Посты канала Dn Abel Kassahun Mekuria
በዚህ የነቢያት ጾም የተከለከሉ ምግቦች:- ❌ ቁጣ ❌ ቅናት ❌ ሐሜት ❌ በቀል ❌ ጥላቻ እነዚህ አደገኛ እና መርዛማ ምግቦች ወደ ሰውነትዎ እንዳይገባ በመከላከል ጾምዎን ይቀድሱ!!! (አስታውሱ: እነዚህ ምግቦች በፍስክም ጊዜ ጨርሶ የማይፈቀዱ ሲሆን፣ በጾም ወቅት ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ዋጋን ስለሚያሳጡ አጥብቀው ይከለከላሉ።) የበረከት ጾም ያድርግልን!!! ዲያቆን አቤል ካሣሁን
Открыть в Telegramበትሕትናው ልዕልናን ላገኘ፣ ለፍጥረታት ባለው ርኅራኄ የአምላክ እናትን ለሚመስል፣ የተቸገሩትን ፈጥኖ መርዳት ልማዱ ላደረገው፣ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ፣ ደግ እና ሰውን ወዳጅ ለሆነው መልአክ ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን። ቅዱሳን መላእክት በአንድ ኃጢአተኛ ወደ እግዚአብሔር መመለስ የሚደሰቱትን ያህል፣ ባልተመለሰው ኃጢአተኛ ደግሞ እንዲሁ ያዝናሉ። በአንዱ ኃጢአተኛ መመለስ የተሰማቸውን ደስታ ፈጣሪያቸውን በማመስገን እንደሚገልጹ፣ ባልተመለሰው ኃጥእ የተሰማቸውን ኃዘን ደግሞ አምላካቸውን "ማረው፣ ይቅር በለው" ብለው በመለመን ያሳያሉ። (ያዕ 5፥13) ቅዱስ ሚካኤል አሁን እንዴት እንደ ሆንን አይቶ ይዘንልን፣ አዝኖም ይለምንልን፣ ለምኖም ያስምረን!!! ዲያቆን አቤል ካሳሁን [email protected]
Открыть в Telegramአንዳንድ ሰዎች “እርሱን እኮ ቤተ ክርስቲያን ነበር ያገኘኁት። እንዴት እንደዚህ ዓይነት ሰው ይሆናል ብዬ ልገምት?“ ብለው ስለ እጮኛቸው ወይም የትዳር አጋራቸው ሲያማርሩ ይሰማል። እነዚህ ሰዎች የዘነጉት ቤተ ክርስቲያን የሕሙማን መታከሚያ ሆስፒታል መሆኗን ጭምር ነው። ልክ አንድ ታማሚን ሐኪም ቤት መሄዱ ብቻ ከበሽታው እንደማያድነው፣ አንድንም ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን መምጣቱ ብቻ ጤናማ አያሰኘውም። በአግባቡ የማይማር፣ ንስሐ የማይገባ እና ምሥጢራትን የማይፈጽም ከሆነ በቤተ ክርስቲያን አጸድ መገኘቱ ብቻ ጥሩ ክርስቲያንነቱን አያረጋግጥም። እኅቴ፣ ቅድሚያ ሐኪም ቤት መመላለሱን ብቻ ሳይሆን ሕክምናውን በአግባቡ የሚከታተል መሆኑን እርግጠኛ ሁኝ! ኢያውብር ለጌታው ለአብርሃም ልጅ ለይስሐቅ ርብቃን ሊያጫት ወደ እርሷ የሮጠው ፣ ወደ ጉድጓድ እንስራዋን ይዛ ስትወርድ እና ያንንም ሞልታ ስትሄድ ስላያት ነው።