Кабинет

Посты канала ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል

сначала новые

#8560Текст
Просмотры4 390+398%к среднему
Пересылки—
Реакции22
Комментарии—
#8559Текст
Просмотры4 360+395%к среднему
Пересылки—
Реакции36
Комментарии—
#8557Текст

ዐሽረል አዋኺር 🌙🤍       <<<<<<<>>>>>> ♦የአላህ መልእክተኛ በመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ፣በሌሎች ላይ ያላደረጉትን ጥረት ያደርጉ ነበር።   እንዲሁም ♦ለይለተል ቀድርን በረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ ባሉ ልዩ ሌሊቶች ፈልጉ ይሉ ነበር። •አላህም(ሱ.ወ) በቅዱስ ቃሉ፣ስለ ለይለተል ቀድር እንዲህ ብሏል:– 【ليلة القدر خير من ألف شهر】 【መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡】 [ አል-ቀድር - 3 ] የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم ከእናታችን ዓኢሻ (ረ.ዐ)   በተዘገበው ሀዲስ ላይ ለይለተል ቀድር ላይ አብዝተን ምንደጋግመውን ዱዓእ አስተምረዋታል !! "እናታችን ዓኢሻ (ረ.ዐ) "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሌሊቱ ለይለተል ቀድር መሆኑን ባውቅ ምን ልበል?" ብላ ስትጠይቃቸው፦ ​“አላሁመ ኢነከ ዓፉዉን ቱሒቡል ዓፍወ ፋዕፉ ዓኒ" (አላህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ፣ ይቅርታንም ትወዳለህ፤ ስለዚህ ይቅር በለኝ በይ) አሏት።      ሱነን አት-ቲርሚዚ (3513) ካለፉት የረመዷን ወር ቀናት አሁን የተቀሩት የበለጠ ውድ ናቸውና፣ በተሻለ መነቃቃት እንጠቀምባቸው!!! በዒባዳ ተግተን ያለፈውን አካክሰን ከጀሃነም እሳት ነፃ የምንሆንበትን እድያ አላህ ይቸረን::

Открыть в Telegram
Просмотры4 550+416%к среднему
Пересылки—
Реакции32
Комментарии—
#8556Текст
Просмотры3 290+273%к среднему
Пересылки—
Реакции19
Комментарии—
#8555Текст

