጠቅሰህ ካንተ የተነሳ : "ጌታ በቂዬ ነህ" ብለህ ባልክ ቅጽበት የምትፈለገውን ስለምተረሳ! (ኤልያስ ሽታኹን)
Open in Telegram"በደረቷ የምትሳብ ርግብ" ( ኤልያስ ሽታኹን ) ከማይሆን ተወዳጅታ ያቺ ወፍ ክንፎቿን ትታ ልክ እንደርሱ ትሆን ያዘች እግሯም ተጎመደ መሬት መሳብ እጣው እባብ የወደደ ። ሲድህ ትድሀለች ሲሳብ ትሳባለች "እሽሽ" ቢሉ አትበርም ክንፏን ረስታለች:: ለትናንቷ ግድ የላትም የለሚታዘብ ለሚያያት : እርሷ ለፍቅር ስትል በደረቷ የምታሳብ ርግብ ናት! ከጉድጓድ ጠልቃ ከጭቃ ተጨማልቃ ከወደደችው ጋ ትቦ ወድቃ አፈር አክብራ - ህዋውን ንቃ ካፈቀረችበት ከወረደችለት አትታገሉ ልትመልሷት... : ለእርሷ ጠላት ናችሁ ክንፏን ብታስታውሷት።
Open in Telegram(ግጥም እግዜር ይስጠው) አልያስ ሽታኹን ልክ መሆን - ደክሞኝ ጤና መሆን - አሞኝ ጨርቄን መጣል ባፍር ለክብር ለስሜ : በጥበብ በውበት ቀስ ብዬ አበድኩ ዕድሜ ለግጥሜ ። አልፎ አልፎ ቀወስ ክብሬን ማፈራረስ መናድ ልምምዴን መቀየር መንገዴን ረስቼ Ego ግብሬን ሳልጠብቅ መስመሬን የህይወት ብቅሸት መስደብ ሲከጅለኝ : ( ወፈፍ ነው በቃ ) ግጥም እግዜር ይስጠው የማይታዘበኝ።
Open in TelegramCbe :- አንድሺ - 1318 - ሰላሳ ሶስት -249 Tele birr :- 0923246010 በአንድ ሺ ብር ብቻ ይማሩ! የከፈሉበትን በዚሁ ቁጥር ቴሌግራም ከሙሉ ስም ጋር ይላኩልን።
Open in Telegramከብዙ ብዙ ነገር በኋላ ከአመታት በኋላም ስታገኙት በመሳቀቅ : " አወቅከኝ ግን ? " ተብሎ የማይጠየቅ ... የሚያውቃችሁ : የሚያውቅላችሁ! ✨ ኢየሱስ ክርስቶስ ! (ኤልያስ ሽታሁን)
Open in Telegram