ኢየሱስ በባህሪህ ውብ የሆንክ ኢየሱስ ሆይ ዓይኖቼ ውበትህን፤ ልቤም ፍቅርህን ይመልከት። ልቤን በፍቅርህ አጥለቅልቃት። ከአንተ ውጪ የሚያሳርፈኝ ምንም አይኑር። ሃሌ ሉያ!! አዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8
Open in TelegramPosts of Adoni Gospel channel
ይመለስላችሁ "አንበጣና ደጎብያ ኩብኩባና ተምች የበላቸውን ዓመታት እመልስላችኋለሁ።" (ኢዩኤል 2:25) እግዚአብሔር የካሳ አምላክ ነው። ካሳ የባከነ ምትክ ነው። ሕይወት ውስጥ ማግኘት እንዳለ ሁሉ ማጣትም አለ። በእኛ ስህተት ምክንያት ያጣነው የስራ እድል፣ ያጣነው ትዳር፣ ያጣነው ወዳጅነት ይኖራል። የባከነባችሁን ጊዜ እግዚአብሔር በበረከት፣ የጠፋውን ደስታ ስቃይ የተመሉ ዘመናትን ወደ ምስጋና ይለውጣል። ያለፉት አመታቶች በጸጸት፣ በኪሳራ፣ በስቃይና በመከራ ቢሞላም የወደፊታችሁ ተስፋ ግን በክብር አለ። እግዚአብሔር ደስታችሁን ይመልስ፣ የተሰወረውን መፍትሄ ይግለጥላችሁ፣ ያመለጣችሁን እድል በእጥፍ ያምጣላችሁ። አዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8
Open in Telegramኢየሱስ የሰውነትን ብቻ ሳይሆን የነፍስን ቁስል የምትፈውስ መድኃኒት ነህ። ዛሬም ፈውሰን!! አሜን አዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8
Open in Telegramኢየሱስ በጅራፍ የተተለተለው ሰውነትህ፤ በእሾህ የተወጋው ራስህ፤ በምስማር የተቸነከሩት እጅና እግሮችህ፤ በጦር የተወጋው ጎንህ ለእኔ ያለህን ፍቅር የሚናገሩ የመዳን ምስክሮቼ ናቸው። ስለማይነገር ስጦታህ አመሰግንሃለው። አዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8
Open in Telegramበጣም አመሰግናችኋለሁ። እያደረጋችሁላት ያለውን መልካምነታችሁን ነግራኛለች በስውር ያደረጋችሁትን እግዚአብሔር በአደባባይ ይካሳችሁ። በእርሷ የደረሰ ችግር በእናንተ አይድረስ። በጣም አመሰግናችኋለሁ። እግዚአብሔር ሰማይ ነድሎ በረከቱን በቤታችሁ ላይ ያውርድ
Open in Telegramቡሩክ ሁኑ!! እግዚአብሔር የልባችሁን ቅንነት ይመልከት በበረከቱ ጠል ያረስርሳችሁ። ዘመናችሁ እንደ ዛፍ በውሀ ዳር ይለምልም። ስራችሁ በፅድቅ፣ ፍሬያችሁ በበረከት ይሙላ። በዘመናችሁ ሁሉ የእጃችሁ ስራ አይክሰር፣ ድካማችሁ ወደ ውጤት፣ ጥረታችሁ ወደ ስኬት፣ ትዕግስታችሁ ወደ ደስታ ይለወጥላችሁ። በፊታችሁ የተዘጋ በር ይከፈትላችሁ፣ የጠፋባችሁ ተስፋ ይመለስላችሁ፣ ነፍሳችሁ ስትደክም ያበርታችሁ። በሄዳችሁበት ሁሉ ሞገስ፣ በኖራችሁበት ዘመን ሁሉ ሰላም ይሁንላችሁ። ከሰው ዘንድ ያላገኛችሁትን ፍቅር ከእግዚአብሔር ዘንድ በብዛት ተቀበሉ። ዘራችሁ ሁሉ ረክላችሁ አዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8
