Account
Ahmed — أحمـــد

Ahmed — أحمـــد

Username
@ahmedrespond
Subscribers6,370
Avg views per post, 7d1,690last 7 days
ERR26.53%last 7 days

Latest posts

#1223Text

አሜሪካዊው ፈላስፋ እና ዐቃቤ እምነት 'አልቪን ፕላንቲንጋ' "Does God Have A Nature?" በተሰኘ መጽሐፉ ላይ ካነሳቸው ግሩም ነጥቦች መካከል :)) ፈላስፋው በአንድ ጎን እንዲህ ያለ ሙግትን ያደረጃል፦ 1. Person ለመሆን interior consciousness (ውስጣዊ ንቃተ-ህሊና) ሊኖርህ ይገባል! 2. Properties ደግሞ በራሳቸው ገለልተኛ ንቃተ-ህሊና የላቸውም! ካላቸው አምላክ ከባህሪያቱ ጋር ተቆጥሮ ስለ ብዙ ማንነት ብሎም ስለ ብዙ አማልክት ማውራት ልንጀምር ነው! 3. ADS ደግሞ አምላክ ከባሕርያቱ ጋር ፍፁም አንድ ወይም Identical ነው ይላል! 4. ስለዚህ በ ADS Explain የሚደረግ አምላክ Consciousness የሌለው Property እንጂ አካል Person አይደለም! So እንደ Simple Conclusion ንቃተ-ህሊና የሌለው አምላክ ደግሞ ግዑዝ ወይም Abstract Object ነው እንጂ ሕያው አምላክ ሊሆን አይችልም! ሲል እንደ ተጨማሪ እና ጠንካራ ሙግት አምላክን እንደ ሁሉን አዋቂ (Omniscient) አምላክን እንደ ሁሉን ቻይ (Omnipotent) እያስረዳን ከሆነና መልሰን አምላክ ከነዚሁ ባህሪያቱ ጋር identical ነው የምንል ከሆነ የአምላክ ሁሉን አዋቂነት በራሱ የአምላክ ሁሉን ቻይነት ነው ማለታችን ነው የሚል ነጥብ ያነሳል፣ ስለዚህ ባህሪያቱ የየራሳቸው ልዩ ማብራሪያ እንዳላቸው (ሁሉን አዋቂነትን እንደ ሁሉንም እውነት የማወቅ ባሕርይ፣ ሁሉን ቻይነትን ሁሉንም ነገር እንደ ማድረግ የመቻል ባሕሪይ) ከተረዳን ዘንዳ በ Identity of Indiscernibles አምክንዮአዊ መሠረት የ ADS አራማጆች ሁለት የተለያየ ማብራሪያ ያላቸው ባሕሪያትን አንድ በማድረግ የ Category Mistake ውስጥ እየወደቁ ነው የሚል ጠንካራ ሀሳብ ያቀርባል! … ባረከላሁ ፊክ አቡኪ!

Open in Telegram
Views11,000+551%vs avg
Forwards—
Reactions109
Comments—
#1222Text

Forwarded from ÀƁÙBEĶEŔ ابوبكر(izharull haq)

