ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ከማረፉ በፊት ምን ተፈጠረ? ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት በወልቂጤ ከተማ ጉብሬ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የዘቢዳር ቢራ ፋብሪካ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ በተጋባዥ ድምፃዊነት በተገኘበት ወቅት ማረፉን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል። የቅርብ የሥራ አጋሮቹ ለዳጉ ጆርናል እንደገለጹት፣ ሚኪያስ በዕለቱ ጠዋት ከሙዚቃ ሥራው በፊት ሕመም እየተሰማው እንደነበር ለአጋሮቹ ተናግሮ ነበር። ሆኖም የመድረክ ሥራውን ለመወጣት በማሰብ ሁለት ሙዚቃዎችን ለማቅረብ ወደ መድረክ ወጥቷል። በመድረክ ላይ ሙዚቃውን እያቀረበ ሳለ ራሱን ሊስት ሲቃረብ፣ በአጠገቡ የነበረ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች ደግፎ ይዞታል። ከዚያም ከመድረክ እንዲወርድ ተደርጎ ወደ አቅራቢያው የጤና ማዕከል ተወስዷል። አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ለመስጠት ጥረት ቢደረግም ሕይወቱን ማዳን አልተቻለም። ዳጉ ጆርናል እንደገለጸው፣ የዕረፍቱን መረጃ ቤተሰቦቹ እስኪያውቁ ድረስ ይፋ ሳያደርግ ቆይቷል። ለድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና አድናቂዎች መጽናናትን እንመኛለን። ምንጭ፦ ዳጉ ጆርናል
Открыть в TelegramПосты канала ጣና ሚዲያ Tana Media
"እኔም ለወገኔ" We Stand for Humanity! Join the Global Fundraising Telethon Organized by the Coalition of Amhara Associations in America (CAAA). 🗓 Dates: November 28–29, 2026 ⏰ Time: 10:00 AM EST (Live Online & On TV) Amhara Guard invites all its followers, collaborators and partners to participate in the fundraising event that is organized by the Coalition of Amhara Associations in America (CAAA). Amhara Guard is a member of CAAA and endorses the effort CAAA is undertaking to alleviate the suffering Amhara people are facing due to war and genocide.
Открыть в Telegramየፈረንሳይ አቢዮት ከተነሳ አይቀር... 1787 ላይ የነበረው የፈረንሳይ አቢዮትን በተመለከተ ኦሾ አንዲት መፅሐፉ ላይ ያሰፈራት ተረክ አለችው። በርግጥ የታሪክ መዛግብት ከፃፉት በእጅጉ ይለያል... "ንጉስ በቃን፤ አሁንስ በዛ! " በሚል የተነሳው አብዮት ተቀጣጥሎ አቢዮተኞቹን ከአደባባይ "ባስቲል" ወደ ተባለ እስር ቤት አደረሳቸው። ባስቲል ሰዎች ገብተው የማይወጡበት እና በየእስረኞች እጅና እግር ላይ ሰንሰለት የሚቆለፍበት እስር ቤት ነው። እዚህ እስር ቤት የገባ ሰው የሚወጣው ሬሳ ሆኖ ብቻ ነው... እናማ እስረኞች ሰንሰለትና ጨለማን አለማቸው አድርገው ሞታቸውን ይጠባበቃሉ። የፈረንሳይ አብዮተኞች ታዲያ የአደባባዩን ሲጨርሱ እስረኞቹን ሊያስለቅቁ እስር ቤቱን ሰብረው ገቡ፤ እስረኞቹንም ከነሰንሰለታቸው ሲንከሻከሹ አገኟቸው። በስኬታቸው እየተፍነከነኩ "በሉ ውጡ፤ ነፃነታችሁን