Open in Telegramየእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን። አንዲት የማውቃት እህት በጽኑ ችግር ላይ መሆኗን አወራችኝ። ትዳር ይዛ የምትኖር ሁለት ልጆች የወለደች አዛውንት እናቷን የምትጦር ተሯሩጣ ቤት ኪራይ፣ የትምህርት ቤት ክፍያ፣ የቤት አስቤዛ የምትሸፍን ጎበዝ ልጅ ነበረች። ባለቤቷን በመኪና አደጋ ካጣች በኋላ ልጆቿን ለብቻዋ ተሯሩጣ በማሳደግ ላይ የነበረች ቢሆንም እናቷ በመታመማቸው ቤት ውስጥ በዳይፐር በመሆናቸው እርሳቸውን የሚንከባከብ አጋዥ ሰው ስለሌላት ቤት ውስጥ መዋል ጀመረች። ብዙ ውጣ ውረድን እያሳለፈች ሲሆን አሁን አቃተኝ ራስሽን አጥፊ እያለኝ ነው ግን ልጆቼ ላይ መጨከን አቃተኝ ብላ የውስጧን ብሶት አጫወተችኝ። እኔም የምችለው እናንተን ወዳጆቼን ማስቸገር ነውና የምትችሉትን የአቅማችሁን ደግፏትና ተስፋዋን እናለምልምላት። በክርስቶስ ሰላም ሁኑልኝ። ተባረኩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፦ 1000581766975 አዜብ ተክሌ እርሷን ለማግኘት 0955366084 0989155354
Open in Telegramኢየሱስ አንተን አርፍደን ወደድንህ፤ ዘግይተን አወቅንህ፤ ብዙ ተሰብረን አገኘንህ፤ በብዙ ዕንባ መሐል ፍቅርህን ተረዳን፤ አንተ ግን አለም ሳይፈጠር አወቅኸን፣ ወደድከን። በእናታችን ማህፀን ገጣጠምከን። እኛ አንተን ለመፈለግ ተቅበዘበዝን፤ አንተ ግን ለልባችን የቀረብህ ነህ። ስንረሳህ አንተ አልረሳኸንም፤ ስንርቅህ አንተ አልተውከንም። ኢየሱስ ሆይ ተመስገን Telegram👉 t.me/adonigospel Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8
Open in Telegramኢየሱስ ይለያል ሠው ሲያየን ያለፈውን ስህተታችንን ያስታውሳል፤ ኢየሱስ ግን በተስፋ የምንለወጥበትን ነገ ያያል። ሠው በውድቀታችን ይፈርድብናል፤ ክርስቶስ ግን እንድንነሳ እጁን ይዘረጋል። ኢየሱስ የሚያድነው ፍፁማንን አይደለም። ወደ እርሱ የሚመጡትን ኃጢአተኞች ነው። Telegram👉 t.me/adonigospel Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8
Open in Telegramለሰው የልባችሁን በር ክፈቱ ነገር ግን ጥበባችሁ ማንን ማስገባት እንዳለበት ይወስን። ሁሉም ዘው የሚልበት ሰው አልባ ቤት አትሁኑ!! መልካም ምሽት!! አዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8
Open in Telegramኢየሱስን ከያዝክ ዛሬ የምታለቅስበት ቦታ ነገ የምታመሰግንበት ቦታ ይሆናል አዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8
Open in Telegramኢየሱስ በኃጢአት የደከመች ነፍስን የምታነፃ ምህረት ነህ። በደምህ ስላጠብከን ተመስገን! አዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8
Open in Telegramኢየሱስ ዕንባ በሞላው ዓይን ውስጥ የሚበራ ተስፋ ነህ ስላለኸን ተመስገን! አዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8
