Кабинет

Посты канала የልቤ ድርሰት የብዕር ጠብታ

сначала новые

#1210Текст
Просмотры198−44%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#1208Фото
Просмотры260−27%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#1203Текст

. . ታክሲ ውስጥ.. ሰውዬው፦ መጽሐፍ አንባቢ ነህ መሰል? እኔ፦ አይ አይደለሁም፤ ሻጭ ነኝ።(ምን ይለኝ ይሆን?) ሰውዬው፦ በወጣትነትህ፤(እንደ ማዘን አሉ) ለምን ሌላ ስራ አትሰራም? ኢትዮጵያ ውስጥ'ኮ እንኳን ገዝቶ የሚያነብ ተውሶ እራሱ የሚያነብ የለም.. (ንዴቴን ውጬ ዝም ስለው ቀጠለ..) ከቻልክ ቢዝነስ ቀይር..ይሄ (ስልኩን እያሳዬኝ) Popo Live የሚባለው የብዙ ሰው ህይወት እየቀየረ ነው። እኔ፦ ጋሼ እርስዎ ግን መጽሐፍ ያነባሉ? ሰውዬው፦ ምን ባክህ መጸሐፍ በ"ያ ትውልድ" በኛ ጊዜ ቀረ። ሁሉንም አልፈንበታል። በዚህ ጊዜ ትምህርት እና መጽሐፍ ምን ሊረባ.. እኔ፦ እና ትርፍ ጊዜዎትን በምን ነው የሚያሳልፉት?(የ"ያ ትውልድ" ሰዎች ግን ሙተው አያልቁም? ለነገሩ ደህናዎቹማ ሞቱ'ኮ እንክርዳዶቹ ናቸው በህይወት ያሉት..?!) ሰውዬው፦ ያው ኳስ አያለሁ ወይ Popo live እቀመጣለሁ.. እኔ፦ ጋሼ ግን በዚህ እድሜዎ Popo መቀመጥ አይከብድም?😏 ሰውዬው፦ 😠 (የታክሲው እረዳት ሲዳምጠን ኑሮ ወደ እኔ እያዬ ፈገግ አለ😁) እኔ፦ ወንድሜ ወራጅ አለ.. ጋሼ ያሳልፉኝ ልኑር..ልውረድበት!! . . ደመወዝ ጎሽሜ "ሦስተኛው ኪዳን" መጽሐፉ ላይ ምን አለ? "እኔ በስርዓት ካላደኩ፤ እነርሱም በስርዓት አላረጁም!" . . ደህና ዋሉ ✌️🙂 ✍Aman YTZ @amanytz

Открыть в Telegram
Просмотры336−5%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#1202Текст

. . ትናንት ማታ የገዛሁት እንጀራ.. አዘውትሬ እንጀራ የምገዛበት ሱቅ..ያለወትሮው ሰው በዝቶ ይርመሰመሳል.. እኔም እንደ ደንበኛነቴ.. ከመድረሴ.. "ወንድሜ ለ'ኔ ሁለት እንጀራ ስጠኝማ.." አልኩት (ሁለት ያልኩት ለእራትና ለቀጣይ ቀን ምሳ ነው ደግሞ🙄) ሻጩም ሳያንገራግር.. ወደ እንጀራ ማስቀመጫው ዞረ.. ታዲያ አንዱን እንጀራ ከአንዱ ለመለዬት ሲታገል ዓመት ሆነ..