Кабинет

Посты канала Ministry of Culture And Tourism – የባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር

сначала новые

#7410Фото
Просмотры258−41%к среднему
Пересылки—
Реакции2
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
5 ч217
10 ч258
  1. Через 6 часов217
  2. Всего сейчас258
#7405Фото

ሁለተኛው የአፍሪካ ፊልም ገበያና ሽልማት መድረክ (AAFMA 2026) በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው:: ህዳር 15/2019 ዓ.ም ​አዲስ አበባ ​የኢ.ፌ.ድ.ሪ. ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እና ኢትዮ-አርክውድ ኢንተርቴይመንት አ.ማ በጋራ ያዘጋጁት ሁለተኛው የአፍሪካ ፊልም ገበያና ሽልማት መድረክ (AAFMA 2026) ከህዳር 18 እስከ 19 ቀን 2019 ዓ.ም. በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እንደሚካሄድ ተገለጸ። መድረኩን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ፤ የመደመር መንግሥት በፓናፍሪካኒዝም እሳቤ የተቃኙ የኪነ-ጥበብ ሥራዎች ተደራሽ የሚሆኑበት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ጠቅሰው፣ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የፊልም ፕሮዳክሽንና የኮንፈረንስ ቱሪዝም (MICE) ማዕከል ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን አስገንዝበዋል። አያይዘውም ኪነ-ጥበብ ሀገራዊ እሴቶችን ለማስተዋወቅ፣ አፍሪካውያን በራሳቸው አንደበት ታሪካቸውን በመተረክ የተሳሳቱ ትርክቶችን ለማረም እንዲሁም የሀገሪቱን የቱሪዝም መዳረሻዎች በማስተዋወቅ የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነትን (PPP) ለማጠናከር ጉልህ ፋይዳ እንዳለው አመልክተዋል። See more https://www.facebook.com/share/1EEKCm8rgb/ www.visitethiopia.et ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት http://mot.gov.et https://www.facebook.com/Ethiopialandoforigins https://web.facebook.com/ https://t.me/tourismethiopia t.me/ethiopialandoforigins ​

Открыть в Telegram
Просмотры322−26%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#7394Фото

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሰራተኞች በተሻሻለው የቱሪዝም ፖሊሲ ዙሪያ ስልጠና ወሰዱ:: ​አዳማ፣ ህዳር 12/2019 ዓ.ም ​ከ18 ዓመታት በላይ ሲያገለግል ቆይቶ ወቅቱን በዋጀ መልኩ ተሻሽሎ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀውን አዲሱን የቱሪዝም ፖሊሲ ወደ ተግባር ለማስገባት ያለመ የሁለት ቀናት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በአዳማ ከተማ ለሚኒስቴሩ ሰራተኞች ተሰጥቷል። ​ስልጠናውን ያስጀመሩት በሚኒስቴሩ የዴሊቨሪ ዩኒት አስተባባሪ አቶ ቴዎድሮስ ደርበው፤ አስፈፃሚ አካላት የፖሊሲውን ምንነት በሚገባ ተረድተው ወደ ትግበራ መግባታቸው ወሳኝ መሆኑን ገልፀው፣ የፖሊሲውን መነሻዎች፣ መርሆች፣ ዓላማዎችና የክለሳውን አስፈላጊነት አብራርተዋል። ​በመድረኩ የዚህዓለም ሲሳይ (ዶ/ር) የፖሊሲውን ዋና ዋና ጉዳዮች በስምንት መሠረታዊ አምዶች ማለትም በመዳረሻ ልማት፣ በቅርስና ተፈጥሮ ጥበቃ፣ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ በግሉ ዘርፍ ተሳትፎ፣ በአገልግሎት ጥራት፣ በግብይትና ማስተዋወቅ፣ በአቅም ግንባታ እና በስልታዊ አጋርነት ዙሪያ ዳስሰዋል። ​አቶ ኢተፋ ጉዲና በበኩላቸው ከፖሊሲው ስለሚጠበቁ ውጤቶች፣ ስለሚወጡ የልማት ፕሮግራሞችና ስለ ትግበራው ገለጻ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል። ተሳታፊዎቹም መድረኩ አቅማቸውን በማጎልበት አዲሱን ፖሊሲ በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልፀዋል።

Открыть в Telegram
Просмотры528+21%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#7386Фото

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መካከለኛ አመራሮች የቤተ መንግሥት ሙዚየምን፣ የቀበና ወንዝ ዳርቻ ልማትን እና የሳይንስ ሙዚየምን ጎበኙ:: **** ​የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መካከለኛ አመራሮች የኢትዮጵያን ታሪካዊ ቅርሶች፣ የተፈጥሮ ሀብቶችና የዘመናዊ ልማት አቅሞችን በተግባር ለመመልከት በአዲስ አበባ የሚገኙትን የቤተ መንግሥት ሙዚየም፣ የቀበና ወንዝ ዳርቻ ልማት እና የሳይንስ ሙዚየምን ዛሬ ጎብኝተዋል። ​አመራሮቹ በጉብኝታቸው ወቅት የሀገሪቱን የዳበረ ታሪክና ቅርስ የሚያስተዋውቁ ሀብቶችን፣ የከተማዋን ውበትና የነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የተከናወኑ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችን፣ እንዲሁም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕውቀትን ለማስፋፋት የተገነቡ ዘመናዊ ማዕከላትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ​እነዚህ የጉብኝት ስፍራዎች ያለፈውን ታሪክ ከዛሬው የልማት ጉዞ ጋር በማስተሳሰር የሀገራችንን እምቅ ጸጋ፣ አቅምና የወደፊት ተስፋ በጉልህ የሚያሳዩ ቁልፍ የቱሪዝም መዳረሻዎች መሆናቸው ተመላክቷል። ጉብኝቱ አመራሮቹ በዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ ሀገራዊ የልማት ሥራዎችን በቅርበት እንዲገነዘቡና የቱሪዝም መዳረሻዎችን የማስተዋወቅ ሥራውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚያግዝ ነው።

Открыть в Telegram
Просмотры580+33%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—