AI-чатbetaКабинет

Посты канала ከፍልስፍና ዓለም™

сначала новые

#4216Аудио
Просмотры937−65%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч645
4 ч903
8 ч937
  1. Через 1 час645
  2. Через 6 часов937
  3. Всего сейчас937
#4215Фото
Просмотры963−64%к среднему
Пересылки—
Реакции13
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
1 ч670
4 ч927
8 ч963
  1. Через 1 час670
  2. Через 6 часов963
  3. Всего сейчас963
#4214Текст

Переслано из THE HUMANIST ROAD™

አብዛኛዉን ጊዜ ከእምነት ጋር በተያያዘ ከምጠየቃቸዉ ጥያቄዎች አንዱ ስለ ሞት ስታስብ ምን ይሰማሃል ፣ዘላለም አትኖርም፣ ሟች ነህ ! ቅብርጥሴ ስለዚህ የዘላለም ህይወት የሚሰጠዉን አካል ተከተል ጲሪሪም ጳራራም የሚሉ ማስፈራሪያ እና ዛቻ መሰለ ዓ.ነገሮችን ነዉ። ያዉ እንደማነኛዉም የሰዉ ልጅ(at least fully human በሆነዉ ጎኔ😁) ስለሞት ሳስብ uncertaintyዉ የስሜት መረበሽ ያደርስብኝ ይሆናል ያ የሚሆነዉ ግን ነገሮችን ከመጠናቸዉ በላይ አግዝፎ በመመልከት ነዉ። ሞትን መፍራት ወይ ከሞት ቡሃላ ስላለዉ እጣፋንታ መስጋት ተገቢ እና ተፈጥሯዊ ሆኖ ሳለ ፤ እንደ አንድ ተፈጥሯዊ የህይወት ዑደት ደሞ ከሱ ጋር ሰላም መፍጠር ያስፈልጋል። ይህ ማለት ግን ለእሱ እጅ መስጠት ማለት አይደለም። ይሄ ሁሉም ነገር ላይ የምትገብረዉ የህይወት መርሔ ነዉ። አንድ ነገር የመሆን እድሉ በጣም ጠባብ እና almost እንደማይሆን እያወቁ እንኳ ለመቀየር የመሞከር አባዜ። ይህም እንደምሞት አዉቃለዉ እና መሞት ችግር የለዉም ተፈጥሯዊ ነዉ የሚለዉን ተቀብሎ በተመሳሳይ ሰዓት ግን በህይወት እስካለሁ ላስቆመዉ እሰራለዉ የሚለዉን ወኔ መታጠቅ ነዉ። ሁሉንም ነገር የማረገዉም በዚህ መሰረት ነዉ። ሰዎች ድንቁርና dominant trait ነዉ፤ መልኩን እየቀያየረ ያለ እና የሚኖርም ነዉ ፤ ስለዚህ አንተ ለምን awareness ለመፍጠር ይሄን ያህል ትባዝናለህ ይሉኛል፤ ደሞም ልክ ናቸዉ በሀሳባቸዉም እስማማለሁ ግን ለእኔ ህይወት እሱ ነዉ። The struggle b/n the destiny. አዎ ድንቁርናን መቅረፍ የሚቻል አይመስልም እነሆ በሰዎች ታሪክ ዉስጥ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የማንነታችን አንድ ክፍል ነዉ እና ! ብሎ አምኖ at the same time ግን ሊጠፋ እንደሚችል ነገር መታገል። ህይወትን መኖር ማለት ልታረጓቸዉ ያሰባቿቸዉ ነገሮች odds against you እንደሆኑ እያወቃቹ  "whatever" ብላቹ ማረግ የሚገባቹን የማረግ ጥበብ ነዉ። ብዙ ሰዎች ህይወት ይዛ ለምትመጣዉ uncertainty እጅ ይሰጣሉ፤ certainty ይሰጠኛል ብለዉ ወደሚያስቡት ነገር ሁሉም ይሮጣሉ። እኔ ግን ከ uncertaintyዉ ጋር ሰላምን እፈጥራለዉ፤አኖረዋለሁም! 99 ለ 1 ቢመራኝ እንኳ ጨዋታዉ እስኪያበቃ ጨዋታዉን እቀጥላለሁ። ህይወት ማለት ይህ ነዉ ! ማሸነፍ ሳይሆን በህይወታቹ ልታረጉ የሚገባቹን ነገር በነፃነት ማረግ። ዉጤቱ ምንም ይሁን ምን። የሞት፣ስቅላት፣ግርፋት፣መገለል፣ድብደባ... ወዘተ ፍራቻ እና የእንዲ ቢሆንስ ሰንሰለት ሊያስራቹ አይገባም። አለም ልክ ተቦክቶ እንደተቀመጠ የሸክላ ጭቃ ለፈለጋቹት ነገር ለመበጀት ዝግጁ ናት፤ ጭቃዉን አንሱት፤እንዳሻቹም አቡኩት፤ እንደፈለጋቹም ጠፍጥፉት፤ በፈለጋቹት ቅርፅም አበጁት... ጭቃዉን ተጠበባቹበትም ተዋቹትም መድረቁ አይቀርም እና። ምናልባት በዛ ጭቃ እናንተን የሚመስል ልዩ ነገር ካስቀመጣቹ ግን በጭቃዉ ዉስጥ እናንተ ትታወሳላቹ ። አሁንም ማወቅ ያለባቹ  ነገር መታወሱ ለናንተ ምንም አይሰራም ! ነገር ግን የህይወትን መኖር byproduct ሆኖ ስለሚመጣ ነዉ። ሞትን ማስቆም ብትችሉ እንኳ ዉበቱ ያለዉ ሞትን ማስቆም በመቻላቹ ዉስጥ ሳይሆን እሱን ልታስቆሙ በሄዳቹበት ጋራ እና ሸንተረር ፤ አቀበት እና ቁልቁለት ዉስጥ ነዉ። አንድ ልጅ ከመዳህ ወደ መራመድ በሚያረገዉ ጉዞ ላይ ትልቁ ኩነት መራመድ መቻሉ ሳይሆን መዉደቅ እና መነሳቱ መልሶም መጣሩ ነዉ ። so you gotta live life for the journey of it not for the destiny, The beauty of life is in its uncertainty ! ተፃፈ በፍጡር አብዝቶ ላሰበበት ተፈጥሮዉ።

Открыть в Telegram
Просмотры1 830−31%к среднему
Пересылки—
Реакции31
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
2 ч511
4 ч742
7 ч891
24 ч1 830
  1. Через 6 часов891
  2. Через 24 часа1 830
  3. Всего сейчас1 830
#4212Текст

◉ እሁድ ከረዘመባችሁ ➊ [ Ship of Theseus ፊልም] "Ship of Theseus" ፍልስፍናዊ ይዘት ያለው አስተካዥ ፊልም ነው። ርዕሱ በጥንታዊ ግሪክ ፍልስፍና ውስጥ ከሚገኘው «Ship of Theseus Paradox» የመጣ ነው። ​«If every component of the Ship of Theseus is replaced, is it still the same ship?» የሚለውን መሠረታዊ የለውጥ ጥያቄ ያነሳል። ፊልሙ በሦስት የተለያዩ ሰዎች ሕይወት ዙሪያ የሚሽከረከር ነው። ነገር ግን በሦስቱም ታሪኮች የምናየው የTheseus መርከብን መንፈስ ነው። ዓይኗ ሳያይ በድምፅና በንክኪ ዓለምን የምትረዳ...አሊያ የምትባል ፎቶግራፈር አለች። የዓይን ብሌን ንቅላት ተደርጎላት ማየት ስትጀምር ግን ነገሮች ይቀየራሉ። በሌላኛው በኩል በእንስሳት ላይ የሚደረግን ምርምር በጽኑ የሚቃወም መነኩሴ አለ። ድንገት ከባድ የጉበት በሽታ ይያዛል። ይህንግዜ ሕይወቱን ለማትረፍ የጉበት ንቅለ ተከላ ያስፈልገዋል። ሕይወቱን ለማቆየት በሚቃወማቸው መንገዶች ውስጥ ማለፍ ነበረበት። ደግሞ በሕገ-ወጥ የኩላሊት ዝውውር ውስጥ የተጎዳን ሰው ለማዳን የሚባክን ካራክተር አለላችሁ። በኋላ ራሱን ሲመረምር «እውን የማደርገው እርዳታ ሰዎችን ለማትረፍ አስቤ ነው ወይስ ራሴን እንደ በጎ አድራጊና ጻድቅ ለማየት?» ብሎ የሚጠይቅ። ሁሉም ሰው በሕይወቱ ውስጥ ድንገተኛ ሽግግር ሲገጥመው «እኔነቴ ምን ሆነ?» ብሎ እንደሚጠይቅ ያሳያሉ። የፊልሙ ገጸ-ባህሪያት በ moral ambiguity ውስጥ ቆመው የሚታገሉ ተራ ሰዎች ናቸው። አዘጋጁ ለተመልካቹ ቀጥተኛ መልስ ወይም መደምደሚያ ከመስጠት ይልቅ.... ጸጥ ያሉ ትዕይንቶችን በመጠቀም ተመልካቹ ራሱ እንዲያስብ ክፍት ቦታ ይተዋል። ➋ [የ Theseus መርከብ ታሪክና ጥያቄ] በጥንታዊ የግሪክ አፈ-ታሪክ Theseus የአቴንስ ጀግና ነበር። ከክሬት ደሴት በሕይወት ሲመለስ የተጠቀመባትን መርከብ... አቴናውያን ለመታሰቢያና ለክብር ወደብ ላይ አቁመው ይጠብቋት ነበር። ​ጊዜ እያለፈ ሲሄድ የመርከቧ የእንጨት ክፍሎች መበስበስ ጀመሩ። መርከቧ እንዳትፈርስና እንድትቆይ፣ ጠባቂዎቿ እያንዳንዱን የበሰበሰ እንጨት እያወጡ በአዲስ እንጨት መቀየር ጀመሩ። ​ከብዙ ዓመታት በኋላ፣ መርከቧ ስትቆረቆር የነበሩት እንጨቶች አንድም ሳይቀሩ በሙሉ ተቀይረው በአዲስ ተተኩ። በዚህ ጊዜ መሠረታዊው ጥያቄ ተነሳ... ​«ሁሉም ክፍሎቿ ተቀይረው በአዲስ ከተተኩ በኋላ፣ ይህች መርከብ አሁንም እውን የ Theseus መርከብ ናት ወይንስ ሌላ አዲስ መርከብ ሆናለች?» የTheseus መርከብ ታሪክ የሰው ልጅ ሕይወቱን እንዲፈክር የሚያስገድድ ጥያቄን ነው የሚያነሳው። ​በሰውነታችን ውስጥ ያሉ cells፣ ሐሳቦቻችን፣ እምነቶቻችንና ልምዶቻችን በጊዜ ሂደት ይቀየራሉ፣ ይታደሳሉ። ​የዛሬ 10 ዓመት የነበርኩት ሰው እና የዛሬው እኔነቴ ለየቅል ናቸው። የምር እኔ የምለው ማንነቴ የቱን ነው ብዬ እጠይቅና «ያኔ ያለፍኩት እኔ ነኝ፣ ዛሬም ያለሁት እኔ ነኝ» ብዬ እመልሳለሁ። የሰው ልጅ ሁሌ በለውጥ ሂደት ውስጥ ነው። የሰው ልጅ የተጠናቀቀ ፍጡር ነው ብዬ አላምንም። በመሰራት ላይ ያለን ያላለቅን ፍጡሮች ነን። ትናንት በጽኑ ያመንኩበት ነገር ዛሬ በሌላ ዓይን ላየው እችላለሁ። የቀድሞው «እኔ» ሲሞት አዲሱ «እኔ» ይወለዳል። ይህ ለውጥ ክህደት አይመስለኝም። የተፈጥሮ ሕግ ነውና። ውሃ ካልፈሰሰ እንደሚበላሸው፤ የሰው ልጅም እንደዛ ነው። ፊልሙም እንዲህ ያሳስባል! ©Mesoud

Открыть в Telegram
Просмотры1 940−27%к среднему
Пересылки—
Реакции26
Комментарии—
#4208Видео
Просмотры2 720+3%к среднему
Пересылки—
Реакции32
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
41 ч2 380
68 ч2 720
  1. Всего сейчас2 720
#4207Текст

