Account

Christian Vent

@chrstianchatbot Use this bot to vent

Username
@christianvent
Subscribers2,620
Avg views per post, 7d309last 7 days
ERR11.81%last 7 days

Average views per post by day

By publication day

Show as table
DateAvg views per post
Nov 27, 2026384
Nov 28, 2026348
Nov 29, 2026202

Most viewed this month

  1. Vent - 3543 👩 ለወጣት ወንድሞቼ እና እህቶቼ የተላከ የህይወት ስንቅ! ካነበብኩት ከተማርኩት ከምኞቴ ....ለእናንተ ወጣትነት የህይወት ወርቃማው ምዕራፍ ነው። ጉልበት፣ ጊዜ እና ትኩስ አእምሮ ያለን ዛሬ ነው። እንደ አንድ ወጣት፣ አንባቢ እና ክርስቲያን በህይወት ጉዟችን ላይ አብረን ልንይዛቸው የሚገቡ 5 ቁልፍ ነጥቦችን ላካፍላችሁ ወደድኩ፦ 1. ጊዜያችንን እና ጉልበታችንን ለዘላለማዊ ነገር እናውለው መጽሐፍ ቅዱስ "የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ" (መክብብ 12:1) ይላል። ወጣትነታችንን ጊዜያዊ በሆኑ ስሜቶች እና ትኩረትን በሚሰርቁ አላስፈላጊ ነገሮች (ለምሳሌ የማህበራዊ ሚዲያ ሱስ) አናባክን። 💡 ከመጽሐፍት ዕንቁ ሀሳብ፦ ጄምስ ክሊር Atomic Habits በተሰኘው መጽሐፉ "የዛሬ ውጤታችን የትናንት ልማዶቻችን ድምር ነው" ይላል። ትናንሽ የሚመስሉ የዕለት ተዕለት ልማዶቻችን (ጸሎት፣ ንባብ፣ ስራ) የነገ ማንነታችንን ይቀርጻሉ። 2. አእምሯችንን በንባብ እናንጽ (መጽሐፍ ቅዱስ + መጽሐፍት) ሮሜ 12:2 "በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ" ይላል። ልባችን የሚታደሰው ደግሞ በምንመግበው እውቀት ነው። በየቀኑ የእግዚአብሔርን ቃል ከማንበብ ጎን ለጎን ጥሩ መንፈሳዊ፣ የስነ-ልቦና እና የታሪክ መጽሐፍትን እናንብብ። 💡 ከመጽሐፍት ዕንቁ ሀሳብ፦ ቻርሊ ጆንስ "ከአምስት ዓመት በኋላ አሁን ካለንበት የምንለየው በሁለት ነገሮች ብቻ ነው፤ በምናነባቸው መጽሐፍት እና በምንገናኛቸው ሰዎች!" ይላል። 3. ወደ እግዚአብሔር መቅረብን የህይወታችን ዋና መሠረት እናድርግ "ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል" (ያዕቆብ 4:8)። በወጣትነት የሚመጡ ፈተናዎችን የምናሸንፈውና እውነተኛ እርካታ የምናገኘው በራሳችን ጥንካሬ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ባለን የጠበቀ ህብረት ነው። በጸሎት፣ በአምልኮ እና በቃሉ ውስጥ ሆነን ከእርሱ ጋር የግል ጊዜ እናሳልፍ። 💡 ከመጽሐፍት ዕንቁ ሀሳብ፦ ሲ.ኤስ. ሉዊስ Mere Christianity በተሰኘው መጽሐፉ "እግዚአብሔር የሰውን ልብ የፈጠረው በራሱ ብቻ እንዲረካ አድርጎ ነው፤ ልክ መኪና በነዳጅ ብቻ እንዲሰራ ተደርጎ እንደተፈጠረው!" ይላል። 4. ራዕይ እና ግልጽ ዓላማ ይኑረን "ራዕይ በሌለበት ሕዝብ መረን ይሆናል" (ምሳሌ 29:18)። ህይወትን በአጋጣሚ አንኑር። እግዚአብሔር በውስጣችን ያስቀመጠውን ልዩ መክሊት እና ዓላማ በጸሎት እና በንባብ ፈልገን እናግኝ። 💡 ከመጽሐፍት ዕንቁ ሀሳብ፦ ሪክ ዋረን The Purpose Driven Life በተሰኘው መጽሐፉ "ህይወት የሚጀምረው ስለ ራሳችን ማሰብ ስናቆምና ፈጣሪ ለምን እንደፈጠረን መኖር ስንጀምር ነው" ይላል። 5. የምንውልበትን ሰው እንምረጥ (ጤናማ ጓደኝነት) "ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል" (ምሳሌ 13:20)። ወደ እግዚአብሔር፣ ወደ መጽሐፍት እና ወደ ዓላማችን የሚያቀርቡንን ጓደኞች እንምረጥ። በፍቅርና በትዳር ጉዳይ ላይም በስሜት ሳይሆን በጸሎትና በመረዳት እንራመድ። 💡 ከመጽሐፍት ዕንቁ ሀሳብ፦ የታወቀው አባባል "የምንውልባቸው 5 የቅርብ ጓደኞቻችን አማካይ ውጤት እኛ ነን" እንደሚለው፣ አካባቢያችን ወደ ላይ የሚስበን መሆኑን እናረጋግጥ። እና "ማንም ታናሽነትህን አይናቀው፤ ነገር ግን በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን።" (1ኛ ጢሞቴዎስ 4:12)። በወጣትነታችን እግዚአብሔርን እያከበርን፣ አእምሯችንን እያነጽን ለትውልድ የምንተርፍ እንሁን! 🙏🔥 "Let’s honor God in our youth, feed our minds with truth, and build lives that echo in eternity. Today's readers are tomorrow's leaders—let’s stay rooted, keep growing, and shine bright!" ✨📖 ━━━━━━━━━━━━━━━ #Other #Youth Telegram | Bot

