አውሮፓ 28% የሚሆነውን የአሞኒያ ማዳበሪያ ምርቷን አቋረጠች - መገናኛ ብዙኃን እየናረ የመጣው የኢነርጂ ዋጋ የአውሮፓ የማዳበሪያ ፋብሪካዎች እንዲዘጉ እያስገደደ መሆኑንና ወደ አምስት ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ የአውሮፓ ዓመታዊ የአሞኒያ የማምረት አቅም ቀድሞውኑ መቆሙን አንድ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል። ✅ መነሻው፦ የተፈጥሮ ጋዝ ከ80 እስከ 90% የሚሆነውን የአሞኒያ የማምረቻ ወጪ ይሸፍናል። በመካከለኛው ምሥራቅ ውጥረቶች እና በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ላይ በተፈጠረው የመርከብ ትራንስፖርት መስተጓጎል ምክንያት፤ የጋዝ የወደፊት መሸጫ ዋጋ በቅርቡ በ1,000 ኩብ ሜትር ከ1,200 ዶላር በላይ በማሻቀብ እ.ኤ.አ ከ2022 ወዲህ ከፍተኛው ደረጃ ላይ ደርሷል። ✅ ተጽዕኖው፦ የዘርፉ መሪዎች ይህ ሁኔታ አውሮፓን በዓለም አቀፍ አቅራቢዎች ላይ በእጅጉ ጥገኛ እንድትሆን በማድረግ፤ ቀጣናውን ለዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ቀውሶች ይበልጥ ተጋላጭ እንደሚያደርገው አስጠንቅቀዋል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramПосты канала ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
የፈጥኖ ደራሽ ኃይል የሎጂስቲክስ ኃላፊና በርካታ አዛዦች የሱዳን ጦርን ተቀላቀሉ 🇸🇩 ሜጀር ጄኔራል አማር መሐመድ ዘይን ራቢህ ከስምንት አዛዦችና በርካታ ተዋጊዎች ጋር በመሆን የሱዳን ጦርን እንደተቀላቀሉ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ቁልፍ ዝርዝሮች፦ ⚡️ ራቢህ በካርቱም አውሮፕላን ማረፊያ ባደረጉት ንግግር፤ ለሱዳን ጦር ተገዢ እንደሆኑ በይፋ ያረጋገጡ ሲሆን ለሉዓላዊው ምክር ቤት ሊቀመንበር አብዱል ፈታህ አል-ቡርሃን እና ለሱዳን ሕዝብ ይፋዊ ይቅርታ በመጠየቅ፤ ቀሪ የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ተዋጊዎች ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል። ⚡️ ውሳኔውን የወሰዱት በአል-ጀዚራ፣ በካርቱም፣ በዳርፉር እና በኤል-ፋሸር አካባቢዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ በተፈጸመው መጠነ ሰፊ በደል፣ ዝርፊያ እና ግድያ ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል። ⚡️ በተጨማሪም ራቢህ በኤል-ፋሸር አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በሚገኙ የጅምላ መቃብሮች ላይ ዓለም አቀፍ ምርመራ እንዲደረግ የጠየቁ ሲሆን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በኒያላ ከእስራኤል ባለሙያዎች የሳይበር ደህንነት እና የሥልጠና ድጋፍ ማግኘቱን ተናግረዋል። ይህ ዜና የቡድኑ አመራሮች በስፋት መኮብለል መጀመራቸው እየተሰማ ባለበት ወቅት የመጣ ነው። ባለፉት ጥቂት ወራት በርካታ ቁልፍ አዛዦች በመቶዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎችንና የውጊያ ተሽከርካሪዎችን ይዘው ብሔራዊ ጦሩን ተቀላቅለዋል። 📹 ከማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ ተንቀሳቃሽ ምሥል በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в Telegramየአየር ንብረት ለውጥ የወባ ወረርሽኝን በመከላከል ረገድ የተገኙ ውጤቶችን አደጋ ላይ ስለመጣሉ ባለሙያዎች ተናገሩ ባለሙያዎቹ ይህን የተናገሩት በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ካለው 5ኛው የአፍሪካ የህብረተሰብ ጤና ጉባኤ ጎን ለጎን ትኩረቱን በአየር ንብረት ለውጥ ላይ አድርጎ በተካሄደ የፓናል ውይይት ላይ ነው። 