Кабинет

Посты канала WeCare ET

сначала новые

#3080Фото
Просмотры219−41%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#3079Текст

🚨የስኳር በሽታ ምልክቶችን መለየት ይችላሉ? 🤕ብዙዎቻችን አንድ ከባድ የጤና እክል ሲከሰት በግልጽ በሚታዩና ጉልህ ምልክቶች ራሱን ያሳያል ብለን እናስባለን፤ ነገር ግን የስኳር በሽታ አብዛኛውን ጊዜ ድምፅ ሳያሰማ በቀላሉ ልብ ሊባሉ በማይችሉ ስውር ምልክቶች ይጀምራል። 👵🏽በዕለት ተዕለት ሕይወት የሚያጋጥሙ አንዳንድ የጤና መጓደሎችን «ዕድሜዬ ስለገፋ ነው»፣ «ሥራ ስለበዛብኝ ነው» ወይም «አዲስ የዓይን መነጽር ስለሚያስፈልገኝ ነው» ብሎ ችላ ማለት የእጅግ የተለመደ ነው። ይሁን እንጂ ከእነዚህ ቀላል ከሚመስሉ ምልክቶች ጀርባ ትኩረት የሚሻ ሥር የሰደደ የጤና እክል ሊኖር ይችላል። 😮‍💨የማያቋርጥ የድካም ስሜት በሰውነት ውስጥ በቂ ኢንሱሊን በማይኖርበት ጊዜ ወይም የሰውነት ህዋሳት ኢንሱሊንን መቀበል ሲያቅታቸው ስኳር (ግሉኮስ) ለኃይል ምንጭነት ወደ ህዋሳት ከመግባት ይልቅ በደም ውስጥ ተከማችቶ ይቀራል። ሰውነትዎ የሚፈልገውን ኃይል ባለማግኘቱም የማያቋርጥ ድካም ይሰማዎታል። 💧ከፍተኛ የውሃ ጥም እና ቶሎ ቶሎ መሽናት ኩላሊቶችዎ በደም ውስጥ ያለውን ትርፍ ስኳር ለማጣራት ከመጠን በላይ ስለሚሠሩ ከሰውነትዎ ኅብረ-ሕዋሳት ተጨማሪ ውኃን ይስባሉ። በዚህም ምክንያት ከሰውነት ብዙ ፈሳሽ ስለሚወጣ በተደጋጋሚ መሽናትና ከፍተኛ የውኃ ጥም ይከሰታል። 👓ብዥ ያለ እይታ በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከፍ ሲል፣ በጊዜያዊነት ፈሳሽ ወደ ዓይንዎ ምስሪቶች (Lenses) እንዲገባ በማድረግ ቅርጻቸውን ይለውጠዋል። ይህም የዓይንዎን የማተኮር (Focus) አቅም በማዛባት ዕይታዎ ብዥ እንዲል ያደርጋል። 🦠ዘግይተው የሚድኑ ቁስሎች እና ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ኢንፌክሽኖች ለረጅም ጊዜ የቆየ ከፍተኛ የደም ስኳር መጠን የደም ዝውውርን ስለሚያዘገይና የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም ሕዋሳት ምላሽ ያዳክማል። ይህም ቁስሎች ቶሎ እንዳይድኑ እና ሰውነትዎ በተደጋጋሚ በኢንፌክሽኖች እንዲጠቃ ያደርጋል። ⚠️ልብ ይበሉ በዓለም ዙሪያ የስኳር በሽታ ካለባቸው አዋቂዎች መካከል ግማሽ ያህሉ በሽታው እንዳለባቸው አያውቁም። በመሆኑም ቀላል የደም ምርመራ በማድረግ የደም ስኳር መጠንዎን አስቀድመው ማወቅና መከታተል እጅግ ተገቢ ነው። 👩‍⚕️👨‍⚕️ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር ☎️ 9394 ላይ ይደውሉ ። #wecareet #health #digitalhealth #healthcare #selamdoctor #9394 #diabetesawareness #diabetesawarenessmonth #diabetes

Открыть в Telegram
Просмотры287−23%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#3075Фото

🚨 ነርስ እየፈለጉ ነው ? 👩🏽‍⚕️ብቃት እና ልምድ ባላቸው ነርሶቻችን የሚያስፈልጎትን እንክብካቤ በቤትዎ በተመጣጣኝ ዋጋ ያግኙ ። 🗣 የምንሰጣቸው አገልግሎቶች 📌አጠቃላይ የ24 ሰዓት የነርሲንግ አገልግሎት 📌 የአረጋውያን እንክብካቤ 📌 የጨቅላ ህጻናት እንክብካቤ 📌በስፔሻሊስት ሐኪሞች ክትትል እና ህክምና 📌የስነ-አእምሮ ህክምና 📌 አጠቃላይ የጤና ምርመራ 📌 የስነ-ምግብ ህክምና 📌የፊዚዮቴራፒ አገልግሎት 📌 የስፒች ቴራፒ አገልግሎት 📌የተሟላ የህክምና ቁሳቁስ ኪራይ 👉👉አገልግሎቱን ለማግኘት እና ለበለጠ መረጃ በ 0964686464 / 9394 ☎️ ላይ ይደውሉ ። 📱የ WeCareET የስልክ መተግበሪያን በመጠቀም ስመጥር ስፔሻሊስት እና ሰብ-ስፔሻሊስት ሐኪሞችን በቀላሉ በቤትዎ ሆነው ቢያሻዎት በቪዲዮ ፣ በስልክ ወይም በፅሁፍ መልዕክት ስለ እርሶ እና ስለ ወዳጆ ጤና ይመካከሩ !!! መተግበሪያውን ዛሬውኑ ያውርዱ እና ይሞክሩት ። 👇👇👇👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient https://user.wecare.et #selamdoctor #wecareet #9394 #homecare #ethiopia #healthcare #doctors #nurses #care #elderlycare #nursingcare

Открыть в Telegram
Просмотры337−10%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#3073Фото
Просмотры366−2%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#3071Текст

🚨ትኩረት እና እንክብካቤ ለሁሉም ህፃናት!! 👧🏽እያንዳንዱ ሕፃን የማደግ፣ የመማር እና በሕይወቱ የተሻለ ደረጃ ላይ የመድረስ ዕድል ሊያገኝ ይገባል። ሆኖም በኢትዮጵያ ለብዙ ሕፃናት መሠረታዊ የጤና አገልግሎቶችን እንዲሁም በሽታዎችን የሚከላከሉና ሕይወትን የሚታደጉ ሕክምናዎችን ማግኘት አሁንም ትልቅ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል። 🇪🇹ሀገሪቱ የሕፃናት ሞትን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ መሻሻል ብታሳይም አስቀድሞ መከላከል የሚቻሉ በሽታዎች፣ ከወሊድ በኋላ በአራስ ሕፃናት ላይ የሚከሰቱ የጤና እክሎች እና የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ክፍተቶች አሁንም የብዙ ሕፃናትን ሕይወት አደጋ ላይ ይጥላሉ። 🗓በየዓመቱ ኅዳር 11 (November 20) የሚከበረውን የዓለም የሕፃናት ቀን አስመልክተን በኢትዮጵያ የሕፃናትን ጤናና ሕልውና የሚያሳዩ ወሳኝ አኃዛዊ መረጃዎችን እንመልከት፦ 🎗ከ20 ሕፃናት አንዱ 5 ዓመት ሳይሞላው ይሞታል። 🎗ከ20 ጨቅላ ሕፃናት አንዱ 1 ዓመት ሳይሞላው ይሞታል። 🎗ከ40 አራስ ሕፃናት አንዱ በተወለደ በመጀመሪያዎቹ 28 ቀናት ውስጥ ይሞታል። 🎗ዕድሜያቸው ከ12–23 ወራት ከሆኑ ሕፃናት መካከል ሁሉንም መሠረታዊ ክትባቶች ሙሉ በሙሉ የወሰዱት 30% ብቻ ሲሆኑ፣ 20% የሚሆኑት ደግሞ ምንም ዓይነት ክትባት አልወሰዱም። 🎗36% ገደማ የሚሆኑ ወሊዶች በሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች እርዳታ የማይከናወኑ ሲሆን፣ 38% የሚሆኑት ደግሞ ከጤና ተቋማት ውጭ ይፈጸማሉ። 🎗ከ10 አራስ ሕፃናት 7ቱ (69%) ከተወለዱ በኋላ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት ውስጥ የድኅረ-ወሊድ የጤና ምርመራ አያገኙም። 🎗ዕድሜያቸው 14 ዓመት እና ከዚያ በታች የሆኑ ከ28,000 እስከ 29,000 የሚደርሱ ሕፃናት ከኤች.አይ.ቪ (HIV) ጋር የሚኖሩ ሲሆን፣ በከተሞች አካባቢ በዚህ የዕድሜ ክልል ባሉ ሕፃናት ዘንድ የቫይረሱ ሥርጭት መጠንም 0.3% እንደሆነ ይገመታል። 🎗ከዚህ ቀደም የተካሄደ አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው ከአምስት ዓመት በታች ከሆኑ የታመሙ ሕፃናት መካከል ተገቢውን የሕክምና አገልግሎት የሚያገኙት 20.9% ብቻ ናቸው። ይህም ማለት ከ5 የታመሙ ሕፃናት መካከል አንዱ ብቻ በቂ ሕክምና ያገኛል። ⚠️እያንዳንዱ ከላይ የቀረበው አሃዝ የአንድን ሕፃን ሕይወት፣ ጤና እና የወደፊት ዕጣ ይወክላል። ይህም ሕፃናት ተገቢውንና ጥራት ያለውን ሕክምና በወቅቱ ማግኘታቸው ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ ያሳያል። 💙እያንዳንዱ ልጅ በሕይወት ከመቆየት ያለፈ ነገር ይገባዋል። ስለዚህ እያንዳንዱ ልጅ ጤናማ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ብሩህ ሕይወት የመኖር ዕድል ሊኖረው ይገባል። በዚህ ዕለት የህፃናትን ጤና ለመጠበቅ እና ለመጪው ትውልድ ጤናማ የወደፊት ሕይወት ለመገንባት ያለንን ቁርጠኝነት እናድስ። 💙መልካም የዓለም የህፃናት ቀን !! 💙 👩‍⚕️👨‍⚕️ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር ☎️ 9394 ላይ ይደውሉ ። #doctors #hakim #wecareet #health #digitalhealth #healthcare #selamdoctor #9394 #WorldChildrenDay #worldchildrenprotection #ChildrensDay #childrenhealth #childrenhappiness❤️❤️❤️

