Посты канала Bule Hora University
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለቅድመ መደበኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት አመራሮች እየተሰጠ ያለው የአቅም ግንባታ ሥልጠና በአግባቡ እየተካሄደ ስለመሆኑ ተገለፀ።
Открыть в Telegramቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የEU-AGRIWAY Erasmus+ Jean Monnet Module ፕሮጀክትን በይፋ አስጀመረ። ***************************************** (ህዳር 11/2019 ዓ.ም ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ) ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በአውሮፓ ህብረት የErasmus+ ፕሮግራም ድጋፍ የሚተገበረውን EU-AGRIWAY (EU Agri-Food Policies, Sustainability and Global Gateway: Implications for Coffee and Horticulture Value Chains in Ethiopia) የተሰኘ የJean Monnet Module ፕሮጀክት በይፋ አስጀምሯል:: ፕሮጀክቱ በአውሮፓ ህብረት የግብርናና ምግብ ፖሊሲዎች፣ ዘላቂነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የEU-አፍሪካ ትብብር ዙሪያ የትምህርት፣ የምርምር እና የፖሊሲ ውይይት ሥራዎችን ለማጠናከር የታለመ ሲሆን፣ በተለይም በኢትዮጵያ የቡናና የሆርቲካልቸር እሴት ሰንሰለቶች ላይ ያተኩራል ተብሏል ። በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ተወካይ እና የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት እጩ ዶ/ር ታሪኩ ገመዳ አንዳሉት ዩኒቨርሲቲው ለዓለም አቀፍ ትብብር፣ ለአካዳሚክ ልህቀት እና በማስረጃ ላይ ለተመሰረተ ምርምር ያለውን ቁርጠኝነት ዳግም አረጋግጠዋል። የEU-AGRIWAY ፕሮጀክት መጀመር የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲን ዓለም አቀፋዊ ተሳትፎ ለማጠናከር፣ የምርምር እና የፈጠራ አቅሙን ለማሳደግ እንዲሁም ለዘላቂ ልማት ያለውን አስተዋፅኦ ለማስፋት የሚያስችል አስፈላጊ እርምጃ አንደሆነም ተገልጿል። ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
Открыть в Telegramውድ የሪሚዲያል ተማሪዎች፣ እንኳን ወደ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በሰላም መጣችሁ! ወደ ዩኒቨርሲቲው ለምትገቡ ተማሪዎች የሚከተሉትን መረጃዎች እናሳስባለን፦ 🚌 የትራንስፖርት አገልግሎት፦ ከዋናው የቡሌ ሆራ መናኸሪያ እስከ ዋናው ግቢ ድረስ ባስ ስለተዘጋጀ፣ ያንን መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። 📝 የምዝገባ ቦታ (Registration)፦ በዋናው ግቢ ውስጥ መመዝገቢያ ቦታው ብሎክ 121 (Block 121) መሆኑን እንገልጻለን። ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
Открыть в Telegramየሐዘን መግለጫ (ህዳር 09/2019 ዓ.ም ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ) በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በግቢ ሰላምና ደህንነት ሥራ አስፈጻሚ ክፍል በባለሙያነት የዩኒቨርስቲው ባልደረባ የነበሩት አቶ ገልቹ ወቲቻ ገልገሎ፣ በድንገት ባጋጠማቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ42 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አቶ ገልቹ ወቲቻ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ዩኒቨርሲቲውን ባላቸው ሙያ ሲያገለግሉ የቆዩ ታታሪና ታማኝ ሠራተኛ የነበሩና የስድስት ሴት እና የሁለት ወንድ ልጆች አባትም ነበሩ። ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በአቶ ገልቹ ወቲቻ ገልገሎ ኅልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል። ፈጣሪ ነፍሳቸውን በገነት ያኑር! ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
Открыть в Telegramለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የe-SHE (e-learning Strengthening Higher Education) የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ ******************************************** (ህዳር 08/2019 ዓ.ም ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ) የሥልጠናው ዓላማ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎች በበይነ መረብ በመታገዝ ትምህርት የሚማሩበትን ሁኔታ ለማጠናከርና ግንዛቤ ለመፍጠር የታለመ ሲሆን፤ ለተማሪዎች ውጤታማነት የሚያግዙ የተለያዩ ትምህርቶችን (Student Success Suite) ተማሪዎች እንዴት ማግኘትና መማር እንደሚችሉ የሚያስረዱ መረጃዎች በሥልጠናው ላይ ተጠቁመዋል። በሥልጠናው ላይ የዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው መምህራን የሆኑት መ/ር ቢንያም አለሙ እና መ/ር ንጉሡ ቢተው የሥልጠናውን ሐሳብ ለተማሪዎቹ አጋርተዋል። ከተማሪዎቹ ለተነሱ ጥያቄዎችም መምህራኑ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተውባቸዋል። ከዚህ ቀደም ለዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ሥልጠና (Life Skill Training) መሰጠቱ አይዘነጋም። ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ስለ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አዳዳስ መርጃ ለማግኘት እና መረጃ ለማቀበል ዌብሳይት:- https://bhu.edu.et/ ቴሌግራም:- https://t.me/BuleHoraUniversity ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/BuleHoraUniversity Email: [email protected] "Where Indigenous knowledge meets Innovation"
Открыть в Telegram