📌 በውይይቱ ከወባ ጋር በተያያዘ በመላው ዓለም ከተመዘገበው 610 ሺህ ሞት ውስጥ 95% ያህሉ በአፍሪካ መመዝገቡን ያነሱት የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ጽሕፈት ቤት ተወካይ ዶ/ር ኤልዛቤት ጁማ፤ ሁኔታው በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየተባባሰ መምጣቱን ተናግረዋል ሲል የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል፡፡ “ተጽዕኖው በቶሎ ካልተገታ ከ2030 እስከ 2045 ባለው ጊዜ ውስጥ ተጨማሪ 550 ሺህ ሞት ሊመዘገብ እንደሚችል” ተናግረዋል። 🔊 የውይይቱ ተሳታፊ ባለሙያዎች፤ ሀገራት የአየር ንብረት ጤና ጉዳይን የፖሊሲዎቻቸው አካል እንዲያደርጉና በመጪው የአየር ንብረት ጉባኤ ኮፕ 32 ላይ አጀንዳ ሆኖ እንዲቀርብ ጠይቀዋል። ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 377 |
| 1 ч | 581 |
- Через 1 час581
- Всего сейчас581
❗️አውሮፓ የሩሲያን ዘይትና ጋዝ አቅርቦት በመተዉ ራሷ ላይ ችግር እየጠራች ነው - ፑቲን የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ይህን ያሉት፤ የአውሮፓ ሀገራት የሩሲያን የኃይል አቅርቦት ለማቋረጥ መወሰናቸውን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ነው። ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 343 |
| 1 ч | 534 |
- Через 1 час534
- Всего сейчас534
❗️ኪየቭ በሩሲያ የነዳጅ ማጣሪያ ተቋማት ላይ ለፈጸመቻቸው ጥቃቶች ያለምንም ጥርጥር አጸፋዊ እርምጃ እንወስዳለን - ፑቲን በነዳጅ ውጤቶች ገበያ ዙሪያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አስቸጋሪ መሆኑንም የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገልጸዋል። ሆኖም የሩሲያ የሀገር ውስጥ የነዳጅ ገበያ ተረጋግቶ መቀጠሉን አክለዋል። ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 37 |
| 1 ч | 557 |
- Через 1 час557
- Всего сейчас557
❗️ኢትዮጵያ የሱዳን ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ሲቪል ኃይሎችን ለማደራደር ሃሳብ አቀረበች 🇪🇹🇸🇩 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በሱዳን ጉዳይ ዙሪያ በአረብኛ ቋንቋ ባወጡት መግለጫ፤ የሱዳን ጦርነት፣ ውድመትና ሰብዓዊ ቀውስ የጎረቤት ሀገር ፖለቲካ ወይም የደኅንነት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን "የኢትዮጵያን ሕዝብ ልብ የነካ ቁስል ነው" ብለዋል። አክለውም አራተኛ ዓመቱን ሊይዝ የተቃረበውን ጦርነት በዝምታ እየተመለከቱ መቆየት እንደማይገባ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው፤ ግጭቱን ለመግታት በሱዳናውያን መሪነት የሚካሄድ አካታች ውይይት እንዲጀመር ጥሪ አቅርበዋል። 👉 ይህ ተነሳሽነት የተደበቀ ፖለቲካዊ ዓላማ እንደሌለው በመጠቆም፤ ኢትዮጵያም ድርድሩን ለማስተናገድ እና ለማመቻቸት ዝግጁ እንደሆነች አስታውቀዋል። ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 174 |
| 1 ч | 588 |
- Через 1 час588
- Всего сейчас588
ኢኮዋስ እስከ 2027 መጨረሻ ድረስ ቀጣናዊ የፀረ-ሽብር ኃይል ሊያሠማራ ነው የቀጣናው የመከላከያ ኤታማዦር ሹሞች በዳካር ባካሄዱት 45ኛ መደበኛ ስብሰባ ማጠቃለያ፤ እስከ ታኅሣሥ 2027 ድረስ ቀጣናዊ የፀረ-ሽብር ኃይል ወደ ሥራ ለማስገባትና ለማሰማራት በሚያስችል ፍኖተ ካርታ ላይ መስማማታቸውን ኅብረቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ይህ ተነሳሽነት የሚከተሉትን ስጋቶች በጋራ የመመከት አቅምን ለማጠናከር ያለመ ነው፦ ▪️ ሽብርተኝነት፣ ▪️ የጽንፍ አመጽ፣ ▪️ የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች፣ ▪️ የባሕር የደህንነት ስጋት። 📍 45ኛው መደበኛ የኢኮዋስ የመከላከያ ኤታማዦር ሹሞች ኮሚቴ ስብሰባ ከኅዳር 8-10 በሴኔጋል ዋና ከተማ ተካሂዷል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 276 |