🙂(እንጀራው እጁ ላይ አለመሻገቱ) የተሰበሰበው ህዝብ ያለ ወረፋዬ እያስተናገደኝ በመሆኑም ሲንጫጩበት.. "በቃ ፕሬንድ ሁለቱን በአንድ ልጠፈው?" አለኝ ተጨንቆ.. እኔም "ኧረ ኖርማል ነው! ጠቅልለው" አልኩትና.. በጥድፊያ ብጣሽ ፊስታል ውስጥ እንጀራውን አስገብቶ ሰጠኝ። ሀምሳ ብር ሰጥቼው ዞር ልል ስል.. "ፕሬንድ የጠቀለልኩት ሶስት እንጀራ ከሆነ አይተህ ነገ እንድትከፈለኝ" ብሎ ፈገግ አለ.. "እሺ😄 ችግር የለውም" ብዬ ላጥ ላጥ እያልኩ ወደ በቴ ገባሁ.. ከዛስ? እራት ልበላ እንጀራውን ከፌስታሉ መንጭቄ ሳዎጣ.. ሶስት ነው? ወይስ ሁለት? ለመለዬት ከበደኝ..ባገላብጠው.. ጠርዙን ብፈትለው..("አንለያይም! አሃ አንለያይም አሄ🎶" ዘፈነብኝ!) ለመለዬት የቀረኝ አማራጭ አንድ ነበር.. "እፍፍፍፍ" አልኩት! ሦስት ነው።🫠 . . ደህና ዋሉ🙌🙂 ✍Aman YTZ @amanytz

Открыть в Telegram
Просмотры310−13%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#1201Текст
Просмотры288−19%к среднему
Пересылки—
Реакции3
Комментарии—
#1200Текст

. . የመጽሐፍ ርዕስ፦ ምናልባት አንድ ቀን... የደራሲው ስም፦ ሄኖክ በቀለ ለማ አሳታሚ፦ ጃፈር መጽሐፍት የገጽ ብዛት፦ 207 የኅትመት ዓመት፦ ነሐሴ 2018 ዓ.ም ሄኖክ በቀለ በቀድሞ እጅግ ተወዳጅ ስራው በ"ሀገር ያጣ ሞት" መጽሐፉ እና "ይናፍቀኛል" በተሰኘው የግጥም መድብል ስራዎቹ እናውቀዋለን። ሄኖክ የክረምቱን ዜማ ጠብቆ ይሄን "ምናልባት አንድ ቀን..." መጽሐፍ ጀባ ካለን ሰነባብቷል። "ይህን መጽሐፍ ካጣጣምነው አንባቢዎች መካከል እኔ አማን ልመሰክርለት እጣ ወደቀብኝ። ሰነበትኩ። ተመሰጥኩ። መጨረስ እንደማይቀርልኝ ሳውቅ ከመጽሐፉ ጋር ጡዤ ወደኩ።"... እንዲህ ስላለ ውብ መጽሐፍ ዳሰሳ ሲጻፍ የሚጀመረው ከየት ነው?...(..እንደሚመስለኝ ሁሉም ከልጅነት/ከመነሻው መጀመር ይኖርበታል") . . ምናልባት አንድ ቀን.. ከእጄ እንደገባ ትንሽ ገለጥ አድርጌ አየሁት "በለው!" ይሄማ ቺት የሚደረግበት ወይ ተደርቦ የሚነበብ አይደለም ብዬ መልሼ አስቀመጥኩት። ከዚያም ጀምሪያቸው የነበሩ መጽሐፍትን ጨርሼና ጥግ አሲዤ "ምናልባት አንድ ቀን.." ጀመርኩት.. እኔ የጊዜ፣ ናፍቆት እና የትዝታ ተጠቂ ነኝ። በነዚህ ዙሪያ ያለ ሐሳብ፣ ምልከታ እና ፍልስፍና.. ሰቅዞ ነው የሚዘኝ። እወዳለሁ። ጥሩ መጽሐፍ ማለት ለኔ "ሳነበው መድገም እንዳለብኝ እንዲሰማኝ የሚያደርግ፣ አዕምሮዬ ውስጥ የመጽሐፉን ፍሰት የጠበቀ ሙዚቃ ሲያጅበው፣ የቋንቋው ውበት፣ የሐሳቡ ልቀት፣ ግምቴን እና ምቾቴን ሲጥስ፣ ሲጋፈጠኝ፣ አለማወቄን ሲያሳዬኝ፣ እንዳያልቅ ስስት ሲለቅበኝ፣ እይታዬን ሌላ አቅጣጫ ሲጠቁመው፣ ጊዜ፣ ፈጣሪን፣ እምነት፣ ትዝታ፣ ናፍቆት፣ ተስፋ፣ ሞት እናም ህይወትን በተለዬ መንገድ ሲዳስስ... ነው። በነዚህ ሁሉ በኩል "ምናልባት አንድ ቀን.." ከሚዛኔ ሞልቶ አጊንቸዋለሁና "ጥሩ መጽሐፍ ነው!" እላለሁ። መጽሐፉ ላይ ያሉ ገጸባህሪያት ለምን የኖርኩትንና ያየሁትን ህይወት ተላበሱ? ህይወት እውነት አዲስ ነገር የላትም? በተለያየ ጊዜ እና ቦታ ተፈጥረን ተቀራራቢ ልጅነት እንዴት ኖረን? የእኔስ እሺ ጓደኞቼ እና የሰፈሬ ሰዎች እንዴት እዚህ ገቡ? ጭራሽ አጎቴ "ጎዳና" የሚባለው ዋና ገጸባህሪ አያት ሆኖ ተከስቷል! ምን ጉድ ነው? (.."አደከምኩት" ብላ አዝናልኝ በጣም በዝግታ ስታለቅስ ይሰማኛል። .. እኔም.. በክንዴ ምሕረት ላይ መውደቋን አስቤ በዝግታ አለቅሳለሁ።")ገጽ 8&9💔 ያለማጋነን "ምናልባት አንድ ቀን.." ለእኔ ባለሁበት ያገኘኝ፤ በስስት ያነበብኩት፤ ደግሜ እስካነበው የምጓጓለት.. በHighlight marker እና እርሳስ አስምሬ አስምሬ የደለዝኩም መጽሐፍ ነው። ደራሲውንም ደግሜ ደጋግሜ የማመሰግንበት ስራው ነው። All Time Favorite ከምላቸው መጽሐፍት "ምናልባት አንድ ቀን..." ዘው ብሎ ገብቷል።("ሀገር ያጣ ሞት" እንዳለ ልብ ይሏል።) . . መጽሐፉ ውስጥ ያሉ ሁሉም ገጸባህሪያት ከስማቸው ጀምሮ ነክተውኛል.. መጽሐፉን አንብቤ ስጨርስ የተሰማኝን ለመጻፍ የቤት ስራ ነው የሆነብኝ። ባይሆን ግን ቢያንስ በሐሳብ ዥው ካደረጉኝና አስምሬ ከያዝኩላቸው መካከል ትንሽ ልበላቹህማ.. "ጎዳና" የተባውን ገጸ ባህሪ እፈራዋለሁ፤ እርሱም'ኮ ፈሪ ነው፤ ግን ፍርሃቱ ሲያሳደው ያሳዝናል። ምስኪንና ነገውን በትናት የተካ ሰው። ርቆ ሄዶ እንኳ ዞሮ ማዬትን የሚመርጥ.. ገጽ 49 ላይ ምን ይላል.. "ልብ ሲለወጥ በስንት ቀን ነው? ለአንዳንድ ሰዎች መለየታቸውን የፈቀድን ጊዜ እረፍታቸው እየተመኘን ነው።"🖤 . . ያለ ቅያሜ፤ ያለ ማንም ስህተት ሆነ በደል "መለያየት" እንዴት ነው? ጎዳና ሆይ.. ገጽ 83 "..ወንድ ልጄን አየሁት።.. አንድ ቀን በአባቴ ቤት ውስጥ አድረን ብንነሣ የስድስት ዓመታት ያህል አደገብኝ።.."