አልመውሪዱል ዓዝብ ክፍል : 75 አቅሪው : ሸይኽ ዩሱፍ አህመድ (ሃፊዞሁሏህ) የሚቀራባቸው ቀናቶች : ሀሙስ : ጁምዓ : ቅዳሜ : እሁድ ሰአት : ከመግሪብ እስከ ዒሻ ቦታ : ባህርዳር, ፈትህ መስጂድ በተጨማሪም : በባህር ዳር አህለልሱና መሻይኾች የቴሌግራም ገፅ https://t.me/alateriqilhaq የኪታቡ ሊንክ https://t.me/alateriqilhaq/6709 كن على بصيرة
Open in TelegramPosts of የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
♦️ዛሬ እውቀት ወይስ ወሬ ነው የበዛው? አል-ፋሳዊ - ረሂመሁሏህ - እንዲህ ብሏል :- "ሃማድ የሚከተለውን እንደተናገረ ሱለይማን ነገረን :- 'ዛሬ እውቀት በብዛት ነው ያለው ወይስ ቀላል ሆኗል?' የሚል ጥያቄ አዩብ ቀረበለት። አዩብም እንዳህ አለ:- 'ዛሬ ብዙ ንግግር አለ ፤ ከዚህ በፊት ግን ብዙ እውቀት ነበር።' 📚 "المعرفة والتاريخ ٢٣٢/٢ ዶክተር ሸይኽ ሁሴን - ሐፊዞሁሏህ - በዚህ ላይ አስተያየት ሰጠዋል :- "ዛሬ በአሊሞች እና በህዝብ መካከል ብዙ ወሬ እና ሐብት ተስፋፍቷል ፤ እውቀት ደግሞ እጅግ አናሳ ሆኗል። ለእውቀት ከመድረሳቸው በፊት አመራር ላይ ተቀምጠው ፣ በትእቢት እና በመንደላቀቅ የሚናገሩ ስንቶቹ ናቸው? በነብዩ መንሐጅ ላይ የሆኑ የእውቀት ባለቤቶችና ሙሐዲሶች የት ነው ያሉ? በመጽሐፍ ወይም ከምድር በታች ካልሆነ በስተቀር ፈጽሞ አላያቸውም። አሏህ እስከሞት ድረስ በቁርአንና በሱና ላይ ጸንተን የምንኖር ያድርገን! https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة
Open in Telegramአልመውሪዱል ዓዝብ ክፍል : 74 አቅሪው : ሸይኽ ዩሱፍ አህመድ (ሃፊዞሁሏህ) የሚቀራባቸው ቀናቶች : ሀሙስ : ጁምዓ : ቅዳሜ : እሁድ ሰአት : ከመግሪብ እስከ ዒሻ ቦታ : ባህርዳር, ፈትህ መስጂድ በተጨማሪም : በባህር ዳር አህለልሱና መሻይኾች የቴሌግራም ገፅ https://t.me/alateriqilhaq የኪታቡ ሊንክ https://t.me/alateriqilhaq/6709 كن على بصيرة
Open in Telegram♦️እውነት የሚታወቀው በማስረጃ ነው አልባኒ - ረሂመሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :- "እውነት የሚታወቀው በብርሃኑና በማስረጃው እንጂ፣ በተራኪውና በተናጋሪው አይደለም። በፍትሃዊ ሰዎች እንጂ ፣ በጭፍን ጥላቻና በዘፈቀደ በሚያምኑ ሰዎች አይደለም።" 📚 سؤال وجواب (٢٨) https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة
Open in TelegramForwarded from قناة الشيخ الدكتور حسين بن محمد
