የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተናን ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ ተመዛኞች በሙሉ ___ የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቃችሁ ጤና ባለሙያዎች በታህሳስ ወር 2019 ዓ.ም የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተና ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም መረጃችሁን ከዚህ ቀደም ወደ ሲስተም ያላስገባችሁ ነባር እና አዲስ ተመዛኞች ከህዳር 21/2019 እስከ ህዳር 30/2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ ይህንን https://hple.moh.gov.et/ ማስፈንጠሪያ/Link/ በመጫን የብሄራዊ መታወቂያ መለያ ቁጥር (National ID FAN 16 Digit) በማስገባት አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት ለምዝገባ እንድትዘጋጁ እናሳስባለን፡፡ ማሳሰቢያ፡- - ይህ መረጃን የማስተሳሰር ሂደት እንዳለቀ የፈተና ጣቢያ መረጣ ሂደት እንደሚቀጥል እናሳውቃለን፡፡ - የመውጫ ፈተና ተፈትናችሁ ያለፉችሁ እና ስማችሁ ወደ ሲስተም ያልገባላችሁ ተመዛኞች የስም ዝርዝራችሁን በተማራችሁበት ተቋም አማካኝነት ወደ ሲስተም ማስጫን የሚጠበቅባችሁ መሆኑን እናሳስባለን። @alluexams Website: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health, Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia LinkedIn: lnkd.in/ewFJ6V
Open in TelegramViews growthHide views growth
Views growth
Hours after publication
Show as table
| Hours after publication | Views |
|---|---|
| 0 h | 0 |
| 19 h | 1,120 |
| 26 h | 1,270 |
- After 24 hours1,270
- Total to date1,270