Posts of አማዶን
ብነቃስ? ከእንቅልፌ እንዲያባንነኝ እፀልይ ነበር። ኤ..ንድ? (አለችኝ በመሰላቸት) ሆነልኝ። ግልግል። ምሳ የት እንብላ በናትህ? አሁን ግን ፥ ይህም በቂ እንዳልሆነ ተረዳሁ። ምኑ? ስለ እንቅልፍክ እንዳይሆን! በቃ ነቃክ ፀልየክ ምናምን አደል እንዴ? አይገባሽም... ምንድነው የማይገባኝ? ብነቃስ ፥ አይኖቼን ማን ይከፍትልኛል? በማሚ ሞት! @amadonart
Open in Telegram01|02|19 ፀሃይ ብትጠልቅም መጨለም በማይጀምርበት ፥ በወቅቱና በቦታው የማታ አንድ ሰዓት ፥ መሬት ላይ በጀርባዬ ተዘርሬያለሁ። አይኔን ጨፍኜ አዳምጣለሁ። ነፋስ ፊቴን እየደባበሰ ያልፋል። ወፎች የጦፈ ክርክር ይዘዋል። ፌንጣ ፥ የሀገር ሽማግሌ ሳትሆን አትቀርም። ጅቦች ከርቀት ይሳሳቃሉ። አጠገቤ የሚርመሰመስና የሚንኮሻኮሽ ነገር እሰማለሁ። እባብ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን አይን የሚያስከፍት ያህል የሚያስፈራ ነገር የለም። በማስተዋል እተነፍሳለሁ። አየር ወደ ውስጥ አስገባለሁ። አየር ወደ ውጪ አወጣለሁ። እኔ አሁን አለሁ። @amadonart
Open in Telegram"ራስህን ወክለህ ተናገር" ይለኛል ድምፅ። "ራሴ ፈቅዷል?" እላለሁ። "ፈቃድ አያስፈልግም" ይለኛል ድምፅ። "በኋላ ቢያስጠይቀኝ ፥ ማን ዋስ ይሆነኛል?" እላለሁ። "አብደሃል ማለት ነው" ይለኛል ድምፅ። "የፈለከውን ብትል ፥ ሪስክ አልወስድም" እላለሁ። @amadonart 📷 ሐዋሳ ሃይቅ
Open in Telegram"በእንባዬ ታዘብኩት ፥ የቤቴን ፈረሳ ይድን መስሎኝ ነበር ፥ በቅጣት በካሳ" https://youtu.be/ekAR8YxWlaw?si=vf1v1luGONmqK2Ak
Open in Telegramአካሌ ውቤን የት አገኘኋት? ሰፊና ረጅም ግራጫ ሱሪ፣ ስኒከር ጫማ፣ የምታድግበት ተብሎ የተገዛ ዘልዛላ ሸሚዝ... ውስጣውስጥ ሆና የምትቀምሰውን በአንድ እጇ ውሃ በእጆቿ ጣቶች ቀለበት ብቻ አካሌ ውቤ ትንሽ ወዝ ወዝ ከፀጉሯ ጋራ በስልት መደነስ... ፀጉሯ ድሬድ ነው። አካሌ ውቤ አይኗን ጨፍና ጃዝ እየሰማች በስልት መደነስ... ፀጉሯ ረጅም ነው። አካሌ ውቤን አይኗን ጨፍና ጃዝ እየሰማች... የት አገኘኋት? ሚስጥር ነው። @amadonart
Open in Telegram"Don't ask for guarantees. And don't look to be saved in any one thing, person, machine, or library. Do your own bit of saving, and if you drown, at least die knowing you were headed for shore." Fahrenheit 451
Open in Telegramቡናዬን... ሰላም እህት። ቦታው ሰው አለው? የለውም ቁጭ በል። ግን ወሬ አልፈልግም። ይሁን እኔም ወሬ አልፈልግ። ቡና በዝምታ ነው የምጠጣው። ደግ አረግሽ የኔ እህት። እኔም የቡና ፀጥታ እወዳለሁ። ይገርምሃል፤ አንዳንዱ ሰው በዚህ ሰዓት ይመጣና "ድነሃል አልዳንክም?" ይልሃል። አንዳንዱ ቡክ እንድትከፍትለት ይነዛነዝሃል። አንዳንዱ "ቢዝነስ መጀመር አለብህ!" "ቢዝነስ ለመጀመር ፥ ዋናው መወሰን ነው!" ምናምን ብሎ ያስበረግግሃል። ልክ ነሽ። ሰዎች ምንም ፋታ አይሰጡም። በጣም እንጂ። በጣም። 