(ዘፍ 24:16-17) የሕይወት ምንጭ ጉድጓድ ወደ ተባለች ቤተ ክርስቲያን እንስራዋን ሳትይዝ የመጣችን ሴት እያጨህ ምንጩን (ቤተ ክርስቲያንን) ለምን ትወቅሳለህ? የማትማር፣ የሰማችውንም ይዛ በተግባር ለመኖር የማትታገለዋን ሰነፍ ተሯሩጠህ ወደ ሕይወትህ አስገብተህ ስትጨርስ “አይ የቤተ ክርስቲያን ሰው!” እያልህ እንዴት ታዛቢ ትሆናለህ? ወንድሜ ቅድሚያ ወደ ውኃው ጉድጓድ መውረዷን ብቻ ሳይሆን እንስራ መያዟን አረጋግጥ! ዲያቆን አቤል ካሣሁን [email protected] https://t.me/Dnabel
Открыть в Telegram“ኃይል የሌለውን ምንኛ ረዳኸው! ብርታት የሌለውን ክንድ ምንኛ አዳንኸው! ጥበብስ የሌለውን ምንኛ መከርኸው! ብዙ እውቀትንስ ምንኛ ገለጥህለት!“ ኢዮ 26:2-3
Открыть в Telegramጥንት በአባቶቻችን ዘመን አስጨናቂ መከራ በተነሣ ጊዜ፣ ልመናን የሚያውቁ አባቶችና እናቶቻችን ራሳቸውን አዋርደው በፍጹም ንስሐ የፈጣሪያቸውን ምሕረት ደጅ ጠኑ። እርሱም ጩኸታቸውን ሰምቶ ዘንበል አለላቸው። መዓቱንም ከእነርሱ መልሶ በገጸ ምሕረቱ ጎበኛቸው። በቁጣው ቀን ተስፋ ያደረጉት ቸርነቱ አላሳፈራቸውም። ዛሬስ? ዛሬም የእኛ ንስሐ እንደ አባቶቻችን እውነተኛ ከሆነ፣ በፈጣሪያችን ቸርነት ላይ ያለን መተማመን ከቀደሙት እናቶቻችን ካላነሰ፣ አምላካችን እኛን ይቅር ለማለት የታመነ ነው። መድኃኔዓለም መለወጥ እንደሚስማማው ደካማ የሰው ልጅ አይደለም። ልክ በፀሐይና በመሬት መካከል ባለ ዑደት (ዙረት) ምክንያት፣ አንዱ የመሬት ክፍል ከፀሐይ ብርሃን ተቀብሎ ሲያበራ በሌላኛው በኩል ያለው ደግሞ በግርዶሽ እንደሚጨልም እንዲሁ፣ የእግዚአብሔር ብርሃን (ቸርነት፣ ምሕረቱ) ለአንዱ አብርቶ ለሌላው የሚጋረድ አይደለም። ለብርሃኑ የተዘጋጀና በኃጢአት ጉድፍ ያልታወረ ዓይነ ልቡና እስካለን ድረስ የምሕረቱ ነጸብራቅ ለዘወትር በእኛ ላይ እንዳበራ ነው። ብቻ ንስሐችን እንደ ቀደሙት እናቶቻችን፣ መመለሳችንም በቃልና በተግባር እንደ ተመለሱት እውነተኞቹ አባቶቻችን ይሁን! አቤቱ በየቀኑ እንደ በግ ለመታረድ የሚነዱ በአርሲ ያሉ ወገኖችህን አስብ!!! ዲያቆን አቤል ካሣሁን [email protected]
Открыть в Telegram“በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ፡ በመዳንም ቀን ረዳሁህ፡ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው” 2ኛ ቆሮ 6:2 https://t.me/Dnabel
Открыть в Telegramቅዱስ ጳውሎስ መጽሐፍ ለ4ኛ ጊዜ ታትሟል። መጽሐፉን ፈልጋችሁ አጥታችሁት የነበራችሁ ሁሉ አሁን በየመጻሕፍት መደብሩ ታገኙታላችሁ። መልካም ንባብ! አምላከ ጳውሎስ ይታረቀን!