ግላውኮንም ሶቅራጠስን እንዲህ ሲል ያስታዉሰዋል... ሌላውን ሁሉ እስማማለሁ፤ ምንም እንኳ ጠቃሚ ጥቅሞችን ጨምሬ ልናገር ብችልም (ሴቶችም አብረው ቢዋጉ ማንም ሊያሸንፋቸው አይችልም)። ነገር ግን ይህ ሕገ መንግሥት ሊፈፀም ይችላል ወይ፣ እንዴት? ይሄንን ይህ ሁሉ ጊዜ ዘልለኸዋል። ይለዋል። ሶቅራጠስ "ሦስተኛውና ከሁሉ የላቀዉ ማዕበል እየመጣብኝ ነው" ይላል። ቀጥሎም... ፍትሕ ምን እንደሆነ ስንፈልግ ዓላማችን ሞዴል (ምሳሌ /paradigm) ማግኘት ነበር ፤ ፍጹም ፍትሐዊው ሰው ምን እንደሚመስል (ቢኖር)፣ ከዚያ ወደ እሱ የቀረበ ሰው ዕጣውም ወደ እሱ እንደሚቀርብ ለማየት ነዉ። ሰው እንደዚህ ሊኖር እንደሚችል ማሳየት ዓላማችን አልነበረም። አንድ ሰዓሊ ውብ ሰውን በፍጹም መልክ ቢስል፣ ነገር ግን እንደዚህ ያለ ሰው ሊኖር እንደሚችል ማሳየት ባይችል ከሠዓሊነቱ አይቀንስም። እኛም በንግግር የጥሩ ከተማ ሞዴል ሠርተናል። ሁሉም ነገር በንግግር በተገለጸው መንገድ በትክክል ሊፈጸም ይችላል? ተግባር ከንግግር ይልቅ እውነትን ያነሰ ይይዛል። ስለዚህ ማሳየት ያለብን የተገለጸው ከተማ በተቻለ መጠን የቀረበ ሊሆን የሚችልበትን መንገድ ነው። በዘመናችን ከተሞች ምን እንደሚከለክል፣ ወደዚህ ሕገ መንግሥት ለመድረስ ሊደረግ የሚችለው ትንሹ ለውጥ (አንድ፣ ካልሆነ ሁለት፣ ካልሆነ ጥቂት) ምን እንደሆነ እናሳያለን። ይላል። ሶቅራጠስም በማከል ፈላስፎች በከተሞቻቸው እንደ ነገሥታት እስካልገዙ ወይም ዛሬ ነገሥታትና መሪዎች የሚባሉት እውነተኛና በቂ ፈላስፎች ሆነው የፖለቲካ ሥልጣንና ፍልስፍና እስካልተዋሐዱ እና ዛሬ አንዱን ብቻ የሚከተሉ ብዙ ተፈጥሮዎች በግድ እስካልተቀላቀሉ ድረስ ከተሞች ከክፋት ዕረፍት አያገኙም፤ የሰው ልጅም አያገኝም፤ እኛ የገለፅነው ሕገ መንግሥትም በተቻለ መጠን አይወለድም፣ የፀሐይም ብርሃን አያይም። ይላል። ሶቅራጠስም ይህን ለመናገር ለረዥም ጊዜ ያመነታበትን ምክንያት ሲገልፅ... ይህ በጣም የማይታመን ይመስላል፤ ከዚህ ሌላ ከተማ ደስታ (በግልም በሕዝብም) የለም ማለት ነውና። ግላዉኮንም ማስጠንቀቂያ ቢጤ ይሰጠዋል...ብዙ ታዋቂ ሰዎች ካባቸውን አውልቀው የደረሰውን መሣሪያ ይዘው ሊያጠቁህ ይሮጣሉ፤ ራስህን በክርክር ካልተከላከልክ በዚህ ፌዝህ ትቀጣለህም።ይለዋል። በመቀጠል ስቅራጠስ እነዚህን ተቃዋሚዎች ለመቋቋም "ፈላስፋ" ማን እንደሆነ መግለጽ አለብን፤ አንዳንዶች በተፈጥሯቸው ለፍልስፍናና ለመምራት የተሠሩ፣ ሌሎች ደግሞ መከተል የሚገባቸው መሆኑን ማሳየት አለብን ይላል። አንድ ነገር እንወዳለን ስንል የተወሰነውን ክፍል ሳይሆን ሙሉውን እንወዳለን እያልን ነዉ። ለምሳሌ... ወጣት ወዳጅ ወንድ ልጅ በሁሉም ባሕርዩ ምክንያት ያገኛል (አፍንጫው ዘለግ ያለ "ንጉሣዊ"፣ ደፍጣጣ "ቆንጆ"፣ ጥቁር "ወንዳወንድ"፣ የገርጣ "የአማልክት ልጅ")፤ የወይን ወዳጆችም ማንኛውንም ወይን ይወዳሉ፤ ክብር ወዳጆች ጄኔራል ካልሆኑ ሻለቃ ይሆናሉ ክብርን በሙሉ ይመኛሉና። ስለዚህ ፈላስፋ ጥበብን በሙሉ የሚመኝ፣ ሁሉንም ዓይነት ትምህርት በደስታ የሚቀምስና የማይጠግብ ሰው ነው። "የሚመርጥ" ተማሪ (በተለይ ወጣት) ፈላስፋ አይደለም። ልክ ምግብ የሚመርጥ ሰው የተራበ ወይም ምግብ ወዳድ ሳይሆን ምግብ መራጭ እንደሆነ ሁሉ። ግላውኮን በዚህ ላይ ተቃዉሞን ያነሳል፤ እንደዚያ ከሆነ የማየት ወዳጆች (ሁሉንም ትርዒት የሚወዱ) እና የመስማት ወዳጆች (ጆሮአቸው በኮንትራት እንደተከራየ ሰው የዳዮኒሶስ በዓሎችን ሁሉ የሚዞሩ) ፈላስፎች ይሆናሉ? ሶቅራጠስ "አይደሉም፤ እነሱ ፈላስፎችን ይመስላሉ።" እውነተኛዎቹ "እውነትን የማየት ወዳጆች" ናቸው። ውብና አስቀያሚ ተቃራኒዎች ስለሆኑ ሁለት ናቸው፤ እያንዳንዳቸው ደግሞ አንድ ናቸው። ፍትሐዊ/ኢፍትሐዊ፣ መልካም/መጥፎ እና ሁሉም ቅርጾች (forms) እንዲሁ እያንዳንዳቸው በራሳቸዉ አንድ ናቸዉ፤ ነገር ግን ከድርጊቶችና ከአካላት፣ እንዲሁም እርስ በርስ ስለሚዛመዱ ብዙ ሆነው ይታያሉ።ይለዋል። በመቀጠል እነኚህ ፈላስፋ መሳዮች እና እዉነተኛ ፈላስፎች በምን እንደሚለዩ ይገልፅለታል... ፈላስፋ መሳዮች ውብ ድምፆችን፣ ቀለሞችን፣ ቅርጾችንና ከእነሱ የተሠሩ ነገሮችን ይወዳሉ ፤ እዉነተኛ ፈላስፎች ግን ውብ ነገሮችን ብቻ ሳይሆን ውበትን ራሱን ማየትና መውደድ ይችላሉ። ፈላስፋ መሳዮች ሐሳባቸው የውበትን ተፈጥሮ ማየት አይችልም። እዉነተኛ ፈላስፎች ግን ውበትን ራሱን በራሱ ማየት ይችላሉ፤ እንዲህ ያሉ ሰዎችም ጥቂት ናቸው። ፈላስፋ መሳዮች በውብ ነገሮች ያምናሉ፤ በውበት ራሱ ግን አያምኑም፤ ወደ እሱ የሚመራቸውንም መከተል አይችሉም፤ ሕልም ውስጥ ናቸው(ምስልን ከራሱ ነገር ጋር የሚያምታታ ሰው ሕልም እያለመ ነውና)። እዉነተኛ ፈላስፋዎች ግን ውበትን ራሱንና የሚሳተፉበትን ነገሮች ሁለቱንም ያያሉ፤ አያምታቱም፤ ነቅተዋል። ፈላስፋ መሳዮች አስተያየት እና እምነት አላቸው። እዉነተኛ ፈላስፋዎች ግን ዕውቀት አላቸው። አማኝ የሆነ ሰው ተቆጥቶ ቢከራከር እንዴት እናሳምነዋለን? ሶቅራጠስ በገርነት ይጠይቃል። ለራሱም ጥያቄ መልስ ይሰጣል... የሚያውቅ ሰው አንድን ነገር ያውቃል። ያ ነገር ያለ (is) ወይ የሌለ (is not) ነዉ።ያለ፣ የሌለን ነገር ማወቅ አይቻልም። ስለዚህ ሙሉ በሙሉ ያለ ነገር ሙሉ በሙሉ የዕውቀት ዓላማ ነው፤ በምንም መንገድ የሌለ ነገር የድንቁርና ዓላማ ነው። ሁለቱም "ያለ" እና "የሌለ" የሆነ ነገር ቢኖር በንጹሕ መኖርና በንጹሕ አለመኖር መካከል ይሆናል፤ ለእሱም በዕውቀትና በድንቁርና መካከል የሆነ ነገር ያስፈልጋል። እምነት (belief) ከዕውቀት የተለየ "ሃይል" ነው፤ ኃይሎች የሚለዩት በሚመለከቱት ነገርና በሚያደርጉት ነው። ዕውቀት የማይሳሳት፣ እምነት ደሞ የሚሳሳት ስለሆነ ሁለቱ የተለዩ ናቸው። የተለዩ ሃይሎች የተለዩ ነገሮችን ይመለከታሉ፤ ዕውቀት "ያለውን" ስለሚመለከት የእምነት ዓላማ ሌላ ነገር መሆን አለበት። እምነት "የሌለን" ማመን አይችልም (ምንም የማያምን ሰው የለም፤ የሌለ ማለት "ምንም" ማለት ነው)። ስለዚህ እምነት ዕውቀትም ድንቁርናም አይደለም፤ ከዕውቀት ያነሰ  ከድንቁርናም የበለጠ እና በመካከላቸው የሚገኝ ነው። ስለዚህ ሁለቱም "ያሉ" እና "የሌሉ" ሊባሉ የሚችሉ ነገሮች የአስተያየት ዓላማ ናቸው። ብዙ ውብ ነገሮችን የሚወደውን ሰው "ከብዙ ውብ ነገሮች ውስጥ አስቀያሚ ሆኖ የማይታይ አለ? ከፍትሐዊዎች ውስጥ ኢፍትሐዊ ሆኖ የማይታይስ?" ብለን ብንጠይቀዉ ሁሉም ተቃራኒ ሆነው እንደሚታዩ መቀበል አለበት። እጥፍ የሆኑ ነገሮች ግማሽም ናቸው፤ ትልቅ፣ ትንሽ፣ ቀላል፣ ከባድ የምንላቸው ከተቃራኒያቸው ባልተናነሰ መልኩ ናቸው። እነዚህ ድግግሞሽ ውስጥ ያሉ ነገሮች እንደ ድግስ ላይ እንቆቅልሾች አጠራጣሪ ናቸው። "ያሉ ወይም የሌሉ፣ ሁለቱም ወይም አንዳቸው" ብሎ መያዝ አይቻልም። ስለዚህ የብዙኃኑ በውበትና በሌሎችም ላይ ያላቸው ብዙ ልማዳዊ ደንቦች በ"የሌለ" እና "ንጹሕ ያለ" መካከል የሚንከባለል ነው። ይቀጥላል... ምንጭ፤ከላይ ከተያያዘዉ መፅሀፍ(Republic) ከገፅ 227 እስከ ገፅ 282

Открыть в Telegram
Просмотры2 670+1%к среднему
Пересылки—
Реакции15
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
45 ч2 380
67 ч2 670
  1. Всего сейчас2 670
#4206Текст