| 1 ч | 629 |
- Через 1 час629
- Всего сейчас629
አውሮፓ የናዚን የአስተዳደር ሥርዓት በመከተል ዩክሬንን ልትመስል ትችላለች — የዱጊን የዲጂታል ትንታኔ የአውሮፓ ሀገራት ሩሲያ ላይ ድል ለመቀዳጀት፤ ጦርነት ቢቀሰቀስ በዩክሬን የተጠቀሙባቸውን ዘዴዎች በመከተል፤ በፍጥነት ወደ ጥብቅና አምባገነናዊ የፖለቲካ ሥርዓት ሊሸጋገሩ እንደሚችሉ ይገልጻል። 🔊 በሩሲያ ተቋማት ላይ የሚፈጸሙ ተደጋጋሚ ጥቃቶች፤ የአውሮፓ ጥምረት ሰፊ ተሳትፎን እንደሚያመለክቱና የግጭቱ ቀጣና ከወዲሁ መስፋቱንም ትንታኔው ያመለክታል። ለዘብት ዓለም አቀፋዊነት ከጽንፈኛ የአስተዳደር ዘዴዎች ጋር ሲዋሃድ ምን ይፈጠራል? አውሮፓስ በእርግጥ ከሩሲያ ጋር ወደ መጠነ ሰፊ ግጭት ውስጥ ለመግባት እየተዘጋጀች ነው? የሩሲያዊው ፈላስፋ @Dugin_Aleksandr የሰው ሠራሽ ዲጂታል ሐተታ በዚህ ጉዳይ ላይ ትንታኔውን ያቀርባል። 👆 ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 242 |
| 2 ч | 676 |
- Через 1 час676
- Всего сейчас676
ስድስት የቶዮታ መኪና ሞዴሎች የደህንነት ማስጠንቀቂያ ተሰጠባቸው 🔥 ሞኤንኮ የመኪና ሞዴሎቹ ባለቤቶች ተሽከርካሪዎቻቸውን እንዲያስፈትሹ አሳስቧል፡፡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 92 |
| 1 ч | 636 |
- Через 1 час636
- Всего сейчас636
❗️ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (ካስ) የ2025ቱ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ሴኔጋል መሆኗን አረጋገጠ በጥር ወር በራባት የተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ በውዝግብ ለ17 ደቂቃ ከተቋረጠ በኋላ፤ ሴኔጋል አዘጋጇን ሞሮኮን በተጨማሪ ሰዓት በተቆጠረ ጎል 1 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን ማንሳቷ የሚታወስ ነው። ይሁንና ካፍ ውጤቱን በመሻር ሞሮኮን አሸናፊ አድርጎ መሰየሙን ተከትሎ፤ የሴኔጋል የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔውን በመቃወም ለካስ አቤቱታ አቅርቦ ነበር። ካስ ዛሬ ባሳለፈው ውሳኔ የሴኔጋልን የፍጻሜ ጨዋታ ድል አጽንቷል። ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 276 |
| 1 ч | 708 |
- Через 1 час708
- Всего сейчас708
የወሎ ኦፓል፦ በተፈጥሮ የማር ወለላ ቅርጽ የተለየ ውድ ማዕድን 🔮 በኢትዮጵያ ወሎ አካባቢ የሚገኘው ኦፓል፤ በአወቃቀሩ ልዩ ከሆኑ የከበሩ ድንጋዮች መካከል ይመደባል። ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 381 |
| 1 ч | 567 |
- Через 1 час567
- Всего сейчас567
የኢራን ፍርድ ቤቶች አሜሪካ ከ290 ቢሊዮን ዶላር በላይ ካሳ እንድትከፍል ወሰኑ 🇮🇷🇺🇸 የኢራን ፍርድ ቤቶች አሜሪካ ለአሥርት ዓመታት በኢራን ላይ ለፈጸመቻቸው የጠላት ድርጊቶችና ላደረሰችው ጉዳት ከ290 ቢሊዮን ዶላር በላይ ካሳ እንድትከፍል የሚያዙ የፍርድ ውሳኔዎችን ማስተላለፋቸውን ፕሬስ ቲቪ ዘግቧል። 💬 የኢራን የፍትሕ አካል የጠበቆች፣ የመደበኛ ባለሙያዎችና የቤተሰብ አማካሪዎች ማዕከል ኃላፊ ሀሰን አብዶሊያንፑር፤ "ዛሬ በአሜሪካ ላይ ከ290 ቢሊዮን ዶላር በላይ የፍርድ ውሳኔዎችን አስወስነናል፤ ከእነዚህም መካከል የተወሰኑት ቀድሞውኑ ተፈጻሚ ሆነዋል" ብለዋል። አብዶሊያንፑር አክለውም፤ በቅርቡ በተካሄዱት የአሜሪካና የእስራኤል ጦርነቶች ወቅት የደረሱ ጉዳቶችን ለመገመትና የተፈጸሙ ወንጀሎችን በሰነድ ለማደራጀት ወደ 19,000 የሚጠጉ ባለሙያዎች መሳተፋቸውን የገለጹ ሲሆን እ.ኤ.አ ከ2020ው የጄኔራል ቃሲም ሱሌይማኒ ግድያ ጀምሮ የአሜሪካ ባለሥልጣናት የሰጧቸው መግለጫዎችና መመሪያዎችም ለሕግ ሂደቱ ግብዓት እንዲሆኑ መሰባሰባቸውን ተናግረዋል። በሕጋዊ ማዕቀፉ መሠረት የተወሰኑ መርከቦችን መያዝ ጨምሮ ተጨማሪ የፍርድ ማስፈጸሚያ እርምጃዎች ሊከተሉ እንደሚችሉም አክለዋል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 264 |
