16/03/2019ዓ.ም የስፖርት ውድድር ጥሪን ይመለከታል ለመንግስትና ለግል አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጉዳዩ፡- የአራዳ ክፍለ ከተማ ማኔጅመንት ባደረገው ውይይት ክፍለ ከተማውን ወክለው የሚጫወቱ ተጫዋቾች ( እግር ኳስ) እንዲመለመሉ እና በቋሚ ግንኙነት ልምምድ እንዲያደርጉ እና ጥሩ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በመወሰኑ በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት መምህራን እና ርዕሰ መምህራን ክፍለ ከተማውን ወክላችሁ ለመወዳደር ፍላጎት የላችሁ ሀሙስ በቀን 17/03/2019ዓ.ም በዳ/ምኒሊክ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ከቀኑ 9፡00 ላይ እንድትገኙና እንድትጫወቹ እያሳስብን የትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን እና ስፖርት መምህራን ይህንን ጥሪ የማስተባበር ስራ እንድትሰሩ እናሳውቃለን በክፍለ ከተማው እግር ኳስ አሰልጣኞች አማካኝነት ተወዳዳሪዎች ይመረጣሉ
Open in TelegramPosts of Arada education office
የግል ቅድመ አንደኛ: አንደኛና 2ኛ ደረጃ ር/መምህር አንድ መምህር ይዛችሁ ዛሬ አርብ (11/03/219 ዓ.ም ) በአፄ ፋሲል ት/ቤት በተጠራው ስልጠና ላይ 2:30 በሰዓት ተገኙ። ጠሪ Edify
Open in TelegramForwarded from Worku Zena
በጣም አስቸኳይ፡ እንደምን ዋላቹህ :- መጸዳጃ ቤት ለመገንባት ቦታ ስለመኖሩና አለመኖሩ አጣርታቹህ እስከ ነገ 6:30 ድረስ አሳውቁን የሚያስፈልገው የቦታ ስፋት 116 ካሬ ነው ዝርዝሮቹ የተመረጡ አይደሉም ገና መረጃው ታይቶ የሚወሰን ስለሆነ በጊዜው ያላከ ከውድድር ውጭ ይሆናል ከላይ ያለው መልዕክት ከአዲስ አበባ ከተማ ስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከት/ቤት መሻሻል ፐሮግራም ዳይሬክቶሮት የተላካ አስቸኳይ መልዕክት ስለሆነ በተላከው ቅፅ መሠረት መፀዳጃ ቤት ለማሠራት ቦተ አለን የምትል የመንግስት ት/ቤት ለነገ 10/3/2019ዓ.ም እስከ 4፡00 ድረስ እንድትልኩ ጥብቅ መልክታችንን እያስተላለፍን በተበላው ሰዓት ባይደርስ ግን የመፀዳጃ ቤት ለመሥራት ቦታ እንደሌላችሁ ወይም ቦታው ቢኖርም ለሌላመሥሪያ ወይም ለማሠራት ያልፈለጋችሁ ስለሆነ በማለት ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የላኩ ት/ቤቶችን ብቻ እናስተላልፋለን ፡፡
Open in Telegramእንደምን አመሻችሁ ✍የሰዓት ለውጥ መደረጉን ስለማሳወቅ:- ለመንግስት ት/ቤት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለንብረት ክፍሎች ነገ በቀን 07/3/2019 ዓ.ም 3፡30 እንዲገኙ ተብሎ ጥሪ እንዲተላለፍ መባሉ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ የሰዓት ማስተካከያ ስላደረግን በዚሁ ቀን ከሰዓት 8፡00 በክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት እንዲገኙ መልክቱ እንዲነገራቸው በማለት እንገልፃለን፡፡
Open in Telegramቀን 03/03/2019 ዓ.ም የስብሰባ ጥሪን ይመለከታል፡- ተሳታፊዎች 1ኛ. የክፍለ ከተማ መምህራን ማህበር ስራ አስፈፃሚ አባላት 2ኛ. የክፍለ ከተማ ወተመ ስራ አስፈፃሚ አባላት 3ኛ. የክፍለ ከተማ የአካል ጉዳተኞች ማህበር አባላት 4ኛ. የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት ዋና ር/መምህራን 5ኛ. የግልና የመንግስት ትምህርት ቤት አንድ የስፖርት መምህር 6ኛ. የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊዎች 7ኛ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ስርአተ ትምህርት ቡድን መሪዎች 8ኛ. የክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ 9ኛ. የክፍለ ከተማው ወጣትና ስፖርት ጽ/ቤት ባለሙያዎች 10ኛ. የትምህርት ጽ/ቤት ቡድን መሪዎች 11ኛ. የአንደኛና 2ኛ ደረጃ ክላስተር ሱፐርቪዥን አስተባባሪዎች የስብሰባ ቦታ፡- ኒውኤራ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ቀን፡- 04/03/2019 ዓ.ም ሰዓት፡ ከሰዓት 7፡30 ማሳሰቢያ፡- በውይይቱ ላይ የተጠራችሁ በሙሉ ሰዓት አክብራችሁ እንድትገኙ እያሳሰብን በዕለቱ መቅረትና ማርፈድ የማይቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