Open in Telegramኢየሱስ የሚወደን ስለምናስፈልገው ሳይሆን ስለሚያስፈልገን ነው። ባህሪው ፍቅር ነውና!! ንጹሐ ባህሪ ኢየሱስ ተመስገን አዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8
Open in Telegram«እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን።» (1ኛ ቆሮንቶስ 1፥23) በዘመናት ውስጥ ብዙ የተሰቀሉ አሉ፤ ግን የተሰቀሉትን ሁሉ አንሰብክም። ብዙ የተወጉ አሉ፤ ግን የተወጉትን ሁሉ አንሰብክም። ብዙ የተገረፉ አሉ፤ ግን የተገረፉትን ሁሉ አንሰብክም። ብዙ የሞቱ አሉ፤ ግን የሞቱትን ሁሉ አንሰብክም። አንዳንዶቹ በወንጀላቸው፣ በበደላቸውና በሕግ መተላለፋቸው ተቀጥተዋል። ክርስቶስ ግን ለራሱ ኃጢአት አልተሰቀለም። ለእኛ ኃጢአት ተሰቀለ! እርሱ ንጹሕ ሆኖ ለበደለኞች ሞተ። እርሱ ጻድቅ ሆኖ ለኃጢአተኞች ተሠዋ። እርሱ ሕይወት ሆኖ ሞትን ተቀበለ፤ እኛ ሕይወትን እንድናገኝ፤ አንድ ጊዜ ለሁልጊዜ ተሰቀለ እኛም አምነን ዳንበት። እኛ የሰውን መስቀል አንሰብክም፤ የክርስቶስን መስቀል እንሰብካለን። የሰው መስቀል የቅጣት ምልክት ሊሆን ይችላል፤ የክርስቶስ መስቀል ግን የፍቅር፣ የይቅርታና የመዳን ምልክት ነው። እኛ የምንሰብከው የተሰቀለውን ብቻ ሳይሆን፣ ለእኛ ተሰቅሎ በሦስተኛው ቀን ከሞት የተነሣውን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ነው! ኢየሱስ የሚሰበክ ስብከት፤ የሚኖር ሕይወት ነው። ተባረክ ኢየሱስ!!! ✍አዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8
Open in Telegramየጸሎት ሸክም ክርስቲያን እርስ በእርሱ ከሚደጋገፍበት ትልቁና ዋነኛው ነገር አንዱ ጸሎት ነው። ጸሎት የመለኮትን እጅ መጋበዝ ነው። ዛሬ ለሁላችሁም የጸሎትን ሸክም ልሰጣችሁ ነው። ብዙ ውጣ ውረዶችን ያለፈች፤ እግዚአብሔርን ብቻ ተስፋዋ አድርጋ የኖረች እንደማንኛውም ሰው የወደፊት ህልም ያላት በጣም ወጣት ልጅ ማርታ የምትባል እህታችን አለች። ማርታ ባደረባት የጡት ካንሰር ህመም እየተሰቃየች ነው። በብርቱ የእኛ የወንድም እህቶቿ ጸሎት ያስፈልጋታል። የእግዚአብሔር ቃል " ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። (ያዕቆብ 5:16) እንደሚል በጌታ ፊት በጸሎት እንድናስባት ወንድማዊ ልመናዬን አቀርብላችኋለሁ። ለእግዚአብሔር የሚሳነው የለም የታመመን ቀርቶ የሞተንም የሚያስነሳ አምላክ ነውና እግዚአብሔር ፈውሱን ይልክላት ዘንድ ዳግም ለምስጋና ያቆማት ዘንድ የኛን ብርቱ ጸሎት ትሻለች። እግዚአብሔር እንዲፈውሳት፣ በህመሟ ጊዜ በእግዚአብሔር ላይ ያላት እምነት እንዳይሸረሸር፣ በእርሱ ላይ እንዳትመረር፣ እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ የሚል እምነትን እንድታዝል የእዮብን እድል ዳግም እንዲሰጣት እንጸልይላት ዘንድ በክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ። ወንድማችሁ አዶኒ እግዚአብሔር ይባርካችሁ!