🔂Loop!? . . መጽሐፉን ትንሽ አነብና እንደገና ደግሜ ለመጀመር ሳስብ ከዚያም ጨርሼ ብደግመው አይሻልም? እያልኩ ገፋ ገፋ ሳደርገው "ሐዋዝ" የሚባል ምስል ጋር ተፋጠጥኩ.. የሐዋዝ አባት እጅግ አስተዋይና በሳል ሰው ነበሩ። ሐዋዝ ደግሞ አማልዕክቶች የወደደውን ነገር ሰጥተው የሚፈትኑት ብኩን.. ገጽ 122 ላይ የሐዋዝ አባት(ጋሽ ባሕሩ) በሐሳቡ ተስለው.. "መሰንቆህስ?" ይሉታል.. ሐዋዝ ይደነግጣል.. እኔን ግን ነዘረኝ!!! ልክ "አዳም የት ነህ?" እንደመባል.. እራሴን አየሁ "የት ነኝ?" አልኩ.. ልጅነቴ በመጽሐፉ ገጽ በኩል ብቅ ብሎ "እርሳስህስ? ህልምህስ? ምኞትህስ? በቀልህስ?.." አለኝ..በሐሳብ ነጎድኩ.. ከሐሳቤ ስመለስ "እረፍቴን አስሳለሁ!" የምትል ጽሁፍ Note app ላይ ጽፌ አገኘሁ፤.. ወደ ንባቤን ተመለስኩ.. ("ስለ ሐዋዝ ሚስትስ? ስለ ሀገሩ ሰዎችስ? ስለ አባቱ? ስለ መሰንቆውስ? ስለ ድምጹስ? ስለ እርሻው? ስለ ስጋውስ? ስለ ተረገዘው ልጅ? ስለ መንገዱስ?.." ብላቹህ እዳትጠይቁኝ፤ ምንም አልልም አንብቡት።) . . ገጽ 127 ላይ "አሜን" የተሰኘው ገጸባህሪ ብቻውን ፊት ፊት እየመራ ጉዞ አስጀመረኝ..(እዚህ ላይ "ተባረክ!" ብዬ ደራሲውን መረኩት) አሜን የማውቀው የሰፈሬ ልጅ ነው?! አብሮ አደጌ.. አሜን እድገቱም ህይወቱም ያሳዝነኛል.. በርሱ ህይወት ዛቢያ ላሉ ቁስለኞች ሁሉ ይታመማል.. ገጽ 129 ላይ እንዲህ ይላል.. "ሁሉም ሲያልፍ ትላንት በቀልባችን ውስጥ የማይነቀል ችካል ተክሎ ያሰቃየናል። ትዝታ ምስኪኖችን ከማሰቃየት ውጪ ሌላ ሥራ የለውም።" ከአሜን ንግግር ወይም ምልከታዎች ሁሉንም ብጽፍላቹህ እንዴት ደስ ባለኝ.. አሳዛኝ ልጅነት ምን አይነት ገጸባህሪን ገነባ? እግዜርስ "ህይወት" በተባለ ሰፊ ጥቁር ምጣዱ ላይ "ኑሮ" በሚባል መቁያ እያገላበጠ እስከመቼ ድረስ ነው እያሳረረ እሚያከስለን? ብዬ እጠይቃለሁ.. . . በሄኖክ በቀለ ለማ "ምናልባት አንድ ቀን.." መጽሐፍ.. በጥልቅ ሳትነኩ፣ Sensitive ከሆናቹህ ደግሞ ሳታለቁሱ፣ በሚያነሳው ሐሳብና እይታ፤ እንዲሁም በቋንቋው ለዛና ውበት ሳትገረሙ አትቀሩም። . . ስለዚህ መጽሐፍ የተሰማኝን ለማጻፍ ስነሳ የቱን ጠቅሼ የቱን ልተው? በጣም ግራ እየተጋባሁ፤ መልሼ መጽሐፉን እያየሁ.. ስለወደዱት መጽሐፍ መናገር እንዲህ ይከብዳል? በእርግጠኝነት ልል የምችለው ለሰው ላወራው የምፈልገውን ውስጥ ቁንጽሉን እንደጻፍኩ ነው። ብቻ የሆነው ሁኖ "ምናልባት አንድ ቀን.."