Кабинет

Посты канала አማዶን

сначала новые

#1672Текст
Просмотры482−7%к среднему
Пересылки—
Реакции17
Комментарии—
#1670Текст
Просмотры922+78%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
#1669Фото
Просмотры915+77%к среднему
Пересылки—
Реакции16
Комментарии—
#1666Текст
Просмотры894+73%к среднему
Пересылки—
Реакции11
Комментарии—
#1664Текст

ቡናዬን... ሰላም እህት። ቦታው ሰው አለው? የለውም ቁጭ በል። ግን ወሬ አልፈልግም። ይሁን እኔም ወሬ አልፈልግ። ቡና በዝምታ ነው የምጠጣው። ደግ አረግሽ የኔ እህት። እኔም የቡና ፀጥታ እወዳለሁ። ይገርምሃል፤ አንዳንዱ ሰው በዚህ ሰዓት ይመጣና "ድነሃል አልዳንክም?" ይልሃል። አንዳንዱ ቡክ እንድትከፍትለት ይነዛነዝሃል። አንዳንዱ "ቢዝነስ መጀመር አለብህ!" "ቢዝነስ ለመጀመር ፥ ዋናው መወሰን ነው!" ምናምን ብሎ ያስበረግግሃል። ልክ ነሽ። ሰዎች ምንም ፋታ አይሰጡም። በጣም እንጂ። በጣም። 'ፋታ' ትላለህ? የሆነ ቀን የመጀመሪያ ሲኒዬን እየጠጣሁ ፥ አንዱ ጣልቃ ገብቶ የባጥ የቆጡን ሲያወራኝ... ምንም ሳላጣጥመው ቡናዬ አለቀብኝ። ቡናዬ ቢያልቅብኝ ፥ ሌላ አስቀዳሁ። ሰውዬውም ሄደ። ሁለተኛውን በሰላም መቅመስ እንደጀመርኩ ፥ ሌላው መጣና የህይወት ታሪኩን ጀመረ። ይህንንም ሲኒ ሳላጣጥመው አለቀ። ሌላ አስቀዳሁ። ሰውዬውም ሄደ። ሶስተኛውን ፉት ስል ፥ ሌላው መጥቶ ፥ ሌላ ስቃይ አስጀመረኝ። ይህንንም ሳላጣጥመው... ይህንንም ሳላጣጥመው! (እንባዋ በአይኖቿ) ይታይህ ወንድሜ... አራተኛ፣ አምስተኛ፣ ስድስተኛ ስደርስ ፥ ባለቤቱ ተጠርቶ መጣና አስቆመኝ። አብጄ የነበርኩ ይመስለኛል። በሁለት ጋርዶች ተይዤና ተደግፌ ወጣሁ። ልቤ እንደ ነጋሪት ይጐሰም ነበር። አሳዛኝ ነው እህታለም። አንተ ደግሞ 'እህቴ' 'እህቴ' ከማለት ወዲያ ፥ ጨዋታም አታውቅ? የሆነ ነገር በል እንጂ። እሱማ መችስ። ቡናውን በዝምታ ብዬ እንጂ። ወግ እቴ። ያልፈለጉ መምሰል እቴ። ኩል አስተዋይ መምሰል እቴ። የተረጋጉ የማይጨነቁ መምሰል እቴ። የተዝናኑ የማይንገበገቡ መምሰል እቴ። ከቴም ባለ አርምሞ። ከቴም ዝምተኛ ወንድ። ከቴም እኔን የማይመኝ ወንድ። ከቴም እኔ ሳወራው የማይደሰት ወንድ። ከቴም ቡናውን ፍለጋ ብቻ የመጣ ወንድ። (እና ቦታ ቀይሬ ተቀመጥኩ። እኔ ፥ ቡናዬን ፍለጋ ብቻ የመጣሁ ወንድ) @amadonart

Открыть в Telegram
Просмотры944+82%к среднему
Пересылки—
Реакции29
Комментарии—
#1661Текст