ፍፁም መለኮታዊ ቀላልነት በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኃሩኃ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው:: አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:- لَوۡ كَانَ فِيهِمَآ ءَالِهَةٌ إِلَّا ٱللَّهُ لَفَسَدَتَاۚ فَسُبۡحَٰنَ ٱللَّهِ رَبِّ ٱلۡعَرۡشِ عَمَّا يَصِفُونَ በሁለቱ (በሰማያትና በምድር) ውስጥ ከአላህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር፡፡ የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡ — አል አንቢያ (21:22) በአረቢኛው البساطة الإلهية المطلقة ወይም በተለምዶ Absolute Divine Simplicity የምንለው በአማርኛ ፍፁም መለኮታዊ ቀላልነት ማለት የአምላክ ማንነት በምንም ዓይነት መልኩ የተገጣጠመ፣ የተደባለቀ ወይም ወደ ትናንሽ ክፍሎች የሚከፋፈል አይደለም የሚል ነው:: ሀሳቡ ከላይ ስንመለከት ጥሩ እና ትክክለኛ ቢመስልም ውስጡ ስንመለከተው ትልቅ ችግር ያመጣል:: ሀሳቡን የዋህደተል ውጁድ አቀንቃኝ የሆነው ኢብኑ ሲና በአመክንዮአዊ ጥገኝነት ሙግቱ ውስጥ ያሰፈረው ሲሆን ሄዶ ሄዶ የአላህ ባህሪያትን እና ስሞችን ወደ ማሯቀት ገብቷል:: የዚህ ሀሳብ ዋና አቀንቃኞች ሙዕተዚላ ብለን የምንጠራቸው አንጃዎች ናቸው:: የሙዕተዚላዎች ሙግት 2 ሲሆን እንዲህ የሚል ነው:: (1) አላህ ባህሪያት አለው ካልን እና ባህሪያቱ ብዙ ከሆኑ አላህ ብዙ ነው ማለት ነው የሚል ነው:: ( ተአዱድ አል አሊሃ) (2) አላህ ጥንታዊ ነው ባህሬያቱም ጥንታዊ ናቸው ስለዚህ ቡዙ ጥንታዊ አሉ ማለት ነው:: (ተአዱድ አል ኡሉሂያ) ዛሬ ቁጥር አንድን የምንመለከት ይሆናል:: ሙዕተዚላዎች የአላህ ባህሪያት (ሲፋት) የራሱ የማንነቱ (የዛቱ) ዐይን ናቸው ወይም "ዛቱ በባህሪያቱ ቦታ ይተካል" ማለታቸው በቡዙ መንገድ ውድቅ ነው:: ሀ) ቋንቋዊ እና አመክንዮአዊ ውድቀት በቋንቋም ሆነ በአእምሮ ህግ "ባህሪ" (ሲፋህ) እና "ባለቤቱ" (መውሱፍ) አንድ ሊሆኑ አይችሉም። አንድ ሰው ሀይለኛ ተብሎ ሊጠራ ይችላል እንጂ እርሱ ራሱ ሀይል ሊሆን አይችልም:: አዋቂ እንጂ እውቀት ሊሆን አይችልም:: ተናዳጅ እንጂ ንዴት ሊሆን አይችልም:: ያለዚያ ወደ አደገኛ ድምዳሜ ይወስደናል እሱም የአላህ እዝነት ማለት ቁጣው ነው የሚል ነው:: እንዴት