ን በእኔ ይሁንባቹህ አንብቡት። ከእያንዳንዱ ክፍል መግቢያ ሁለት ስንኝ ግጥም ጀምሮ፤ ስለ ጊዜ፣ ቦታ፣ ትዝታ፣ ሐገር፣ ፍቅር፣ ልጅነት፣ ህልም፣ የህይወት Cycle፣ እምነት፣ እውነት.. የሚያነሳቸው ሐሳቦችና የሚተርክባቸው አውዶች፤ የመጽሐፉ ርዕስ፣ የሽፋን ገጽ፣ ሕትመት፣ ቅንብር.. ወድጄ አመስግኘ ያነበብኩት.. የታየሁ፣ የተሰማሁ፣ ለካ ሁላችንም መጻፍ የለብንም! አንዳንዴ ዘመናችን ላይ የተከሰተን ደራሲ አምነን መኖር ነው ያለብን!! ያስባለኝ መጽሐፍ ነው። ሄኖክ ቀጣይ ደግሞ ምን ያስነብበን ይሆን? . . ለዚህ ጽሁፍ መዝጊያ.. ይህ ጉደኛ መጽሐፍ ብሎ ብሎ ወደ መጨረሻ የሚያመጣትን.. "አምሳለ"(ሀምሳለ)ን መዝሙር ዘምረን እንቋጭ.. "ኧረ አምሳለ! ኧረ ሆይ! አለሁ በመከራ እንባዬን ሳዘራ.. አገዳም የለኝ፤ ምስኪን ድሃ ነኝ፤ ምስኪን ደሃ ሆነሽ ምን በልተሽ ታድሪያለሽ? ባገኝም በልቼ፤ ባጣም ተደፍቼ" . . አመሰግናለሁ። ✍️ Aman Ytz @amanytz ጥቅምት 19/2019ዓ.ም

Открыть в Telegram
Просмотры487+37%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#1198Фото
Просмотры1 330+275%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#1197Текст

. . "#እረፍቴን_አስሳለሁ!" . . በተከፈተው መስኮቴ.. ዘልቆ የሚገባውን የተጉተመተመ ድምጽ አጥርቼ ለመስማት እየሞከርኩ ለሰዓታት ተወዘትኩ.. "ምን እየጠበኩ ነው?" ውስጤ ይጠይቃል.. "እነሆ የምስራች፤ የእግዜር መንፈስ ባንተ ላይ ነው፤ ከቸሩ አምላካችን ከፍጥረታት ሁሉ ጌታ ባለመዋልነትን አግኝተሃልና ደስ ይበልህ!" የሚል የመላዕክ ድምጽ እየጠበኩ ነው? "የጀግናው፤ አርበኛ፤ ለተገፉና በችግር ለሚገላቱ ወገኖች ሁሉ ፈጥኖ ደራሽ የሆነው፤.. መኖሪያ ቤት'ኮ እዚያ የተከፈተው መስኮት እሚታይበት ፎቅ ላይ ነው። ዘመኑ ሁሉ የተባረከ ይሁን።" እያሉ.. እየተጠቋቆሙ ስለእኔ ቸር ነገር የሚያዎሩ ሰዎችን.. "ኧረ መስኮቱ ክፍት ነው፤ እንጥራው? ወጥቶ አብሮን ባይውል እንኳ ሰላም ካለን በቂ ነው፤ ድሮ ድሮ'ኮ በመስኮቱ ብቅ ብሎ አድናቂዎችን ያዬን ነበር.. አቤት ቁንጅናው፤ ግርሞገሱ.. አሁን አሁን ግን..ጠፋ!.. እሱን ያገባች ሴት ምንኛ የታደለች ናት?" ዓይኔን ለማዬት የሚጓጉ..የእንስቶችን አድናቆት.. . . ሙዚቃ ይሰማኛል..🎶🎶 "..Don't wake me i'm not dreaming.. past lives could never hold me down. lost love.. i've got the strangest feeling.."