አግኝታችኃል" አሏቸው:: እስረኞቹ መጀመሪያ ደነገጡ፤ ከዚያ ማልቀስ ጀመሩ። አብዮተኞቹ ግራ ገባቸው... "ለቅሶው የደስታ ነው? " እስረኞቹ ከእንባቸው ጋር ተንበርክከው ይለምኑ ጀመር:: "ውይ ሰንሰለቱን እንድንፈታላቸው ይሆናል" አሉና ቁልፍም ሳያስፈልጋቸው ሰንሰለቱን በመጥረቢያ ቆረጡላቸው... የእስረኞቹ ለቅሶና ጩኸት ግን ባሰ... "እኛ መውጣት አንፈልግም... የእኛ አለም ይሄ ነው ፤ እግራችን መራመድ የሚችለው በሰንሰለቱ ልክ ነው፤ አይናችን የሚያውቀው ጨለማን ነው፤ በብርሀን አይናችንን ልታጠፉት ነው እንዴ?" አሉ። አብዮተኞቹ ትዕግስታቸው ተሟጠጠ... ሲጀምር በአንድ ጊዜ ትዕግስተኛ እና አብዮተኛ የሆነ ሰው በአለም ላይ የለም። ትዕግስቱን ጨርሶ ነዋ አብዮተኛ የሚሆነው.... "አይ በጣም ተሞላቀቃችሁ..." አሏቸውና እየጎተቱ ማስወጣት ጀመሩ። አስበኸዋል ሰው ከእስር ቤት ተጎትቶ ሲወጣ? ብቻ በትነዋቸው እስር ቤቱን ቆልፈው ሄዱ። በማግስቱ... እስረኞቹ ከየሄዱበት ተመልሰው እስር ቤቱ ጋ ተኮልኩለው ተገኙ። አብዮተኞቹ "እንዴ ጤነኞች አይደላችሁም እንዴ?" "እናንተ ከዚህ እስክታስወጡን ጤነኛ ነበርን፤ ስንወጣ ነው ያመመን" "ቆይ ምን ሆንን ነው የምትሉት?" "ምንም! መልሳችሁ አስገቡን፤ ሰንሰለቱንም መልሱልን... እኛ የሰንሰለቱ ክብደት ሳይጫነን እንቅልፍም አይወስደን..." አብዮተኞቹ አንገታቸውን ነቅንቀው እያዘኑ ወደ እስር ቤታቸው መለሷቸው። ያው አንዴ በሆነ ነገር አትታሰር ለማለት ነው ታሪኩን የነገርኩህ... ገመድህን ከለመድከው፣ እግርና እጅህን ለሰንሰለቱ እያስማማህ ከኖርክ፣ ሰንሰለቱን አምባር ማጌጫ ነው የምታደርገው... ሰንሰለትህን ቢያወልቁልህ ጌጥህን እንደተነጠቅህ መጮህህ ተጠባቂ ነው... ጌታዬ የአሜሪካ የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት አብርሃም ሊንከንን ለአሳዳሪዎቻቸው ተደርበው የወጉ ጥቁሮች አሉ አሉ እኮ... 'ከአሳዳሪዎቻችን አስወጥቶ ምናባቱ ሊያደርገን ነው?' ብለው ማለት ነው በእርግጥ ይሄንንም የተሰነዱ የታሪክ መጻሕፍት ላይ አታገኘውም... በአፍ የሚነዳ ታሪክ ላይ እንጂ... ብቻ ዋናው ነገር ነፃነት ተሰፍሮም ተዘግኖም ቢሰጥህ ዋጋ የለውም:: መጀመሪያ የምትወስድበትን ከረጢት ሰፍተህ ካላዘጋጀህ ልልህ ነው። #everyonefollowers #viralpost ©️Etsegenet Kebede
Открыть в Telegramየሰው ክብደት የሚመዘነው ለእኛ በሆነልን መሆን አይደለም... ለሌላውም በሚያሳየው ልኩ እንጂ... መንግሥትም እንደዛው... ድህነቴን ታሪክ አደረገልኝ ተብሎ "ድህነትን ታሪክ አድራጊ መንግስት" አይባልም፤ አንድ ሰው ምሳ ጋበዘኝ ተብሎ " ውይ...እሱ እኮ ደግ ነው፤ ከበር መልስ እኮ ነው የሚጋብዘው..." እንደማይባለው... ማለቴ ነው:: በጥቅማችሁ ሚዛናችሁን ባትቀያይሩ...🤨 ይቅርታ ተመላለስኩባችሁ🙄😁 ©️Etsegenet Kebede
Открыть в Telegram🕊 🌺 🕊 💛 [ በመስቀሉ ገነትን ከፈተ ! ] 💛 🕊 🌺 🕊 ❝ ተስፋ ላጡ ተስፋ የሆነው መስቀል ለዓለም ሁሉ ሕይወትን አስገኘ ፣ ለምናምን ለኛ ደስታችን ነው ፣ ለነገሥታት ታላቅነታቸው ግርማቸው ነው ፣ የቤተ ክርስቲያን መሠረት የባሕር መረጋጋት ለመርከቦች ወደብ ነው መስቀል። በመስቀሉ ገነትን ከፈተ ፣ በመስቀሉ መድኃኒትን አደረገ ፣ [ በመስቀሉ ] አጋንንትን አባረረ ፣ ከመስቀሉ ወርዶ ቤዛ ሆነን ፣ ለዕረፍትም ሰንበትን መሠረተ። ❞ [ ድጓ ዘዮሐንስ ] 🕊 🕊 ❝ በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው። እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል።❞ [ ቆላስ.፪፥፲፬ ] ❝ በመስቀሉም ደም ሰላምን አደረገ ፤ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ አስታረቀ ❞ [ ቆላ.፩፥፳ ] እንጎሮጎባሽ!!! እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ!!! 🌸 🌸 ††† ✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟ 🕊 💖