| 1 ч | 765 |
| 3 ч | 1 080 |
- Через 1 час765
- Всего сейчас1 080
የፓን-አፍሪካኒዝም አቀንቃኙ የጥቁር ሕዝቦች ነጻነት ምልክት በሆነችው ኢትዮጵያ ጉብኝት አካሄደ ብሪቲሽ-ጋናዊው ድምፃዊ ፊውዝ ኦዲጂ በኢትዮጵያ ቆይታው ዩኒቲ ፓርክንም ጎብኝቷል፡፡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 1 |
| 1 ч | 705 |
| 4 ч | 1 030 |
- Через 1 час705
- Всего сейчас1 030
ለአዲስ አበባ የውሃ እጥረት ኢኮኖሚያዊና የፋይናንስ አቅም ውስንነት ማነቆ እንደሆኑ ተገለጸ 🚰 የመዲናዋን የውሃ እጥረት በዘላቂነት ለመፍታት 2.2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን አስታውቋል። 📊 ተጨማሪ ዝርዝሮችን ከስፑትኒክ ኢትዮጵያ ምሥላዊ መግለጫ ያግኙ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 207 |
| 1 ч | 758 |
| 3 ч | 1 050 |
- Через 1 час758
- Всего сейчас1 050
"የተዘጋን በር ለመክፈት መሞከር ተገቢ ነው” - ጁሊየስ ኒየሬሬ ስፑትኒክ አፍሪካ የመጀመሪያው የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ጁሊየስ ካምባራጌ ኒየሬሬ ስለዕድገት የሰጡትን አስተያየት ያቀርባል። ኒየሬሬ አፍሪካውያን የተሻለ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለመገንባት ቆራጥ መሆን እንዳለባቸው ባሳሰቡበት ንግግራቸው፤ ለውጥ ለማምጣት በዜጎቻቸው ላይ ጉዳት ማድረስ እንደሌለባቸውም አስጠንቅቀዋል። በሰው ሠራሽ አስተውህሎት ዳግም ሕያው የተደረጉትን የአኅጉሪቱን ታላላቅ ሰዎች ይተዋወቁ። ቃላቸው፣ ድምፃቸውና መልዕክታቸው! 🔸 ያዳምጡ፣ ይነሳሱ፣ ያጋሩ! #የአፍሪካታላላቅሰዎች ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 394 |
| 1 ч | 627 |
| 3 ч | 1 030 |
- Через 1 час627
- Всего сейчас1 030
በበጎ ፈቃደኛ ለጋሾች 99.8 በመቶ የሚሆነው የደም አቅርቦት እየሸፈኑ መሆኑ ተገለፀ 🩸 የኢትዮጵያ ደምና ሕብረ ሕዋስ ባንክ አገልግሎት በሀገሪቱ የበጎ ፈቃደኝነት የደም ልገሳ ባሕል እየተጎለበተ መጥቷል ማለቱን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል። ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 4 |
| 1 ч | 654 |
| 3 ч | 1 010 |
- Через 1 час654
- Всего сейчас1 010
ሩሲያ በወታደራዊ ቴክኖሎጂና በሰው ኃይል ሥልጠና ለኢትዮጵያ ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገች ነው - የኢትዮጵያ አየር ኃይል 🛰 የኢትዮጵያ የአየር መከላከያ ቴክኖሎጂዎችና የአቪዬሽን መሣሪያዎች በአብዛኛው የሩሲያ ቴክኖሎጂ ምርቶች መሆናቸውን የኢትዮጵያ አየር ኃይል የኤሌክትሮኒክ ጦርነት ዲቪዥን ኃላፊ ኮሎኔል ሽፈራው ኢብሳ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። 💬 “በዚህ ዘርፍ በቴክኖሎጂዎቹ ላይ የሰው ኃይልን በማሠልጠን፣ በማብቃት ጥሩ ትብብር የሚደረግበት እና የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ጥሩ ደረጃ የደረሰበት ሁኔታ ነው ያለው” ሲሉም አክለዋል። ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 329 |
| 2 ч | 723 |
| 3 ч | 966 |
- Через 1 час723
- Всего сейчас966
