Account

Posts of Bule Hora University

newest first

#9234Photo

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የEU-AGRIWAY Erasmus+ Jean Monnet Module ፕሮጀክትን በይፋ አስጀመረ። ‎***************************************** ‎ (ህዳር 11/2019 ዓ.ም ‎ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ) ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በአውሮፓ ህብረት የErasmus+ ፕሮግራም ድጋፍ የሚተገበረውን EU-AGRIWAY (EU Agri-Food Policies, Sustainability and Global Gateway: Implications for Coffee and Horticulture Value Chains in Ethiopia) የተሰኘ የJean Monnet Module ፕሮጀክት በይፋ አስጀምሯል:: ‎ ‎ፕሮጀክቱ በአውሮፓ ህብረት የግብርናና ምግብ ፖሊሲዎች፣ ዘላቂነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የEU-አፍሪካ ትብብር ዙሪያ የትምህርት፣ የምርምር እና የፖሊሲ ውይይት ሥራዎችን ለማጠናከር የታለመ ሲሆን፣ በተለይም በኢትዮጵያ የቡናና የሆርቲካልቸር እሴት ሰንሰለቶች ላይ ያተኩራል ተብሏል ። ‎ ‎በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ተወካይ እና የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት እጩ ዶ/ር ታሪኩ ገመዳ አንዳሉት ዩኒቨርሲቲው ለዓለም አቀፍ ትብብር፣ ለአካዳሚክ ልህቀት እና በማስረጃ ላይ ለተመሰረተ ምርምር ያለውን ቁርጠኝነት ዳግም አረጋግጠዋል። ‎ ‎የEU-AGRIWAY ፕሮጀክት መጀመር የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲን ዓለም አቀፋዊ ተሳትፎ ለማጠናከር፣ የምርምር እና የፈጠራ አቅሙን ለማሳደግ እንዲሁም ለዘላቂ ልማት ያለውን አስተዋፅኦ ለማስፋት የሚያስችል አስፈላጊ እርምጃ አንደሆነም ተገልጿል። ‎ ‎ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ

Open in Telegram
Views4,660+7%vs avg
Forwards—
Reactions17
Comments—
#9233Photo
Views5,260+20%vs avg
Forwards—
Reactions41
Comments—
#9232Photo
Views5,250+20%vs avg
Forwards—
Reactions48
Comments—
#9226Photo

ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የe-SHE (e-learning Strengthening Higher Education) የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ ‎******************************************** ‎(ህዳር 08/2019 ዓ.ም ‎​ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ) የሥልጠናው ዓላማ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎች በበይነ መረብ በመታገዝ ትምህርት የሚማሩበትን ሁኔታ ለማጠናከርና ግንዛቤ ለመፍጠር የታለመ ሲሆን፤ ለተማሪዎች ውጤታማነት የሚያግዙ የተለያዩ ትምህርቶችን (Student Success Suite) ተማሪዎች እንዴት ማግኘትና መማር እንደሚችሉ የሚያስረዱ መረጃዎች በሥልጠናው ላይ ተጠቁመዋል። ‎ ‎​በሥልጠናው ላይ የዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው መምህራን የሆኑት መ/ር ቢንያም አለሙ እና መ/ር ንጉሡ ቢተው የሥልጠናውን ሐሳብ ለተማሪዎቹ አጋርተዋል። ከተማሪዎቹ ለተነሱ ጥያቄዎችም መምህራኑ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተውባቸዋል። ‎ ‎​ከዚህ ቀደም ለዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ሥልጠና (Life Skill Training) መሰጠቱ አይዘነጋም። ‎ ‎​ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ‎ ‎ስለ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አዳዳስ መርጃ ለማግኘት እና መረጃ ለማቀበል ‎ዌብሳይት:- https://bhu.edu.et/ ‎ቴሌግራም:- https://t.me/BuleHoraUniversity ‎ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/BuleHoraUniversity ‎Email: [email protected] ‎"Where Indigenous knowledge meets Innovation"

Open in Telegram
Views6,030+38%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—