Open in Telegramዛሬ ትልቅ ችግር፣ ትልቅ ፈተና፣ ትልቅ ትግል እየተጋፈጥህ ይሆናል። ግን አይዞህ በፍርሀት ውስጥ እንዳትኖር። ተንበርከክ ለችግሩ ሳይሆን ለጸሎት፤ ጥበብን ለምን በአቋራጭ ለማለፍ ሳይሆን በትክክለኛው መንገድ ለመሄድ ተስፋ አድርግ በራስህም በሰውም ሳይሆን በእግዚአብሔር! ምክንያቱም የሰው አቅም የራስ ጉልበት የሚያበቃበት ጊዜ አለ። እግዚአብሔር ግን ያለመከልከል ተስፋ ይሆንሀል። ታዲያ የምታገለው ችግር፣ የማልፍበት ፈተና፣ የተናነቅኹት መከራ መፍትሄው ምንድነው? እያልክ ይሆናል። መፍትሄው "እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ አበረታሃለው እረዳህማለው፤ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለው" ያለህ እግዚአብሔር ነው። ልብህን ይሙቀው ሰማይና ምድርን በመዳፉ ላይ የያዘ እግዚአብሔርን የሚያህል አምላክ አለህ። እግዚአብሔር ሆይ ልጅህን አበርታው፤ ልጅህን አበርታት! አሜን ✍አዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8
Open in Telegramአቤቱ🙏 ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ተመስገን። አንተ ሞተን የወደድከን ለምፃም ሳለን ሳትጸየፍ ያፈቀርከን ደጉ ወዳጃችን እናመሰግንሃለን። እንደ ከራድዮን ወፍ በሽታችንን ወስደህ ህይወትን የዘራህብን ሲዖል ወርደህ ያወጣኸን በሞትህ ከሞት የቀሰቀስከን የፍቅር አባት ተመስገን። ተስፋ በተቆረጠበት ቦታ ተስፋን፣ መንገድ በጠፋበት ቦታ መውጫን፣ ጨለማ በበዛበት ቦታ ብርሃንን፣ በዝግ በሮች ፊት ቆመን ሳለ በማንም ኃይል ያልተከፈተውን በር ዐለት የሆነው ክንድህ ስለከፈተልን መድኅን ሆይ እናመሰግንሃለን። በድካማችን ጊዜ ኃይል፣ በፍርሃታችን ጊዜ ሰላም፣ በችግራችን ጊዜ መጠለያ ሆነኸናል። ሰው ሊረዳን ባልቻለበት ጊዜ አንተ አልተውከንም። እንባችንን አባሽ፣ ምስጢራችንን አዋቂ፣ ጩኸታችንን ሰሚ ሆነህ በከፍታም በዝቅታም ከእኛ ጋር ስለሆንክ የናዝሬቱ ኢየሱስ አንተን እናመሰግንሃለን። ነገርን ሁሉ ለበጎ የቀየርክልን፣ በጸሎት የጠየቅነውን በራስህ ጊዜ ስለሰጠኸን፣ የኛ ብልሃት ሳይሆን ያንተ ጸጋ እዚህ ስላደረሰን፣ የኛ ኃይል ሳይሆን እጅህ፣ የኛ ጥበብ ሳይሆን መሪነትህ እዚህ ስላደረሰን፣ ያሰብነውን መልካም ነገር ሁሉ ስላሳካህልን አማኑኤል ሆይ እናመሰግንሃለን። ደግሞም በእኛ የጀመርከውን ስራ እስከ መምጣትህ ቀን ድረስ ፈፅምልን። ለሰጠኸን ሕይወት፣ ላበዛህልን ሰላምና ጤና፣ ለሰጠኸን መልካም ወዳጆች መልካም ቤተሰቦች ሁሉ ክርስቶስ ሆይ ምስጋና ይብዛልህ። አሜንንን!! ✍አዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8