Открыть в Telegramሰው አያከብርህም? ሰው ሲሰድብህ ትናደዳለህ? የሚያዋርድ እና አንገት የሚያስደፋ ነገር ቢያደርግብህስ በቁጣ ትገነፍላለህ? ግን አንድ ጊዜ ቆም ብለህ እስኪ ራስህን ጠይቅ? ከአንተ በላይ አንተን የሰደበ፣ ከአንተ በላይ አንተን ያዋረደ እና አንገት የሚያስደፋ ነገር ያደረገብህ አለ? ከአንተ በላይ አንተነትህን ዋጋ ቢስ ያደረገ ማን ነው? አንተ አይደለህ? አንተው መልስ! ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚለው ለሰው ጠላቱ ማንም አይደለም፤ ራሱ ነው። የሕይወትን ዛፍ ቸል ብሎ ወደ እጸ በለስ የሚሮጠው፣ የብርሃኑን ልብሱን ጥሎ ቅጠል ማገልደም የሚያምረው፣ ከወንድሙ ጋር በሰላም ከመኖር ይልቅ ደሙን አፍስሶ ዚቅበዘበዝ መኖር የሚመርጠው ሰው ራሱ ነው። ሌላውን ከመውቀስህ በፊት መጀመሪያ አንተ ራስህን ታከብራለህ? በአንተ ዘንድ የአንተነትህ ዋጋው ስንት ነው? ከልብስ ይልቅ ሰውነትህን ከመብልስ በፊት ነፍስህን ታስቀድማለህ? አንተ ራስህን በክፋት እና በበደል እንዲህ እያጎሳቆልክ “ማንም አያከብረኝም” እንዴት ትላለህ? ዲያቆን አቤል ካሣሁን [email protected] https://t.me/Dnabel
Открыть в Telegramእግዚአብሔርም በአደባባይ የማይወቅሰን ፍቅር እንጂ እልህ እንዳያሸንፈን ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ: “ጥፋተኛን ሰው የፈለገ ብትወቅሰው የኅሊናውን ያህል ግን ከሳሽ ልትሆንበት አትችልም” ይላል። አንተ ስታገኘው ይሆናል “እንዲ አደረግህ” ብለህ ጥፋቱን የምትነግረው፤ ሕሊናው ግን የትም ሸሽቶ ሊያመልጠው በማይችል በማያቋርጥ ጩኸት ቀን እና ሌት ይወነጅለዋል። https://t.me/Dnabel
Открыть в Telegramየአርሲ ክርስቲያኖችን (ራሳችንን) ባሰብን ጊዜ! #በተደጋጋሚ ክርስቲያን ወንድም እና እኅቶቻችን ላይ እየሆነ ያለውን ሳስብ፣ ከግሪካዊው ኤዞፕ ተረቶች አንዱ ትዝ ብሎኝ ይህን ግጥም አስጫረኝ። አንድ ጊዜ ቀበሮ በግን ምግቤን ሰርቃ በላችብኝ ብሎ በሐሰት በመክሰስ ሸንጎ ፊት አቆማት። በጓም እየተገረመች “ኸረ እኔ ሣር እንጂ ሥጋ አልበላም። ምን ብዬ የእርሱን ምግብ እሰርቃለሁ” አለች። ነገር ግን የፍርድ ቤቱ ዳኛ ተኩላ ስለ ነበር፤ “አንቺ በግ ምንም ምግቡን ባትበይ እንኳ መከራከሪያሽ አሳማኝ አይደለምና ጥፋተኛ ነሽ። ስለዚህ ሥጋዋ ታርዶ ለፍርድቤቱ አባላት ይከፋፈል። ቆዳዋ ደግሞ ለከሳሽ ቀበሮ ይሰጥ” ብሎ ፈረዱባት።(ታሪኩን ካነበብሁ ስለቆየሁ በብዥታ ነው የተረክሁት) ፍትሕ ከወዴት ትምጣ?! https://t.me/Dnabel
Открыть в Telegram“ ‘ወዳጄ ሆይ፥ የሰርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት ወደዚህ ገባህ?’ አለው እርሱም ዝም አለ” ማቴ 22:12 እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ይህን የይቅርታ ልብስ ካለበስን ወደ ሰርጉ ማን ያስገባናል? ጌታ ሆይ ለዚህ የሰርግ ልብስ የተገባን አድርገን!!!
Открыть в Telegram“እርሱ ግን መሐሪ ነው፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር አላቸው፥ አላጠፋቸውምም፤ ቍጣውንም መመለስ አበዛ፥ መዓቱንም ሁሉ አላቃጠለም” መዝሙር 78:38
Открыть в Telegramእንደማይድን የተነገረንን የሥጋ ቁስል እንኳ “በምናልባት” ተስፋ የምንንከባከብ ከሆነ፣ የሚድነውን የነፍስ ቁስል ቶሎ ለማድረቅ እንዴት ዳተኞች ሆንን?
Открыть в Telegram