Account

Posts of Dn Abel Kassahun Mekuria

newest first

#2055Text
Views3,250−51%vs avg
Forwards—
Reactions178
Comments—
#2054Text
Views4,130−38%vs avg
Forwards—
Reactions264
Comments—
#2052Photo

አንዳንድ ሰዎች “እርሱን እኮ ቤተ ክርስቲያን ነበር ያገኘኁት። እንዴት እንደዚህ ዓይነት ሰው ይሆናል ብዬ ልገምት?“ ብለው ስለ እጮኛቸው ወይም የትዳር አጋራቸው ሲያማርሩ ይሰማል። እነዚህ ሰዎች የዘነጉት ቤተ ክርስቲያን የሕሙማን መታከሚያ ሆስፒታል መሆኗን ጭምር ነው። ልክ አንድ ታማሚን ሐኪም ቤት መሄዱ ብቻ ከበሽታው እንደማያድነው፣ አንድንም ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን መምጣቱ ብቻ ጤናማ አያሰኘውም። በአግባቡ የማይማር፣ ንስሐ የማይገባ እና ምሥጢራትን የማይፈጽም ከሆነ በቤተ ክርስቲያን አጸድ መገኘቱ ብቻ ጥሩ ክርስቲያንነቱን አያረጋግጥም። እኅቴ፣ ቅድሚያ ሐኪም ቤት መመላለሱን ብቻ ሳይሆን ሕክምናውን በአግባቡ የሚከታተል መሆኑን እርግጠኛ ሁኝ! ኢያውብር ለጌታው ለአብርሃም ልጅ ለይስሐቅ ርብቃን ሊያጫት ወደ እርሷ የሮጠው ፣ ወደ ጉድጓድ እንስራዋን ይዛ ስትወርድ እና ያንንም ሞልታ ስትሄድ ስላያት ነው።(ዘፍ 24:16-17) የሕይወት ምንጭ ጉድጓድ ወደ ተባለች ቤተ ክርስቲያን እንስራዋን ሳትይዝ የመጣችን ሴት እያጨህ ምንጩን (ቤተ ክርስቲያንን) ለምን ትወቅሳለህ? የማትማር፣ የሰማችውንም ይዛ በተግባር ለመኖር የማትታገለዋን ሰነፍ ተሯሩጠህ ወደ ሕይወትህ አስገብተህ ስትጨርስ “አይ የቤተ ክርስቲያን ሰው!” እያልህ እንዴት ታዛቢ ትሆናለህ? ወንድሜ ቅድሚያ ወደ ውኃው ጉድጓድ መውረዷን ብቻ ሳይሆን እንስራ መያዟን አረጋግጥ! ዲያቆን አቤል ካሣሁን [email protected] https://t.me/Dnabel

Open in Telegram
Views8,190+22%vs avg
Forwards—
Reactions283
Comments—
#2047Photo

ጥንት በአባቶቻችን ዘመን አስጨናቂ መከራ በተነሣ ጊዜ፣ ልመናን የሚያውቁ አባቶችና እናቶቻችን ራሳቸውን አዋርደው በፍጹም ንስሐ የፈጣሪያቸውን ምሕረት ደጅ ጠኑ። እርሱም ጩኸታቸውን ሰምቶ ዘንበል አለላቸው። መዓቱንም ከእነርሱ መልሶ በገጸ ምሕረቱ ጎበኛቸው። በቁጣው ቀን ተስፋ ያደረጉት ቸርነቱ አላሳፈራቸውም። ዛሬስ? ዛሬም የእኛ ንስሐ እንደ አባቶቻችን እውነተኛ ከሆነ፣ በፈጣሪያችን ቸርነት ላይ ያለን መተማመን ከቀደሙት እናቶቻችን ካላነሰ፣ አምላካችን እኛን ይቅር ለማለት የታመነ ነው። መድኃኔዓለም መለወጥ እንደሚስማማው ደካማ የሰው ልጅ አይደለም። ልክ በፀሐይና በመሬት መካከል ባለ ዑደት (ዙረት) ምክንያት፣ አንዱ የመሬት ክፍል ከፀሐይ ብርሃን ተቀብሎ ሲያበራ በሌላኛው በኩል ያለው ደግሞ በግርዶሽ እንደሚጨልም እንዲሁ፣ የእግዚአብሔር ብርሃን (ቸርነት፣ ምሕረቱ) ለአንዱ አብርቶ ለሌላው የሚጋረድ አይደለም። ለብርሃኑ የተዘጋጀና በኃጢአት ጉድፍ ያልታወረ ዓይነ ልቡና እስካለን ድረስ የምሕረቱ ነጸብራቅ ለዘወትር በእኛ ላይ እንዳበራ ነው። ብቻ ንስሐችን እንደ ቀደሙት እናቶቻችን፣ መመለሳችንም በቃልና በተግባር እንደ ተመለሱት እውነተኞቹ አባቶቻችን ይሁን! አቤቱ በየቀኑ እንደ በግ ለመታረድ የሚነዱ በአርሲ ያሉ ወገኖችህን አስብ!!! ዲያቆን አቤል ካሣሁን [email protected]

Open in Telegram
Views8,490+27%vs avg
Forwards—
Reactions173
Comments—
#2042Link preview

ሰው አያከብርህም? ሰው ሲሰድብህ ትናደዳለህ? የሚያዋርድ እና አንገት የሚያስደፋ ነገር ቢያደርግብህስ በቁጣ ትገነፍላለህ? ግን አንድ ጊዜ ቆም ብለህ እስኪ ራስህን ጠይቅ? ከአንተ በላይ አንተን የሰደበ፣ ከአንተ በላይ አንተን ያዋረደ እና አንገት የሚያስደፋ ነገር ያደረገብህ አለ? ከአንተ በላይ አንተነትህን ዋጋ ቢስ ያደረገ ማን ነው? አንተ አይደለህ? አንተው መልስ! ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚለው ለሰው ጠላቱ ማንም አይደለም፤ ራሱ ነው። የሕይወትን ዛፍ ቸል ብሎ ወደ እጸ በለስ የሚሮጠው፣ የብርሃኑን ልብሱን ጥሎ ቅጠል ማገልደም የሚያምረው፣ ከወንድሙ ጋር በሰላም ከመኖር ይልቅ ደሙን አፍስሶ ዚቅበዘበዝ መኖር የሚመርጠው ሰው ራሱ ነው። ሌላውን ከመውቀስህ በፊት መጀመሪያ አንተ ራስህን ታከብራለህ? በአንተ ዘንድ የአንተነትህ ዋጋው ስንት ነው? ከልብስ ይልቅ ሰውነትህን ከመብልስ በፊት ነፍስህን ታስቀድማለህ? አንተ ራስህን በክፋት እና በበደል እንዲህ እያጎሳቆልክ “ማንም አያከብረኝም” እንዴት ትላለህ? ዲያቆን አቤል ካሣሁን [email protected] https://t.me/Dnabel

Open in Telegram
Views9,100+36%vs avg
Forwards—
Reactions177
Comments—
#2040Photo
Views10,400+56%vs avg
Forwards—
Reactions175
Comments—
#2039Photo
Views10,100+51%vs avg
Forwards—
Reactions229
Comments—