ሶቅራጠስ አራቱን አንጃነላሹ አገዛዞች ለመግለፅ ሲዘጋጅ ፖሌማርኮስ የአዴይማንቶስን ልብስ ጎትቶ በጆሮው አንድ ነገር ሹክ አለው፤ አዴይማንቶስም "አንለቅህም!" ብሎ ጮኸ ምክንያቱም ሶቅራጠስ ስለ ሴቶችና ልጆች በጋራ መጠቀም(ጓደኞች ሁሉንም በጋራ ይጋራሉ) ብሎ በቀላሉ አልፎ ሄዷል። እነሱም ይህ ሕገ መንግሥቱ ትክክል መሆን አለመሆኑን ሁሉ ይወስናል ብለው ያስባሉ ስለዚህ እንዴት እንደሚደረግ፣ ልጆች እንዴት እንደሚወለዱና እንደሚያድጉ ማብራራት አለበት።ግላውኮንም በዚህ ጣልቃ ይገባል፤ ትራስማኮስም "የሁላችንም ውሳኔ ነው"  ይላል። ሶቅራጠስ በማማረር ቅላፄ "ብዙ ክርክር እየቀሰቀሳችሁ ነው፤ ለዚህ ነበር ርዕሱን ዝም ያልኩት።ይላቸዋል። ትራስማኮስም መለስ አርጎ እዚህ የመጡት ክርክር ለመስማት እንጂ ብረት ለማቅለጥ እንዳልሆነ ይነግረዋል። ሶቅራጠስም አንድ ጥያቄ ያቀርብላቸዋል ...ጠባቂ ውሾች ሴቶችና ወንዶች ሲሆኑ፣ ሴቶቹ ከወንዶቹ ጋር መጠበቅና ማደን ላይ ይሳተፋሉ ወይስ ቡችላ በመውለድና በማሳደግ ምክንያት በቤት ይቀራሉ? ግላውኮን "ሁሉንም ይጋራሉ፤ ሴቶችን ግን እንደ ደካማ፣ ወንዶችን እንደ ጠንካራ እንጠቀማለን" ይላል። ከዚያ ሶቅራጠስ ይቀጥላል፤ እንስሳትን ለተመሳሳይ ሥራ ስንጠቀም ተመሳሳይ ትምህርት መስጠት አለብን፤ ስለዚህ ሴቶችም ሙዚቃ፣ የአካል ሥልጠናና ወታደራዊ ሥልጠና ይማራሉ፤ በተመሳሳይ ሥራዎችም ይመደባሉ። ሴቶች (ወጣትም አዛውንትም) ከወንዶች ጋር በአካል ማሠልጠኛ ቦታ ልብስ አልባሳቸውን አውልቀው (ወይም ያለ ካባ) ሲሠለጥኑ ማየት በአሁኑ ሁኔታ አስቂኝ ይሆናል። ግሪኮች በጥንት ወንዶች ራቁታቸውን መታየትን እንደ አሳፋሪና አስቂኝ ይቆጥሩት ነበር፤ ቀርጤሳውያንና ከዚያ ስፓርታውያን ጂምናዚየም ሲጀምሩ ኮሜዲ ጸሐፊዎች አሾፉባቸው። ነገር ግን አዲሱ ልማድ የተሻለ መሆኑ ሲታወቅ ሳቁ ጠፋ። ስለዚህ ከመጥፎና ከሞኝነት ሌላ ነገርን አስቂኝ የሚያደርግ ወይም ከመልካም ሌላ የውበት መለኪያ የሚወስድ ሰው ሞኝ ነው።አላቸዉ። ሶቅራጠስ በመቀጠል ሌላ ሊነሳ የምችለዉን ተቃዉሞ ይጠቅሳል... ከተማ ስንመሠርት እያንዳንዱ በተፈጥሮው የሚስማማውን አንድ ሥራ ይሥራ ብለን ተስማምተን ነበር። ሴትና ወንድ በተፈጥሮ በጣም የተለያዩ ናቸው፤ ታዲያ ተመሳሳይ ሥራ እንዲሠሩ መናገራችሁ ራሳችሁን አይቃረንም? ግላውኮንም ወዲያውኑ ለጥያቄዉ መልስ ያጣለታል። ሶቅራጠስ ግን "ትንሽ ገንዳ ይሁን ወይም ታላቅ ባሕር፣ መዋኘት ግድ ነው" ይላል  ዶልፊን እስኪያድነን እንጠብቃለን በማለት የኦሪዮንን ታሪክ ያሳታዉሳቸዋል። በመቀጠልም የጥያቄዉን አጣብቂኝ ወደ መፍታት ይሻገራል... የተቃዋሚው ክርክር በቃል ጨዋታ (eristic) እንጂ በትክክለኛ ተቃርኖ (dialectic) ላይ የተመሰረት አይደለም፤ ምክንያቱም "የተለያየ ተፈጥሮ" ስንል የትኛውን ልዩነት እንደምንመለከት አልመረመርንም። ለምሳሌ መላጦች ጫማ ሠሪ ከሆኑ ረጅም ፀጉር ያላቸው ጫማ ሠሪ መሆን የለባቸውም ልንል እንችላለን? ይህ አስቂኝ ነው፤ ምክንያቱም የምንመለከተው ከሥራው ጋር የሚዛመደውን ልዩነት ብቻ ነው። በሌላ ምሳሌም ብናይ ለሕክምና ተስማሚ ነብስ ያላት ሴትና ወንድ ተመሳሳይ ተፈጥሮ አላቸው፤ ሀኪም እና አናጢ (ሁለቱም ወንዶች ቢሆኑ እራሱ) ግን የተለያየ ተፈጥሮ አላቸው። ሴቷ የምትወልደው፣ ወንዱ የሚያስወልደዉ ልዩነት ብቻ ከሆነ ለከተማ አስተዳደር ሥራዎች ሴት ከወንድ እንደምትለይ እስካሁን አልተረጋገጠም። ለአንድ ሥራ በተፈጥሮ የተስማማ ማለት በቀላሉ ይማራል፣ ከትንሽ ትምህርት ብዙ ያገኛል፣ አካሉ አእምሮውን ያገለግላል ለማለት ነዉ እንጂ በእነዚህ ነገሮች ወንዱ ሁልጊዜ ከሴቷ ይበልጣል፤ሁሉም ሥራ ውስጥ (መሸመንና ምግብ ማብሰልንም ጨምሮ ግላውኮን "ብዙ ሴቶች ከብዙ ወንዶች በብዙ ነገር ይሻላሉ" ይላል፤ በአጠቃላይ ግን እውነት ነው)። ስለዚህ ለከተማ አስተዳደር የሚያገለግል ሥራ በሴትነት ምክንያት ለሴት ወይም በወንድነት ምክንያት ለወንድ የሚመደብ የለም፤ ተፈጥሯዊ ችሎታዎች በሁለቱም ፆታዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ይሰራጫሉ፤ ሴት በሁሉም ሥራ ልትሳተፍ ትችላለች፣ ግን ለሁሉም ዓላማ ከወንድ ደካማ ናት። አንዲት ሴት ለሕክምና ተስማሚ ነች፣ ሌላዋ አይደለችም፤ አንዲት ለሙዚቃ፣ ሌላዋ አይደለችም፤ አንዲት ለአካል ሥልጠናና ለጦርነት፣ ሌላዋ ጦር ጠል ነች፤ አንዲት ፈላስፋ (ጥበብ ወዳድ)፣ ሌላዋ ጥበብ ጠል (misosopher)፤ አንዲት ስሜታዊ፣ ሌላዋ ስሜት የለሽ። ስለዚህ ጠባቂ ለመሆን የተስማማች ሴትም የማትስማማም አለች፤ ተስማሚዎቹ ከወንድ ጠባቂዎች ጋር በተፈጥሮ ዝምድና ያላቸው ናቸው፣ ከወንዶቹ ጋር አብረው መኖርና መጠበቅ አለባቸው። ይህ ሕግ ሊሆን የሚችል ነው ነገር ግን ከተፈጥሮ ጋር የሚስማማ ሲሆን ብቻ። ለከተማ ምርጥ ወንዶችና ምርጥ ሴቶች እንዲኖሩ ከማረግ የተሻለ ነገር የለም፤ የሙዚቃና የአካል ሥልጠና ድብልቅ ይህንን ያደርጋል። ስለዚህ ሴት ጠባቂዎች "በጎነትን እንደ ካባ ይለብሳሉ" በጦርነትና በጥበቃ ይሳተፋሉ፤ ነገር ግን በሴትነት ደካማነት ምክንያት ቀለል ያሉ ሥራዎች ይሰጣቸዋል። ሴቶች ለሚጠቅም ነገር ሲሠለጥኑ የሚስቅ ሰው "ያልበሰለ የጥበብ ፍሬ" እየነጠቀ ነው፤ ምክንያቱም "የሚጠቅመው ውብ፣ የሚጎዳው አስቀያሚ" ነው።  ሶቅራጠስም አንድ ማዕበል እንዳስወገደ ይናገራል፤ ግላውኮን ግን "ትንሽ ማዕበል አይደለም" ይላል ፤ ሶቅራጠስም "ቀጣዩን ስታይ ይህ ትንሽ ይመስልሃል" ይለዋል። በመቀጠል ሕጉን ሲያስረዳ ሁሉም ሴቶች ከሁሉም ወንዶች ጋር በጋራ ይሆናሉ፤ አንድ ሴትና አንድ ወንድ በግል ጋብቻ አብረው አይኖሩም፤ ልጆችም በጋራ ይሆናሉ፤ ወላጅ ልጁን፣ ልጅ ወላጁን አያውቅም። ግላውኮን ይህ "ከመጀመሪያው ይልቅ ይበልጥ አጠራጣሪ" እንደሆነ ይናገራል በጥቅሙም ሆነ በመቻሉ። ሶቅራጠስ ግን የመቻል ጥያቄውን ለጊዜው እንዲተው ይለምናል፤ እንደ ሰነፍ ብቻውን በእግር ሲሄድ ለሚያስበው ምኞት በሐሳብ እንደሚደሰት ሰው፣ ከተፈጸመ ገዥዎች እንዴት እንደሚያደራጁትና ለከተማ እንደሚጠቅም ብቻ ይመረምራል። ሴትና ወንድ ጠባቂዎች በጋራ መኖሪያ፣ በጋራ ምግብ፣ በጋራ ሥልጠና ስለሚኖሩ ወደ ግብረ ሥጋ ግንኙነት "በተፈጥሮ ግዴታ" (erotic necessity) ይነሳሳሉ። ነገር ግን ያልተመራ ግንኙነት ከደስተኞች ከተማ ጋር አይስማማም፤ ስለዚህ ጋብቻዎች "በተቻለ መጠን ቅዱስ" ይሆናሉ፤ ቅዱስ ማለት ጠቃሚ ማለት ነው። ሶቅራጠስ በእርባታ ምሳሌም ይመስለዋል፤ ግላውኮንን ስለ አደን ውሾቹና ስለ ወፎቹ ይጠይቃል። ከምርጦቹ ብቻ፣ በወጣትነት ዘመናቸው የሚራቡ ስለሆኑ፣ እንዲህ ካልሆነ ዘሩ ይባባሳል። ሰው ከዚህ የተለየ ካልሆነ ገዥዎች እጅግ ጥሩ መሆን አለባቸው።"መድኃኒት" ሆኖ ዉሸት ሊሆን የሚችል ቀደም ብለን እንዳልነው፤ ውሸትና ማታለል ለገዥዎች እንደ መድኃኒት ጠቃሚ ነው። ምርጦቹ ከምርጦቹ ጋር እንዲጣመሩ፣ ዝቅተኛዎቹ እንዲገደቡ፤ ይህ ሁሉ ከገዥዎች በቀር ማንም ሳያውቅ መከናወን አለበት። በዚህም መሰረት ዝርዝር ሕጉ.... በጋብቻ ወቅት በገዥዎች ሥርዓት የተወሰኑ በዓላትና መሥዋዕቶች ይደረጋሉ፤ ባለቅኔዎች ለጋብቻዎች መዝሙር ይጽፋሉ፤ የጋብቻዎች ቁጥር በገዥዎች ይወሰናል (ከጦርነት፣ ከበሽታ ጋር ተመጣጥኖ የወንዶች ቁጥር እንዲቆይ)። ከዛ በተጨማሪ ብልሃተኛ ዕጣ አወጣጦች ይቋቋማሉ፤ ዝቅተኛ ሰው ገዥዎችን ሳይሆን ዕድልን እንዲወቅስ።በጦርነትና በሌሎች የጥበቃ አገልግሎቶች ጥሩ የሆኑ ወጣቶች ከሌሎች ሽልማቶች በተጨማሪ ከሴቶች ጋር ለመሆን ተጨማሪ ዕድል ያገኛሉ፤ ብዙ ልጆች ከእነሱ እንዲወለዱ።