Открыть в Telegram
Просмотры431+15%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#3066Фото
Просмотры406+9%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#3065Фото
Просмотры507+36%к среднему
Пересылки—
Реакции1
Комментарии—
#3064Фото

🚨 ዊኬር የቤት ለቤት ህክምና !! 👩🏽‍⚕️ብቃት እና ልምድ ባላቸው የጤና ባለሙያዎቻችን የሚያስፈልጎትን ህክምና እና እንክብካቤ በቤትዎ በተመጣጣኝ ዋጋ ያግኙ ። 🗣 የምንሰጣቸው አገልግሎቶች 📌አጠቃላይ የ24 ሰዓት የነርሲንግ አገልግሎት 📌 የአረጋውያን እንክብካቤ 📌 የጨቅላ ህጻናት እንክብካቤ 📌በስፔሻሊስት ሐኪሞች ክትትል እና ህክምና 📌የስነ-አእምሮ ህክምና 📌 አጠቃላይ የጤና ምርመራ 📌 የስነ-ምግብ ህክምና 📌የፊዚዮቴራፒ አገልግሎት 📌 የስፒች ቴራፒ አገልግሎት 📌የተሟላ የህክምና ቁሳቁስ ኪራይ 👉👉አገልግሎቱን ለማግኘት እና ለበለጠ መረጃ በ 0964686464 / 9394 ☎️ ላይ ይደውሉ ። 📱የ WeCareET የስልክ መተግበሪያን በመጠቀም ስመጥር ስፔሻሊስት እና ሰብ-ስፔሻሊስት ሐኪሞችን በቀላሉ በቤትዎ ሆነው ቢያሻዎት በቪዲዮ ፣ በስልክ ወይም በፅሁፍ መልዕክት ስለ እርሶ እና ስለ ወዳጆ ጤና ይመካከሩ !!! መተግበሪያውን ዛሬውኑ ያውርዱ እና ይሞክሩት ። 👇👇👇👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient https://user.wecare.et #selamdoctor #wecareet #9394 #homecare #ethiopia #healthcare #doctors #nurses #care #elderlycare #nursingcare

Открыть в Telegram
Просмотры481+29%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#3062Фото

🚨የማህፀን እና ጽንስ ስፔሻሊስት ሐኪም ማማከር ይፈልጋሉ !! 👨🏽‍⚕️ዶ/ር ይርጋ ውበቱ የስፔሻላይዜሽን ትምህርታቸውን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያጠናቀቁ የማህፀን እና ጽንስ ስፔሻሊስት ሐኪም ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማገልገል ላይ ይገኛሉ። 🗣የ WeCare ET የስልክ መተግበሪያን በመጠቀም የማህፀን እና ጽንስ ስፔሻሊስት ሐኪም የሆኑትን ዶ/ር ይርጋ ውበቱን ጨምሮ ሌሎች ስመጥር ስፔሻሊስት እና ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪሞችን በቀላሉ በቤትዎ ሆነው ቢያሻዎት በቪዲዮ ፣ በስልክ ወይም በፅሁፍ መልዕክት ስለ እርሶ እና ስለ ወዳጆ ጤና ይመካከሩ !! መተግበሪያውን ዛሬውኑ ያውርዱ እና ይሞክሩት። 👇👇👇👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient 💻በኮምፒውተር ታግዘው ለማማከር ካሾት የWeCareETን የታካሚዎች ድህረ-ገጽ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ። 👇 https://user.wecare.et 👩‍⚕️👨‍⚕️ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር ☎️ 9394 ላይ ይደውሉ ። #wecareet #health #digitalhealth #healthcare #selamdoctor #9394 #gynecology #gynecologist #reproductivehealth

