አላህ ያውቃል ብላችሁ ተስፋ ላደረጋችሁት ነገር ፣ አልሀምዱሊላህ ብላቹ ለማመስገን ያብቃቹ 🤍 @Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
Open in TelegramPosts of ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
عيدكم مبارك، كل عام وأنتم بخير، تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال ❤ 🌙 @Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
Open in Telegramኢድ እና ጁምዓ ባንድ ላይ ምን አይነት ቀን ነዉ ጀማዉ😊 ከራህመቱ ወር 1 ቀን የጨመረልን ጌታ ምስጋና ይገባው الحمد لله رب العالمين @Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
Open in Telegram🚨 ሰበር መረጃ 👉 የዒድ አል-ፊጥር በዓል #አርብ ይከበራል ። ዛሬ ጨረቃ ባለመታየቷ ነገ ረመዷን 30 ሆኖ ዒድ አል ፊጥር በዓል ደግሞ #አርብ መጋቢት 11 እንደሚከበር ይፋ ተደርጓል ። @Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
Open in Telegramረመዳን በመጣ ቁጥር ትዝ የሚለኝ ጨዋታ 😁 አንዱ ክርስቲያን ጀለስ ልክ ረመዳን ሲደርስ ሰለመ ፤ የረመዳንን ፆም መፆም በጣም ከበደው ፤ አንዳንዴ ፆሙን ለማጥፋት ሁሉ ይወሰወሳል ፤.... ረመዳን እስኪ ወጣ ጨነቀው... የረመዳን የመጨረሻዎቹ አስርቱ ቀናት በነሻጣ ተሀጁድ ወጥሮ መስገድ ጀመረ ....የመጨረሻዎቹ 4,5 ቀናት በተለይ 27ተኛው ለይል ላይ ቁኑት ላይ በሚደረገው ዱዓ በጣም ሲለቀሰ አየ በጣም ግራ ተጋብቶ እንዲህ አለ..... "ምን ሆናቹ ነው ምታለቅሱት ፆሙ ይራዘም ተባለ እንዴ ?"😂😭 @Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
Open in Telegramተፀፀት ተመለስ .. አላህ ይምርሃል 🤍 በስንዝር ተጠጋው .. በክንድ ይቀርብሃል❤️🩹 الله🤍 @Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
Open in Telegramዐሽረል አዋኺር 🌙🤍 <<<<<<<>>>>>> ♦የአላህ መልእክተኛ በመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ፣በሌሎች ላይ ያላደረጉትን ጥረት ያደርጉ ነበር። እንዲሁም ♦ለይለተል ቀድርን በረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ ባሉ ልዩ ሌሊቶች ፈልጉ ይሉ ነበር። •አላህም(ሱ.ወ) በቅዱስ ቃሉ፣ስለ ለይለተል ቀድር እንዲህ ብሏል:– 【ليلة القدر خير من ألف شهر】 【መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡】 [ አል-ቀድር - 3 ] የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم ከእናታችን ዓኢሻ (ረ.ዐ) በተዘገበው ሀዲስ ላይ ለይለተል ቀድር ላይ አብዝተን ምንደጋግመውን ዱዓእ አስተምረዋታል !! "እናታችን ዓኢሻ (ረ.