መሰላቹ:: አላህ ባህሪውን ነው ካልን አላህ ቁጣ ነው አላህ እዝነት ነው ስለዚህ እዝነቱ ቁጣ ነው ማለት ይሆናል:: ለ) ባህሪያትን ወደ መካድ የሚያደርስ መንገድ ነው ​ሙዕተዚላዎች "ባህሪያቱ ከዛቱ ጋር አንድ ናቸው" ሲሉ ዓላማቸው ባህሪያቱን ማረጋገጥ ሳይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ ባህሪያት የሚባሉ እውነተኛ ነገሮች መኖራቸውን መካድ (ተዕጢል) ነው። ​"አላህ ያለ ዕውቀት አዋቂ ነው፣ ያለ ኃይል ቻይ ነው" ማለት በተጨባጭ ምንም ባህሪ የሌለውን ባዶ( ማዕዱም) ነገር እንደ መግለጽ ነው። ባህሪ የሌለው ነገር ደግሞ በአእምሮ ምናብ ውስጥ እንጂ በተጨባጭ ውጫዊ ዓለም ሊኖር አይችልም። ሐ) ለቁርኣን እና ለሐዲስ ግልጽ ቃላት ተቃራኒ መሆን ​ቁርኣን አላህ እውነተኛ ባህሪያት እንዳሉት በግልጽ አስቀምጧል፦ ​«በዕውቀቱ አወረደው» _ (አን-ኒሳእ 4: 166) ዕውቀትን እንደ ባህሪ ጠቅሷል። ​«እርሱ የብርቱ ኃይል ባለቤት ነው» _ (አዝ-ዛሪያት 51: 58) ​ነቢዩም (ﷺ) በዱዓቸው፦ "በዕውቀትህ መልካሙን እጠይቅሃለሁ በኃይልህም ችሎታን እለምንሃለሁ" ብለዋል። {አል ቡኻሪይ 1166} "ባህሪው ራሱ ዛቱ ነው" ከተባለ እነዚህን ግልጽ መረጃዎች ማጣመም (ተእዊል) ወይም መካድ ግድ ይላል። እና እንዴት አብራራዋለሁ ? አሰሪዮች ፈላስፎቹ ሆን ብለው ሁለት የተለያዩ ነገሮችን እንደቀላቀሉ ይገልጻሉ። በርካታ ዘላለማውያን መኖራቸው ችግር የሚሆነው እያንዳንዳቸው ራሳቸውን የቻሉ የተለያዩ አምላኮች (ዘዋት ሙስተቂላህ) ናቸው ከተባለ ብቻ ነው። ነገር ግን «ባህሪ» (ሲፋህ) ራሱን ችሎ የሚቆም አካል አይደለም የሚኖረው ከተገለጸው አካል (አል-መውሱፍ) ጋር ብቻ ነው። አንድ ዘላለማዊ አምላክ ዘላለማዊ ዕውቀትና ኃይል አለው ማለት ብዙ አምላኮች አሉ አያሰኝም አንድ ሰው ዕውቀትና እይታ አለው ሲባል ብዙ ሰዎች እንደማይባለው ሁሉ ማለት ነው። በተጨማሪም ምንም ዓይነት እውነተኛ ባህሪ የሌለው (ባዶ ማንነት) በሰው ምናብ ውስጥ ብቻ እንጂ በተጨባጭ ዓለም ውስጥ ፈጽሞ ሊኖር አይችልም። በውጫዊው ተጨባጭ ዓለም ያለ ማንኛውም ሕያው አካል ከሌሎች የሚለይበት እውነተኛ መገለጫዎች ሊኖሩት ግድ ነው። ስለዚህ ያለው አንድ ዘላለማዊ አምላክ ብቻ ሲሆን እርሱም ሙሉ በሆኑ ዘላለማዊ ባህሪያቱ የተገለጸ ነው። ይህም በሙሥሊም ሙሁራኖች ዘንድ "ኻሪጂ" እና "ዚህኒ" ተብሎ ይቀመጣል:: ሀሳቡ ቀላል መሰለኝ በጥሞና እና በእርጋታ ጊዜ ወስዳቹ አንብቡት:: ወንድም አቡበከር https://t.me/buki145