    Text
    Views412
    Forwards—
    Reactions20
    Comments—
  2. Vent - 3546 👩 ከአንድ ወንድም ጋር እያወራን በቅርቡ ስለገጠመው ነገር አጫውቶኝ ነበር ይኸውም! በአንድ ቸርች ውስጥ ከሚያውቃትና ከአምስት ወር በላይ በጓደኝነት ብቻ ከሚቀርባት ሴት ፍቅር እንደያዘው ነገረኝ እናም ብዙውን ጊዜ ወሬያቸው በሙሉ በቴክስት ላይ የተወሰነ በመሆኑ አካላዊ ግንኙነታቸው እምብዛም ነበር። ከአምስት ወራት በላይ ሲያወሩ እርስ በእርስ ያላቸው መተማመንና የሚሰጣጡት እረፍት እጅግ ትልቅ እንደነበረም ጨምሮ ነገረኝ። እንደውም ሁል ጊዜ ዘውትር ያለመታከት እንደሚፀልይላትና ፍቅሩ በስሜት ላይ ያልተጣደ ዘላቂ እንዲሆን የጌታን ፍቃድ በብርቱ ይጠይቅም ጭምር ነበር። ከሁለት ቀን በፊት አምኖበትና ጉዳዩን በጌታ ፊት አቅርቦበት ጉዳዩን ቀለል አድርጎ ጫና ሳይሰማትና በነፃነት ተሞልታ እንዲሁም  የትኛውንም ውሳኔ ብትወስን ፍፁም እንደሚያከብርላት ነግሯት ከእርሷ ጋር ግንኙነት መመስረት እንደሚፈልግ ነገራት። እርሷም ለአንድ ደቂቃ ያህል ትንሽ  ፈገግ እንደማለትና እንደማፈርም እያለች እንፀልይበት(የእግዚአብሄር ፍቃድ እንዳለበት እንወቅ) እናም ትንሽ ላስብበትም  ብላ እንደመለሰችለት ነገረኝ። እናም እርሱ የጠየቀኝ ነገር  "አስባበትና ፀልያበት ምላሿን ለመስማት ምን ያህል የጊዜ ቀነ ገደብ መጠበቅ ይኖርብኝ ይሆን?" የሚልና " አሁን ምላሿን እስክሰማ ድረስ ከእርሷ ጋር ያለኝን ወሬ በምን አይነት ስሜት መቀጠል አለብኝ?" ምን ትመክሩታላችሁ(ትመልሱለታላችሁ) ለዚህ ወንድም! ━━━━━━━━━━━━━━━ #Relationship Telegram | Bot

    Text
    Views399
    Forwards—
    Reactions12
    Comments—
  3. Vent - 3545 👨 ​Guys, endet nachu quick question especially for the ladies here in this vent. ​Everyone says wend ena set cannot be best friends.en gn  Suppose you have a guy best friend and you're 100% sure he has zero romantic feelings for you. Beka yhen chance O nw bilachu wisedut ena Would you still keep him as your bestie, or do you still stand by "men and women can't be best friends"? ​Reason I'm asking is this dynamic is usually lenante yadelal malet kewendu yeteshale bezi relationship mititekemut enante nachu . lemasle Campus eyalen, I had a girl best friend who expected all my attention and care, beka bzu ngr endaderglat mitfelg lechgrochua hulu kegonua endhon mitetbk gen summer break lay sinhon we gibim hona malasfelgat kemeselat chrash atawkegnm beka malet lesua mnm neberku endewm yehone time yegna gibi rebsha tefetro wendoch akebabi hulet lijoch motew federal gebto mnamn letnsh ameletku ena timhrtm tekuarto lewer mnamn wchi mader jemre nbr bezi gize enkuan yet neh bila alteyekechignm yhen yahl nbr . She only called when she felt lonely or down lemaslae to take her to a café, buy her food, or bring chocolate to her dorm mnamn . At first I thought it was normal, then I realized I was being used and stopped. Keza eske graduation we never spoke again, even at fellow and church programs. now yeteleyaye bota yerasachinn life eyenorn nw anyhow ​Be real: is the issue really about "catching feelings," or do you just know the dynamic itself isn't fair? Because kemtagegnut with out responsibikity mitfelgutn care ena attention silemtagegnubet ━━━━━━━━━━━━━━━ #Other #Youth #Relationship Telegram | Bot

    Text
    Views391
    Forwards—
    Reactions5
    Comments—
  4. Views390
    Forwards—
    Reactions13
    Comments—

Latest posts

#4299Text
Views115−63%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#4298Text
Views185−40%vs avg
Forwards—
Reactions17
Comments—
#4296Text
Views239−23%vs avg
Forwards—
Reactions18
Comments—
#4293Text
Views343+11%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—

All posts