'ፋታ' ትላለህ? የሆነ ቀን የመጀመሪያ ሲኒዬን እየጠጣሁ ፥ አንዱ ጣልቃ ገብቶ የባጥ የቆጡን ሲያወራኝ... ምንም ሳላጣጥመው ቡናዬ አለቀብኝ። ቡናዬ ቢያልቅብኝ ፥ ሌላ አስቀዳሁ። ሰውዬውም ሄደ። ሁለተኛውን በሰላም መቅመስ እንደጀመርኩ ፥ ሌላው መጣና የህይወት ታሪኩን ጀመረ። ይህንንም ሲኒ ሳላጣጥመው አለቀ። ሌላ አስቀዳሁ። ሰውዬውም ሄደ። ሶስተኛውን ፉት ስል ፥ ሌላው መጥቶ ፥ ሌላ ስቃይ አስጀመረኝ። ይህንንም ሳላጣጥመው... ይህንንም ሳላጣጥመው! (እንባዋ በአይኖቿ) ይታይህ ወንድሜ... አራተኛ፣ አምስተኛ፣ ስድስተኛ ስደርስ ፥ ባለቤቱ ተጠርቶ መጣና አስቆመኝ። አብጄ የነበርኩ ይመስለኛል። በሁለት ጋርዶች ተይዤና ተደግፌ ወጣሁ። ልቤ እንደ ነጋሪት ይጐሰም ነበር። አሳዛኝ ነው እህታለም። አንተ ደግሞ 'እህቴ' 'እህቴ' ከማለት ወዲያ ፥ ጨዋታም አታውቅ? የሆነ ነገር በል እንጂ። እሱማ መችስ። ቡናውን በዝምታ ብዬ እንጂ። ወግ እቴ። ያልፈለጉ መምሰል እቴ። ኩል አስተዋይ መምሰል እቴ። የተረጋጉ የማይጨነቁ መምሰል እቴ። የተዝናኑ የማይንገበገቡ መምሰል እቴ። ከቴም ባለ አርምሞ። ከቴም ዝምተኛ ወንድ። ከቴም እኔን የማይመኝ ወንድ። ከቴም እኔ ሳወራው የማይደሰት ወንድ። ከቴም ቡናውን ፍለጋ ብቻ የመጣ ወንድ። (እና ቦታ ቀይሬ ተቀመጥኩ። እኔ ፥ ቡናዬን ፍለጋ ብቻ የመጣሁ ወንድ) @amadonart
Open in Telegram14|01|18 "ቡና ምን ያህል ብትወድ ነው?" ትለኛለች ጠጋ ብላ፤ የጀበና ቡናውን ፥ ወንድ አስተናጋጅ ሲቀዳው እያየች "ወግ ታጠብቂያለሽ አንቺ" አልኳትና "አባ ፥ እጣን አምጣልን እስቲ" አልኩ። በቅንድቡ 'እሺ' ብሎ ሄደ። ደንግጣ ወደ እኔ ዞረች "አንተ የምርህን ነው?" "ምነው?" "የምር እጣኑን እሱ እንዲያመጣው?" "ምን ችግር አለው?" "አንተማ የሆነ ነገር ሆነሃል። ጀዝበሃል።" ይህንን ከማለቷ ፥ ልጁ እጣኑን ይዞ ወደኛ መቅረብ ጀመረ። ከመቀመጫዋ ተስፈንጥራ ተነሳች። ወደ ልጁ ሮጠች። ነፍስ ለማዳን በሚመስል (እጣኑ ነፍስ ቢሆን) በጥንቃቄም፣ በፍጥነትም ተቀበለችው። "ሂድ እወስደዋለሁ" ስትል እሰማታለሁ። እጣኑን እራሷ ይዛው መጣች። ቀጥላ ፥ ለስለስ ባለ ሁኔታ እያስቀመጠችው "አንተማ ነገር አለሙን ትተኸዋል። በል አሁን ጠጣ" አለች። ቡናውን ጨርሼዋለሁ። ይህንን ስታይ "ጠጣኸው?" አለች በሌላ ድንጋጤ "ታዲያ ምን ላረገው ነበር?" "ያለ እጣን? አንተ ሰውዬ... ምን ነካህ?" "ቆይማ" ብያት አስተናጋጁን በአይኔ መፈለግ ጀመርኩ። "ምንድነው?" አለች እጅግ በመቁነጥነጥ። በመጨነቅ። ወደዛ ወደዚህ በመማተር። "ቡና ልደግም" "ተውው እራሴ እሄዳለሁ" ብላ ከወንበሯ ዘለለች። "እዚህ ሀገር ጤናም የላችሁ" "ኧራ... አንቺ ሴትዮ ፌሚኒስት አልነበርሽም ወይ?" "ምን አገናኘው? ምኑ ይገናኛል? ምኑንና ምኑን ታገናኘዋለህ?" እና የጀበና ቡናውን ይዛው መጣች። @amadonart