Открыть в Telegram"ወትባርክ አክሊል ዓመተ ምሕረትከ ፥ በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ መዝ. ፷፬፥፲፩ እንኳን ከዘመነ ቅዱስ ማርቆስ ወደ ዘመነ ቅዱስ ሉቃስ፣በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን። 🙏 እንቁጣጣሽ 🌻🌼🌻 #ምርቃት በሰለሞን አያሌው እነሆ፦ -ዓመቱ ግጥማችን ይሁን፤ -ሆሳው ይነሳ፤ -እማይበጀን ገለል ይበል፤ -ለከርሞው በአማን ያድረሰን፤ -ለአገርና ለህዝብ ደግደጉን ያምጣልን፤ -እንደበሬ ሻኛ ከሰው በላይ ያውላችሁ፤ -የእድሜ ጎዳና ይስጥልን፤ -አገሩ ጥጋብ ቀየው ሰላም፤ -አበባውን ፍሬአማ ያድርግልን፤ አሜን!!! መልካም ዘመን መልካም አዲስ ዓመት። ይኩን💚💛❤ይኩን!!!
Открыть в Telegramሰላም እንዴት ናችሁ!! 👉#ለደብረታቦር ፬ቱ ጉባኤያት ቤተመጽሐፍት መጻሕፍትን እያሰባሰብን ስለሆነ ማንኛውም ሳይንሳዊ፣ፍልስፍናዊና ሃይማኖታዊ መጽሐፍት ድጋፍ ማድረግ ከፈለጋችሁ እንድታመጡልን ስል ጥሪየን አቀርባለሁ። 0927688782 -ደውሉልኝ ወይም በውስጥ ጻፉልኝ!!! 👏👏👏 💚💛❤
Открыть в Telegram✍️✍️✍️ ቸር ናችሁ ተወዳጆች በገናውያን!!! ❤❤❤ #እንኳን ለጾመ ፍልሰታ አደረሳችሁ። #ይቺን የፍልሰታን ጾም አስመልክቶ የቤተክርስቲያናችን አገልግሎት በሌሊትም በቀንም የጎላ እንደሆነ ይታወቃል። #ስለዛም በተለይ ወደ ገጠር አካባቢ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ብዙ ነገር ያስፈልጋቸዋል። 👉ለምሳሌ፦ -ሻማ -ጧፍ -እጣን -ዘቢብ .......እንዲሁም ሌሎች ንዋያተ ቅድሳት የምትችሉ ገዝታችሁ ብትልኩ በረከት ታገኛላችሁ። 👉የሚያስፈልጋቸው አብያተ ክርስቲያናት ለመጠቆም ያክል፦ -ጎንባት ቅዱስ ጊዮርጊስ -ሮቢት በዓታ -ዘንዘልማ ቅዱስ ጊዮርጊስ -ይባብ ቅዱስ ያሬድ -ዘጌመስመር አርባዕቱ እንስሳ ኪሩቤል -ይነሳ ኢየሱስ -ማይሐጹራ አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ ......እንዲሁም ሌሎች ብዙ አሉ። ለሌሎችም አድርሱት የሚችሉ ሁሉ ይላኩ፤ ይሳተፉ፤ ያድርሱ። 👏👏👏 ቸር ጊዜ!!! ❤❤❤
Открыть в Telegramየዘር ማጥፋት ወንጀል ሲጋለጥ የቤተ መንግሥቱ የውሸት መግለጫ ፣የሰላም ሚንስትሩ የውሸት መግለጫ፣የኢሰመኮ የውሸት መግለጫ ፣የመንግሥት ሚዲያ የውሸት ዘገባ፣የኦሮሚያ ኮሚንኬሽን የውሸት መግለጫ፣የአርሲ ዞን ኮሚንኬሽን ቢሮ የውሸት ፕሮፓጋንዳ፣የአሰኮ ወረዳ የውሸት ፕሮፓጋንዳ ፣የአክራሪ ወሀቢያዎች የውሸት ፕሮፓጋንዳ የሐሰተኛ ሽማግሎችና አባገዳዎች ንግግር፣የአርሲ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የቄስ ከፍያለሁ የቅጥፈት ንግግር አፍኖ ሊያስቀረው ያልቻለው በአርሲ አሰኮ ኦርቶዶክሳውያን ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥፋት።እኛ እውነት የሆነውን እግዚአብሔር ነው የምናመልከው በሐሰት አንመራም። ማን ጽንፈኛና ማን ሀገር አፈርራሽ እንደሆነ ከተግባራችን ይታወቃል። via ትህትና...!!!