Open in Telegramሰላም ር/መምህራን ቅዳሜ ህዳር 5/2019 ዓ.ም የማህደረ ተግባር ክዋኔ ተመዛኝ መምህራን በ3 የመፈተኛ ጣቢያ ድልድይ የተሰራ በመሆኑ ለመምህራን እንድታሳውቁ እያልን ያልተመደበ መምህር ካለ ፈጥናችሁ አሳውቁን።
Open in TelegramForwarded from Yoseph
ቀን 30/02/2019ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ መረጃ መጠየቅን ይመለከታል ለመንግስትና ለግል አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በዚህ ቅፅ መሰረት 1. 1. የአንደኛ ደረጃ በወረዳ በኩል ተጠምሮ ወረዳዎች በተባለው ቅን ለክፍለ ከተማ እንድትልኩልን 2. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለክፍለ ከተማ በስርዓተ ትምህርት ቡድን መሪ በግል ቴሌግራም እስከ ቀን 1/03/2019ዓ.ም እስከ 5፡00 ድረስ እንድትልኩ እናሳስባለን ማሳሰብያ ፡-መረጃ በወቅቱ ባለመላካችሁ ክፍለ ከተማችን እየተወቀሰ በመሆኑ ትኩረት ይሰጠው
Open in Telegramየአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራአስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ኡመር በበኩላቸው የክፍለ ከተማው አስተዳደር ትምህርት ለሀገር ግንባታ መሰረት የሚጣልበት ዘርፍ መሆኑን በመረዳት በርካታ የትምህርት መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ለአገልግሎት ዝግጁ በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጸው በገነት ትምህርት ቤት የሚካሄደው የማስፋፊያ ግንባታ የማህበረሰቡን ጥያቄ እንደሚመልስ በመጠቆም የክፍለ ከተማው አስተዳደር ግንባታው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ጥራቱን ጠብቆ ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲሆን ክትትል የሚያደርግ መሆኑን አስገንዝበዋል።
Open in Telegramበአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በሚገኘው ገነት ቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለ አራት ወለል ህንጻ የማስፋፊያ ግንባታ ተጀመረ። (ጥቅምት 27/2019 ዓ.ም) የማስፋፊያ ግንባታው በሁለት ወር ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የሚደረግ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራአስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ኡመር ጋር በመሆን ግንባታውን አስጀምረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የማስፋፊያ ግንባታው አዲስ አበባ ከተማን ህጻናትን ለማሳዳግ ምቹ አፍሪካዊት ከተማ እንድትሆን በክብርት ከንቲባችን የተቀመጠውን ሌጋሲ ስኬታማ እንዲሆን ከማስቻሉ ባሻገር ትምህርት ተቋማትን ሳቢና ማራኪ በማድረግ የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነትን ለማረረጋግጥ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ውጤታማ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል። ኃላፊው አያይዘውም ግንባታውን በሁለት ወር በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ዝግጁ ለማድረግ እንደሚሰራ ጠቁመው የማስፋፊያ ግንባታውን የሚያካሂዱ ኮንትራክተሮችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካል ግንባታው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ጥራቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
Open in Telegram