Posts of DW Amharic
የዕለተ ረቡዕ ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም. የስርጭት ማስታወቂያ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የትግራይ ኃይሎች ባድሜ አቅራቢያ በሚገኘው ገመሃሎ ከባድ ውጊያ ማካሄዳቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። ይህን እና ሌሎች የዓለምአቀፍ ዋና ዋና ዜና ካሰማን በኋላ በዕለቱ ዜና መጽሔታችን አራት ርዕሰ ጉዳዮችን በቅደም ተከተል እናስተነትናለን። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ለሱዳናዉያን ተፋላሚዎች ያቀረቡት የተነጋገሩ ጥሪ እና አንድምታው ፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በድንበር አካባቢ ከባድ የእግረኛ ዉጊያ እያካሄደ መሆኑን ነዋሪዎች መናገራቸው ፣ በአፋር እና የሶማሌ ኢሳ ጎሳ መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት አለመቆሙ አሳስቧል መባሉ እና በትግራይ ክልል ተራ ግድያ እና ጥቃት በነዋሪው ዘንድ ብርቱ ስጋት መደቀኑን የተመለከቱ ዘገባዎች ይቀርባሉ። ሳምንታዊዎቹ ከኤኮኖሚው ዓለም ዝግጅታችን የውጭ ባንኮች “በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ” የኢትዮጵያ ባንኮችን ለመግዛት ማሟላት ስለሚገባቸው ከብዙ በጥቂቱ ይዳስሳል። የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዝግጅታችን የማይክሮሶፍት የአገልግሎት መቋረጥ ለአፍሪካ የማንቂያ ደወል? ይሆን ሲል ይጠይቃል። ጠብቁን!
Open in Telegramለዓመታት በግጦሽ ሳር፣ በውሃ እና በመሬት ይገባኛል ምክንያት ሲከሰት የቆየው የአፋር እና የሶማሌ ኢሳ ማህበረሰቦች ግጭት፣ አሁን ከቀን ወደ ሌሊት በተሸጋገረ ከባድ ውጊያ መቀጠሉ የአካባቢውን ነዋሪዎች ለከፋ ስጋት ዳርጓል። ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት የፌደራል መንግስት እና የሀገር ሽማግሌዎች ያደረጓቸው የእርቅ ስምምነቶች ዘላቂ ባለመሆናቸው፣ የአካባቢው ሰላም ተደጋግሞ እየተናጋ እና ዜጎች ለመፈናቀል እየተዳረጉ መሆናቸውን ነዋሪዎች ይገልጻሉ።ዳግም አገርሽቶ አንድ ወር እንዳስቆጠረ የሚነገረው የአፋር የሶማሌ ኢሳ ጎሳ የድንበር ግጭት ከዚህ ቀደም ከነበረበት የአፋር ክልል ዞን 3 ሀሩካ፣ አቢዳ እና አርጋቶ የድንበር አካባቢ አሁን ደግሞ ወደ ዞን 1 ገርቢ አካባቢ ከትላንት ሰኞ ጀምሮ መቀጠሉን ነው የአካባቢው ነዋሪዎች የሚገልጹት። ዝርዝሩን ከሬዲዮ ዝግጅታችን ከአንድ ሰዓት በኋላ ተከታተሉ።
Open in Telegramየሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል RSF ማክሰኞ ለሊት በብሉ ናይል ግዛት በፈጸመው የድሮን ጥቃት 19 ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ 20 ቆሰሉ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል RSF ማክሰኞ ለሊት በብሉ ናይል ግዛት በፈጸመው የድሮን ጥቃት 19 ሰላማዊ ሰዎችን ሲገደሉ ሌሎች 20 ደግሞ መቁሰላቸውን የሱዳን የሰብዓዊ መብቶች ቡድን የአስቸኳይ ጊዜ ጠበቆች አስታወቁ። በግዛቲቱ ሁለት ከተሞች የድሮን ጥቃቶች መድረሳቸውን ነዋሪዎችም ለሮይተርስ አረጋግጠዋል። «የሱዳን የአስቸኳይ ጊዜ ጠበቆች ቡድን» በፌስቡክ ባወጣው መግለጫ ማክሰኞ ለሊት በግዛቲቱ ዋና ከተማ በዳማዚን ሦስት የመኖሪያ ሰፈሮች ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ስድስት ሴቶችን ጨምሮ 19 ሰዎች ተገድለዋል ። ከሟቾቹና ከቆሰሉት 15ቱ የሦስት ቤተሰብ አባላት ናቸው። ጥቃቶቹ በተለይ ደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያን በሚያዋሰኑት በመላ ብሉ ናይል ግዛት የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ሊያስታጉሉና ብሔራዊውን የኤሌክትሪክ ኃይል መረብም ሊጎዳ እንደሚችልም ቡድኑ አስጠንቅቋል። ምስል፤ የዩክሬይን የረዥም ርቀት ድሮን