Открыть в Telegram(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ራሳቸው በራሳቸው ገጽ ላይ በለጠፉት ፎቶ በእጃቸው ያሰሩት ሰዓት የበርካቶችን ትኩረት ስቧል። በፎቶው ላይ በግልጽ እንደሚታየው... ፕሬዝዳንቱ ያደረጉት ሰዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ በውድነቱ እና በቅንጦቱ የሚታወቀው Rolex GMT-Master II "Root Beer" የተሰኘው ሞዴል ነው። የዚህ ሰዓት የገበያ ዋጋ እንደየሁኔታው ከ16,000 እስከ 24,000 የአሜሪካ ዶላር ያወጣል፤ ይህ ማለት አሁን ባለው የምንዛሬ ተመን ሲሰላ በሚሊዮኖች የሚቆጠር የኢትዮጵያ ብር ማለት ነው። ዘ ሀበሻ
Открыть в Telegram"...እንዲህ ያለ ትግል ነው የገጠመን...." አለ መንጌ!!! 🤔🤔🤔 ምድረ አሽቃባጭ ወራዳ ሁላ!!! አድር ባይነት በዚህ ልክ...ዱቄት ሁላ!!! በሰው እንባ..... አሁን ከእናንተ ጋርም ሌላው ደጋፊ...!!!
Открыть в Telegram"እኔም ያልተገደልኩት አርሲ ላይ ስላልተገኘሁ ነው።" በመላው ዓለም ያለን ኦርቶዶክሳውያን ይኽን ስሜት ተጋርተን በቤተ ክርስቲያንና በክርስቲያኖች ላይ ስለሚደርሰው አሠቃቂ ግድያና ግፍ ልናለቅስ ይገባል። በአርሲና አካባቢው ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ግን ራሳቸውን አደራጅተው ከንቱ ሞት ከመሞት ራሳቸውን መከላከል አለባቸው። 8 ዓመት ሙሉ እያለቀሱ እየነፈረቁ መሞት አይሰለችም? እስቲ ደግሞ የወንዶቹን ሞት ለመሞት ይሞክሩት። የወለጋዎችን ልምድ ይውሰዱ። ይኽን ለማድረግ በአርሲ አካባቢና አጎራባች ያሉ ኦርቶዶክሳውያን የጊዜው ተዋጊዎች እገዛ ያድርጉላቸው። ያሰልጥኗቸው። ያስታጥቋቸው። እውነተኛ የአማራ ተቆርቋሪ የኾነ ካለ ይኽንን ያስተባብር፤ ያስፈጽም፤ ያግዝ። ይኽ ካልኾነ ነገም እያለቀሱ መሞት እየነፈረቁ መሳደድ የማይቀር ነው። አራጁ አካል በመዋቅር የተሰገሰገ መመሪያ እየተቀበለ የሚያስፈጽም እስከኾነ ድረስ ተደራጅተህ በመጣበት መንገድ ካላስተናገድከው በቀር ሌላ መፍትሔ የለውም። ቤተ ክህነት ላሉት ለእነዚያ ጥቋቁር ቁራዎች ግን....... ሞት ለእነርሱም የማይቀር መኾኑን ስናስብ እንጽናናለን።
Открыть в Telegram