የሩሲያ ቲ-80ቢቪ ታንኮች በዛፖሮዥዬ የጠላት ሰርጎ ገብ ጥቃቶችን አከሸፉ የሩሲያ ቮስቶክ የጦር ቡድን የታንክ ክፍል የጠላትን ግስጋሴ በስኬት ማስቆማቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የዘመቻውን ተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ በማድረግ አስታውቋል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 1 |
| 1 ч | 666 |
| 4 ч | 978 |
- Через 1 час666
- Всего сейчас978
ፑቲን ከሺ እና ትራምፕ ጋር ባደረጉት ውይይት የተገኙ ውጤቶችን ለፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላት አብራሩ - ክሬምሊን በዲሚትሪ ፔስኮቭ የተሰጡ ሌሎች መግለጫዎች፦ ➖ ፑቲን በሼንዘን በተካሄደው ስብሰባ ላይ ለትራምፕም ሆነ ለሺ ጂንፒንግ ምንም ዓይነት ሰነድ አልሰጡም። ➖ በሩሲያ፣ በአሜሪካ እና በዩክሬን መካከል ለሚካሄደው ቀጣይ ዙር የሦስትዮሽ ድርድር ገና ቀን አልቶቆረጠም። ➖ አውሮፓውያን በዩክሬን የሰላም ሂደት ውስጥ ምን ዓይነት አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ እንደሚችሉ ሩሲያ እስካሁን ግንዛቤው የላትም። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 229 |
| 1 ч | 710 |
| 3 ч | 927 |
- Через 1 час710
- Всего сейчас927
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ከ11 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ህጻናት የፖሊዮ ክትባት እንደሚሰጥ ገለጸ 📍ዘመቻው በኦሮሚያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች የፖሊዮ ቫይረስ መገኘቱን ተከትሎ የመጣ እንደሆነ የሀገር ውስጥ የዲጂታል ሚዲያ ዘግቧል፡፡ 💉 የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻው፤ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ 11.3 ሚሊዮን ህጻናት ይሰጣል። ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 1 ч | 387 |
| 1 ч | 621 |
| 3 ч | 1 030 |
- Через 1 час621
- Всего сейчас1 030
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የዋጋ ጭማሪ እና የክብደት ማጉደል ጥሰት በፈጸሙ 61 ዳቦ አምራቾች ላይ እርምጃ ወሰደ 🥖 ቢሮው በመዲናዋ በሚገኙ 188 ዳቦ ቤቶች ላይ ባደረገው ድንገተኛ ምልከታና ክትትል፤ የንግድ ሕጉን ተላልፈው በተገኙ 61 የዳቦ አምራቾች ላይ የመጀመሪያ ደረጃ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል። እርምጃ የተወሰደባቸው አምራቾች 70 ግራም ዳቦ ከ13 ብር በላይ ሲሸጡ፣ ከ70 ግራም በታች የሆነ ዳቦ ለገበያ ሲያቀርቡ እና የዋጋ ዝርዝር ሳይለጥፉ ሲሠሩ ተገኝተዋል። 👉 ሸማቹ ማኅበረሰብ መሰል ሕገ-ወጥ የግብይት ተግባራት ሲያጋጥሙት ጥቆማ እንዲሰጥ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል። በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 182 |
| 1 ч | 709 |
| 3 ч | 970 |
- Через 1 час709
- Всего сейчас970
#viral | የአፍሪካ መዲና ያሸበረቀ ገፅታ ከአዲስ አበባ አዳዲስ ገፅታዎች አንዱ የሆነው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አካባቢ በድሮን ምሥል ሲቃኝ ልዩ መልክ ተጎናጽፏል። ከማኅበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘ ተንቀሳቃሽ ምሥል ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 155 |
| 1 ч | 717 |
| 3 ч | 994 |
- Через 1 час717