ልጆች ከተወለዱ በኋላ በዚህ ኃላፊነት በተሾሙ ባለሥልጣኖች (ወንድም ሴትም) ይወሰዳሉ፤ የጥሩ ወላጆች ልጆች በከተማዋ በተለየ ክፍል ወደሚገኝ "የሕፃናት ማሳደጊያ" ለልዩ ሞግዚቶች ይሰጣሉ፤ የዝቅተኛ ወላጆች ልጆችና የአካል ጉድለት ያለባቸው ሕፃናት በምስጢራዊና ባልታወቀ ቦታ ይደበቃሉ። እናቶች ወተት ሲሞላ ወደ ማሳደጊያው ይመጣሉ፤ ማንም እናት ልጇን እንዳታውቅ የተለያዩ ዘዴዎች ይተገበራሉ፤ ወተት ካነሰ ሌሎች ሴቶች ያጠባሉ፤ የሌሊት ሥራ ለሞግዚቶች ይሰጣል።ሴት ለከተማ ከ20 እስከ 40 ዓመት፤ ወንድ ከሩጫ ጥንካሬው ጫፍ በኋላ እስከ 55 ዓመት ድረስ ያገለግላል። ከዚህ ዕድሜ ውጭ ወይም ገዥዎች ሳያጣምሩ የተወለደ ልጅ "ሕገ ወጥ፣ ያልተፈቀደ፣ ርኩስ" ተብሎ ይቆጠራል (ያለ መሥዋዕትና ጸሎት በጨለማ የተወለደ ተደርጎ ይታሰባል)። ከዕድሜ ገደብ በኋላ ወንዶችና ሴቶች ከተወሰነ የቅርብ ዘመድ (ሴት ልጅ፣ እናት፣ የልጅ ልጅ፣ የእናት ዘር፣ ወዘተ) በስተቀር ከማንም ጋር ሊሆኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን እርግዝና ቢፈጠር ልጁ እንዳይወለድ ወይም ከተወለደ እንዳያድግ ማዘዝ ይገባል። ማን ማን እንደሆነ እንዴት ያውቃሉ? ይላል ግላዉኮኝ ሶቅራጠስም፣ አያውቁም። ከጋብቻው ቀን በኋላ በ7ኛውና በ10ኛው ወር የተወለዱትን ሁሉ "ልጆቼ" ይሏቸዋል፤ እነሱም "አባቴ፣እናቴ" ይሏቸዋል። የእነዚህ ልጆች ልጆች "የልጅ ልጆች" ፣ የእሱ ቡድን "አያቶች" ይባላሉ፤ ከአንድ ወቅት የተወለዱት "ወንድሞችና እህቶች" ይባላሉ፤ ስለዚህ እርስ በርስ ከመጋባት ይታቀባሉ። ሆኖም ዕጣው ቢያወጣና የዴልፊ ቄስ ቢፈቅድ ወንድም ከእህት ጋር እንዲሆን ሕጉ ይፈቅዳል። ብሎ ይመልሳል። ለከተማ ትልቁ ክፋት የሚበታትናትና ከአንድ ወደ ብዙ የሚያደርጋት ነገር ነዉ፤ ትልቁ መልካም ደግሞ የሚያስተሳስራትና አንድ የሚያደርጋት ነው። ደስታና ሥቃይን በጋራ ማካፈል ያስተሳስራል፤ "የእኔ" እና "የእኔ አይደለም" የሚሉትን ቃላት በአንድነት መጠቀም አለመቻል ይበትናል። ለምሳሌ አንድ ሰው ጣቱን ቢጎዳ መላው ሰውነት (አካልና ነብስ በአንድ ሥርዓት በገዥው ክፍል ሥር የተሳሰሩ) በአንድነት ሥቃዩን ይሰማሉ፤ "ሰዉየዉ ይሠቃያል" ይባላል። የተሻለውም ከተማ ተመሳሳይ ነው ፤ ማንኛውም ዜጋ ደስታ ወይም ሥቃይ ሲያጋጥመው መላው ከተማ "የእኔ ነዉ" ይላል። በሌሎች ከተሞች ገዥዎች ተገዥዎችን "ባሪያዎች" ፣ ተገዥዎች ገዥዎችን "ጌቶች" ይላሉ። በእኛ ከተማ ተገዥዎች ገዥዎችን "አዳኞች/ጠባቂዎችና አጋዥዎች"፣ ገዥዎች ተገዥዎችን "ደመወዝ ከፋዮችና አስተናጋጆች" ይሏቸዋል፤ ገዥዎች እርስ በርስ "አብሮ ጠባቂዎች" ይባባላሉ።ሁሉም ዘመድ ነው። ጠባቂ የተገናኘውን ሁሉ እንደ ወንድም፣ እህት፣ አባት፣ እናት፣ ልጅ ወይም የዘር ሐረግ አባል አድርጎ ይቆጥራል፤ ስሞቹ ብቻ ሳይሆኑ ተግባሮቹም (አክብሮት፣ እንክብካቤ፣ መታዘዝ) ይከተላሉ ፤ አለበለዚያ በአማልክትና በሰዎች ፊት ያልፀደቀ ይባላል። በዚህም ክስና ቅሬታዎች ይጠፋሉ (ከሰውነታቸው ሌላ የግል ንብረት ስለሌላቸው)፤ በሀብትና በቤተሰብ ምክንያት የሚነሣ ጥል አይኖርም። እኩዮች እርስ በርስ እራሳቸውን መከላከል ይችላሉ (ለአካል ብቃት ይጠቅማል፣ ስሜታዊ ቁጣ ወደ ከባድ ጥል እንዳያድግ ይረዳል)፤ ታናናሾች አዛውንቶችን በፍርሃትና በአፍረት ያስተናግዳሉ። በዚህ የህይወት መንገድም ሀብታሞችን ማሞካሸት፣ ልጆችን የማሳደግ ጭንቀት፣ ለቤተሰብ ወጪ ገንዘብ ማግኘት፣ ብድርና ዕዳ የመሳሰሉ ነገሮች አይኖሩባቸዉም። በዚህ የአኗኗር ዘይቤም ጠባቂዎች "ከሁሉ የተባረከው" ከሆነው የኦሊምፒክ አሸናፊዎች ሕይወት የበለጠ ደስተኛ ሆነው ይኖራሉ፤ ምክንያቱም ድላቸው መላውን ከተማ ማዳን ነው፤ ኑሯቸውም ከሕዝብ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ይሸፈናል፤ በሞታቸው ጊዜም ክብር ያለዉ ቀብር ያገኛሉ። ስለዚህ የአዴይማንቶስ ቀደም ብሎ የነበረው ተቃውሞ ( ጠባቂዎች ደስተኛ አይደሉም) ተመልሷል ፤ ዓላማው ከተማዋን በሙሉ ደስተኛ ማረግ ነበር። ጠባቂ በተገባ ኑሮው ካልረካ ሁሉን ለራሱ ለመውሰድ ቢሞክር የሄሲዮድን አባባል "ግማሹ ከሙሉው ይበልጣል" የሚለውን እውነትነት ይማራል። ሶቅራጠስ እዛዉ ላይ በማከል ይጠይቃል ሴቶች ከወንዶች ጋር በትምህርት፣ በልጆችና በጥበቃ ይሳተፉ፤ በከተማ ቢቆዩም በጦርነት ቢወጡ አብረው እንደ ውሾች ይጠብቁና ያድኑ ፤ ይህ ከተፈጥሯቸው ጋር የሚስማማ እንጂ የሚቃረን አይደለም ግላውኮንም "እስማማለሁ" ይላል። የሚቀረው ለሰው ልጆችም ይቻላል ወይ፣ እንዴትስ ይሆናል? የሚለው ነው። ሴቶችና ወንዶች አብረው ወደ ጦርነት ይሄዳሉ፤ ልጆችም ከብቃታቸው በኋላ አብረው ይወሰዳሉ ፤ ልክ የሸክላ ሠሪ ልጆች ሸክላ ከመንካታቸው በፊት ረዥም ጊዜ እንደሚያዩና እንደሚረዱ። ማንኛውም እንስሳ በልጆቹ ፊት በተሻለ ይዋጋል። ግላውኮን አደጋውን ይጠቅሳል (ሽንፈት ቢመጣ ልጆችም ይሞታሉ)፤ ሶቅራጠስ ሁሉንም አደጋ ማስወገድ አይቻልም፤ ዋጋ ያለው አደጋ ብቻ መወሰድ አለበት ይላል። ስለዚህ አባቶች አደገኛ ዘመቻዎችን ያውቃሉ፤ ጥሩ መሪዎች ይሾማሉ፤ ልጆች በፈጣን ፈረሶች ላይ ተጭነዉ አስፈላጊ ሲሆን እንዲሸሹ ይደረጋል። የሚከተሉት የጦር ሕጎችም ይወጣሉ... ቦታውን ትቶ የሸሸ ወይም ጋሻ የጣለ ፈሪ ወደ ሙያተኛ ወይም ገበሬ ደረጃ ዝቅ ይደረጋል። በጠላት በሕይወት የተያዘ ለአጥቂዎቹ እንደ ምርኮ ይሰጣል። በጦርነቱ ጀግንነትን ያሳየ ደሞ አብሮ የሚዘምቱ ወጣቶችና ልጆች ዘውድ ያደርጉለታል፤ እጁን ይጨብጣሉ፤ ማንም እሱ መሳም የሚፈልገውን ሰው ሊከለክል አይችልም፤ ይህም ለሌሎች አርአያ ይሆናል። ያ ደፋር ሰው ለጋብቻም ተጨማሪ ዕድል ያገኛል። በመሥዋዕትና ግብዣዎች የክብር መቀመጫ፣ የምርጥ ሥጋ ቁራጭና የተሞላ ጽዋ ይሰጠዋል። ያማረ እና በክብር የተንቆጠቆጠ ቀብር ይደረግለታል "የወርቅ ዘር" ነው ተብሎም ይታወጃል፤ በሄሲዮድ መሠረት ከሞቱ በኋላ "በምድር የሚኖሩ ንጹሕ ዳይሞኖች" (ከክፋት ጠባቂዎች) ይሆናሉ፤ የአምላክ (አፖሎ) መመሪያ ተከትለው ይቀበራሉ፤ መቃብራቸው የዳይሞን መቃብር ተደርጎ ይመለካል። ተመሳሳይ ክብር በሕይወት ዘመኑ በጣም ጥሩ ሆኖ ለታወቀ ሰው ሞት ይሰጣል። ሌላም ተጨማሪ ሕግ ይወጣል እሱም ከጠላቶቻችን ጋር የምንተዳደርበት ነዉ ሕጉም ይሄን ይመስላል... ባርነትን በተመለከተ ግሪክ ግሪክን አይገዛም፤ ሌሎች ግሪኮችም እንዳያደርጉ ይመከራሉ (ግሪኮች ወደ ባዕዳን እንዲዞሩ)፤ ከጠላት አስክሬን ላይም ከጦር መሣሪያ በስተቀር ማንኛውም ነገር አይወሰድም (አልያ ግን ለስግብግብነትና ፈሪዎችን ሰበብ የሚሰጥ ነው፤ አስከሬንን እንደ ጠላት መቁጠር ትንሽ አእምሮነትና "ሴትነት" ነው፣ ድንጋይ በጣለው ሰው ሳይሆን በድንጋዩ እንደሚናደድ ውሻ ይመስላል) ፤ የግሪክ መሣሪያዎች ወደ መቅደስ አይቀርቡም (ጎሳን ማርከስ ስለሆነ) ፤ የግሪክ መሬት አይወድምም፣ ቤቶች አይቃጠሉም፤ የዓመቱ ሰብል ብቻ ይወሰዳል። ከጥፋተኞች ጥቂቶች ብቻ ይቀጣሉ ፤ አብዛኛው ነዋሪ ወዳጅ ነው። ሶቅራጠስም ሁለቱን ይለያል፤ "ጦርነት" ከባዕድ ጋር የሚደረግ ጠላትነት፣ "አንጃነት" (faction) ከራስ ዘመድ ጋር የሚደረግ ነዉ። ግሪኮች ለራሳቸው ዘመዶች፣ ለባዕዳን ደግሞ ባዕድ ናቸው። ግሪክ ከባዕዳን ጋር ስትዋጋ ጦርነት፤ ግሪክ ከግሪክ ጋር ስትዋጋ ግን "ግሪክ ታማለች፣ ወደ አንጃነት ተከፍላለች" ነው የሚባለው። የእኛ ከተማ ግሪክ ስለሆነች ዜጎቿ ግሪኮችን የሚወዱ ናቸው፤ ከግሪኮች ጋር ያላቸውን ግጭት "አንጃነት" እንጂ "ጦርነት" አይሉትም፤ ዓላማቸውም እርቅ ነው፤ ጠላቶቻቸውንም እንደ "አስተካካዮች" እንጂ እንደ ጠላቶች አይቀጡም።