Открыть в Telegram
Просмотры454+22%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#3061Текст

🚨ሰማያዊ ብርሃንን የሚከላከሉ መነጽሮች ((Blue-cut lenses) በእርግጥ ይሰራሉ? 👓ሰማያዊ ብርሃንን የሚከላከሉ መነጽሮች (Blue-cut glasses) ከዲጂታል ስክሪኖች የሚወጣውን ሰማያዊ ብርሃን ለማጣራት ተብለው ልዩ ሽፋን ተደርጎባቸው የሚሰሩ መነጽሮች ናቸው። 👁 ምንም እንኳን በገበያ ላይ ከፍተኛ ተወዳጅነት ቢኖራቸውም ዓይንን ከስክሪን ጉዳት የመጠበቅ ፋይዳቸው እጅግ አነስተኛ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ። እንደ አሜሪካ የዓይን ሕክምና አካዳሚ (AAO) እና የኦፕቶሜትሪስቶች ኮሌጅ (College of Optometrists) ያሉ ታላላቅ የዓይን ጤና ተቋማትም ለዕለት ተዕለት የስክሪን አጠቃቀም እነዚህን መነጽሮች ማድረግ አስፈላጊ ስለመሆኑ በቂ ማስረጃ እንደሌለ ይገልጻሉ። 👉ሳይንሳዊ ጥናቶች ምን ይላሉ? 👓የዓይን መድከምን፣ ራስ ምታትን ወይም ከስክሪን ጋር የተያያዘ ምቾት ማጣትን በመቀነስ ረገድ ከተለመዱት ግልጽ መነጽሮች (Regular clear lenses) የተለየ ውጤት አላሳዩም። 👓ከስክሪን ጋር የተያያዘ የዓይን ድካም አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው ዓይንን በበቂ ሁኔታ ካለማርገብገብ (የዓይን መድረቅን ያስከትላል)፣ ከብርሃን ነጸብራቅ (Glare)፣ ባልታረሙ የዕይታ ችግሮች እና ስክሪኖችን ወደ ዓይን በጣም አቅርቦ ከመመልከት ጋር የተያያዘ እንጂ በሰማያዊ ብርሃን ምክንያት አይደለም። 👓ከስክሪን የሚወጣው ሰማያዊ ብርሃን በዓይን ብሌን (Retina) ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ የሚያሳይ አስተማማኝ ማስረጃ የለም። ከዚህም በተጨማሪ በስክሪን ምክንያት የምንጋለጠው ሰማያዊ ብርሃን መጠን ከተፈጥሮ የፀሐይ ብርሃን ከምናገኘው ጋር ሲነጻጸር እጅግ አነስተኛ ነው። 👓ለመተኛት ሲቃረቡ ለሰማያዊ ብርሃን መጋለጥ «ሜላቶኒን» (Melatonin) የተባለውን የእንቅልፍ ሆርሞን ሊገታ ይችላል። ለዚህም ሰማያዊ ብርሃንን የሚከላከሉ መነጽሮች የተወሰነ ጥቅም ሊሰጡ ይችላሉ ነገር ግን በስልክ ወይም በኮምፒውተር ላይ "Night Shift" ወይም "Eye Comfort" የተባሉ አማራጮችን መጠቀም አሊያም ከመተኛትዎ አንድ ሰዓት በፊት ስክሪን መመልከትን ማቆም የበለጠ ውጤታማ ነው። 👓አንዳንድ ሰዎች መነጽሩን ሲያደርጉ የተሻለ ምቾት እንደሚሰማቸው ይናገራሉ። ይህም በዋናነት የሚመጣው ከሰማያዊ ብርሃን ማጣራት ባሕሪው ሳይሆን መነጽሮቹ ካላቸው ተጨማሪ ፀረ-ነጸብራቅ ሽፋን (Anti-reflective coating) እና ብርሃንን የመቀነስ አቅም አሊያም «ይጠቅመኛል» ከሚል ስነ-ልቦናዊ እምነት (Placebo effect) የተነሳ ነው። 👩‍⚕️👨‍⚕️ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር ☎️ 9394 ላይ ይደውሉ ። #wecareet #health #digitalhealth #healthcare #selamdoctor #9394 #BlueCutLenses #glasses #DigitalEyeStrain

Открыть в Telegram
Просмотры504+35%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—