Open in Telegramየደቡብ አፍሪቃ ፍርድ ቤት በፕሬዚዳንት ራማፎዛ ላይ የቀረበውን ክስ ውድቅ አደረገ በገንዘብ ማጭበርበር ክስ የተመሰረተባቸው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ ዛሬ ከፊል ስኬት ተጎናፀፉ። ክሱን የተመለከተው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ራማፎዛ በገንዘን ማጭበርበር ወንጀል ለመሳተፋቸው በማስረጃነት የቀረበውን ሰነድ ስህተት አለበት ሲል ውድቅ አድርጓል። እጎአ በ2020 ራማፎዛ የገቢ ግብር ህግን እና የውጭ ምንዛሪ ቁጥጥር ደንቦችን በመጣስ ተወንጅለው ነበር። ከዚህም በተጨማሪ በራማፎዛ የግል የከብት እርባታ በተፈጸመ ዘረፋ ፍራሽ ውስጥ የተደበቀ ግማሽ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተዘርፏል። ራማፎዛ ዘረፋውን ለፖሊስ ቢያመለክቱም ስለተሰረቀው ጥሬ ገንዘብ ግን ለፖሊስ አላሳወቁም ነበር። ራማፎዛ ኋላ ላይ ገንዘቡ የተገኘው ለአንድ የደቡብ ሱዳን ነጋዴ ከተደረገ የከብት ሽያጭ እንደሆነ አብራርተዋል። ሆኖም ግን፣ ከብቶቹ እርባታ ቦታው መቆየታቸው ጥያቄ አስነስቷል። ይህ ክስተት ራማፎዛን እጎአ 2022 ስልጣን ሊያሳጣቸው ደርሶ ነበር። ይሁንና ፓርላማው በራማፎሳ ላይ ስልጣን እንዲለቁ የሚያደርገው የክስ ሂደት እንዳይደረግ ወስኗል። ያኔም ራማፎዛ ማስረጃው እንዲመረመርላቸው ፍርድ ቤትን ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱ እጎአ በ 2023 እና በ2024 እንዲሁም ግንቦት 2026 የቀረቡባቸውን ክሶች በሙሉ ውድቅ አድርጓል። ተቃዋሚዎቻቸው ግን ራማፎዛ ስልጣን እንዲወርዱ እና ይግባኝ ሲያስገቡ ቆይተዋል።
Open in Telegramሦስት የአፍሪቃ ሀገራትን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ፍራንክ-ቫልተር ሽታይንማየር ዛሬ ጠዋት የመጨረሻዋ የሚጎበኟት ሀገር የሆነችው ኬንያ ገብተዋል። ናይሮቢ ሲደርሱም የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አቀባበል አድርገዉላቸዋል። ሽታይንማየር ናይሮቢ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትን ይጎበኛሉ፤ ከሁለቱም ሀገራት የንግድ ዘርፍ ቡድኖች እና ልዑካን ጋርም ይገናኛሉ ተብሎ እቅድ ተይዟል። ጀርመን በጎርጎረሳዉያኑ 2025 ከአፍሪቃ ጋር ያደረገችዉ የንግድ ልውውጥ በ 10.5 በመቶ አድጎ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ተነግሯል። ከአፍሪቃ ጋር ያለውን የንግድ ትስስር ማጠናከር እንደሚገባ ሰሞኑን ያሳሰቡት ሽታይንማየር ከኬንያ በፊት ጋናን እና አይቮሪ ኮስትን ጎብኝተዋል።
Open in Telegramበየዓመቱ በጎርጎሮሲያኑ ህዳር 25 ቀን በሴቶች ላይ የሚፈጸምን ጥቃት ለማስቆም የሚደረገው ዘመቻ ይታወሳል። ይህ ዓለም አቀፍ ቀን Orange Day ወይም „ብርቱካናማ ቀን “ ይባላል። የብርቱካናማው ቀለም በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት የሌለበትን የወደፊት ጊዜ ለማመልከት የታሰበ ነው። ይህ ቀን ሲታወስ 45 ዓመታት ገደማ ሆኖታል። ይሁንና ዘንድሮ ይህንን ቀን አስታኮ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያወጣው መግለጫ እንደሚጠቁመው በየሰዓቱ አምስት ሴቶች በቤተሰብ አባላት ወይም በፍቅረኞቻቸዉ ይገደላሉ። ትናንት ይፋ የሆነው የድርጅቱ መግለጫ 47,000 የሚጠጉ ሴቶችና ልጃገረዶች ባለፈው የጎርጎሮሲያኑ 2025 በአጋሮቻቸው ወይም በቤተሰብ አባሎቻቸው ተገድለዋል ይላል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ከ122 ሀገራት የተሰባሰበ ሲሆን፤ ከፍተኛው ቁጥር (22,100) ግድያ የተመዘገበው አፍሪቃ ዉስጥ ነው። በመቀጠል እስያ 15,100 ተጠቂዎች ነበሯት። በሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ 7,400 በአውሮፓ ደግሞ 2,100። ይህን አኸዝ ስትሰሙ ምን ተሰማችሁ? በሴቶች ላይ የሚፈጸምን ጥቃት እንዴት ማስቆም ይቻላል? የእያንዳንዳችንስ ሚና ምን መሆን አለበት?
Open in Telegram