በፍፁም ሊያመልጣችሁ የማይገባ የ 4 ቀናት የ #coffeetour ጉዞ ከ @guzoadwahiking ጋር ከህዳር 24-27 (ሐሙስ-እሁድ) / Dec 03-06 2026 ሊካሄድ ነው:: ዝግጁ ናችሁ? የቡና ቱሪዝምን ከ ሃይኪንግ ወዳጆች ጋር እንዲሁም ቡና አፍቃሪያን ጋር ለማስተዋወቅ ታስቦ የተዘጋጀው የዚህ ዓመት የ 4 ቀናት #የCoffee_tour የቡና ጉዞ ፓኬጅ ወደ ደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን ይወስደናል:: የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን በመስከረም 2016 ዓ.ም በ UNESCO ዓለም ቅርስነት የተመዘገበ ባሕላዊ መልክዓ ምድር (cultural landscape) ፣ ጥቅጥቅ ያለ ደንና የተለያዩ ትክል ድንጋዮች ያሉትና፣ ልዩ የሆነ የመሬት አያያዝ ጥበብ ፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ ትክል ድንጋዮች፣ የዋሻ ላይ ጽሑፍና በባሕላዊ መንገድ ብቻ የሚተዳደሩ ደኖች ይገኙበታል፡፡ በዚህ ጉዞ በይርጋጨፌ የቡና ጉብኝት እና ትምህርዊ ውሎ የቡና እርሻዎችን ይጎበኛሉ ፣ ቡና ለቀማ ፣ ስለ ቡና አመራረትና ባህል ይማራሉ፣ ከቡና እርሻ እስከ ስኒ ድረስ ያለውን ሂደት ይለማመዳሉ። ከይርጋጨፌ የቡና ጉብኝት (coffee tour ) በኃላ የይርጋጨፌን ተፈጥሯዊ ውበትና የአካባቢውን ባህል እንዲሁም የጨልባ ቱቲቲ የትክል ድንጋይ እንጎበኛለን:: እንዲሁም ወደ ሌላኛው የጌዴኦ ዞን የቱሪዝም ሀብቶች ወደሚገኙበት የቡሌ ወረዳ እናቀናለን:: 👉አስቀድሞ ቦታ በማስያዝ የክፍያ ቅናሽ ዕድሉን አሁኑኑ ይጠቀሙ ! ለተጨማሪ መረጃዎች በ +251929176542, +251 92 159 8973 ይደውሉልን:: @guzoadwahiking @guzoad
Open in Telegram
Guzo Adwa updates
Average views per post by day
By publication day
Show as table
| Date | Avg views per post |
|---|---|
| Nov 18, 2026 | 796 |
| Nov 23, 2026 | 703 |
Most viewed this month
- 01Views1.03KForwards—Reactions—Comments—
- 02Views714Forwards—Reactions—Comments—
- 03Views703Forwards—Reactions—Comments—
- 04Views644Forwards—Reactions—Comments—
Latest posts
ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ እና እሁድ ላይ በመሠረተ ወገራም የገጠር መንደር የማይረሳ የጉዞ ቆይታን አሳልፈን ተመልሰናል:: የአካባቢውን ሰንሰለታማ ተራሮች ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ በእግር ጉዞ ብንጎበኛቸውም በዚህኛው ጉዟችን ግን በተለምዶ “የእምዩ ጡት” የተባለውን አዲስ የተራራ ጫፍ 🏔️ በተሳካ ሁኔታ መውጣት ችለናል። የዚህ ጉዞ ትልቁ ድምቀት የተፈጥሮ ውበቱ ብቻ ሳይሆን የአካባቢው ማህበረሰብ አስደናቂ እንግዳ ተቀባይነት ነበር። በቆይታችንም የሶዶ ጉራጌ ባህላዊ ጭፈራ ፣ ሙዚቃ እና የአኗኗር ዘይቤ በቅርበት ከማየታችንም በላይ ጣፋጭ የሆኑ ባህላዊ ምግቦቻቸውንም በሚገባ አጣጥመን ተመልሰናል። የጉዞ ዓድዋ ሃይኪንግ ቀጣዩ የ 4 ቀናት ጉዞ ቡናን መሰረት አድርጎ ወደ ጌዲኦ ዞን/ይርጋጨፌ ይወስደናል :: 📅 ህዳር 24–27 2019 ዓ.ም / 03-06 Dec 2026 በዚህ ጉዞ በታዋቂው የይርጋጨፌ ቡና መገኛ አካባቢ የቡና እርሻዎችን፣ የቡና ማቀነባበሪያ ሂደቶችን፣ የአካባቢውን ባህልና የኑሮ ዘይቤ በቅርበት እንቃኛለን። የጌዲኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር የኢትዮጵያ ውድ ባህላዊ ቅርስ ሲሆን በዚህም ስፍራ ድንቅ መልክዓ ምድር፣ አስገራሚ የመሬት አያያዝ፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ ትክል ድንጋዮች፣ የዋሻ ላይ ጽሑፍና በባሕላዊ መንገድ ብቻ የሚተዳደሩ ደኖች ይገኙበታል፡፡ ይህም መስከረም 2016 ዓ.ም በ ዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ አስችሎታል:: 📞ቦታ ለማስያዝና ለስለጉዞው ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት በተከታዮቹ አድራሻዎች ብቻ ያገኙናል:: +251 92 159 8973 +251 929 176 542 @guzoad @guzoadwahiking
Open in TelegramConnections
Similar channels
Ministry of Culture And Tourism – የባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር@tourismethiopiaTravel4.54K
4winds Holidays@fourwindstravelTravel3.7K
Водная Ривьера термальный источник@vodnayariveraTravel5.27K
Українці в Іспанії 🇪🇦🇺🇦@dopomoga_spaineTravel5.27K
Тревел-блог Дмитрия Кустарниченко@dmitry_k_travelTravel5.28K
Анапа😍Viktor93.rus@ekskursii_viktorTravel5.26K
Билет в Мадрид 🇪🇸@destinomadridTravel5.26K
travelobiz - Travel News & Updates@travelobizTravel5.26K