Открыть в Telegram
Просмотры2 260−14%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
45 ч1 930
67 ч2 260
  1. Всего сейчас2 260
#4205Текст

Переслано из HATETA Perspective

እርግጥ ነዉ ከላይ የሚታየዉ ስዕል በመስታዉት ዉስጥ የሚታየዉ የወጣቷ ልጅ ምስል ነፀብራቅ አደለም ይልቁንም የአስቃያሚ አሮጊት ምስል ነዉ የሚታየዉ ። እኔ ስለዚህ panting ለማዉራት አይደለም ይልቁንም ወጣት ስለሆንሽዉ እና ስለ ወጣቷ ልጃገረድ ለማዉራት ነዉ ፍላጎቴ ምን መሰለሽ girl ወጣት ነሽ ምናልባትም እንደ ፀደይ አበባ ነሽ እናም ምን ያክል ወጣትነትሽን እየተደሰትሽበት ነዉ ? ማደረግ የምትፈልጊዉንስ ምን ያክል እያደረግሽ ነዉ ? ምን ያክል ከድሪቶ ባህል እና ከሃይማኖት ትብታብ ነፃ ነሽ ? ከማህበረሰቡ አሉታዊ ተፅዕኖ ምን ያክልስ ተላቀሻል ? ኢትዮጵያ ዉስጥ እየኖርሽ ከነዚህ ሁሉ ተፅእኖዎች ምን ያክል ነፃ እንደሆንሽ እርግጠኛ አደለሁም! እናም ይሄን ልነግርሽ እፈልጋለሁ ምናልባትም እድለኛ ሆነሽ በወጣትነሽ ካልሞትሽ ከላይ እንዳለችዉ የወጣቷ ልጅ ምስል ነፀብራቅ እንደሆነችዉ አስቀያሚ ፣ ጨቃጭቃ ፣ነገረኛ ፣ ተራጋሚ ፣ ማድቤት ( ኪችን ) ተቀምጣ በወጣትነቷ ያላደረገችዉን እያሰበች የምትፀፀት ... ብቻ ብዙ አይነት ልትሆኝ እንደምትችይ ከወዲሁ ላስታዉስሽ እፈልጋለሁ! ስለዚህም ወጣቷ ሆይ እልሻለሁ ለማግባት ከመወሰንሽ በፊት ምን ያክል በወሲብ ዘና እንደሚያደርግሽ አረጋግጭ ከነጠረቀኝ በኋላ ትቶኝ ቢሂደስ የሚለዉን እርግፍ አድርገሽ እርሽዉ በምላሹ አንቺም ካልተሰማማሽ ከዚህ ልትሄድልኝ ይገባል በይዉ ዘና ካላደረገሽ ምናባቱን ያደርግልሻልና! ምናልባትም በዙሪያሽ የማለልሽለት ወንድ ካለ እና የምትወጂዉ ከሆነ እንዲነጭሽ ፍቀጅለት ( ግን ጆከር እንዳያሲዝሽ ተጠነቀቂ ) ሰሞኑን አንድ ትሬንድ እየተመለከትኩ ነበር በግልፅ ለመናገር ያክል በቀልድ መስሎ የቀረብ ግን ከጀርባ የሆነ ዓይነት አመፅ የያዘ ይመስላል በታሪክ ዉስጥ እንዲህ በቀልድ እና በምፀት የቀረቡ ሀሳቦች ናቸዉ ወደ እዉነተኛ አብዮት የተቀየሩት በግሌ ትሬንዱ ይቀጥል ብያለሁ! እናም ወጣቷ ሆይ የሚያስደስትሽን ነገር ለማድረግ የማነንም ፈቃድ አትብቂ ወግ ባህል አስጠባቂ ነኝ የሚለዉንም እርሽዉ ምክንያቱም የሀገሪቱ ባህል ከተሸረሸረ ሰንበትበት ብሏል የምዕራቡን ዓለም ባህል በሯን በርግዳ ካስገባችም ቆይታለች ስለዚህ ባህል ወግ አስጠባቂ ነኝ የሚሉ አጫፋሪዎችን እርሻቸዉ ። የሃይማኖት ሰባኪዎችን ቀሳዉስቶችን ፣ ኡስታዞችን ፣ ፓስተሮችን እርሻቸዉ እነሱ ህይወትን በምላዕት እንዳትኖሪ የሚያደርጉ እንቅፋቶች ናቸዉ ። ሀገሪቱም እንደምታያት ሺት የሆነች ሀገር ሁናለች ። ስለዚህም ወጣቷ ሆይ እኔም እልሻለሁ ሃይማኖት ፣ ባህል ፣ ብሔር ፣ ነገድ ሳይገድብሽ የሚያስደስትሽን ነገር እያደረግሽ ኑሪ ከዛም ያ አስቀያሚነት አሮጊትነት ቢመጣ አንዳች ፀፀትም ሆነ ድንጋጤ አይሰማሽም!

Открыть в Telegram
Просмотры2 030−23%к среднему
Пересылки—
Реакции38
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
62 ч1 960
67 ч2 030
  1. Всего сейчас2 030
#4204Фото

Переслано из HATETA Perspective

Без текста

Открыть в Telegram
Просмотры1 870−29%к среднему
Пересылки—
Реакции8
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
62 ч1 830
67 ч1 870
  1. Всего сейчас1 870
#4203Фото
Просмотры2 780+5%к среднему
Пересылки—
Реакции55
Комментарии—
#4202Фото

በዛሬዉ እለት ከ 13 አመታት ጥበቃ ቡሃላ GTA 6 ተለቋል...ያዉ ቢያንስ አብዛኞቻችን የቀድሞዉን versionዎቹን GTA vice city እየተጫወትን ነዉ ያደግነዉ እና ትዉስታዉ አይረሳም... እናም አሁን ላይ 13 አመት የተለፋበትን እና በቢሊየን ዶላሮች መሃለ ነዋይ የፈሰሰበትን ጌም review እያየዉ ነበር እና ይበል የሚያሰኝ Real life simulation ያለዉ አሪፍ ጌም ሆኗል። እና ይህ የቴክኖሎጂ ዝማኔ በዚዉ ከቀጠለ እና የሰዉን ልጅ consciousness ወደ Virtual Reality map ወይም upload ማድረግ ከተቻለ (ያዉ አሁን ላይ በ VR & AR ማለትም  vritual Reality እና Augmented Reality የስሜት ህዋሶቻችንን በመጠቀም ገሀዱ አለም ላይ እየተፈጠረ ያልሆነን ነገር እየተፈጠረ እንዳለ እንዲሰማን ማረግ ተችሏል) እና ህይወቶቻችንን በዛዉ simulated የሆነ Reality ዉስጥ መግፋት እድል ከኖረ ያንን ለማድረግ ፍቃደኛ ናቹ ወይስ አሁን እየኖራቹ ያላቹትን የገሀዱ አለም experience ትመርጣላችሁ ?😁 I know ኢትዮጵያ ዉስጥ ካለዉ ኑሮ ምንም እንመርጣለን የሚያስብል situation ላይ ሀገሪቷ እንዳለች ግን ይሄን ጠለቅ ብላቹ እንድታስቡበት እፈልጋለዉ ምክንያቱም ብዙ ማገናዘብ የሚጠይቅ ፍልስፍናዊ ጥያቄ ስለሆነ። Virtual world ዉስጥ ብትገቡ እና ስሜቱ ከእውነተኛው ልዩነት ከሌለው፣ እዉነተኛዉ "እውነተኛ" መሆኑ ለምን ይጠቅማል? Virtual worldዉን እኛዉ ስለምንሰራዉ ተድላ እና ደስታ የምናገኝበት ክፋቶችም የሌሉበት ልናረገዉ እንችላለን እና ህመም ብሎም ችግር ህይወትን ትርጉም የሚሰጡ ነገር ናቸዉን? ሁሉም ነገር በፈለግነዉ መንገድ የሚሆንበት ዓለም ውስጥ ድል  ትርጉም ይኖረዋልን ? ኑሮን ለመቀጠልስ ምክንያት ይኖረናል ?

Открыть в Telegram
Просмотры2 960+12%к среднему
Пересылки—
Реакции25
Комментарии—
#4201Текст

በመቀጠል ሶቅራጠስ በዚህ ዓይነት ዘዴ በምንጠቀምባቸው ንግግሮች ይህን ጉዳይ በትክክል መቼም አናገኘውም ብዬ አምናለሁ ፤ ወደዚያ የሚያደርስ ሌላ ረዘም ያለና ብዙ ጊዜ የሚፈጅ መንገድ አለ። ግን ምናልባት ከቀደምት ንግግሮቻችንና ምርመራዎቻችን ደረጃ ጋር ልንደርስ እንችላለን። ይላል። በመቀጠል ሶቅራጥስ እነዛ የከተማ ባሕሪያት እራሱ ከሰዉ ልጆች እንደቀዱ ያስረዳል... ከተሞች ስሜታዊነትን (spiritedness) ከግለሰቦች ባሕርይ ያገኙት ነው።እንደ ትራክያውያን፣እስኩቴሶችና ሰሜን የሚኖሩ ሌሎች ሕዝቦች የሚያሳዩት ሲሆን፤ እውቀትን መውደድ ከእኛ (ግሪክ) አካባቢ ጋር የተያያዘ ነው፤ ገንዘብን መውደድ ደሞ ከፊንቄያውያንና ከግብፃውያን ጋር። በመቀጠል አንድ መርሕን ያስተዋዉቃል እሱም አንድ ነገር በአንድ ጊዜ፣ በአንድ ረገድ፣ በአንድ ነገር ላይ ተቃራኒ ነገሮችን ሊያደርግ ወይም ሊቀበል አይችልም የሚል ተቃርኖን የሚያስተዳድር መርሕ ነዉ። ስለዚህ ይህ በነብስ ውስጥ ከተከሰተ አንድ ነገር ሳይሆን ብዙ እንደሆኑ እናውቃለን። ለምሳሌ.... አንድ ሰው ቆሞ ራሱንና እጁን ቢያንቀሳቅስ "ቆሟል እና ይንቀሳቀሳል" አንልም፤ በአንድ ረገድ ቆሟል፣ በሌላ ይንቀሳቀሳል።በሌላ በኩልም ለሚሽከረከር ኮርኪስ "ቆሟል እና ይንቀሳቀሳል" ብለን አንናገርም፤ ዘንጉ ቋሚ ነው (ቆሟል)፣ ዙሪያው ይሽከረከራል (ይንቀሳቀሳል) ስለዚህ በልዩ ልዩ ረገዶች ይገለፃል። ሶቅራጠስ ሌሎች ተቃውሞዎችን አንድ በአንድ ለመመለስ ከመጓዝ ይልቅ ይህ መርሕ ትክክል እንደሆነ በቅድመ ግምት በመቀበል ይነሳል፤ ከተሳሳተ ከዚህ የተገኙት ድምዳሜዎች ሁሉ ይፈርሳሉ። መስማማት (assent) እና አለመስማማት፣ መፈለግና አለመፈለግ፣ መውሰድና መተዉ እነዚህ ተቃራኒ ጥንዶች ናቸው። ምኞት (ጥም፣ረሃብ) በመፈለግ፣ አለመፈለግ በአለመመኘት ክፍል ውስጥ ይገባሉ። ጥም ራሱ ለመጠጥ ብቻ ነው፤ለሞቀ ወይም ለቀዘቀዘ፣ ለብዙ ወይም ለጥቂት መጠጥ ሳይሆን፤ እነዚህ ከጥሙ ጋር በተጨመሩ ነገሮች ይመጣሉ። ረሃብም ለምግብ ብቻ ነው። ስለዚህ "ሰዎች የሚፈልጉት ጥሩ መጠጥ ነው" የሚለው ተቃውሞ ተቀባይነት የለውም። ሌላዉ ደሞ ይበልጥ ከዚህ ጋር፣ ሁለት እጥፍ ከግማሽ ጋር፣ ከባድ ከቀላል ጋር፤ እውቀት "ራሱ" ለሚማር ነገር "ራሱ"፣ ልዩ እውቀት (ለምሳሌ የሕክምና እውቀት) ለልዩ ነገር (ጤና/በሽታ)። በተመሳሳይ ልዩ ጥም ለልዩ መጠጥ፣ ጥም ራሱ ለመጠጥ ራሱ በሚል ይሰራል። አንድ ሰው ጥሙ እያለበት መጠጣት ባይፈልግ (ብዙ ሰዎች ይህንን ያደርጋሉ) ፤ በነብሱ ውስጥ አንዱ እንዲጠጣ የሚገፋና ሌላ የሚከለክል ነገር አለ። ይህ ሁለተኛው የሚመነጨው ከምክንያታዊ ስሌት፣ የመጀመሪያው ደግሞ ከስሜትና ከበሽታ ነው። ለምሳሌ ቀስተኛ አንድ እጅ ቀስቱን ይገፋል፣ ሌላው ደሞ ይስባል ሁለት የተለያዩ ክፍሎች ናቸዉና። ስለዚህ በነብስ ዉስጥ ሁለት የቱለያዩ ክፍሎች አሉ እነሱም... አመክኖአዊ ክፍል (በእሱ ነብስ ታሰላስላለች) እና ምኞታዊ ክፍል (በእሱ ትራባለች፣ትጠማለች፣ በሌሎች ምኞቶች ትነሣሳለች) ይህም ከአንዳንድ የመሞላት መንገዶችና ደስታዎች ጋር ወዳጅ የሆነ፣ ከምክንያት የራቀ ክፍል ነዉ። ሶቅራጠስ በመቀጠል ቁጣን የምንሰማበት ስሜታዊ ክፍል ከሁለቱ አንዱ ነው ወይስ ሦስተኛ ? በማለት ግላውኮንን ይጠይቀዋል ፤ ምናልባት ከምኞታዊዉ ጋር አንድ ነው ይላል። ግላዉኮን። ሊዮንቲዮስ ከፔሬየስ ወደ አቴንስ ሲመለስ በሰሜን ግንብ ውጭ የመንግሥት ገዳይ አጠገብ ሬሳዎች ተኝተው አየ። ሬሳዎቹን ለማየት ምኞት ነበረው፣ ግን ተጸየፈ፣ ፊቱን አዞረ፤ ለተወሰነ ጊዜ ታግሎ ዐይኑን በእጁ ሸፈነ፤ በመጨረሻ በምኞቱ ተሸንፎ ዐይኑን በሰፊው ከፍቶ ወደ ሬሳዎቹ ሮጠ "እናንተ ክፉ ጭራቆች፣ ከውብ ዕይታው ጥገቡ!"  እያለ ለራሱ ጮኸ። ይህም ቁጣ አንዳንድ ጊዜ በምኞቶች ላይ እንደ አንድ ነገር በሌላ ላይ ጦርነት ያደርጋል። ምኞት አንድን ሰው ከምክንያታዊ ስሌቱ ተቃራኒ ሲያስገድደው ራሱን ይወቅሳል፣ ያስገደደው ክፍል ላይ ይቆጣል፤ ስሜቱ(spirit) የምክንያት አጋር ይሆናል። ስሜት ከምኞት ጋር ተባብሮ ምክንያት ያልፈቀደውን ሲያደርግ ማንም አይቶ አያውቅም።  ሰው ፍትሐዊ ቅጣት ሲደርስበት (ረሃብ፣ቅዝቃዜ) ለመቆጣት ያመነታል፤ ኢፍትሐዊ ሲደረግበት ግን ስሜቱ ይፈላል፣ ከፍትሐዊው ወገን ጋር ይዋጋል፤ ሥቃይ ቢደርስም ይጸናል፤ ዓላማውን እስኪያሳካ ወይም እስኪሞት ወይም እረኛ እንደሚጠራው ውሻ በምክንያት እስከሚጠራና እስከሚለዝብ ድረስ አያቆምም። ግላውኮን "አጋዥዎቻችንን እንደ ታዛዥ እረኛ ውሾች ያደረግናቸው ለዚህ ነው" ይላል። ከአመክኖም የተለየ ነው። ትንንሽ ልጆች ከተወለዱ ጀምሮ በስሜት የተሞሉ ናቸው፤ ምክንያታዊ ስሌት ግን አንዳንዶች ፈጽሞ ያላገኙት፣ ብዙዎቹ ዘግይተው የሚያገኙት ነው። እንስሳትም ይህን ያሳያሉ። ሆሜር "ደረቱን መታ ልቡን እንዲህ ተናገረው" ሲል ስለ ጥሩና መጥፎ ያሰላውን ክፍል በምክንያት የሌለው ቁጣ ላይ ሲገስጽ ያሳያል። በዚህም የተነሳ ነብስ ሦስት ክፍሎች አላት። ልክ ከተማዋ ሦስት ክፍሎች (ገንዘብ ሠሪ፣ አጋዥ፣ አማካሪ/ገዥ) እንዳሏት፣ ነብስም ሦስት ክፍሎች አሏት። ምኞታዊ (appetitive)፣ ስሜታዊ (spirited)፣ አመክኖአዊ (rationally calculating)። ስሜታዊው ክፍል የአመክኖ ተፈጥሯዊ አጋዥ ነው ፤ በመጥፎ አስተዳደግ ካልተበላሸ በቀር። ስለዚህ ይህን ካወቅን ዘንድ በከተማዋ ያሉትን አራቱን በጎነቶች በነብስ ዉስጥ ለማየት እንሞክር... የመጀመሪያዉ ጥበብ ሲሆን፤ ሰው ጥበበኛ የሚባለው በትንሹ ገዥ ክፍል (አመክኖ) ምክንያት ነው። ይህ ክፍል ለእያንዳንዱ ክፍልና ለሦስቱ አንድነት የሚጠቅመውን ዕውቀት ይይዛል። ሁለተኛዉ ደሞ ድፍረት ሲሆን፤ ሰው ደፋር የሚባለው በስሜታዊው ክፍል ምክንያት ነው። ይህ ክፍል የአመክኖን ውሳኔ (ምን ማስፈራት እንዳለበት) በሥቃይና በደስታ ሳይለቅ ሲጠብቅ ነዉ። ሶሰተኛዉ ደሞ ራስን መግዛት ነዉ፤ ሰዉ ራሱን ገዝቷል የሚባለዉ ገዥውም ሁለቱ ተገዥዎችም የአመክኖዉ ክፍል መግዛት እንዳለበት ሲያምኑና በእሱ ላይ ሳያምፁ ሲቀር ነዉ። አራተኛዉ እና ዋነኛዉ ፍትሕ ደሞ እያንዳንዱ ክፍል የራሱን ሥራ በመግዛትና በመገዛት ረገድ ሲሠራ ነዉ። ሁለቱ ክፍሎች (አመክኖና ስሜት) በሙዚቃ እና በአካል ሥልጠና ድብልቅ ይስማማሉ፤ ሙዚቃ አመክኖን በጥሩ ቃላትና ትምህርት ያጠነክራል፤ ስሜትን በዜማና ምት ያለዝባል፣ ያረጋጋል። እነዚህ ሁለት ክፍሎች በእውነት ተምረው በነብስ ውስጥ ከሁሉ ትልቅና በተፈጥሮ ገንዘብን በጣም የሚመኘውን ምኞታዊ ክፍል ይቆጣጠራሉ። እንዳይሞላና እንዳይበረታ፣ ሥራውን ትቶ የማይገባውን ክፍሎች እንዳይገዛና የሰውዬውን ሕይወት ሁሉ እንዳይገለብጥም ያረጋሉ። ሁለቱም ደግሞ ነብስንና አካልን ከውጭ ጠላቶች ይጠብቃሉ  አንዱ በማሰላሰል፣ሌላው በመዋጋት። ሶቅራጠስ ይህንን ትርጓሜ በተራ ፈተናዎች ይለካዋል፤ በተፈጥሮና በትምህርት ከከተማችን ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሰው በአደራ የተቀበለውን ወርቅ ወይም ብር ይመዘብራል? የቤተ መቅደስ ዝርፊያ፣ ስርቆት፣ በግል ሕይወት ወዳጆችን ወይም በሕዝብ ሕይወት ከተማን መክዳት ያደርጋል? ቃል ኪዳኖችን ይጥሳል? ምንዝርና፣ ወላጆችን አለማክበርና አማልክትን መተው ከሌሎች ዓይነት ሰዎች ይልቅ እሱን ይገልጻሉ? ግላውኮንም "በፍጹም አይሆንም" ይላል። ምክንያቱም እያንዳንዱ ክፍል በመግዛትና በመገዛት ረገድ የራሱን ሥራ ስለሠራ። ፍትሕ በእውነት "የራስን ሥራ ከውጭ መሥራት" አይደለም ፤ ይህ ፍትሕ የሚመስል ምስል ብቻ ነው (ጫማ ሠሪ ጫማ ሠሪ፣ አናጢ አናጢ) ነዉ። ፍትሕ ውስጣዊ ነው፤ ሰውዬው በነብሱ ውስጥ ያሉት ሦስት ክፍሎች እያንዳንዳቸው የሌላውን ሥራ እንዲሠሩ አይፈቅድም፣ እርስ በርሳቸው እንዲገቡ አይፈቅድም። የራሱን የሆነውን በደንብ ያስተዳድራል፣ ራሱን ይገዛል፣ ራሱን በሥርዓት ያደርጋል፣ የራሱ ወዳጅ ይሆናል፣ ሦስቱን ክፍሎች ልክ እንደ ኦክታቭ ሦስት ዋና ድምፆች (ዝቅተኛ፣ ከፍተኛ፣ መካከለኛ) ያስማማል። ከብዙ ወደ አንድ፣ ራሱን የሚገዛና የተስማማ ይሆናል። ከዚያ ብቻ ወደ ተግባር ይዞራል ፤ ሀብት ማግኘት፣ የአካል እንክብካቤ፣ ፖለቲካ ወይም የግል ውሎች ላይ ይገለጣል። ማንኛውንም ይህንን ውስጣዊ ስምምነት የሚያቆይና የሚያግዝ ድርጊት ፍትሐዊና ውብ ይለዋል፤ ይህንን የሚቆጣጠረው እውቀት ጥበብ፤ ስምምነቱን የሚያፈርስ ድርጊት ኢፍትሐዊ፣ ይህንን የሚቆጣጠረው እምነት ደሞ ድንቁርና ተብሎ ይፈረጃል ። ሶቅራጠስ አሁን " ፍትሐዊውን ሰው፣ ፍትሐዊውን ከተማና ፍትሕን በእነሱ ውስጥ ምን እንደሆነ አግኝተናል ብንል ሙሉ ውሸት አንናገርም " ይላል፤ ግላውኮንም ይስማማል። ሶቅራጠስም አክሎ ይህ ከመጽሐፍ 2 መጀመሪያ ከተማ ሲመሠረት የነበረው "ሕልም" (ምናልባት በአምላክ እርዳታ የፍትሕን ምንጭና ንድፍ ማግኘት) ሙሉ በሙሉ እንደተፈጸመ ይናገራል። በመቀጠልም ኢፍትሐዊነትን ሲያብራራ እንዲህ ይላል፤ ኢፍትሐዊነት በሦስቱ ክፍሎች መካከል የሚደረግ ሁከት ነዉ፤ እርስ በርስ መግባትና የሌላውን ሥራ መሥራት፤ የነብስ አንድ ክፍል በጠቅላላው ላይ ማመፅ፣ በተፈጥሮው ለገዥው ባሪያ መሆን የሚገባው ሲሆን መግዛት መፈለግ...የመሳሰሉት።ይህ ሁከትና መንከራተት የኢፍትሐዊነት፣ልቅነት፣ፈሪነት፣ድንቁርና፣በአጠቃላይ የሁሉም መጥፎነት ምንጭ ነዉ። ፍትሐዊ ድርጊቶች ፍትሕን፣ ኢፍትሐዊ ድርጊቶች ኢፍትሐዊነትን ያመነጫሉ። ልክ ጤናማ ድርጊቶች ጤናን፣ ጤና-የለሽ ድርጊቶች በሽታን እንደሚያመነጩ ሁሉ። ጤና ማለት የአካል ክፍሎች በተፈጥሯዊ የመግዛትና የመገዛት ግንኙነት ሲኖሩ፤ በሽታ ከተፈጥሮ ተቃራኒ ሲሆን ነዉ። እንዲሁም ፍትሕ የነብስ ክፍሎች በተፈጥሯዊ መግዛትና የመገዛት ግንኙነት፤ ኢፍትሐዊነት ከተፈጥሮ ተቃራኒ ሲሆን ነዉ። ስለዚህ በጎነት የነብስ ዓይነት ጤና፣ ውብና ጥሩ ሁኔታ ነው፤ መጥፎነት ደግሞ አሳፋሪ በሽታና ድካም ነዉ። ሶቅራጠስ የቀረውን ጥያቄ ያቀርባል... ፍትሐዊ ድርጊት፣ ውብ ልምዶች ፍትሐዊ መሆናችን ቢታወቅም ባይታወቅም ከኢፍትሐዊነት (ቅጣት ሳይከፈልና በቅጣት ሳይሻሻሉ) ይበልጥ ይጠቅማሉን? ግላውኮን ጥያቄው አሁን አስቂኝ ሆኖብኛል። ሲል ይመልሳል። የአካል ተፈጥሯዊ አወቃቀር ከተበላሸ ሕይወት ዋጋ አይኖረውም። ሁሉም፤ ምግብና መጠጥ፣ ሀብትና ሥልጣን ቢኖርም። ታዲያ የምንኖርበት ነገር (ነብስ) ተፈጥሯዊ አወቃቀሯ ከተበላሸና ከተናወጠ ከመጥፎነትና ከኢፍትሐዊነት ነፃ የሚያደርገንንና ፍትሕንና በጎነትን የሚያስገኘንን ብቻ ካልሆነ ሁሉን ማድረግ ቢቻል እንዴት ዋጋ ይኖረዋል? ሶቅራጠስም በዚህ ይስማማል፣ ነገር ግን አሁን ከደረሱበት ከፍታ ላይ ነገሮች በግልጽ እንደሚታዩ በመጠቆም ማቆም እንደሌለባቸው ይናገራል። ሶቅራጠስ ከዚህ ከፍታ እንደሚታየው አንድ ዓይነት በጎነት እና ብዙ ዓይነት መጥፎነቶች እንዳሉ ይናገራል፤አራቱ ብቻ የሚጠቀሱ። ስለዚህ አምስት ዓይነት ሕገ መንግሥቶች፣ አምስት ዓይነት ነብሳት አሉ። የመጀመሪያው ዓይነት እኛ የገለጽነው ነው፤ አንድ ልዩ ሰው ከገዥዎች መካከል ቢወጣ ንጉሣዊ አገዛዝ (kingship)፤ ከአንድ በላይ ከሆኑ መኳንንታዊ አገዛዝ (aristocracy) ይባላል። ሁለቱም እንደተገለጸው ከተማሩ የከተማዋን ጠቃሚ ሕጎች አይለውጡም። ይቀጥላል... ምንጭ፤ ከላይ ከተያያዘዉ መፅሀፍ(Republic) ከገፅ 180 እስከ ገፅ 224

