Account

Posts of Adventist information አድቬንቲስት መረጃ

newest first

#3802Photo
Views755−31%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#3801Text

ቤተክርስቲያን 22 ፓስተሮችን በቅስና አገልግሎት ሾመች! በምስራቃዊ ኢትዮጵያ ዩኒየን ሚሽን የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም. በአቃቂ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን በተካሄደ ልዩ የአምልኮ መርሐ ግብር ላይ 22 ፓስተሮችን በቅስና አገልግሎት ሾማለች። የቅስና ሹመት የተቀበሉት አገልጋዮች፦ ፓስተር ዮሐንስ ተስገራ ፓስተር ሸዋለም ብንቅር ፓስተር ይትባረክ ሕዝቅኤል ፓስተር አዲሱ በዛብህ ፓስተር ታምራት ወይላምቦ ፓስተር ኢሳያስ አተጋ ፓስተር ወርቁ ጊነዶ ፓስተር አየሩ አብደታ ፓስተር ወንድሙ አረጋ ፓስተር አለሙ አማረ ፓስተር ኤፍሬም ዳዊት ፓስተር ሙሉጌታ ሽፈራው ፓስተር ደበላ ቶሎሳ ፓስተር ዳንኤል ቡልቲ ፓስተር አለማየሁ ከበደ ፓስተር አስፋው አንቱቴ ፓስተር ተመስገን ኢጃራ ፓስተር እስራኤል ነጋሳ ፓስተር አብርሃም ዋቅጋሪ ፓስተር ዳባ መገርሳ ፓስተር ሹሚ ሄርጳ ፓስተር ተፈራ አበበ ለተጨማሪ አገልግሎት የሚያዘጋጅ ስልጠና ከቅስና ሹመቱ በፊት፣ አገልጋዮቹ ከባለቤቶቻቸው ጋር ለሦስት ቀናት በተለያዩ የአገልግሎት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ልዩ ስልጠና ወስደዋል። ስልጠናው በምስራቃዊ ኢትዮጵያ ዩኒየን ሚሽን የሚኒስትሪያል ክፍል አስተባባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን፣ በዩኒየኑ የተለያዩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች አማካኝነት ተሰጥቷል። የዩኒየኑ የሚኒስትሪያል ክፍል ዋና ኃላፊ ፓስተር አንጋው ጌታሁን እንደገለጹት፣ የቅስና ሹመቱ ዋና ዓላማ አገልጋዮቹ በተጨማሪ የአገልግሎት ዘርፎች ቤተ-ክርስቲያንን እንዲያገለግሉ ማስቻል ነው። ሹመቱም እንደ ጥምቀት፣ ጋብቻ እና የቀብር ሥነ ሥርዓቶችን የመሳሰሉ የአገልግሎት ኃላፊነቶችን እንዲወጡ ሥልጣን የሚሰጥ መሆኑን አብራርተዋል። የምስራቃዊ ኢትዮጵያ ዩኒየን ሚሽን ለተሾሙት አገልጋዮችና ለቤተሰቦቻቸው የተባረከ፣ ፍሬያማና በታማኝነት የተሞላ የአገልግሎት ዘመን ይመኛል። የምስራቃዊ ኢትዮጵያ ዩኒየን ሚሽን የግንኙነትና ሚዲያ ክፍል #EEUM #SeventhDayAdventist #Ordination #ChurchMinistry @AdventistEthio @metagesy

Open in Telegram
Views685−38%vs avg
Forwards—
Reactions17
Comments—
#3800Photo
Views3,680+235%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
#3797Photo
Views1,450+32%vs avg
Forwards—
Reactions28
Comments—
#3784Photo

የምሥራቃዊ ኢትዮጵያ ዩኒየን ዓመታዊ ካምፖሪ በሀዋሳ ከተማ በደመቀ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ይገኛል! «ጌታ ሆይ ተናገር!» በሚል አነቃቂ መሪ ቃል በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ያለው የምሥራቃዊ ኢትዮጵያ ዩኒየን ዓመታዊ የፓዝፋይንደር (Pathfinder) ካምፖሪ በርካታ መንፈሳዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን በማቀናጀት በታላቅ ድምቀት ቀጥሏል። የመርሐ ግብሩ ዋና ዋና ሁነቶች፦ አለምአቀፍ የልምድ ልውውጥና ስልጠና፦ ከውጭ ሀገር የመጡ ከ30 በላይ የAngaza West (AGW) Pathfinder Drum Corps የቡድን አባላት በሀዋሳ አድቬንቲስት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ለካምፖሪው የልምድ ልውውጥ ስልጠና እየሰጡ ይገኛሉ። የደም ልገሳ መርሐ ግብር፦ የወጣቶችን የማህበረሰብ አገልግሎት ፍቅር በሚያሳይ መልኩ በካምፖሪው ግቢ ውስጥ የበጎ ፈቃድ የደም ልገሳ ስራ ተከናውኗል። የጎዳና ላይ የወንጌል ስርጭት፦ በሀዋሳ ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ የወንጌል መልእክት ለህዝቡ የማድረስና አወንታዊ ተፅዕኖ የመፍጠር ስራ ተካሂዷል። ይህ ታላቅ ካምፖሪ የወጣቶችን ህብረት፣ የመንፈሳዊ አገልግሎት ቁርጠኝነት እና የወንጌል ስራን በስፋት ማጠናከርን ዓላማ ያደረገ ሲሆን፣ እስከ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የተለያዩ አነቃቂ መርሐ ግብሮችን በማካተት የሚቀጥል ይሆናል። #PathfinderCamporee #EasternEthiopiaUnion #Hawassa #SpeakLord #AngazaWestDrumCorps #SDA #YouthMinistry #Pathfinders #Ethiopia Via:- HopechannelEthiopia @AdventistEthio @metagesy

Open in Telegram
Views1,880+71%vs avg
Forwards—
Reactions10
Comments—