Open in Telegramጸሎት በገንዘብ እጥረት ለሚሰቃዩ እግዚአብሔር ሆይ የሰው ሁሉ ተስፋ አንተ ነህ። ተስፋችንን ከሰቀልንበት ሁሉ ላይ አንስተን አንተ ላይ እናደርጋለን። አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ አንተ በሚያምንህም በሚክድህም ሁሉ ላይ ፀሀይን የምታወጣ ሁሉን አደላዳይ አምላክ ነህና የተሰበሩትን ልብ እንድትፈውስ፣ የተጠሙትን ምንጭ ሆነህ እንድታረካ፣ የተራቡትን በበረከትህ ጠል እንድታጠግብ፣ በገንዘብ እጥረት የሚሰቃዩትን ሁሉ በምህረትህ እንድትመለከት እለምንሃለው። ቸሩ ሆይ ለልጆቻቸው የዕለት ጉርስ ማቅረብ የተሳናቸውን እጃቸው ያጠረባቸውን ቤተሰብ ተመልከት፣ ለልጆቻቸው የትምህርት ቤት ክፍያ መክፈል ያቃታቸውን ወላጆች እንድትመለከት በጌታ በኢየሱስ ስም ለመንኩህ። ዕዳ የከበዳቸውን በመንገድ ሲሄዱ በሃሳብ የሚዋልሉትን ወገኖች፣ ቤተሰባቸውን መመገብ የሚችሉበትን አቅምና ገንዘብ አጥተው በህሊናቸው የሚሰቃዩትን፣ ስራ ፈልገው ማግኘት ያልቻሉ ወንድም እህቶችን፣ በደጃቸው ጎዳና የመውጣት የሰው እጅ የማየት አደጋ የተጋረጠባቸውን፣ ሲያጡ ሰው ሁሉ የራቃቸውን ሁሉ የረሳቸውን አንተ ታስባቸው ዘንድ እለምንሃለው። አገልጋዮችህ ስለ ዕለት ጉርሻ እያሰቡ ወንጌልህን መሸቀጫ እንዳያደርጉት፣ በድህነት የተጎዱት በተስፋ መቁረጥ እንዳይመቱ የአንተ ምህረት ይያዛቸው። ቸሩ ሆይ አንተ ሰማይና ምድርን በእጅህ መዳፍ የያዝህ የሁሉ ነገር ገዢና ፈጣሪ ገንዘብ ለሚያስጨንቃቸው ሁሉ ታቀርብላቸው ዘንድ እለምንሃለው። ገንዘብ በማጣት የሚጨነቁትን ሁሉ እጃቸው ባዶ ከመሆን ታደጋቸው። ያላሰቡትን የበረከት ጠል ሰማይህን ነድለህ አፍስስላቸው። የሚሰሩትን ስራ ትባርክላቸው፣ ድካማቸውን በፍሬ ታጅብላቸው ዘንድ፣ የገቢ ምንጭ ላጡ ትከፍትላቸው ዘንድ ግራ ግብት ያላቸውን አዕምሯቸውን በማስተዋል ትጎበኘው ዘንድ፣ በራሳቸው አቅምን የማይችሉትን በአንተ ጉልበት እንዲችሉ ጥበብና ኃይልን ስጣቸው። በተቸገሩበት ነገር ሁሉ የሚረዳቸውን መልካም ሰው ታዘጋጅላቸው ዘንድ እለምንሃለው። የተዘጉ በሮችን ትከፍትላቸው፣ የራቃቸውን በረከት ታቀርብላቸው ዘንድ እለምንሃለው። ገንዘብ ስትሰጣቸው በትዕቢት እንዳይሞሉ፣ በብዛት ስትባርካቸው አንተን እንዳይረሱ፣ በእጃቸው የሚገባውንም በጥበብ እንዲጠቀሙበት አስተምራቸው። አቤቱ ለሌሎች የሚቆረስ ልብ ያጡትን ልባቸው የደነደነባቸው፣ ገንዘብን ለማከማቸት እንጂ ለመስጠት እጃቸው ያጠረባቸውን ሁሉ ትፈውስ ዘንድ እለምንሃለው። ያለንን ከሌላቸው ጋር መካፈልን አስተምረን። የድሆችን ጩኸት እንዳንንቅ፣ የተራቡትን እንዳንረሳ፣ በችግር የወደቁትን እንዳንፈርድባቸው ልባችንን በፍቅርህ ሙላው። ሀብት ሲመጣ ትዕቢተኞች እንዳንሆን፣ በድህነት ስንኖርም ተስፋ እንዳንቆርጥ ጠብቀን። በሁሉም ሁኔታ አንተን እንድንታመንና ለወገኖቻችን የምሕረት እጅ እንድንዘረጋ እርዳን። በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለመንኩህ። ስለሰማኸን ተመስገን!!! ✍አዶኒ Telegram👉 t.me/adonigospel Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8
Open in Telegram