Открыть в Telegram
Просмотры3 160+20%к среднему
Пересылки—
Реакции16
Комментарии—
#4200Текст

አዴይማንቶስ ጣልቃ ገብቶ ሶቅራጠስን እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል...ሰዎች ጠባቂዎችህን ደስተኛ አላደረግሃቸውም ብለው ቢከሱህ? እንዴት ትከላከላለህ? ከተማዋ በእውነት የእነሱም ናት፤ ግን ከእሷ ምንም ጥቅም አያገኙም። ሌሎች መሬት ያገኛሉ፣ ትላልቅ ቤቶች ይሠራሉ፣ ዕቃ ይገዛሉ፣ የግል መሥዋዕት ያቀርባሉ፣ እንግዳ ያስተናግዳሉ፣ ወርቅና ብር ይይዛሉ ብሎም ደስተኛ ለመሆን የሚያስፈልገው ሁሉ አላቸዉ። እነዚህ ግን እንደ ዜጋ ሳይሆን እንደተቀጠሩ አጋዥ ወታደሮች ሆነው ተቀምጠዋል። ሶቅራጠስ እዚህ ላይ ይጨምርበታል ...ሥራቸው ለምግብ ብቻ ነው፣ ከዚያ በላይ ደመወዝ የላቸውም፤ ስለዚህ ለጉዞ፣ ለፍቅረኛ ስጦታ ወይም ደስተኞች እንደሚያደርጉት ለማንኛውም ወጪ ገንዘብ አይኖራቸውም። ይህንንም ወደ ክሶቹ ዝርዝር ላይ እንጨምር። በመቀጠል ሶቅራጠስ ለጥያቄዉ እንዲህ ሲል ይመልሳል... ዓላማው ሙሉ ከተማዋን ደስተኛ ማረግ ነው። ከተማዋን የምንመሠርተው ከተማዋ በአጠቃላይ ደስተኛ እንድትሆን እንጂ አንድን ክፍል በተለየ ሁኔታ ለማስደሰት አይደለም። ፍትሕ እራሷን በደንብ የምታስተዳድር ከተማ ውስጥ እንደሚገኝ፣ኢፍትሐዊነትም ደግሞ በከፋ አስተዳደር ከተማ ውስጥ እንደሚገኝ ስላሰብንም ነዉ ይሄን ያረግነዉ። ሁለቱን ከተሞች በማወዳደር ጥያቄያችንን ለመፍታትም ይረዳናል። ሐውልት ስንቀባ አንድ ሰው "ዐይኖች የሐውልቱ ከሁሉ ውብ ክፍል ናቸው፣ ለምን በሐምራዊ ሳይሆን በጥቁር ቀባሃቸው?" ቢለን፤ የምንምልሰዉ...ዐይኖቹ ዐይን መሆናቸውን እስኪያቆሙ ድረስ ማስዋብ አያስፈልግም፤ እያንዳንዱን ክፍል በተገቢው ቀለም ቀብተን መላው ሐውልት ውብ እንዲሆን ነው ዓላማችን። ስለዚህ ጠባቂዎቻችንን ጠባቂዎች መሆን እስኪያቆሙ የሚያደርግ ደስታ አንሰጣቸውም። ገበሬዎችን ሐምራዊ ልብስና የወርቅ ጌጥ አልብሰን "ሲፈልጉ ይረሱ" ማለት፣ ሸክላ ሠሪዎችን በእሳት አጠገብ ተደላድለው እየጠጡና እየበሉ "ሲፈልጉ ሸክላ ይሥሩ" ማለት እንችላለን። ግን ይህ ከሆነ ገበሬ ገበሬ፣ ሸክላ ሠሪ ሸክላ ሠሪ አይሆንም፤ ከተማን የሚያቋቁሙ ክፍሎች ሁሉ ዓይነታቸውን ይለቃሉ።ጫማ ሠሪዎች ክፉና አስመሳይ ቢሆኑ ከተማዋን ብዙ አይጎዱም። ጠባቂዎች ግን ጠባቂ መስለው የማይሆኑ ከሆነ ከተማዋን ፈጽመው ያጠፋሉ፤ ከተማዋን በደንብ ሊያስተዳድሩና ደስተኛ ሊያደርጉ የሚችሉትም እነሱ ብቻ ናቸው። ስለዚህ ጠባቂዎችና አጋዥዎች በራሳቸው ሥራ ምርጥ ባለሙያዎች እንዲሆኑ እናስገድዳለን ወይም እናሳምናለን፤ ከዚያ ከተማዋ በደንብ እያደገችና እየተተዳደረች ስትሄድ እያንዳንዱ ክፍል ተፈጥሮ የሰጠውን የደስታ ድርሻ ያገኛል። በዚህም ሶቅራጠስ ሀብት እና ድህነት ወደዛች ከተማ መግባት የለበትም ይላል ፤ ጠባቂዎች ሀብትንና ድህነትን ወደ ከተማ ሳይታወቅ እንዳይገቡ በሁሉም መንገድ መከላከል አለባቸው። ሀብት ቅንጦትን፣ ስንፍናንና አብዮትን፤ ድህነት ደግሞ ርካሽነትን፣ መጥፎ ሥራንና አብዮትን ያመጣልና። አዴይማንቶስም እዚህ ጋር ጥያቄ ያነሳል... ከተማችን ሀብት ከሌላት እንዴት ከታላቅና ሀብታም ከተማ ጋር ትዋጋለች? ሶቅራጠስ ለዚህ  በምሳሌዎች ይመልሳል... በጣም በደንብ የሠለጠነ አንድ ቦክሰኛ ሁለት ሀብታም ወፍራም ሰዎችን በቀላሉ ሊዋጋ ይችላል። ስለዚህ የእኛ አትሌቶች ሁለት ወይም ሦስት እጥፍ ቁጥር ያለውን ሠራዊት ይዋጋሉ። ሌላዉ ደሞ ወደ ሌላ ከተማ ልዑክ ልከን "እኛ ወርቅና ብር አንጠቀምም፤ በመለኮታዊ ሕግ ተከልክሏል፤ ለእናንተ አልተከለከለም። ከእኛ ጋር ተዋጉና የጠላታችንን ንብረት ውሰዱ" ብንል፤ ማንም ጠንካራ ቀጭን ውሾችን ከመዋጋት ይልቅ ከውሾች ጋር ሆኖ ወፍራምና ለስላሳ በጎችን መዋጋት ይመርጣል። አዴይማንቶስም አክሎ... ግን የሌሎች ከተሞች ሀብት ሁሉ በአንድ ከተማ ቢሰበሰብ የእኛን ሀብት አልባ ከተማ አያሰጋም? ሲል ይጠይቃል ሶቅራጠስም ከእኛ ከተማ በቀር ሌላ ማንኛውንም "ከተማ" ብሎ መጥራት የዋህነት ነው። ሌሎቹ እያንዳንዳቸው ብዙ ከተሞች ናቸው፤ቢያንስ ሁለት፣ የድሃው ከተማና የሀብታሙ ከተማ እነሱም እርስ በርስ የሚዋጉ። በእያንዳንዳቸው ውስጥ ደግሞ ሌሎች ብዙ ከተሞች አሉ። ስለዚህ አንዱን ሀብትና ሥልጣን ለሌላው ብትሰጥ ብዙ አጋሮችንና ጥቂት ጠላቶችን ታገኛለህ። ብሎ ይመልሳል። በመቀጠል ከተማዋ አንድ ከተማ ሆና ለመቆየት እስከፈለገች ድረስ ማደግ ትችላለች፤ ከዚያ በላይ አይቻልም። ጠባቂዎች ከተማዋ "በመጠን ትንሽ፣ በዝና ታላቅ" እንዳትሆን፣ ይልቁንም በመጠን በቂና በቁጥር አንድ እንድትሆን ሁሉንም ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። ከዛ ከዚህ በፊት የተናገረውን ደንብ ይደገመዋል ማለትም የጠባቂ ልጅ ዝቅተኛ ተፈጥሮ ካለው ወደ ሌሎች ዜጎች ይላካል፣ የሌሎች ዜጎች ልጅ ምርጥ ተፈጥሮ ካለው ወደ ጠባቂዎች ይገባል። ዓላማው እያንዳንዱ ዜጋ በተፈጥሮው ወደሚስማማው አንድ ሥራ እንዲመደብ፣ እያንዳንዱ ብዙ ሳይሆን አንድ ሆኖ ከተማዋም አንድ እንድትሆን ነው። ሶቅራጠስ እነዚህ ትእዛዞች ቀላልና ጥቂት እንደሆኑ ይናገራል፤ ጠባቂዎች "አንድ ታላቅ ነገር" (ወይም ታላቅ ሳይሆን በቂ) ከጠበቁ ማለትም ትምህርታቸውና አስተዳደጋቸው እንደዛ ከሆነ ፤ ይህ ጥሩዉ ትምህርትም መካከለኛ ሰዎችን ከፈጠረ እነዚህ ሰዎች ሌላውን ሁሉ የሴቶች ባለቤትነት፣ ጋብቻና የልጆች መውለድ፣ ከ"ወዳጆቻቸዉ ጋር ሁሉን በጋራ ይጋራሉ" ከሚለው ጥንታዊ ምሳሌ ጋር በተቻቻለ መጠን እንዲሄድ ራሳቸውን ያስማማሉ። ሌላዉ ደሞ ሕገ መንግሥቱ ጥሩ ጅምር ካገኘ በክብ ያድጋል ጥሩ ትምህርትም ጥሩ ተፈጥሮዎችን ያፈራል፤ ጥሩ ተፈጥሮዎች ደግሞ ትምህርቱን በመቀበል ከቀደሙት የተሻሉ ይሆናሉ፣ ልክ እንደ ሌሎች እንስሳት ልጆች። በሙዚቃም ሆነ በአካል ሥልጠና ከተቋቋመው ሥርዓት ውጭ ምንም አዲስ ነገር መግባት የለበትም። "ሰዎች ከአፍ አዲስ የሚፈልቀውን ዘፈን ይወዳሉ" የሚለውን ጥቅስ (ከኦዲሴይ) ባለቅኔው አዲስ የዘፈን መንገድ ማለቱ እንደሆነ ልንተረጉም አይገባም።  ምክንያቱም የሙዚቃ ሥልጠና ዘዴ ከተቀየረ ታላላቅ የፖለቲካ ሕጎች ሳይቀየሩ አይቀሩምና። የጠባቂዎች ጠባቂ ቤት በሙዚቃ ትምህርት ላይ መሠራት አለበት፤ ምክንያቱም እንዲህ ያለ ሕግ አልባነት በቀላሉ ሳይታወቅ ይገባል  እንደ ጨዋታ ስለሚታይ ጉዳት የለውም ይባላል። አዴይማንቶስም እዚህ ላይ ያክልበታል...