قال العلامة الألباني -رحمه الله-: " الحق يعرف بِنوره ودلائله؛ لا بِحاكيه وقائله عند أهل الإنصاف، وليس عند ذوي التعصب والاعتساف ". 📚سؤال وجواب (٢٨)
Open in Telegram" التعليقات الأثرية على شرح عقيدة الواسطية " " አተዕሊቃቱል አሰሪያህ አላ ሸርሂ አቂደቲል ዋሲጢያህ " አዘጋጅ :- ሸይኽ አህመድ ብን የህያ አንነጂሚ ደርሱን የሚሰጠው :- በሸይኽ ዩሱፍ አህመድ ክፍል= 51 የባህርዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ https://t.me/alateriqilhaq የኪታቡ ሊንክ https://t.me/alateriqilhaq/6761 كن على بصيرة
Open in Telegram🔷ለአሏህ ብሎ መስራት ፣ ከአሏህ ወልዮች ያስመድባል ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያ - ረሂመሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :- "በቅንነት ለአሏህ ብሎ ሃይማኖታዊ ተግባራትን የሚፈጽም ከሆነ ፣ ጥንቁቅና የቋሚ ጸጋ ባለቤት ከሆኑት የአሏህ ወልዮች ይሆናል።" 📚 الفتاوى ٨/١ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة
Open in Telegram♦️ተፎካካሪዎች ሊፎካከሩበት የሚገባ ጉዳይ ኢብን አልቀይም - ረሂመሁሏህ - እንዲህ ብሏል :- "አንድ አሊም እውቀቱን ለሌሎች አካፍሎ ከሞተ ፣ ምንዳው ሁሌም ሳይቋረጥ ይቀጥላል ፤ ዘወትር ሲታዎስም ይኖራል። ይህ ለእርሱ ሁለተኛ ሂዎቱ ፣ ሌላው ህልውናው ነው። እናም ይህ ተፎካካሪዎች ሊፎካከሩበት ፣ ፈላጊዎች ሊፈልጉት የሚገባ ጉዳይ ነው።" 📚 مفتاح دار السعادة ٤١٦/١ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة
Open in Telegram" التعليقات الأثرية على شرح عقيدة الواسطية " " አተዕሊቃቱል አሰሪያህ አላ ሸርሂ አቂደቲል ዋሲጢያህ " አዘጋጅ :- ሸይኽ አህመድ ብን የህያ አንነጂሚ ደርሱን የሚሰጠው :- በሸይኽ ዩሱፍ አህመድ ክፍል= 50 የባህርዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ https://t.me/alateriqilhaq የኪታቡ ሊንክ https://t.me/alateriqilhaq/6761 كن على بصيرة
Open in Telegram“የአሏህን ብርሀን፣ በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ፡፡ አሏህም - ከሀዲዎች ቢጠሉም እንኳ - ብርሀኑን መሙላትን እንጅ ሌላን አይፈቅድም፡፡” (አል-ተውባ፣ 32) ስልጣን ላይ ያለው መንግስት፣ የፈለገ ቢጀነጅኑት እንደ አቶ ደርግ ሮጦ የሚያስር፣ ተንደርድሮ ቃታ የሚስብ አይደለም፡፡ ሙፍቲ - ይህ አልገባቸውም፡፡ መንግስት ወይም መንግስትን የሚዘውረው የገዢው ፓርቲ “አይዞህ፣ አይዞህ” ሲል፣ ሁሌምና በሁሉም መንገድ አለመሆኑም ለሙፍቲ አልተገለጠላቸውም… ከንቲባውና ሌሎቹ የመንግስት ሀላፊዎች፣ መጅሊሱ የጀመረው ህገወጥ አካሄድ አግባብ አለመሆኑን ገልፀው፤ በህገ መንግስቱ መሰረት፣ መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ እንደማይገባና ማንኛውም የሀይማኖት ቡድን የራሱን እምነትና አመለካከት በሌላው ላይ መጫንና ማስገደድ እንደማይችል መደንገጉን አብራሩ፡፡ መንግስት ጣልቃ የሚገባው በዜጎች መካከል ሁከት እና ግጭት ተፈጥሮ፣ ያገሪቱ ሰላም እንዳይታወክና በአጥፊው ወገን ላይ በህግ አግባብ እርምጃ ለመውሰድ መሆኑን በማሳሰብ፤ ህገ መንግስቱንና ህጉን መሰረት በማድረግ ዜጎች እምታቸውን በሰላማዊ መንገድ የማራመድ መብት ያላቸው መሆኑን አስረግጠው ገለፁ፡፡ “የውይይት” መድረኩም በዚሁ ተዘጋ፡፡ አሏህ በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ ይላል፡- “አሴሩ፤ አሏህም አሴረባቸው (ሴራቸውን አከሸፈባቸው)፡፡ አሏህም ከሴረኞች ሁሉ በላጭ ነው፡፡” (አሊ ኢምራን 54) ዝግጅት በዶክተር ጀማል ሙሐመድ - ሐፊዞሁሏህ - https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة
Open in Telegram🔻🔻የተውሂድ ጠላቶች ሴራ🔻🔻 🔴🔴 የሙፍቲ የአቋም መግለጫi 🔴🔴 🟣 ጥያቄ፡- የተውሂድ ሰዎች ሲሞቱ፣ ከሙስሊሞች መቃብር እንዳይቀበሩ ሙፍቲና መጅሊሳቸው ማዘዝ ይችላሉን⁉️ ባለፉት ፅሁፎች፣ ወደ ተሟሟቀ ውይይት መግባት ጀምሮ የነበረውን ስብሰባ፤ ሙፍቲ በማንአለብኝነት ስሜት በማቋረጥ፣ ፈትዋ መስጠት መጀመራቸውን ጠቅሰናል፡፡ አንዱና ዋነው ፈትዋቸውም - ቃል በቃል - የሚከተለው ነው፡- “ኢስቲጋሳ ቢገይሪሏህ (ከአሏህ ውጭ ያለን አካል መንፈሳዊ እርዳታ መጠየቅ) ይቻላል፡፡የሚዳረሱበት አካል በህይወት ያለም ይሁን የሞተ፤ አቅለኛም ይሁን አቅል የሌለው (እብድ) ተወሱል (መዳረስ) ይበቃል ፡፡ ተወሱል (መዳረስ) ከአሏህ ውጭ በሆነ አካል ይበቃል፡፡” ይህ ፈትዋ ራሱ ከኢስላም የሚያስወጣ ሆኖም እያለ፣ ሙፍቲ “ሞቼ እገኛለሁ እንጂ ትክክለኛ እምነት ነው” ካሉ፣ እሳቸውም ሆኑ ሌሎች ሱፍያና አህባሾች - በኢትዮጵያ ህገ መንግስት መሰረት - የፈለጉትን የማምለክ ሙሉ መብታቸው የተከበረ ነው፡፡ ችግር የመጣው፣ ይህን እምነታቸውን ሌላውም ሙስሊም - ወደደም፣ ጠላም - “መከተልት አለበት” ሲሉ ነው፡፡ በባህር ዳሩ ስብሰባም የሆነው ይሄው ነው፡፡ “ፈትዋ” ተብዬውን ከሰጡ በኋላ፣ “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ይህን መቀበል አለበት” የሚል ውሳኔ አስተላለፉ፡፡ ምን ይሄ ብቻ? በዚሁ መድረክ ላይ፣ ከዚህ የከፉ ተጨማሪ ውሳኔዎችንም አስተላለፉ፡፡ በዚህ እሳቸው ፈትዋ ብለው በሰጡት ጉዳይ ላይ (“ከአሏህ ውጭ ያለን አካል መንፈሳዊ እርዳታ መጠየቅ ይቻላል” በሚለው) ያላመነ ሰው፣ ሙስሊም አለመሆኑን በአደባባይ አወጁ፡፡ 🟣 አደገኛው የአቋም መግለጫ ሙፍቲ በዚህም አልበቃቸው፡፡ ይልቁንም ከስብሰባው በፊት በጓዳ ያፃፉትን “የአቋም መግለጫ” ተብዬ ፅሁፍ - በወቅቱ የሰላም በር መስጊድ ኮሚቴ አባል የነበረ - ሁሴን እድሪስ የሚባል ግለሰብ መድረክ ላይ ቆሞ እንዲያነብ አዘዙ - ተወያይ የሆኑት አካላት ከእሳቸው ጋር ሊስማሙ ይቅርና ሀሳባቸውን በወጉ ባልገለፁበት ሁኔታ፡፡ ሰውዬው ገና ማንበብ ሲጀምር፣ አህለ ሱናዎችን ወክለው የገቡት ተሳታፊዎች፣ ስብሰባውን ረግጠው ወጡ - የጋራ አቋም በምንም ጉዳይ ላይ ባልተያዘበት ሁኔታ የሚነበበው ፅሁፍ፣ የአቋም መግለጫ ሳይሆን፣ የሙፍቲና የመጅሊሳቸው የፍላጎት መግለጫ ሆኖ ስላገኙት‼️ በመግለጫው ፍፁም የማይስማሙ መሆናቸውን ለመግለፅ ያላቸው ብቸኛ አማራጭ፣ አቋርጦ መውጣት ስለሆነም ጭምር‼️ “የአቋም መግለጫ” ተብዬው ፅሁፍ፣ እጅግ አደገኛ ሀሳቦችን የያዘ ሲሆን፤ የፈትዋውን ሰነድ ባልተቀበለ ሰው ላይ የሚከተሉት እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ያውጃል፡- ❌️ ሙስሊም ስላልሆነ በሙስሊም መቃብር እንዳይቀበር፣ ❌️ ሶላተል ጀናዛ እንዳይሰገድበት፣ ❌️ በማንኛውም የማህባራዊ አገልግሎት - እንደ ሀዘንና ሰርግ የመሳሰሉት- ላይ እንዳይሳተፍ፣ ❌️ መንግስትም፣ “ኢስቲጋሳ ቢገይሪላህ አንቀበልም” ያሉ ቡድኖች የሚጠቀሙበትን መስጊዳቸውን እንዲዘጋና እንቅስቀሴያቸውን እንዲያስቆም እና ❌️ ስለተውሂድ ትምህርት የሚሰጡና የሚያስተባብሩ ኡለሞች እና ሙስሊም ወጣቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወስድ፡፡ وَقَدْ مَكَرُوا مَكْرَهُمْ وَعِنْدَ اللَّهِ مَكْرُهُمْ وَإِنْ كَانَ مَكْرُهُمْ لِتَزُولَ مِنْهُ الْجِبَالُ ሴራቸውንም በእርግጥ አሴሩ፡፡ ሴራቸውም አሏህ ዘንድ (የታወቀ) ነው፡፡ ሴራቸውም ተራራዎችን የሚያስወግድ አልነበረም፡፡ (ኢብራሂም 46) የአቋም መግለጫው የፈለጉትን እምነት የመከተል መብታቸው በህገ መንግስቱ የተረጋገጠላቸው ዜጎች እምነት እንዲጨፈለቅ የሚጠይቅ ብቻ ሳይሆን፣ “የእኔን እምነት ያልተከተለ፣ ሙስሊም አይደለም” ከማለትም አልፎ፣ በጉልበት ቀብር እስከ መከልከልና ማህበራዊ ትስስርን እስከ መበጣጠስ የደረሰ ነውና ሽብር የሚነዛ ሰነድ ነው፡፡ የክልሉ መንግስት ልሳን የሆነችው በኩር ጋዜጣ በበኩሏ፣ በወቅቱ “ፅንፈኞቹ የውይይቱን መድረክ ረግጠው ወጡ” አይነት ዘገባ ማቅረቧን አስታውሳለሁ፡፡ ሙፍቲ በፈላጭ-ቆራጭነት ስብሰባውን በመምራት፣ የፈላጭ-ቆራጭ ውሳኔ በማሳለፍና በጓዳ ያፃፉትን ኹከትና ብጥብጥ የሚጋብዝ ደርጋዊ የአቋም መግለጫ ሲያስነብቡ፣ እትዬ በኩር በአይኗ በብረቱ አይታ ስታበቃ፣ እንዲህ ያለ፣ ራሱ ፅንፈኛ የሆነ ዘገባ ለምን ፃፈች? በእሷ ቤት መጅሊሱን ሳይሆን፣ ጌታዋን - መንግስትን - ማስደሰቷ ነው፡፡ "ውሻ በበላበት ይጮሀል" አይደል ተረቱ‼️ 🟣 ሲጠቃለል፡- “መንግስት ከጎኔ ነው” በሚል ስሜት፣ የልብ ልብ ስለተሰማቸው፣ ስብሰባውን በፈለጉት መንገድ እያሽከረከሩ ሲመሩ የቆዩት ሙፍቲ፤ ተደጋጋሚ ማኖዎችን ነኩ - “ይቅር” ሊባሉ የሚችሉና “ይቅር” ሊባሉ የማይችሉ ማኖዎችን፡፡ ⭕️ ማኖ አንድ - ስብሰባውን የቡድናቸውን ሐሳብ ለማቀንቀን ብቻ ሳይሆን የተቃራኒዎቻቸውን ድምፅ ለማፈን ተጠቅመውበታል፡፡ ሆኖም ይህ ማኖ መንካታቸው፣ “ይቅር” የሚባል ነው - መቼስ መጅሊሱ የኢህአዴግ የጡት ልጅ አይደል⁉️ አባት በልጁ አይጨክን ነገር‼️ ⭕️ ማኖ ሁለት - መጅሊሱ የተውሂድ ተከታዮችን፣ ቢያንስ በሶስት ወንጀሎች ሲከሳቸው ኖሯል:- 1️⃣ “አዲስ ሀይማኖት አምጥተዋል”፤ 2️⃣ “አሸባሪ ናቸው”፣ 3️⃣ “ለመንግስት ስጋት ናቸው”በማለት፡፡ ሆኖም በስብሰባው ላይ “ወሀብያዎቹ” በየጊዜው ለመንግስት ሲከሰሱባቸው ከነበሩት ወንጀሎች መካከል፣ የተጋለጠ ወይም ይፋ የሆነ አንድም ነገር የለም፡፡ ሙፍቲም ይህ “ወሀብያዎቹ” የሚከሰሱበት ወንጀል፣ ሊጋለጥ በሚችልበት መንገድ ስብሰባውን መምራት አልቻሉም - ማኖ ሁለት፡፡ በስብሰባው አዳራሽ ይፋ የሆነው ነገር፣ “ወሀብያዎች” እየተባሉ የሚከሰሱት ሰዎች፤ በእስልምና ሀይማኖታቸው መፃህፍት ያልታዘዙትን ነገር እንዲሁም በባህልና በልማድ የመጡ እምነቶችን “አንከተለም” ማለታቸው ብቻ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ በዚህ በኩል ያለውንም ማኖ ፖለቲከኞቹ “ይቅር” አሉ - መቼስ አንጀታቸው በመጅሊስ ለመጨከን ይቸገር የለ‼️ ⭕️ ማኖ ሶስት - “መግለጫ” ተብዬው፣ ከፈረሱ የቀደመ ጋሪ ብቻ ሳይሆን ደርጋዊ ነው፡፡ ሙፍቲ - መሟሟቅ የጀመረውን ውይይት “ፈትዋ” በማለት ማጨናገፋቸው ሳያንስ፣ ከመጅሊሶቻቸው ጋር በጓዳ ያስፃፉትን “መግለጫ” ተብዬ አስነበቡ፡፡ ይሄኛው ማኖ የሚታለፍ አልሆነም፡፡ በዚህ ደርጋዊ መግለጫ፣ ከንቲባው ማርዬና አብረውት ያሉት ባለስልጣናት ተቆጡ - “ውይይቱ ሳይቋጭ እንዴት እንዲህ ይደረጋል?” በማለት፡፡ የመግለጫው ይዘትም ሰላምና ስምምነትን የሚያጠናክር ሳይሆን፣ በሙስሊሞች መካከል ግጭትና ብጥብጥ እንዲነሳ የሚቀሰቅስ መሆኑ ደግሞ፣ በእሳት ላይ ቤንዚን ማርከፍከፍ ሆነ፡፡ ኢህአዴግ ደርግ አለመሆኑን ሙፍቲ የተረዱት አይመስልም፡፡ አቶ ደርግ፣ “እከሌ ፀረ ህዝብ ነው፤ አቆርቋዥ ነው፤ ኢህአፓ ነው” ተብሎ ከተነገረው፣ ለማሰርም ሆነ ለመግደል ሰባራዋ ወፍ አትቀድመውም፡፡ አቶ ሙፍቲም ከአዲስ አበባ ተንደርድረው ባህር ዳር የሄዱት፣ “ከአሏህ ውጭ የሆነ አካል መንፈሳዊ እርዳታ አይሰጥም” የሚሉትን የተውሂድ ባለቤቶች መስጊዶች አሳሽገውና መሪዎቹንም በፅንፈኝነት በመፈረጅ ለመንግስት አሳልፈው በመስጠት፣ የአሏህ አንድ ቁጥር ሀቅ የሆነውን የተውሂድ ብርሀን እፍ ብለው ሊያጠፉ ነው፡፡ يُرِيدُونَ لِيُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَاللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ
Open in Telegram▶️ የሙሐዲሶች ደረጃ ኸጢብ አል'በግዳዲ - ረሂመሁሏህ - እንዲህ አሉ :- "ሙሐዲሶች የነብዩን ሐዲሶች በአግባቡ በመጠበቅ ፣ በመሰብሰብ ፣ ከመነሻ ምንጮቻቸው በማውጣትና የሐዲሶችን ሰነድ (የዘጋቢዎችን ሰንሰለት) በመፈተሽ ላይ የሚያደርጉት ጥረት ባይኖር ኖሮ ፣ ሸሪዓው በተበላሸ ፤ ሕግጋቶቹም ተግባራዊነታቸው ይቀር ነበር።" 📚 الكفية في علم الحديث ص/ ٥ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة
Open in TelegramForwarded from قناة الشيخ الدكتور حسين بن محمد
✍🏻 *فضل علماء الحديث* *قال الخطيب البغدادي رحمه الله:* « *وَلَوْلَا عِنَايَةُ أَصْحَابِ الْحَدِيثِ بِضَبْطِ السُّنَنِ وَجَمْعِهَا وَاسْتِنْبَاطِهَا مِنْ مَعَادِنِهَا وَالنَّظَرِ فِي طُرُقِهَا ، لَبَطَلَتِ الشَّرِيعَةُ ، وَتَعَطَّلَتْ أَحْكَامُهَا* ». «الكفاية في علم الرواية» (ص5)
Open in Telegram♦️የአይን ጥቅሻ ያህል እንኳ ከጌታችን (አሏህ) ጋር ያለን ግንኙነት ሊቋረጥ በፍጹም አይገባም ኢብን አልቀይም - ረሂመሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :- "ባሪያው ወደጌታው ያለው ፍላጎት ከማንኛውም ፍላጎት በላይ ነው። ይህንንም ፍላጎት ከሌላ ማንኛው ፍላጎት ጋር ማነጻጸር አይቻልም። ምክንያቱ አሏህ ምህረቱን ፣ ተውፊቁን ፣ (ወደ ትክክለኛው ጎዳና) መምራቱን ለአንድ የአይን ጥቅሻ ያህል እንኳ ከከለከለው ይከስራል ፣ ይጠፋልም።" 📚 إغاثة اللهفان ١٢٩/١ https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة
Open in TelegramForwarded from Т𝚎𝚣𝚔𝚒𝚛𝚊 || ተዝኪራ
🔴 ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም 🔴 🗓 የሚካሄድበት ጊዜ - ህዳር 12, ቅዳሜ ማታ 🎀 ተጋባዥ እንግዶች🎀 1⃣ሸይኽ ሙሐመድ ሐያት ከሀራ (ሰሜን ወሎ) 📌ርዕስ - የማህበራዊ ሚዲያ ጥቅምና ጉዳት - በኢስላም እይታ ⏰ ሰዓት: በኢትዮ. አቆጣጠር 3:00 2⃣ኡስታዝ ሰዕድ አብዱ ለጢፍ ከባህር ዳር 📌ርዕስ - የኢኽላስ አንገብጋቢነት ⏰ ሰዓት: በኢትዮ. አቆጣጠር 3:30 📹ይህን ልዩ የዳእዋ ፕሮግራም እንዲከታተሉ እንጋብዛለን:: 👥 ለሌሎችም በማድረስ ከቤተሰብዎ ጋር ይከታተሉ :: ✔️ቻናሎቻችን⤵ ✈️https://t.me/bilalmesji 💭 imo https://s.imoim.net/tBLAMO?from=copy_link
Open in Telegram