Open in Telegram12|01|18 ውቂያኖስ ዳር ቁጭ ብላ ትተክዛለች። አልፎ አልፎ ዘወር ትላለች። ርቀቴን ጠብቄ በፍርሃት አያታለሁ። "ከእኔ የተሻለ ፥ ሰው ከተገኘብኝ ፍቅር ወርቅ አምባር ነው መውለድ ነው ያለብኝ" አለችና ተነሳች። እንደ ነፋስ እያፏጨች ፥ ወደ እኔ አቅጣጫ መሮጥ ጀመረች። ልትይዘኝ። ነፍስ ግቢ፣ ነፍስ ውጪ ተፈተለኩ። ከዛ ግን ቆምኩ። እና አልኳት "ግን እኮ እኔ መውለድ አልችልም" "አውቀህ ነው!" አለች። "ምን አስዋሸኝ?" "ዶክተር አይቶሃል?" "አዎ" "ማን የሚባል?" "ስሙን እንጃ..." "ምን የሚመስል?" "የእባብ ሽማግሌ" "በቃ እሱ ካለማ። እሱማ ካለ..." ውቂያኖስ ዳር ቁጭ ብላ ፥ በዝምታ ታለቅሳለች። አልፎ አልፎ ትባትታለች። ርቀቴን ጠብቄ በፍርሃት አያታለሁ። "ከእኔ የተሻለ ፥ ሰው ከተገኘብኝ ፍቅር ወርቅ አምባር ነው ይቅር ግድ የለብኝ" አለችና አወላልቃ ውሃው ውስጥ ገባች። በእርጋታ እየዋኘች... እየዋኘች... ከእይታ እየራቀች... እየጠፋች ሄደች። ግን መስሎኝ ነው። እንደገና ውቂያኖሱ ዳር ቁጭ ብላለች። ቀኑ ዘፈኑ ነው። ዘፈኑም ለዘላለም ተከፍቷል። @amadonart
Open in Telegram09|01|19 በፍቅሯ መዳኔን ፥ መጀመሪያ ለካህን ማሳየት እንዳለብኝ ስጠይቃት ትስቃለች። አያታለሁ። በፍቅሯ የተነሳ ፥ "ምድርን ከአትላስ ጋራ ተሸክሜያለሁ" የሚለውን ደቃቃ ብርቱ (በዕውቀቱ ስዩም የተባለ) እሱን ጨምሬ ልሸከም እንደምችል 'ላሳይሽ?' ስላት ትስቃለች። አያታለሁ። በፍቅሯ የተነሳ ፥ ጥልቅ ሰላም በውስጤ እንደሰፈነና ነፋስ ብሆን ሁሉንም የአለም ጦርነቶች ማጥፋት እንደማይከብደኝ ስነግራት ትስቃለች። አያታለሁ። በፍቅሯ የተነሳ ፥ የተስፋ ባሪያ እንደሆንኩና 'የለም' ስለው የኖርኩትን ነገር እያገለገልኩ እንዳለሁ ስነግራት ትስቃለች። አያታለሁ። ቆንጆ ሴት ትስቃለች። አያታለሁ። @amadonart
Open in Telegram3|13|18 ለብዙ የህልም ሰዓታት ፥ ሳለቅስና ሳለቃቅስ በዝምታ ሲሰማኝ ቆይቶ "ፓራራም... ታራራም... ብዙ ወሬ ወሬ ወሬ... ብዙ ሱሱሱሱ... ልትድን ትወዳለህ?" አለኝ። "እ?" (ሰምቻለሁ) "ልትድን ትወዳለህ?" ለመመለስ ጊዜ ፈጀብኝ... @amadonart
Open in Telegram23|12|18 "አቶ ደስታን ፈልጌ ነበር" አለች። እኔ ነኝ ደስታ! እርስዎ ነዎት ደስታ? እኔ ነኝ! ካላመንሽ ንኪኝ። ዳስሽኝ። ጨብጪኝ። አይ! አይ! አይ! አይሆንም። ለምን አይሆንም? "ፈልጊ" እንጂ "አግኚ" አላሉኝም እርስዎን። ግን አገኘሽኝ። ግን አላገኘሆትም። @amadonart
Open in Telegramእንዲሁም በአንድ ወቅት... አይኔን ጨፍኜ ፥ ትናንሽ ሳሮች በሚኖሩበት መሬት በጀርባዬ ተኝቼ ነበር። ከላይ ከሾላው ዛፍ የሚነፍሰውን ነፋስ ፥ እየጠጣሁና ጥላውን እያጣጣምኩ ፥ የሚከተለውን 'እውነት' አልኩ:- ይሄ... (የተፈጥሮ ውበት፣ የዚህች አለም ውበት) ከየትኛውም ክፋት (የአለም ክፋት) ይበልጣል። @amadonart
Open in Telegram09|12|18 እንዲያው ልበል እንጂ 'አደ'ኩ ፤ ዘመን አየሁ በእያንዳንዷ ስሜት እኩል ተጐበኘሁ ኖርኩኝ ፤ ልምድ አካበትኩ አወ'ኩ ብዙ ነገር አለምን ከመጥላት ከልብ እስከ ማፍቀር...' የማታ የማታ ዋናውን አሰብኩት... እራሴን ናፈቅኩት። @amadonart
Open in Telegram