- Всего сейчас994
ከፍተኛ የዕዳ ጫና የአፍሪካን የወረርሽኝ ዝግጁነት እያዳከመ መሆኑን የኤይድስ ኬር ፋውንዴሽን አስጠነቀቀ 🌍🏥 እየጨመረ የመጣው የውጭ ዕዳ ጫና የአፍሪካ ሀገራት ለጤና አገልግሎትና ለወረርሽኝ ዝግጁነት ሊያውሉ የሚገባቸውን ውስን ሀብት ለዕዳ ክፍያ እንዲመድቡ እያስገደዳቸው ነው ሲሉ የፋውንዴሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፔኒናህ ኢቱንግ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ከሚገኘው 5ኛው የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ ጎን ለጎን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። “ሀገራት የውጭ ዕዳቸውን ከመክፈልና የሕዝባቸውን ጤና ከመጠበቅ አንዱን እንዲመርጡ መገደድ የለባቸውም፤ የዕዳ እፎይታና መልሶ ማዋቀር እንዲሁም የሀገር ውስጥ የሀብት ማሰባሰብ አቅምን ማጠናከር ያስፈልጋል” ማለታቸውን ጠቅሶ የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል። በተጨማሪም አፍሪካ በዓለም አቀፍ የጤና ድርድሮች ያላትን የጋራ ድምፅ ማጠናከርና ለክትባቶች፣ ለመድኃኒቶችና ለሌሎች ወሳኝ የጤና ቴክኖሎጂዎች ፍትሐዊ ተደራሽነት መታገል እንዳለባትም ገልጸዋል። 🗣 ተቋማቸው ከጉባኤው ጎን ለጎን የውጭ ዕዳ በሕዝብ ጤና ፋይናንስ ላይ ያለውን ተጽዕኖና አፍሪካ የዓለም አቀፍ የጤና ሥርዓትን በመቅረጽ ረገድ ያላትን ተጽዕኖ ለማጠናከር ያለሙ ሁለት ውይይቶችን ስለማዘጋጀቱም ተናግረዋል።
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 19 |
| 1 ч | 714 |
| 3 ч | 1 020 |
- Через 1 час714
- Всего сейчас1 020
የዩክሬን ወታደራዊ ሎጂስቲክስ በሩሲያ ጥቃት በእጅጉ ተገቷል - ባለሙያ በኪየቭ ድልድዮች ላይ እየተካሄዱ ያሉት ተከታታይ የሩሲያ ጥቃቶች፤ የዩክሬን ወታደራዊ የአቅርቦት መስመሮችን በከፍተኛ ሁኔታ እንደገቱ ሩሲያዊው የወታደራዊ ጉዳዮች ባለሙያ የቭጌኒ ሚካይሎቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል። ባለሙያው ያነሷቸው ሌሎች ዋና ዋና ነጥቦች፦ ◻️ ተገማች መስመሮች፦ የትራፊክ ፍሰቱን ወደ ቀሩት ድልድዮች ማዘዋወር መጨናነቅና መዘግየት ከመፍጠር ባለፈ፤ የአቅርቦት መስመሮችን ይበልጥ ለጥቃት ተጋላጭ ያደርጋቸዋል። ◻️ የደቡባዊ ድልድይ መመታት፦ በዚህ ወሳኝ የመኪና እና የባቡር መሻገሪያ ላይ የደረሰው ጉዳት፤ የድኔፐር ወንዝ መሻገሪያ ላይ ስጋት ደቅኗል። ◻️ የወንዙ የግራ ዳርቻ ለአደጋ ተጋልጧል፦ ያለ ባቡር ትስስር በግራ ዳርቻ የሚገኙ የዩክሬን ኃይሎች ከባድ የጦር መሣሪያዎችና ነዳጅ ለማጓጓዝ በመንገድ ትራንስፖርት ላይ ለመወሰን ይገደዳሉ፤ ይህ ደግሞ አዝጋሚ፣ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ እና ለከፋ ጥቃት ተጋላጭ ነው። ይህንን የባቡር አቅም ማጣት ከጊዜያዊ መጓተት ባለፈ፤ የሎጂስቲክስ ሰንሰለቱ ሙሉ በሙሉ እንዲበጠስ ሊያደርግ ይችላል ሲሉ ሚካይሎቭ አጠቃለዋል። 📹በኪየቭ ለዩክሬን ጦር የሎጂስቲክስ አገልግሎት የሚሰጥ ድልድይ ሲመታ የሚያሳይ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ተንቀሳቃሽ ምሥል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 200 |
| 1 ч | 699 |
| 3 ч | 971 |
- Через 1 час699
- Всего сейчас971
