የጥናት መምሪያው ተዘጋጅቷል! አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ለተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች መጽሐፋ እንዲደርስ አድርገናል! ዛሬ የጥናት መምሪያው (Study Guide) ለጥናት ተዘጋጅቷል PDF version የምትፈልጉ በነጻ ማግኘት ትችላላችሁ! https://drive.google.com/.../1eSPZXS7gJcxaN.../view... ለጥናት መምሪያው ዝግጅት ወንድም አሸናፊ አሰፋንና ወንድም ተስፋ ጺዮን አበራን በብዙ ልናመሰግናቸው ይገባል! ጌታ ይባርካችሁ! በቅርቡ በሕይወት ቴሌቪዥን የመጽሐፋ ጥናት ይጀመራል (ለአንድ ዓመት) ይተላለፋል! ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!
Открыть в TelegramDr. Tesfaye Robele
ተስፋዬ ሮበሌ (ዶ/ር) ሥነ መለኮት እና ፍልስፍና ያጠና ባለ ጥልቅ እውቀት አቅብተ እምነት ነው። ሥነ መለኮትን እና ፍልስፍናን ለመማር ከፈለጉ ይቀላቀሉን። ይህ ቻናል የራሱ (የዶክተር ተስፋዬ) አይደለም፤ ነገር ግን እኛ መውደዳችንን ለመግለፅና ሰው ሁሉ የእርሱን ጽሑፍ ወይም ቪድዮ በቀላሉ ማግኘት እንዲችል ካለን ፍላጎት የተከፈተ ነው። Ethiopia No: +251921319299 @chereGC
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 18 нояб. 2026 г. | 3 553 |
| 19 нояб. 2026 г. | 2 310 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры3,71 тыс.Пересылки—Реакции40Комментарии—
- 02Просмотры3,49 тыс.Пересылки—Реакции52Комментарии—
- 03Просмотры3,46 тыс.Пересылки—Реакции11Комментарии—
- 04Просмотры2,31 тыс.Пересылки—Реакции74Комментарии—
Новые посты
ከዐሥራ ሁለት ዓመት በፊት፣ በሰሜን አሜሪካ እየታተመ የሚሠራጭ፣ “ተስፋ” የሚባል የምርምር መጽሔት (Journal) አዘጋጅቼ ማሳተምና ማሠራጨት ጀምሬ ነበር! አይ የእኔ ነገር!
Открыть в Telegramውድ ወንድሞና እኅቶቼ እንኳን ለዐዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! ዐዲሱ ዓመት ብዙዎች ወደ ጌታ የሚመጡበት፣ ጌታን ያወቅነው በቃሉና በምግባር የምናድግበት እንዲሆን እመኛለሁ! እጸልያለሁም! እወዳችኋለሁ! ተባረኩልኝ! “ጌታ ሆይ፤ አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መጠጊያችን ሆንህልን። ገና ተራሮች ሳይወለዱ፣ ምድርንና ዓለምን ከመፍጠርህ በፊት፣ አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነህ።” (መዝሙር 90:1-2 አመት)
Открыть в Telegramየዛሬ ሪፓርት ከተስፋዬ ሮበሌ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ባቀረቡት የርዳታ ጥሪ መሠረት ዛሬ በውስጥ መስመር አንድ ሺሕ ሦስት መቶ ዶላር ተሰብስቧል። ስጦታችሁን +16166174746 እንዲሁም በGoFundMe (https://gofund.me/39a7427d6) መስጠት ትችላላችሁ። እግዚአብሔር ፈቃዱ ከሆነና በዚህ መጠን በልግስና የሚሰጡ ሰዎች ከተገኙ በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉ ይህን መጽሐፍ እንደምናዳርስ እሙን ነው! ይህ ($1,300) ዛሬ በውስጥ መስመር የተሰበሰበው ብቻ እንደ ሆነ ልብ ይሏል! እግዚአብሔር ይባርካችሁ!