የአላህ መልዕክተኛና ﷺ ሰሐቦቻቸው የፆም ወቅት ላይ ናቸው። ከገዛ ሀገራቸው ከተባረሩ ሰነባብተዋል፤ ቂብላው ወደ መካ ከተቀየረ በኃላም መካ በሙስሊሞች እጅ አለመሆኑ የቀን ተሌት ጭንቀታቸው ከሆነ ቆይቷል። አቡ ሱፊያን የቁረይሽ ባለሟሎችና ህዝቦች የሆነው ቅፍለት አደጋ ላይ እንደሆነና እሱን ማስመለስና ማስጠበቅ እንዳለባቸው ዜና ባደረሳቸው ሰአት ቁረይሾች በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን፤ የሚያዝናንዋቸውን ሴቶች፤ በየቀኑ የሚያርዱትን ግመል ይዘው ወጡ! የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ቅፍለቱን ማጥቃት ላይ ከሰሐቦቻቸው ጋር ውይይት ሲያደርጉ ኡመርና አቡበከርን ጨምሮ በሀሳባቸው ተስማሙ ! የአቀባ ስምምነት ላይ ቃል የገቡላቸውንም አንሳሮች ሀሳብ ጠየቁ ! ለዚህኛው ዘመቻ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ዘመቻዎችም የሚኖራቸውን ታዛዥነት ለማወቅ ጠየቋቸው የበድር ዘመቻ ሙሐጂሮችና አንሳሮች ለሸፊዒ የነበራቸው መሐባና ስስት የታየበት ታላቅ ገዝዋ ነበርና ሂጅራ ካደረጉ በሁለተኛው ዓመት ይህ ያልተጠበቀ ዘመቻ ተከሰተ፤ ውስን መሆናቸው ከዘመቻው እንዲሸሹ አላደረጋቸውም! 313ቱም ሰሐቦች ሐቢበላህ ጎን መሰለፍ'ን፣ መስዋዕት መሆንን በፍቅር ተቀበሉ። ከሙሐጂሮች ሚቅዳድ፣ ከአንሳሮች ደግሞ ሰዓድ ኢብን ሙዓዝ ተነስተው ቃልኪዳናቸውን ሰጡ። ሚቅዳድ'ም ከፍ ባለው ድምፁ ንግግሩን እንዲህ ጀመረ: يا رسول الله, لا نقول لك كما قال قوم موسى لموسى: اذهب أنت وربك فقاتلا إنا هاهنا قاعدون ، ولكنا نقاتل عن يمينك وعن شمالك ، ومن بين يديك ومن خلفك «ያ ረሱለላህﷺ! እኛ ልክ እንደ ሙሳ ህዝቦች ነቢዩላህ ሙሳን "ሂዱ! አንተና አምላክህ በጋራ ጠላታችሁን ተጋደሉ።" እንዳሉት የምንል አይደለንም። ይልቁኑ በቀኝህም፣ በግራህም፣ ከፊትህም ፣ከኃላህም አብረንህ በመሆን እንዋጋቸዋለን።» በማለት የምስክርነት ቃሉን ሰጠ። ቀጥሎ'ም ሰዓድ ኢብን ሙዓዝ የአንሷሮች ውዴታና የሱ አይነታነት የታየበትን ድንቅ የፍቅር ንግግር ተናገረ: "يا رسول الله! فقد آمنا بك وصدقناك ، وشهدنا أن ما جئت به هو الحق ، وأعطيناك على ذلك عهودنا ومواثيقنا ، على السمع والطاعة .... 🥹 «ያ ረሱለላህ ﷺ! ባንቱ አምነናል። እውነትን እንደሚናገሩ መስክረናል። አንቱን ለመጠበቅ፤ መስዋዕት ለመሆንና ታዛዥ ለመሆን፤ ሰማን ታዘዝንም ለማለት ቃላችንን ሰጥተናል። እንግዲያውስ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ሆይ! እውነትን እንዲያሰፍኑ በላኮት አምላክ ትዕዛዝ መሰረት ሰራዊቶን አሰልፉ፤ ባህርን ልሻገር ነው ቢሉን እንኳን አንዳችንም ሳንቀር አብረንዎት እንሻገራለን፤ ነገ ጠላቶቻችንን ብንገናኝ የምንጠላ አይደለንም። በእውነቱ በጦርነት ላይ ታጋሾች ነን የጦር ሜዳ ላይ ግን ኀይለኞች ነን። በጦርነቱ ወቅት እኛን አይተው የሚደሰቱበት ያድርግልዎ። በአላህ ፍቃድ አብረንዎ እንድንዘምት ይፍቀዱልን።»በማለት ተናገረ! ረሱለላህ ﷺ በሰዓድ’ም በሚቅዳድም ንግግር እጅግ በጣም ተደሱ። ድል'ም የእነሱ ኾነ ኣህ በድር!... እንግዶችሽ ምነኛ አማሩ። ከሰዎች ሁሉ ምርጥ ሰዎችን፣ ከመላእክቶች ሁሉ ምርጥ መላእኮችን አስተናገድሽ። በአንድ ባንዲራ ስር መልዕክተኛው ከሰይዲና ጂብሪል ጋር ሆነው ጠላትን አንበረከኩ። ሰሐቦችም ለጌታቸውና ለጌታቸው ሐቢብ ﷺ ያላቸውን ውዴታ በግልፅ አሳዩ! ... ምንዳቸውም ከፍ አለ። 🥰 በድር ላይ የተሳተፉ ሙስሊሞች 'አፍደሉል ሙስሊሚን' ሲባሉ በድር ላይ የተሳተፉ መላዒኮችም እንደዛው ምርጥ ተባሉ። ከዓብ ኢብኑ ማሊክ ረዲየላሁ አንህ የነበረውን ውብ ትዕይንት ባማረ መልኩ እንዲህ ይገልፀዋል: وبيوم بدرٍ حين تمحى وجوههم جبريل تحت لوائنا ومحمدُ 🥰 በዛ የበድር ቀን፤ በዛ ፊታቸው(የቁረይሽ ሀይሎች) የተዋረደበት ቀን!...ጂብሪልና ሙሐመድ ﷺ ባንዲራችን ስር ቆመው የነበሩበት! 🥰✨ ድልን መንሳት አሸናፊና ጥበበኛ በኾነው አላህ ዘንድ እንጂ በሌላ አይደለምና ድልን አጎናፀፋቸው! ውሸት ከእውነት የተለየበት ዘመቻ ሆነ። ብርሃን ጨለማን ገረሰሰ! ኢማን በክህደት ላይ ነገሰ። ጉረኞችን አሳፈረ! ትዕቢተኞችን አዋረደ! እንደ አቡ ጀሃልና ኡቅባ ኢብን ሙዒጥ አይነት ካሐዲዎች ህይወትም አበቃለት! የነህጁ አህመድ ሸውቂ እንዲህ ይላሉ: •••• محبة الله ألقاها وهيبته على ابن آمنة في كل مصطدم «ጠላቶች እሳቸውን ለመዋጋት በሞከሩ ቁጥር፣ አላህ ፍቅሩን እና ግርማው'ን በአሚና ልጅ ሙሐመድ ﷺ ላይ ያደርጋል።» •••• كأن وجهك تحت النقع بدر دجى يضيء ملتثما أو غير ملتثم «በዛ አቧራ በሞላው ዘመቻ፣ በዛ ጨለማ ምሽት፣ ሰማዩ በደመናዎች ተሸፍኖም ሳይሸፈንም ፊትዎ ﷺ እንደ ሙሉ ጨረቃ ያበራ ነበር።» •••• بدر تطلع في بدر فغرته كغرة النصر تجلو داجي الظلم «ልክ እንደሙሉ ጨረቃ(በድር) ሙሐመድ ﷺ በድር ላይ አፈኩ፣ ገፅታቸውም ጨለማ በኾነው ምሽት ውስጥ ድል'ን እንደሚያበስር አዲስ ጨረቃ ያበራ ነበር።» ይላል ነህጁ ላይ! አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ሰይዲና ሙሐመድﷺ 🥰

Открыть в Telegram
Просмотры3 990+353%к среднему
Пересылки—
Реакции16
Комментарии—
#8554Текст
Просмотры3 160+259%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
#8553Текст
Просмотры4 640+427%к среднему
Пересылки—
Реакции31
Комментарии—
#8533Текст
Просмотры16 000×18к среднему
Пересылки—
Реакции28
Комментарии—
#8450Фото
Просмотры31 400×36к среднему
Пересылки—
Реакции100
Комментарии—
#8449Текст
Просмотры22 500×26к среднему
Пересылки—
Реакции50
Комментарии—