14|01|18 "ቡና ምን ያህል ብትወድ ነው?" ትለኛለች ጠጋ ብላ፤ የጀበና ቡናውን ፥ ወንድ አስተናጋጅ ሲቀዳው እያየች "ወግ ታጠብቂያለሽ አንቺ" አልኳትና "አባ ፥ እጣን አምጣልን እስቲ" አልኩ። በቅንድቡ 'እሺ' ብሎ ሄደ። ደንግጣ ወደ እኔ ዞረች "አንተ የምርህን ነው?" "ምነው?" "የምር እጣኑን እሱ እንዲያመጣው?" "ምን ችግር አለው?" "አንተማ የሆነ ነገር ሆነሃል። ጀዝበሃል።" ይህንን ከማለቷ ፥ ልጁ እጣኑን ይዞ ወደኛ መቅረብ ጀመረ። ከመቀመጫዋ ተስፈንጥራ ተነሳች። ወደ ልጁ ሮጠች። ነፍስ ለማዳን በሚመስል (እጣኑ ነፍስ ቢሆን) በጥንቃቄም፣ በፍጥነትም ተቀበለችው። "ሂድ እወስደዋለሁ" ስትል እሰማታለሁ። እጣኑን እራሷ ይዛው መጣች። ቀጥላ ፥ ለስለስ ባለ ሁኔታ እያስቀመጠችው "አንተማ ነገር አለሙን ትተኸዋል። በል አሁን ጠጣ" አለች። ቡናውን ጨርሼዋለሁ። ይህንን ስታይ "ጠጣኸው?" አለች በሌላ ድንጋጤ "ታዲያ ምን ላረገው ነበር?" "ያለ እጣን? አንተ ሰውዬ... ምን ነካህ?" "ቆይማ" ብያት አስተናጋጁን በአይኔ መፈለግ ጀመርኩ። "ምንድነው?" አለች እጅግ በመቁነጥነጥ። በመጨነቅ። ወደዛ ወደዚህ በመማተር። "ቡና ልደግም" "ተውው እራሴ እሄዳለሁ" ብላ ከወንበሯ ዘለለች። "እዚህ ሀገር ጤናም የላችሁ" "ኧራ... አንቺ ሴትዮ ፌሚኒስት አልነበርሽም ወይ?" "ምን አገናኘው? ምኑ ይገናኛል? ምኑንና ምኑን ታገናኘዋለህ?" እና የጀበና ቡናውን ይዛው መጣች። @amadonart

Открыть в Telegram
Просмотры1 050+103%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
#1660Текст

12|01|18 ውቂያኖስ ዳር ቁጭ ብላ ትተክዛለች። አልፎ አልፎ ዘወር ትላለች። ርቀቴን ጠብቄ በፍርሃት አያታለሁ። "ከእኔ የተሻለ ፥ ሰው ከተገኘብኝ ፍቅር ወርቅ አምባር ነው መውለድ ነው ያለብኝ" አለችና ተነሳች። እንደ ነፋስ እያፏጨች ፥ ወደ እኔ አቅጣጫ መሮጥ ጀመረች። ልትይዘኝ። ነፍስ ግቢ፣ ነፍስ ውጪ ተፈተለኩ። ከዛ ግን ቆምኩ። እና አልኳት "ግን እኮ እኔ መውለድ አልችልም" "አውቀህ ነው!" አለች። "ምን አስዋሸኝ?" "ዶክተር አይቶሃል?" "አዎ" "ማን የሚባል?" "ስሙን እንጃ..." "ምን የሚመስል?" "የእባብ ሽማግሌ" "በቃ እሱ ካለማ። እሱማ ካለ..." ውቂያኖስ ዳር ቁጭ ብላ ፥ በዝምታ ታለቅሳለች። አልፎ አልፎ ትባትታለች። ርቀቴን ጠብቄ በፍርሃት አያታለሁ። "ከእኔ የተሻለ ፥ ሰው ከተገኘብኝ ፍቅር ወርቅ አምባር ነው ይቅር ግድ የለብኝ" አለችና አወላልቃ ውሃው ውስጥ ገባች። በእርጋታ እየዋኘች... እየዋኘች... ከእይታ እየራቀች... እየጠፋች ሄደች። ግን መስሎኝ ነው። እንደገና ውቂያኖሱ ዳር ቁጭ ብላለች። ቀኑ ዘፈኑ ነው። ዘፈኑም ለዘላለም ተከፍቷል። @amadonart

Открыть в Telegram
Просмотры919+77%к среднему
Пересылки—
Реакции11
Комментарии—
#1659Текст
Просмотры952+84%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
#1658Текст
Просмотры1 090+110%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#1655Текст
Просмотры1 330+157%к среднему
Пересылки—
Реакции11
Комментарии—
#1653Текст
Просмотры1 310+153%к среднему
Пересылки—
Реакции24
Комментарии—
#1652Текст
Просмотры1 400+170%к среднему
Пересылки—
Реакции13
Комментарии—