ዐ) "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሌሊቱ ለይለተል ቀድር መሆኑን ባውቅ ምን ልበል?" ብላ ስትጠይቃቸው፦ “አላሁመ ኢነከ ዓፉዉን ቱሒቡል ዓፍወ ፋዕፉ ዓኒ" (አላህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ፣ ይቅርታንም ትወዳለህ፤ ስለዚህ ይቅር በለኝ በይ) አሏት። ሱነን አት-ቲርሚዚ (3513) ካለፉት የረመዷን ወር ቀናት አሁን የተቀሩት የበለጠ ውድ ናቸውና፣ በተሻለ መነቃቃት እንጠቀምባቸው!!! በዒባዳ ተግተን ያለፈውን አካክሰን ከጀሃነም እሳት ነፃ የምንሆንበትን እድያ አላህ ይቸረን::
Open in Telegramالعشر الأواخر ዐሽረል አዋኺር /የረመዷን የመጨረሻዎቹ አሥርቱ ምርጥ ቀናት/ ዛሬ ማታ ይጀምራሉ ። ኢዕቲካፍ መግባት ተሀጁድ መቆም ቁርአን መቅራት ዚክር ማብዛት ሰደቃ ማድረግ የተለያዩ የኸይር ሥራዎችን ማብዛት በነኚህ ቀናትና ምሽቶች ውስጥ ይወደዳሉ። አሏህ ለይለተል ቀድርን ይወፍቀን። በዱዐቹህ
Open in Telegramየአላህ መልዕክተኛና ﷺ ሰሐቦቻቸው የፆም ወቅት ላይ ናቸው። ከገዛ ሀገራቸው ከተባረሩ ሰነባብተዋል፤ ቂብላው ወደ መካ ከተቀየረ በኃላም መካ በሙስሊሞች እጅ አለመሆኑ የቀን ተሌት ጭንቀታቸው ከሆነ ቆይቷል። አቡ ሱፊያን የቁረይሽ ባለሟሎችና ህዝቦች የሆነው ቅፍለት አደጋ ላይ እንደሆነና እሱን ማስመለስና ማስጠበቅ እንዳለባቸው ዜና ባደረሳቸው ሰአት ቁረይሾች በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን፤ የሚያዝናንዋቸውን ሴቶች፤ በየቀኑ የሚያርዱትን ግመል ይዘው ወጡ! የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ቅፍለቱን ማጥቃት ላይ ከሰሐቦቻቸው ጋር ውይይት ሲያደርጉ ኡመርና አቡበከርን ጨምሮ በሀሳባቸው ተስማሙ ! የአቀባ ስምምነት ላይ ቃል የገቡላቸውንም አንሳሮች ሀሳብ ጠየቁ ! ለዚህኛው ዘመቻ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ዘመቻዎችም የሚኖራቸውን ታዛዥነት ለማወቅ ጠየቋቸው የበድር ዘመቻ ሙሐጂሮችና አንሳሮች ለሸፊዒ የነበራቸው መሐባና ስስት የታየበት ታላቅ ገዝዋ ነበርና ሂጅራ ካደረጉ በሁለተኛው ዓመት ይህ ያልተጠበቀ ዘመቻ ተከሰተ፤ ውስን መሆናቸው ከዘመቻው እንዲሸሹ አላደረጋቸውም! 313ቱም ሰሐቦች ሐቢበላህ ጎን መሰለፍ'ን፣ መስዋዕት መሆንን በፍቅር ተቀበሉ። ከሙሐጂሮች ሚቅዳድ፣ ከአንሳሮች ደግሞ ሰዓድ ኢብን ሙዓዝ ተነስተው ቃልኪዳናቸውን ሰጡ። ሚቅዳድ'ም ከፍ ባለው ድምፁ ንግግሩን እንዲህ ጀመረ: يا رسول الله, لا نقول لك كما قال قوم موسى لموسى: اذهب أنت وربك فقاتلا إنا هاهنا قاعدون ، ولكنا نقاتل عن يمينك وعن شمالك ، ومن بين يديك ومن خلفك «ያ ረሱለላህﷺ! እኛ ልክ እንደ ሙሳ ህዝቦች ነቢዩላህ ሙሳን "ሂዱ! አንተና አምላክህ በጋራ ጠላታችሁን ተጋደሉ።" እንዳሉት የምንል