የኢትዮጵያ አየር ኃይል የምሥረታ በዓል “በድል እና በመስዋዕትነት የደመቀ የኢትዮጵያ ሰማይ አለኝታ” በሚል መሪ ሃሳብ ይከበራል - ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ 🇪🇹✈️ በዓሉ ህዳር 20 ቀን 2019 ዓ.ም ዓለም አቀፍ አትሌቶች በሚሳተፉበት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በቢሾፍቱ እንደሚከበር፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ 91ኛውን የኢትዮጵያ አየር ኃይል የምሥረታ በዓል አስመልክቶ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል። በተጨማሪም ሰኞ ህዳር 21 ቀን 2019 ዓ.ም በዋና መምሪያው ቅጥር ግቢ ውስጥ የተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚኖሩ ዋና አዛዡ ተናግረዋል። 👉 ሁሉም ኢትዮጵያውያን በቢሾፍቱ ከተማ በሚካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ እና በሌሎች ዝግጅቶች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል። ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 85 |
| 1 ч | 712 |
| 3 ч | 1 010 |
- Через 1 час712
- Всего сейчас1 010
በመቐለ ከተማ ነዳጅ አቅርቦት ችግር ለማቃለል ነዳጅ ማደል ተጀመረ በትግራይ ክልል ዋና ከተማ ከዛሬ ኅዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ስርጭት በይፋ ተጀምሯል። ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 283 |
| 2 ч | 773 |
| 3 ч | 1 010 |
- Через 1 час773
- Всего сейчас1 010
የአውሮፓ ኅብረት እና የሩዋንዳ የስደተኞች ስምምነት በምሥራቃዊ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሚንቀሳቀሱ አማጽያንን በገንዘብ የመደገፍ ስጋት አለው - የኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር "ያለመረጋጋት፣ የግጭት እንዲሁም የመፈናቀል እና የግዳጅ ስደት እምብርት የሆነች ሀገር፤ መጠለያ እና […] ዓለም አቀፍ ሕግን የምታከብር ታማኝ አጋር ተደርጋ መታየቷ ግራ የሚያጋባ ነው" ሲሉ ቴሬዝ ካይክዋምባ ዋግነር ለአንድ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ዋና ዋና ስጋቶችንም እንደሚከተለው ዘርዝረዋል፦ ▪️ግጭትን በገንዘብ መደገፍ፦ የአውሮፓ ኅብረት የሚሰጠው ገንዘብ በአሜሪካ ማዕቀቦች ምክንያት የተፈተነውን የሩዋንዳን የውጭ ምንዛሪ እጥረት በመሸፈን፤ አማጽያንን ለመደገፍ ሊውል ይችላል የሚል ስጋት በኪንሻሳ በኩል አለ። ▪️ስትራቴጂካዊ ማዘናጊያ፦ ስምምነቱ ኪጋሊ የታላላቅ ሐይቆች ቀጣናን በማተራመስ ረገድ ያላትን ሚና የመሸፈን አደጋ አለው። ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፤ ሩዋንዳ በምሥራቃዊ ኮንጎ የሚንቀሳቀሱትን የኤም23 አማጽያንን ትደግፋለች ስትል በተደጋጋሚ የምትከስ ቢሆንም፤ ኪጋሊ ግን ክሱን ታስተባብላለች። 🔙 ኦስትሪያ፣ ጀርመን፣ ግሪክ፣ ዴንማርክ እና ኔዘርላንድስ ከሩዋንዳ ጋር በመሆን፤ ከአውሮፓ ኅብረት ውጭ የስደተኞች መመለሻ ማዕከል ማቋቋም የሚችሉበትን መንገድ እያጤኑ እንደሆነ ቀደም ሲል ተዘግቧል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 358 |
| 1 ч | 647 |
| 4 ч | 1 130 |
| 6 ч | 1 370 |
- Через 1 час647
- Через 6 часов1 370
- Всего сейчас1 370
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና ለኮፕ 32 ዝግጅት ያላትን ጽኑ ድጋፍ በድጋሚ አረጋገጠች 🇦🇪🇪🇹 ይህ የተገለፀው የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታዎች ሁለተኛውን ዙር የጋራ የፖለቲካ ምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ባካሄዱበት ወቅት ነው። የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ ሼክ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን ምን አሉ? 