Open in Telegram
Views7,730+357%vs avg
Forwards—
Reactions33
Comments—
#1207Text

Forwarded from عبدالفتاح🖋️ Abdulfetah

በነቢይነታቸው አሥረኛ ዓመት፣ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ባለቤታቸውን እናታችን ኸዲጃን እና አጎታቸውን አቡ ጣሊብን በሞት ካጡ በኋላ፣ በቁረይሾች በኩል የሚደርስባቸው መከራና እንግልት በእጅጉ በረታ። በዚህም ምክንያት የመካ ሰዎች ጥሪያቸውን ባለመቀበላቸው፣ የእስልምናን መልእክት ለማድረስና ድጋፍ ለማግኘት ከአጎታቸው ልጅ ዘይድ ኢብኑ ሐሪሳ ጋር በመሆን ወደ ጣኢፍ ለመሄድ ተነሱ። ወደ ጣኢፍም በሄዱ ጊዜ የሰቂፍ ጎሳ መሪዎች ወደሆኑት ወደ ሦስቱ ወንድማማቾች — ዐብድ ያሊል፣ መስዑድ እና ሐቢብ — ዘንድ በመሄድ የእስልምናን ጥሪ አቀረቡላቸው፤ ከቁረይሾች ጥቃትም እንዲጠብቋቸው ጠየቋቸው። ነገር ግን መሪዎቹ በጥሪው ላይ አፌዙ፤ በጣም ባልተገባና ነቀፌታ በተሞላው መንገድ ጥሪያቸውን ውድቅ አደረጉት። መሪዎቹ ጥሪውን ውድቅ ከማድረጋቸውም በላይ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በአስቸኳይ ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ አዘዙ። ከከተማዋ ሲወጡም የከተማዋን እብዶች፣ ባሪያዎችና ሕፃናት በሁለት መስመር አሰልፈው ድንጋይ እንዲወረውሩባቸው አደረጉ። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና ዘይድ ኢብኑ ሐሪሳ ከተማዋን ለቀው እስኪወጡ ድረስ በድንጋይ ተደበደቡ፤ እግራቸው በደም ተለወሰ፤ ዘይድም ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ለመከላከል ሲሞክር ራሱ ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰበት። ከከተማዋ ትንሽ ራቅ ብሎ በሚገኘው የቁረይሽ ከበርቴዎች በነበሩት በኡትባ እና ሸይባ የአትክልት ስፍራ በደረሱና ባረፉ ጊዜም፣ ውዱ ነቢይ ወደ አላህ እንዲህ ሲሉ ጥሪያቸውን አሰሙ፦ "اللَّهُمَّ إِلَيْكَ أَشْكُو ضَعْفَ قُوَّتِي، وَقِلَّةَ حِيلَتِي، وَهَوَانِي عَلَى النَّاسِ، أَنْتَ رَبُّ الْمُسْتَضْعَفِينَ وَأَنْتَ رَبِّي، إِلَى مَنْ تَكِلُنِي؟ إِلَى بَعِيدٍ يَتَجَهَّمُنِي؟ أَمْ إِلَى عَدُوٍّ مَلَّكْتَهُ أَمْرِي؟ إِنْ لَمْ يَكُنْ بِكَ غَضَبٌ عَلَيَّ فَلَا أُبَالِي، وَلَكِنَّ عَافِيَتَكَ هِيَ أَوْسَعُ لِي، أَعُوذُ بِنُورِ وَجْهِكَ الَّذِي أَشْرَقَتْ لَهُ الظُّلُمَاتُ، وَصَلَحَ عَلَيْهِ أَمْرُ الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، مِنْ أَنْ تُنْزِلَ بِي غَضَبَكَ، أَوْ يَحِلَّ عَلَيَّ سَخَطُكَ، لَكَ الْعُتْبَى حَتَّى تَرْضَى، وَلَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلَّا بِكَ». አላህ ሆይ የጉልበቴን ደካማነት የመላዬን (የብልሃቴን)ማነስ በሰዎች ዘንድ ማነሴን (መናቄን) አቤቱታዬን ወደ አንተ አቀርባለው ።አንተ የደካሞች ጌታ ነህ ፤ አንተም ጌታዬ ነህ ። ለማን አሳልፈህ ትሰጠኛለህ? በጭካኔ ለሚያስተናግደኝ ሩቅ ሰው ወይስ ጉዳዬን ለሰጠኸው ጠላት? አንተ ካልተቆጣህብኝ ሌላው ግድ አይሰጠኝም ፤ ሆኖም የአንተ ጥበቃና እዝነት ለእኔ የበለጠ ሰፊና በቂ ነው ። ቁጣህ በኔ ላይ እንዳይወርድ መዓትህም በኔ ላይ እንዳይሆን ጨለማን በሚያበራውና የዚህን ዓለምም ሆነ የመጨረሻውን ዓለም ጉዳዮች በሚያስተካክለው በፊትህ ብርሃን እጠበቃለው ። አንተ እስክትረካ ድረስ ይቅርታህን እሻለው ፤ ከአንተ ውጪ ምንም ዓይነት ሃይልም ብርታትም የለም ። ይህን ሁኔታቸውን በአትክልት ስፍራው የሚያገለግል አንድ ባሪያ ባየ ጊዜ፣ በሁኔታቸው አዝኖ ወደ እነሱ ተጠግቶ የወይን ፍሬ ሰጣቸው። ረሱልም (ሰ.ዐ.ወ) ፍሬውን ከመብላታቸው በፊት "ቢስሚላህ" ባሉ ጊዜ፣ ይህ ባሪያ በንግግራቸው በመደነቅ «የዚህ አካባቢ ሰዎች ይህን ቃል አይጠቀሙም» አለ። ረሱልም (ሰ.ዐ.ወ) የየት ሀገር ሰው እንደሆነና ሃይማኖቱ ምን እንደሆነ ጠየቁት። እርሱም የነይነዋ (የነቢዩላህ ዩኑስ ሀገር) ሰው እንደሆነና ሃይማኖቱም መሲሐዊ (ክርስቲያን) እንደሆነ ነገራቸው። ዓዳስ (ባሪያው) ስለ ነቢዩላህ ዩኑስ በምን እንደሚያውቁ በጠየቃቸው ጊዜ «እርሱ ወንድሜ ነው፤ ነቢይም ነበር፤ እኔም ነቢይ ነኝ» አሉት። ይህን በሰማ ጊዜ ባሪያው ግንባራቸውን፣ እጃቸውን እና እግራቸውን በመሳም እስልምናን ተቀበለ። ይህንን ያየው አሳዳሪውም «ወየውልህ! የዚህን ሰው እጅ፣ እግርና ግንባር ትስማለህ?» ብሎ በጠየቀው ጊዜ፣ ባሪያውም «ከዚህ የተሻለ ነገር ምን አለ? ነቢይ እንጂ ሌላ የማያውቀውን ነገር ነገረኝ» በማለት መለሰለት። ከዚህም በኋላ ጉዟቸውን በመቀጠል ላይ ሳሉ፣ 'ቀርኑል መናዚል' የሚባል ስፍራ ላይ በደረሱ ጊዜ አላህ መላእክትን ላከላቸው። የመላእክት አለቃ ጅብሪልም ሰላምታ ካቀረበ በኋላ እንዲህ አላቸው፦ «አላህ የሕዝቦችህን ምላሽ ሰምቷል። የተራሮችን መልአክም እነሱ ላይ የፈለግከውን እንድታዝባቸው ልኮልሃል።» የተራሮች መልአክም ሰላምታ ካቀረበ በኋላ  «ጌታህ በእርግጥም ወደ አንተ ትእዛዝህን እንድፈጽም ልኮኛል። ከፈለግክ እነዚህን ሁለቱን ተራሮች በጣኢፍ ሕዝቦች ላይ አጣብቄ ላጥፋቸው።» አለ። መልአኩ ይህን ቢላቸውም፣ ለዓለማት እዝነት ሆነው የተላኩት የኛ ነቢይ መልስ ግን በጣም አስገራሚ ነበር። «በእርግጥ ከእነዚህ ሕዝቦች ውስጥ ወደፊት አላህን በብቸኝነት፣ ማንንም ሳያጋሩ የሚያመልኩ ትውልዶች ይፈጠራሉ ብዬ እከጅላለሁ።» በማለት እነዚህን ሕዝቦች ከመጥፋት ታደጓቸው።