🎶🎶 . . "ዛሬም መስኮቱ ክፍት ነው፤ የዚያ ሰነፍ ጨለል፤ ተኝቶ እንዳላደረ ሰው ሁሉ ተኝቶ የሚውል፤ የልጅ ኪሳራ። እናቱ ወልዳ፤ መከራዋን አይታ አሳድጋ መናዋን አስቀራት!" የሰፈር ሰዎች ስሜን በክፉ ሲያነሱ ለመስማት.. "ከዚህ መስኮት ብቻ አንድ ቀን ዘሎ እራሱን እንዳያጠፋ ነው እምፈራው። ለነገሩ አሁንስ ኖረ ይባላል? ሞቷል'ኮ! ቀባሪ አጣ እንጂ.." የሩቅ ዘመዶቼ የቀብሬን ድግስ በማሰብ ሲያሟርቱብኝ.. "ልክ እዚያ ፎቅ ላይ እንደሚኖረው ወጣት የፀላይ መጫዎቻ እንዳትሆኑ እና ተስፋቹ ተሟጦ የሰው መጠቋቆሚያ ከመሆን እንድትጠበቁ፤ ልጆቼ ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ተደገፉ!" ለንስሃ አባቴ የመጥፎ ምሳሌ ግብዓት መሆኔን.. "ለምን? እዚህ ቁጭ ብለህ ጊዜህን ታጠፋለህ፤ ወጣ እንበልና ያስከፉህን፤ እንዲህ ያደረጉህን ሰዎች ሁሉ በመበቀል ላግዝህ!" ሰይጣን በመስኮቴ አጮልቆ.. "ጥሩ ጓደኛዬ ነበር'ኮ ግን ብመክረው አይሰማም፤ እንቢ ማለትና የማይፈልገውን ነገር ለሰዎች ሲል ማድረጉን ካላቆመ ዛሬ እራሱን እዚህ ቦታ ሊያገኘው እንደሚችል፤ ነግሬው ነበር። ለሁኔታዬ ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስዱ ጓደኞቼ.. "ፍቅር ምንድን ነው? ነፍሴ እስኪጠፋ አፈቀርኩት፤ እርሱ ግን ህልሜ፣ ጥበብ፣ ደግነት..("በማቅለል ውስጥ መኖር") እያለ እራሱ ቀሎ እኔንም አቅልሎኝ ነበር፤ ለትንሽ ነው እንደርሱ ከመሆን የተረፍኩት.. የድሮ ፍቅረኛዬ ድምጽ.. . . "በጣራው ላይ ሲረማመድ የዝናቡ ልዝብ ኮቴ፣ መጋረጃው ሲውለበለብ ሰንደቅ ሆኖ ለመስኮቴ፤" . . ከተቀመጥኩበት ሳልነሳ፣ ውስጤ ወጣ አንዳች ሐያል ሽውታ፣ መስኮቱን ገፍትሮ ግጥም አድርጎ ዘጋው፤ ድምጾቹን ከወደ መስኮቱ ስጠብቃቸው፣ ከውስጤ እያስተጋቡ ሰማኋቸው.. ከተቀመጥኩበት ሰፍተው ያዙኝ.. ድምጾቹ ሃየሉ.. በዙ ተባዙ.. የሰራ አካላቴን ሞሉት.. በዚህ ሁሉ ጭቅቅት ውስጥ ከእልፍ አዕላፍ ጫጫታ በቀር ወደ ጀሮዬ የእግዜር ድምጽ አልመጣም ነበር፤ ስለዚህ እኔ ወደርሱ ብሄድ ሳይሻል አይቀርም ብዬ ወሰንኩ.. ከመቀመጥ ብዛት እግሬ እየተንቀጠቀጠ ወደ መስኮቴ ዐመራሁ.. መስኮቴን ከፍቼ ከደፉ ላይ ቆምኩ.. በቅጽበት በየ አቅጣጫው ሰዎች ተሰበሰቡ.. "በስተመጨረሻም ወሰነ?! በቃ ሊዘል ነው፤ ለራሱም ለቤተሰቡም ግልግል ነው!.. ሲሉ ይሰማኝ ጀመር። ድንገት ዓይኔ እንባ ሞላ.. ከመስኮቴ ስር ያሉ ጥቁር እራሶች ደብዝዘው