🟠 ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና ከዚያም ባሻገር ለምትጫወተው ስትራቴጂካዊ ሚና ዕውቅና ሰጥተዋል፣ 🟠 ሀገራቸው ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ አንድነት እና የግዛት ሙሉዕነት ያላትን ሙሉ ድጋፍ አረጋግጠዋል፣ 🟠 ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው የኮፕ 32 ጉባኤ ስኬት ሀገራቸው ድጋፏን እንደምትቀጥል አስታውቀዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ያነሷቸው ነጥቦች፦ 🔶 የኤምሬቶች ባለሀብቶች በቴሌኮም፣ በባንክ፣ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በማዕድን፣ በኢነርጂ፣ በሎጂስቲክስ፣ በቱሪዝም እና በአይሲቲ ዘርፎች ኢንቨስትመንታቸውን እንዲያሰፉ ጥሪ አቅርበዋል። 🔶 ለኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ምርቶች የገበያ ዕድል እንዲሰፋ ጠይቀዋል። 🔶 የጋራ የፖለቲካ ምክክሮችን ማጠናከር፣ በየጊዜው ከፍተኛ ደረጃ የልዑካን ልውውጦችን ማካሄድ እንዲሁም አሁን ያሉትን የሁለትዮሽ ስምምነቶች መገምገምና በተግባር ላይ ማዋል እንደሚያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተዋል። ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 212 |
| 1 ч | 700 |
| 3 ч | 1 040 |
| 6 ч | 1 290 |
- Через 1 час700
- Через 6 часов1 290
- Всего сейчас1 290
ወደ 1,000 የሚጠጉ የፈረንሳይ ወታደራዊ ባለሙያዎች በዩክሬን ይገኛሉ - ሩሲያዊ ባለሙያ "እነዚህም የግል ወታደራዊ ኩባንያዎች አባላት እንዲሁም የጦር መሣሪያ አቅርቦት፣ ሥልጠና እና ስትራቴጂካዊ ወታደራዊ ጉዳዮችን የሚመሩ የፈረንሳይ ጄኔራሎችን ያካትታሉ" ሲሉ የሩሲያ የሮኬትና መድፈኛ ሳይንስ አካዳሚ አማካሪ ኦሌግ ኢቫኒኮቭ ለአንድ የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። ቅጥረኛ ፈረንሳውያን ወታደሮች ላለፉት በርካታ ዓመታት በሩሲያ ጥቃቶች ሲገደሉ መቆየታቸውንም ገልጸዋል። 🗣 ፈረንሳውያንን ጨምሮ የውጭ አሠልጣኞች የሚሠሩባቸው የዩክሬን ወታደራዊ ማሠልጠኛ ማዕከላት የሩሲያ ጦር ቀዳሚ ዒላማዎች እንደሆኑ የሩሲያ ጀግና ሜጀር ጄኔራል ሰርጌይ ሊፖቮይ ቀደም ሲል መግለጻቸው ይታወሳል። ኅዳር 8 ቀን ፓሪስ ወታደራዊ ባለሙያዎቿ በዩክሬን ምድር እንደሚገኙ ማረጋገጧ ይታወቃል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 126 |
| 1 ч | 683 |
| 3 ч | 1 050 |
| 6 ч | 1 270 |
- Через 1 час683
- Через 6 часов1 270
- Всего сейчас1 270
የናይጄሪያ ጦር 18 ሕፃናትን ከአሸባሪዎች እገታ ነፃ አወጣ 🇳🇬 የቦይስ ኤንድ ገርልስ ብሪጌድ አባላት የሆኑት ሕፃናት፤ እሁድ ማለዳ በካቺያ/ካጁሩ አካባቢ በሚገኘው የማዘር-ካት ማኅበረሰብ ውስጥ የጠዋት የቡድን የእግር ጉዞ በሚያደርጉበት ወቅት መታገታቸውን የጦሩ ቃል አቀባይ ኮሎኔል አፖሎኒያ አኔሌ መናገራቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ዋና ዋና ዝርዝሮች፦ ⚡️ ዘመቻው የተካሄደው 'ፋንሳን ያማ' (የምዕራብ ነፃነት) በተሰኘው የጦር ዘመቻ አካል በሆኑ የ1ኛ ክፍለ ጦር ወታደሮች ነው። ⚡️ ወታደሮቹ አጋቾቹን በቁጥቋጦዎች ውስጥ በማሳደድ ወደ ሬሂና የወንዝ ዳርቻ ያመሩ ሲሆን በዚያም የተወሰኑ ታጋቾች ተጥለው ተገኝተዋል። ⚡️ የቀጠለው ወታደራዊ ጫና አጋቾቹ ቀሪዎቹን አራት ሕፃናት ይዘው ወደ ጥቅጥቅ ደን እንዲሸሹ አስገድዷቸዋል። ⚡️ የናይጄሪያ ጦር የጠፉትን ታዳጊዎች ለማግኘት በአንክዋ–ካቦዴ–ፓቺ አገናኝ መንገድ እና ወደ አዎን እና አክዎንዶ አካባቢዎች አሰሳውን አስፍቷል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Открыть в TelegramДинамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 1 ч | 406 |
| 1 ч | 660 |
| 4 ч | 1 090 |
| 7 ч | 1 290 |
- Через 1 час660
- Через 6 часов1 290
- Всего сейчас1 290