Open in Telegram
Views15,000+788%vs avg
Forwards—
Reactions203
Comments—
#1015Text

ምሁራኑ ይህንን ጥያቄ ከ ተፈጥሮ ሥርዓት ጋር አያይዘው ሰፋ ያለ መረዳታቸውን አስቀምጠዋል። አምላክ አለምን የሰራት ዘፈቀዳዊ ሳይሆን ቋሚ በሆኑ ህግጋት (Laws Of Nature) እንድትመራ አድርጎ ነው። እነኚህ እንደ ስበት፣ ሙቀት፣ እንቅስቃሴ ያሉ መሰል ህግጋት ካልተለወጡና ቋሚ ከሆኑ ብቻም ነው ዓለም ሥርዓት አላት ልንል የምንችለው። ዛሬ የምበላውን መብል ያሞቀ እሳት ነገ ያቀዘቅዘዋል ብለን የማንጠብቀው፣ ድንጋይ ከላይ ሲለቀቅ ወደ ታች እንደሚወድቅ እርግጠኛ መሆን የምንችለው የተፈጥሮ ሕግ ቋሚ እና የማይለዋወጥ ስለሆነ ነው። በሃይማኖት ፍልስፍና (Philosophy Of Religion) ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደረው አሜሪካዊ ፈላስፋ 'ብሩስ ራይከንባክ' እነዚህ ሕጎች በጎ ነገርን ለማምጣት አስፈላጊ የሆኑትን ያህል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሥቃይን የማምጣት ውጤት ይኖራቸዋል ሲለን እንግሊዛዊው ደራሲ 'ሲ. ኤስ. ሉዊስ' እ.ኤ.አ በ 1910 ባበረከተው "The Problem Of Pain" የተሰኘ መጽሐፉ ላይ የሰው ልጆች እርስ በርስ ለመግባባትና ነፃ ምርጫቸውን ለመለማመድ ገለልተኛና የማይለወጥ መድረክ ያስፈልጋቸዋል። ይህ መድረክ ደግሞ ቋሚው የተፈጥሮ ሕግ ነው። ሕጎቹ እንደፈለጉ የሚቀያየሩ ቢሆኑና አምላክ ጣልቃ ቢገባ ማኅበራዊ ሕይወትና ሥነ ምግባር ሊኖር አይችልም ነበር ሲል አበክሮ ይሟገታል። ከነዚህ ትርጓሜዎች በመነሳት ተፈጥሯዊ እኩይ (Natural Evil) በ ኢስላማዊው ሥነ-መለኮት ውስጥ ሁለት ተያያዥ ገጽታዎችን ይይዛል። የመጀመሪያው የሥነ ፍጥረቱ ሥርዓት አካል መሆኑን ቁርዓን እንዲህ ሲል ያስረዳል “እኛ ሁሉንም ነገር በልክ (በልክም) ፈጠርነው።“ — 54:49 ይህንን አንቀጽ በ 20ኛው ክ/ዘመን ከነበሩ ታላላቅ ሊቃውንት መካከል ቱኒዝያዊው 'ሙሐመድ አጥ ጣሂር ኢብን ዓሹር' እንዲህ ሲሉ ፈትተውታል፦ “ሸይእ (ነገር) ማለት፦ በባህሪያትና በአካላት (በቁስ) መካከል ያለ ነባራዊ ነገር ማለት ነው። ይኸውም፦ ሁሉንም ነባራዊ ነገሮች፣ አካላቶቻቸውንና ባህሪያቶቻቸውን በልክ ፈጠርናቸው ማለት ነው።“[⁴] ሲሉ በዚሁ በልክ የተሰራ ፍጥረተ አለም ላይ የሚታየው ተፈጥሯዊ እኩይ (Natural Evil) በውስጡ መካተቱን እንድንረዳ በር ከፍተውልናል፣ ሁለተኛው ደግሞ "ወርቅ በእሳት ይፈተናል" እንዲሉ አበው የሰው ልጅ በ ህመም የ ጤናን በ ማጣት የ ማግኘትን ፀጋ እንዲያስተውል በ መከራ ትዕግስትን በ ረሀብ ርኅራኄን የሚማርበት "የ ነፍስ ስሪት ፍትሐ መለኮትን (Soul Making Theodicy)" ያስይዘናል። የነገረ እኩይ ጥያቄዎችን በምክንያታዊነት ብቻ ለመፍታት የሚሞክሩ ምሁራን፣ በመጨረሻ የሚጋጩት ከሰው ልጅ አእምሮ በላይ ካለው ጥበብ ጋር ይሆናል። እዚህ ጋር ነው መለኮታዊ ጥበብን የመመርመር ገደብ ወይም "Skeptical Theism" የሚባለው እሳቤ የሚመጣው። ይህ እሳቤ አምላክ ክፋትን እንዲኖር የፈቀደበት በቂ ምክንያት ቢኖረውም፣ እኛ የሰው ልጆች ያንን ምክንያት የመረዳት አቅሙ የለንም የሚል ነው። በነቢዩ ሙሳ እና በኸድር ታሪክ ውስጥ ሙሳ በጉዞው ላይ ኸድር ምስኪኖች የሚጠቀሙባትን ጀልባ ሲበሳ፣ አንድን ወጣት ሲገድል እና በማይቀበሏቸው ሰዎች መንደር ውስጥ የወደቀ ግንብ ሲያቀና ይመለከታል። ለሙሳ እነዚህ ድርጊቶች "እኩይ" (Evil) መስለው ቢታዩትም፣ ኸድር በመጨረሻ ጀልባዋ የተበሳችው ጀልባዎችን ከቀማኛ ንጉሥ ለመታደግ፣ ወጣቱ የተገደለው ለወላጆቹ የተሻለ ልጅ ለመተካት፣ ግንቡ የታደሰው ደግሞ ከሥሩ ያለውን የየቲሞች ሀብት ለመጠበቅ እንደነበር ሲያስረዳው እንመለከታለን። በዚህ ታሪክ ውስጥ "Relative Evil" (አንጻራዊ እኩይ) የምንለው ነገር፣ በመለኮታዊው እቅድ ውስጥ ለበለጠ በጎ ነገር (Greater Good) መንገድ የሚጠርግ መሆኑን እንረዳለን። ከመሆኑም ጋር፣ አንድ አማኝ በምድር ላይ ለሚገጥመው መከራና ክፋት ሊኖረው የሚገባው ምላሽ አምላክ ሁሉን አዋቂ መሆኑን በማመን፣ ከቁጥጥራችን ውጭ ለሆኑ ነገሮች አምላክን ተጠያቂ ከማድረግ መታቀብ ነው። መከራ ለአማኙ ስብዕና መገንቢያና ወደ ፈጣሪው መቃረቢያ ድልድይም ነውና፣ በሁኔታዎች ሁሉ አመስጋኝ ባሪያ ሆኖ በመቆየት በዚህች ዓለም ላይ ከሚገጥመው አንጻራዊ ክፋት ይልቅ፣ ከፈተናው በኋላ ያለውን ዘላለማዊ ህይወት ተስፋ በማድረግ ጉዞውን ሊቀጥል ይገባዋል እላለሁ። "ነገረ እኩይ አምላክ የለም ለማለት የሚያበቃ ጽንሰ ሀሳብ ነው!" የሚለውን መረዳት ወደ ጎን በማድረግ፣ ይልቁንም አምላክ ከእኛ እውቀት በላይ መሆኑን የምንረዳበት ምስጢር አድርገን መውሰዱ ወደ እኛ በተወረወረው ጠጠር ቤታችንን እንደ መገንባት ያለ ብልህነት ነው የሚል ግንዛቤ አለኝ። ደኅና ቆዩኝ። __ ማጣቀሻዎች፦ [1] Leibniz, Theodicy, Part I, Section 21 [2] ሀዲስ አለማየሁ፣ የልምዣት (1980)፣ ገጽ 108 [3] Alvin Plantinga, The Nature Of Necessity (1974), pp. 167 [4] Muhammed At Tahir Ibn Ashur, Tafsir At Tahrir Wa At Tanwir (2021), Volume 11, pp. 171 ... Written By: Akhi Ahmed Respond https://t.me/ahmedrespond

Open in Telegram
Views42,300×25vs avg
Forwards—
Reactions190
Comments—

All posts

Connections

Mentions