ይታዩኝ ጀመር.. ማረፊያ የሚሆነኝን ድምጽ አሰስኩ.. እጆቼን ቀራኒዮ ላይ እንደተሰቀለው "እየሱስ" ዘረጋሁ.. ዘለልኩ.. ግን አልወደኩም.. በ ረ ር ሁ . . ሙዚቃው ይሰማኛል.. . . ---------------------- "..Sometimes Dreamers finally wokeup.. don't wake me i'm not Dreaming.. don't wake me i'm not.."🎶🎶🎶 . . ጥቅምት 15/2019ዓ.ም ✍Aman YTZ @amanytz

Открыть в Telegram
Просмотры381+7%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#1192Текст

የመጽሐፍ ርዕስ፦ ጻማ የደራሲዋ ስም፦ ትዕግስት ታፈረ ሞላ አሳታሚ፦ ጃፈር መጽሐፍት እና ታሪክ አሳታሚ የገጽ ብዛት፦ 262 የኅትመት ዓመት፦ ሐምሌ 2018 ዓ.ም "ጻማ"ን አነበብኩት.. . . (የመጀመሪያ ጥያቄዬ፦ "ትዕግስት እንዲህ ያለ መጽሐፍ ለመጻፍ እንዴት ደፈረች?") . . ትዕግስት ታፈረ ሞላ ከዚህ በፊት "የባስሊቆስ እንባ" በተሰኘ ተወዳጅ ስራዋ እናውቃታለን፤ ታዲያ በቅርቡ "ጻማ" የተሰኘ መጽሐፏን እና ገበያ ላይ ለዓመታት ጠፍቶ የነበረውን "የባስሊቆስ እንባ"ን 2ተኛ እትም ባንድ ቀን አሳትማ "እነሆ በረከት" ብላን ሰነባብታለች። ለ"ጻማ" ያለኝን ምልከታ(ዳሰሳ ቢጤ) ከህትመቱ፣ ከሽፋን ገጹና ከውስጥ ገጽ ቅንብሩ ልጀምር.. የሽፋን ገጽ፦ ህትመቱ ጥርት ያለና የተዋበ ቢሆንም ከፊት ያለው ሽፋን ስዕል "ገላጭ" ወይም ከምጽሐፉ ይዘት ጋር ተያያዥነት ያለው ያህል ስሜት አልሰጠኝም። የጀርባው የሽፋን ገጽ ግን ፀዴ ነው። ህትመቱ፦ ምንም አይወጣለትም ጥርት ያለ "font" ወረቀቱ ሽሮ ከለር(የዓይን ሶፋ) ነው። የውስጥ ገጽ ቅንብር፦ ደስ የሚልና ከጽሁፉ ጋር የተዋደደ ነው። እንቀጥል.. በዋነኛነት "ጻማ" መጽሐፍን ስናነብ "ኒሻን፣ ጋዜ፣ መሴ፣ ከረኔ፣ ባሪያው እና ጨንገር" የተኙ ገጸባህሪያትን እናገኛለን፤ ገጸባህሪያቱ ከ"ኒሻን" በስተቀር ለኔ ተስማምተውኛል..(ለራሷ ስለማታስብ እና ብኩን ስለሆነች ይሆን?) "ጻማ" መጽሐፍ ከላይ ከጠቀስኳቸው ገጸባህሪያት በልዩነት ሦስቱን ማለትም "ኒሻን፣ ከረኔና መሴ"ን እንደ ምዕራፍ በመጠቀም እጅግ ልብ የሚሰብሩና የማያሰለቹ ታሪኮችን ታስነብበናለች። መጽሐፉን ግን "በይበልጥ" እስከመጨረሻው ለማጣጣም ሆነ ለመውደድ እንደ እኔ ጎንደር አካባቢ ማደግ ወይ እዛ አካባቢ የኑሮ ልምድ ቢኖር ጥሩ ይመስለኛል፤ ምክኒያቱም