አይደለንም። ይልቁኑ በቀኝህም፣ በግራህም፣ ከፊትህም ፣ከኃላህም አብረንህ በመሆን እንዋጋቸዋለን።» በማለት የምስክርነት ቃሉን ሰጠ። ቀጥሎ'ም ሰዓድ ኢብን ሙዓዝ የአንሷሮች ውዴታና የሱ አይነታነት የታየበትን ድንቅ የፍቅር ንግግር ተናገረ: "يا رسول الله! فقد آمنا بك وصدقناك ، وشهدنا أن ما جئت به هو الحق ، وأعطيناك على ذلك عهودنا ومواثيقنا ، على السمع والطاعة .... 🥹 «ያ ረሱለላህ ﷺ! ባንቱ አምነናል። እውነትን እንደሚናገሩ መስክረናል። አንቱን ለመጠበቅ፤ መስዋዕት ለመሆንና ታዛዥ ለመሆን፤ ሰማን ታዘዝንም ለማለት ቃላችንን ሰጥተናል። እንግዲያውስ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ሆይ! እውነትን እንዲያሰፍኑ በላኮት አምላክ ትዕዛዝ መሰረት ሰራዊቶን አሰልፉ፤ ባህርን ልሻገር ነው ቢሉን እንኳን አንዳችንም ሳንቀር አብረንዎት እንሻገራለን፤ ነገ ጠላቶቻችንን ብንገናኝ የምንጠላ አይደለንም። በእውነቱ በጦርነት ላይ ታጋሾች ነን የጦር ሜዳ ላይ ግን ኀይለኞች ነን። በጦርነቱ ወቅት እኛን አይተው የሚደሰቱበት ያድርግልዎ። በአላህ ፍቃድ አብረንዎ እንድንዘምት ይፍቀዱልን።»በማለት ተናገረ! ረሱለላህ ﷺ በሰዓድ’ም በሚቅዳድም ንግግር እጅግ በጣም ተደሱ። ድል'ም የእነሱ ኾነ ኣህ በድር!... እንግዶችሽ ምነኛ አማሩ። ከሰዎች ሁሉ ምርጥ ሰዎችን፣ ከመላእክቶች ሁሉ ምርጥ መላእኮችን አስተናገድሽ። በአንድ ባንዲራ ስር መልዕክተኛው ከሰይዲና ጂብሪል ጋር ሆነው ጠላትን አንበረከኩ። ሰሐቦችም ለጌታቸውና ለጌታቸው ሐቢብ ﷺ ያላቸውን ውዴታ በግልፅ አሳዩ! ... ምንዳቸውም ከፍ አለ። 🥰 በድር ላይ የተሳተፉ ሙስሊሞች 'አፍደሉል ሙስሊሚን' ሲባሉ በድር ላይ የተሳተፉ መላዒኮችም እንደዛው ምርጥ ተባሉ። ከዓብ ኢብኑ ማሊክ ረዲየላሁ አንህ የነበረውን ውብ ትዕይንት ባማረ መልኩ እንዲህ ይገልፀዋል: وبيوم بدرٍ حين تمحى وجوههم جبريل تحت لوائنا ومحمدُ 🥰 በዛ የበድር ቀን፤ በዛ ፊታቸው(የቁረይሽ ሀይሎች) የተዋረደበት ቀን!...ጂብሪልና ሙሐመድ ﷺ ባንዲራችን ስር ቆመው የነበሩበት! 🥰✨ ድልን መንሳት አሸናፊና ጥበበኛ በኾነው አላህ ዘንድ እንጂ በሌላ አይደለምና ድልን አጎናፀፋቸው! ውሸት ከእውነት የተለየበት ዘመቻ ሆነ። ብርሃን ጨለማን ገረሰሰ! ኢማን በክህደት ላይ ነገሰ። ጉረኞችን አሳፈረ! ትዕቢተኞችን አዋረደ! እንደ አቡ ጀሃልና ኡቅባ ኢብን ሙዒጥ አይነት ካሐዲዎች ህይወትም አበቃለት! የነህጁ አህመድ ሸውቂ እንዲህ ይላሉ: •••• محبة الله ألقاها وهيبته على ابن آمنة في كل مصطدم «ጠላቶች እሳቸውን ለመዋጋት በሞከሩ ቁጥር፣ አላህ ፍቅሩን እና ግርማው'ን በአሚና ልጅ ሙሐመድ ﷺ ላይ ያደርጋል።» •••• كأن وجهك تحت النقع بدر دجى يضيء ملتثما أو غير ملتثم «በዛ አቧራ በሞላው ዘመቻ፣ በዛ ጨለማ ምሽት፣ ሰማዩ በደመናዎች ተሸፍኖም ሳይሸፈንም ፊትዎ ﷺ እንደ ሙሉ ጨረቃ ያበራ ነበር።» •••• بدر تطلع في بدر فغرته كغرة النصر تجلو داجي الظلم «ልክ እንደሙሉ ጨረቃ(በድር) ሙሐመድ ﷺ በድር ላይ አፈኩ፣ ገፅታቸውም ጨለማ በኾነው ምሽት ውስጥ ድል'ን እንደሚያበስር አዲስ ጨረቃ ያበራ ነበር።» ይላል ነህጁ ላይ! አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ሰይዲና ሙሐመድﷺ 🥰