Открыть в Telegramበውስጥ የደረሰኝ መልእክት! ዶ.ር እንዴት ቆየክ ? ሁሉ ሰላም ነው ? ቤተሰቦችህ ፣ ልጆች ፣ አገልግሎት ፣ ስራ ሁሉ እንዴት ነው ? ሁሉም በእግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት መልካም እንደሆነ እርግጠኞች ነን። Dr. እኔ ይሁን ኢያሱ እባላለሁ። በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የነጭ ሳር ካምፓስ የ 4ኛ ዓመት የህክምና(Medicine ) ተማሪ እና አሁን ላይ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነጭ ሳር ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት በሰብሳቢነት የማገለግል መሪ ነኝ። Dr. ይህንን መልእክት ልጽፍልዎት የደፈርኩት አንድ ትንሽ ጥያቄና ልመና ስላለን ነው። እርስዎ የጻፏቸውን መጽሐፍት ተማሪዎች በማንበብ እንዲማሩና በእምነታቸውም እንዲያድጉ በጣም ፍላጎት አለን። በተለይም በፌሎሺፓችን ውስጥ ብዙ ተማሪዎች መጽሐፍትን ለማንበብ ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖራቸውም፣ በኢኮኖሚያዊ ሁኔታቸው ምክንያት መጽሐፍትን መግዛት አይችሉም። ስለዚህ Dr. በትህትና ልንጠይቅዎት የፈለግነው፣ ከመጽሐፍትዎ የተወሰኑ ቅጂዎችን ለፌሎሺፓችን ልትለግሱልን ብትችሉ በጣም ትልቅ ስጦታ ይሆንልናል። እኛ የምንፈልገው ለግል ጥቅም ወይም ለሽያጭ ሳይሆን በፌሎሺፓችን ውስጥ በ Financial አቅም ማጣት ምክንያት መፅሐፍ ገዝተው ማንበብ ለማይችሉ ልጆች አንድ ትንሽዬ ቤተ-መጽሐፍት መጀመር እንፈልጋለን። መጽሐፍቱን መግዛት የማይችሉ ተማሪዎች በነፃ እንዲያነቡ፣ እንዲማሩባቸውና የተማሩትንም በሕይወታቸውን እንዲገነቡ ነው ዓላማችን። Dr. አንድ ተማሪ የእርሶን መጽሐፍ አንብቦ ቢማርና ቢባረክ ነገ ለብዙ ሰዎች ሊተርፍ ይችላል ብለን እናምናለን። ስለዚህ ከእጅዎ የሚመጣ ማንኛውም መጽሐፍ፣ ብዛቱ ምንም ይሁን ምን፣ ለእኛ ትልቅ ዋጋ አለው። እርስዎ ያደረጉትን ይህንን አገልግሎት እናከብራለን። ስለዚህ ይህንን ጥያቄ ስናቀርብ በጣም በትህትና ነው። የሚችሉ ከሆነ ከመጽሐፍትዎ የተወሰኑትን ለፌሎሺፓችን በልግስና ቢሰጡን እኛም በዩኒቨርስቲ ግቢያችን ለተማሪዎች በረከት እንዲደርስ ብናስችል። ይህ ለእኛ ብቻ የሚደረግ እርዳታ ሳይሆን፣ እነዚህን መጽሐፍት ለሚያነቡ ብዙ የዩኒቨርስቲ ወጣቶች እና በኋላ ለሚያገለግሉት ሰዎች የሚደርስ የእውቀትና የመንፈሳዊ ውርስ እንደሚሆን እናምናለን። ጊዜዎን ወስደው ይህንን መልእክት ስላነበቡልን በጣም እናመሰግናለን Dr. እግዚአብሔር በጽሑፍ አገልግሎትዎ ብዙ ሕይወቶችን እንዲነካ እና እንዲጠቀምዎት ጸሎታችን ነው። ይሁን ኢያሱ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የነጭ ሳር ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረት ሰብሳቢ አረንጓዴው መጽሐፍ ለተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች መስጠት የምትፈልጉ በgofundme ተሳተፉ!
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል@dania_islamicРелигия10,3 тыс.
እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net@ewnetlehuluРелигия10,2 тыс.
ፍቁረ እግዚእ ሚዲያ Fikure Egzi Media – FEM@fikureegzi4Религия10,2 тыс.
ISLAMIC SCHOOL@islam_and_scienceРелигия10,2 тыс.
አስ-ሱናህ ቴቪ | As-Sunnah TV@assunnahtvofficialРелигия10,7 тыс.
ኢስላማዊ እውነታ@islamictruethРелигия9,92 тыс.
GODOLIYAAS@kalabhiyahuРелигия10,9 тыс.
ABX@muhammedseidabxРелигия11,3 тыс.