እኔ እስከማውቀው፤ መጽሐፉ ላይ የተካተቱ "Myth"(አፈታሪኮች) እስከ አሁን ድረስ በሙሉ በአምሓራ ማህበረሰብ በተለይም ቆላማ በሁኑ ቦታዎች የሚነገር እና የሚታመኑ ስለሆኑ፤ ምናልባት እኒያን አፈታሪኮች አቃሎ የሚያይ ወይ የማያውቅ ሰው መጽሐፉን በሆነ መልኩ ላይረዳው ወይ ላይወደው ይችላል የሚል ስጋት አለኝ። እኔ ግን እልሻለሁ "ትዕግስት ታፈረ ሆይ" በበኩሌ ለዚህ መጽሐፍ አመሰግንሻለሁ። (ግን በዚህ አንላቀቅም!) ስሰማው ያደኩትን እና እንደ እውነት የማዬውን(የማምነውን) አልፎም ብዙ ጊዜ "Research" እሰራበታለሁ ወይ "ልቦለድ" አድርጌ እጽፈዋለሁ ብዬ የማስበውን ርዕስ እንዲህ ከበርካታ የማላውቃቸው ነገሮች ጋር አካተሽ ስለጻፍሽ ምስጋናዬ ይድረስሽ። "ጻማ"ን "Spoil" ሳላደርግ ስለ መጽሐፉ መናገር የምችል አይመስለኝም። ስለዚህ በአጭሩ🙄 መጽሐፉ የአጻጻፍ ስልቱም ሆነ ቋንቋው አልጎረበጠኝም። አንድ ቅሬታ አለኝ እርሱም የመጽሐፉ አስተላለቅ ላይ ነው! እዚህ ላይ ብጽፈው ለአንባቢውም ስለማይጠቅም እራሷን ትዕግስት ታፈረን አጊንቼ ላ'ንድ ለሁለት ሰዓት ያክል አውርቼ የምፈታው ይመስለኛል። መጽሐፉ በሐሳብ ጅው አድርገው በሚዎስዱና ጥያቄ በሚጭሩ አረፍተነገሮች የተሰናዳ ነው። ገጽ 70 ላይ.. "ስንዴ መሬት መውደቅን ባይቀበል ፀድቆ ሰዎች አያዩትም ነበር።" ገጽ 85/86 ላይ.. "ጥቁር የነበረው ከሰል ሲራገብ ሌላ መልክ ያወጣል። የፍም ከለር ምንድን ነው? ብቻ ከሰል ፈገግ ገለጥ ሲል ያምራል። እያንዳንዷ መርገብገብ ውበቱን ትገልጣለች፤ እያንዳንዷ መገለጥ ግን ወደ አመድነት ወደ መክሰም ትወስዳለች።" እንዲሁም ገጽ 142 ላይ ደግሞ.. "ኹሉም ሰው የፈጣሪን ነገር አምላክ ሆኖ እንዲያየው የተረገመ ይመስለኛል።" ትለናለች.. . . በመጨረሻም ትዕግስት ታፈረ.. ልቦለድ ጻፈች ለማለት አልደፍርም፤ በቀድሞ ስራዋ "የባስሊቆስ እንባ"ም ቢሆን በእኔ እምነት ሁለቱም መጽሐፎች እጅግ በጣም ወደ ኢ-ልቦለድ የሚያጋድሉ ስራዎች ናቸው። (ለነገሩ ልቦለድስ ቢሆን ከመኖር አደል የሚቀዳው!?) "ጻማ"ን አንብቡት፤ እኔ Relate የማደርገው ነገሬ ብዙ ስለሆነ ወድጀዋለሁ። . . ✍️ Aman Ytz  @amanytz Tiktok ላይ👇 http://tiktok.com/@aman_ytz http://tiktok.com/@aman_ytz

Открыть в Telegram
Просмотры475+34%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—