Open in Telegramከዛሬ 15 ቀን በፊት በዚህ ሰዐት የመጀመሪያውን ተራዊህ ሰገድን ከ15 ቀናት በኋላ ደግሞ በዚህ ሰዐት ኢንሻአላህ የኢድ ተክቢራ እንላለን ሳናውቀው አጋምሰነዋል ማን በአግባቡ እንደተጠቀመባቸዉ አላህ ይወቅ
Open in Telegramረመዳን ነገ አንድ ብሎ ይጀምራል. ......እንኳን ለታላቁ ረመዳን ወር በሰላም አደረሰን..... ረመዳን ነገ ይጀምራል፣ ኢንሻ አላህ። የእዝነት፣ የምህረት እና የትልቅ ምንዳ ወር በላያችን ላይ መጥቷል። አላህ ጾማችንን፣ ሶላታችንን እና መልካም ስራዎቻችንን ይቀበለን.... በዚህ የተባረከ ወር አላህ ጥንካሬውን ይስጠን።❤
Open in TelegramForwarded from በረካ shopping 🛍️
Ramadan Countdown calendar 📅 💰Price - 1400 ብር ብቻ Order ለማድረግ 👉 @yeazizalij @bereka_shopping
Open in TelegramForwarded from በረካ shopping 🛍️
የኢድ-አል ፊጥር በዓል ነገ ይከበራል !! የሸዋል ጨረቃ በሳውዲ አረቢያ መታየቷን ተከትሎ የኢድ አል-ፊጥር በዓል በነገው እለት እሁድ መጋቢት 21 የሚከበር ይሆናል። Eid Mubarek!🥰 @bereka_shopping
Open in Telegram🌙 ረመዳን ሙባረክ🌙 የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ በመታየቷ ነገ ቅዳሜ የረመዳን የመጀመሪያው ቀን ይሆናል። አህለን ቢከ ያ ረመዳን❤ @Dania_Islamic
Open in TelegramForwarded from በረካ shopping 🛍️
የረመዳን decor 3.5ሜትር dim light 💡 💰Price 2500 ብር ብቻ Order yours 👉 @yeazizalij Join 👉 @bereka_shopping
Open in TelegramForwarded from ፍቅር ሰባኪ TemUd
ረመዳን ይመላለስብን❤ عيد مبارك ! كل عام وأنتم بخير! تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال!!! እንኳን ለ1445 ዓ.ሂ የዒድ አል - ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ። @Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
Open in TelegramForwarded from ፍቅር ሰባኪ TemUd
የሸዋል ወር አዲስ ጨረቃ ባለመታየቷ የኢድ አልፊጥር በዓል እሮብ ሚያዝያ 2 መሆኑ ተገልፆል:: ነገ ማክሰኞ ሚያዝያ 1 የረመዳን የመጨረሻው 30ኛ ቀን ሆኗል አላህ ፆማችንን ይቀበለን!🌙 @Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
Open in Telegram