ጉዳቱ ቀስ በቀስና በዝምታ ወደ ልማድና ተግባር ይለወጣል፤ ከዚያ በታላቅ ኃይል ወደ የግል ውሎች፣ ከዚያም በከፍተኛ ንቀት ወደ ሕጎችና ሕገ መንግሥት፣ በመጨረሻ የሕዝብንና የግል ነገርን ሁሉ ይገለብጣል። ስለዚህ ልጆች ከመጀመሪያዉኑ ሕጉን አክባሪ ጨዋታዎች ብቻ ማድረግ አለባቸው፤ ጨዋታቸው ሕግ አልባ ከሆነ ጥሩና ሕግ አክባሪ ሰዎች ሆነው ሊያድጉ አይችሉም። በመቀጠል ሶቅራጠስ ልማዳዊ ሥነ ስርዓቶችን ማለትም በሽማግሌዎች ፊት ዝም ማለት፣ መቀመጫ መልቀቅ፣ የወላጅ እንክብካቤ፣ የፀጉር አሠራር፣ ልብስ፣ ጫማ፣ የአካል ገጽታ እና የመሳሰሉትን በሕግ ማዘዝ የዋህነት ነው፤ በቃልም ሆነ በጽሑፍ ትእዛዝ ሊሰፍሩ አይገባም፤ አይቆዩምም። ይላል። የትምህርት ጅምር ተከታዩን ይወስናል ተመሳሳይም ተመሳሳይን ይስባል። ነገር ግን መደበኛ ስርዓቶች ማለትም የገበያ ውሎች፣ ስድብ፣ጉዳት፣ ክሶች፣ ዳኞች  ማቋቋም፣ ግብር፣ ወደብ ደንብ እና የመሳሰሉትን ጥሩና መልካም ሰዎች በራሳቸው በቀላሉ ያገኛሉ፤ አምላክ ቀደም ብለን የገለጽናቸውን ሕጎች ሳይጓደሉ ከጠበቃቸው እኛ ልናዛቸዉ አይገባም። በመቀጠል ሶቅራጠስ ሕጎቹ መጠበቅ ካልቻሉ ምን እንደሚፈጠር በምሳሌ ያመሰጥራል... ሕጎቹ ካልተጠበቁ ሰዎች ሕይወታቸውን ሕጎችን በመጻፍና በማሻሻል ያሳልፋሉ ፤ ልክ ልቅ የሆኑ ታማሚዎች መጥፎ አኗኗራቸውን ሳይተዉ ሁልጊዜ አዲስ መድኃኒት እንደሚፈልጉ። እውነቱን የሚነግራቸውን (ስካርን፣ ሆዳምነትን፣ ፍትወትንና ስንፍናን ካልተዉ ምንም መድኃኒት፣ ማቃጠል ወይም ቀዶ ሕክምና፣ ዛቻ ወይም ማታለያ እንደማይረዳቸው) እንደ ከፉ ጠላታቸው ይቆጥራሉ። እንዲሁም በመጥፎ የሚተዳደሩ ከተሞች ሕገ መንግሥታቸውን የሚቀይርን ሰው በሞት ይቀጣሉ፤ የሚያባብላቸውንና ፍላጎታቸውን የሚያስቀድመውን ግን እንደ ጥበበኛ ያከብራሉ። እነዚህን ሕጎች የሚያሻሽሉ ፖለቲከኞች "የሃይድራን ራስ እየቆረጡ" ነው (የሃይድራ አንድ ራስ ቢቆረጥ ሁለት ሌሎች ይበቅላሉ)። ይህኔ አዴይማንቶስ "ታዲያ ለሕግ አውጪነት ምን ይቀራል?" ሲል ሶቅራጠስ "ለእኛ ምንም፤ ለዴልፊ አፖሎ ግን ከሁሉ ታላቅ፣ ውብና ቀዳሚ ሕግ አወጣጥ ይቀራል" ይላል። የቤተ መቅደሶች መቋቋም፣ ለአማልክት፣ ለዳይሞኖችና ለጀግኖች መሥዋዕት፣ የሙታን ቀብርና የሙታንን ሞገስ የሚያስገኙ አገልግሎቶች። ምክንያቱም እኛ ስለእነዚህ ነገሮች ዕውቀት የለንም፤ ስለዚህ ከተማ ስንመሠርት አእምሮ ካለን ከቀደምት ተርጓሚያችን በቀር ሌላ ማንንም አንመክርም። የምድር እምብርት ላይ የተቀመጠው አምላክ የሚሰጠው ትርጓሜ ደሞ ለሁሉም የሰው ልጆች መሪ ነው። ሶቅራጠስ ቀጠል አርጎ ለግላውኮን እና ወንድሞቹ እንዲህ ይላል... የአሪስቶን ልጅ፣ ከተማህ አሁን የተመሠረተች ትመስላለች። ቀጥሎ በውስጧ ፍትሕና ኢፍትሐዊነት የት እንዳሉ፣ እንዴት እንደሚለያዩ፣ እና ደስተኛ ለመሆን ከሁለቱ የትኛውን መያዝ እንደሚገባ ከአማልክትና ከሰዎች ቢደበቅም እይ። ግላውኮንም በተቃዉሞ ድምፅ "ይህ ከንቱ ነው! ፍትሕን በሁሉ መንገድ እንደምትከላከል ቃል ገብተሃል፤ አንተ ራስህ ፈልግ" ሲል ይመልስለታል። ሶቅራጠስም ለማብራራት በመስማማት ነገር ግን ግላውኮን እንዲረዳ ይጠይቃል። ከተማችን በትክክል ከተመሠረተች ሙሉ በሙሉ ጥሩ ናት፤ ስለዚህ በእርግጥ ጥበበኛ፣ ደፋር፣ ራሷን የምትገዛና ፍትሐዊ ናት። ከአራቱ ሦስቱን ካገኘን የቀረው አራተኛው ፍትሕ መሆኑ ግልጽ ነው ፤ ልክ እንደ ማንኛውም አራት ነገር፤ አንዱን ስንፈልግ ሦስቱን ቀድመን ብናውቅ የቀረው ያ ነው።  ከተማ "ጥበበኛ" የምትባለው ብልሃተኛ (prudent) ስለሆነች ነው፤ ብልሃት ሲባል ደሞ በዓይነተኛ እውቀት እንጂ በድንቁርና አይደለም። ግን በከተማ ብዙ ዓይነት እውቀት አለ። ከተማ በአናጢዎች እውቀት "ጥበበኛ" አትባልም፤ "በአናጺነት የተካነች" ትባላለች። በብረት ሠሪዎች ወይም በገበሬዎችም እንዲሁ። ጥበብ የሚሰጠው እውቀት የሚያስብለት ስለ አንድ ልዩ ነገር ሳይሆን ስለ ከተማዋ በአጠቃላይ ውስጣዊና ከሌሎች ከተሞች ጋር ያላት ግንኙነት በተቻለ መጠን ምርጥ እንዲሆን ሲወስን ነዉ። ይህ እውቀት የጠባቂነት ሙያ ነው፤ ይህን ጥበብም የያዙት ሙሉ ጠባቂዎች እና ገዥዎች ናቸዉ። በከተማ ብረት ሠሪዎች ከእውነተኛ ጠባቂዎች በጣም ይበልጣሉ፤ ስለዚህ ከተማዋ በተፈጥሮ ከሁሉ ትንሹ ክፍል (የሚገዛዉ) ጥበበኛ ናት ይህ ክፍል ብቻ በእውነት "ጥበብ" ተብሎ ሊጠራ የሚገባውን እውቀት ይይዛል። ከተማ "ደፋር" ወይም "ፈሪ" የምትባለው በሚከላከልላትና በሚዋጋላት ክፍል (አጋዥዎች) ምክንያት ነው፤ የሌሎች ድፍረት ወይም ፈሪነት ከተማዋን አይወስንም። በሌሎች ድፍረት ማለት ደሞ ጥበቃ ነዉ። በሕግ በትምህርት የተሰጠውን እምነት ስለ ምን ነገሮች (እና ምን ዓይነት ነገሮች) በሁሉም መንገድ (በሕመም፣ በደስታ፣ በምኞትና በፍርሃት) አለመተው ነዉ። ለምሳሌ.... ሱፍን ሐምራዊ ለመቀባት ቀለም ሠሪዎች መጀመሪያ ከብዙ ቀለም ሱፎች በተፈጥሮ ነጭ የሆኑትን ይመርጣሉ፤ ከዚያ ብዙ ዝግጅት ያደርጉላቸዋል፤ ከዚያ ብቻ ወደ ሐምራዊ ቀለም ይነከራሉ። እንዲህ የተቀባ ቀለም በምንም ማጽጃ አይወጣም። ያለ ዝግጅት የተቀባ ግን "የታጠበና አስቂኝ" ይመስላል። እኛም ወታደሮችን የመረጥነውና በሙዚቃና በአካል ሥልጠና ያስተማርነው ሕጎችን እንደ ቀለም በደንብ እንዲይዙ ነው፤ ምክንያቱም ትክክለኛ ተፈጥሮና አስተዳደግ ስላላቸው እምነታቸው ከሁሉም "ማጽጃ" እንደ ደስታ፣ ሥቃይ፣ ፍርሃትና ምኞት ባሉት እንዳይወጣ ተደርጓል። በእንስሳትና በባሮች ውስጥ የሚገኝ ትምህርት ወይም ሕግ የሌለው ትክክለኛ እምነት "ድፍረት" አይባልም። ሶቅራጠስ ይህንን "የፖለቲካ ድፍረት"(political courage) ብሎ ይጠራዋል፤ ሙሉ ውይይቱን ለሌላ ጊዜ ይተዋል...አሁን ጥያቄያችን ፍትሕ ነው። ሶቅራጠስ ግላውኮንን እንደ አዳኞች በጫካ ዙሪያ ቆመው ፍትሕ እንዳያመልጥ እንዲጠነቀቁ ይጋብዛል። ቦታው ጨለማና ለመፈለግ ከባድ ነው፤ ግን ዱካ ያገኛል። "ከመጀመሪያው በእግራችን ስር ሲንከባለል ነበር፣ እኛ ግን እንደ ቂሎች አላየነውም!" በእጃቸው የያዙትን ዕቃ እንደሚፈልጉ ሰዎች ሩቅ እያየን ነበርም። ይለዋል። ከተማዋን ስንመሠርት ያቀድነው እያንዳንዱ ሰው በተፈጥሮ የሚስማማውን አንድ ሥራ መሥራት ፤ ያ ወይም የዚያ አንዳች ዓይነት ፍትሕ ነው። ብዙዎች "ፍትሕ የራስን ሥራ መሥራትና በሌላ ጉዳይ አለመግባት ነው" ሲሉ ሰምተናል። ነገር ግን... ጥበብን፣ ድፍረትንና ራስን መግዛትን በከተማ ውስጥ እንዲኖሩ የሚያስችል፣ ከተገኙም በኋላ የሚያቆይ ኃይል ይህ ነው። ከአራቱ የቱ ከተማዋን በጣም ጥሩ ያደርጋል ? ሁሉም የራሱን ሥራ መሥራቱ ከጥበብ፣ ከራስን መግዛትና ከድፍረት ጋር ይወዳደራል። ዳኞች ፍርድን ሲያስተላልፉ ዓላማቸው ማንም ዜጋ የሌላውን እንዳይወስድ፣ የራሱንም እንዳያጣ ነው፤ ይህ ፍትሐዊ ነው። ስለዚህ የራስን መያዝና መሥራት ፍትሕ ነው። አናጢና ጫማ ሠሪ ሥራ ቢለዋወጡ ከተማን ብዙ አይጎዳም። ነገር ግን በተፈጥሮ ሙያተኛ ወይም ገንዘብ ሠሪ የሆነ ሰው በሀብት፣ በድምፅ ብልጫ ወይም በጥንካሬ ተነፍቶ ወደ ወታደሮች ክፍል ቢገባ፣ ወይም የማይገባው ወታደር ወደ ዳኛና ጠባቂ ክፍል ቢገባ  ወይም አንድ ሰው ሁሉንም ለመሥራት ቢሞክር  ከተማዋን ያጠፋል። ስለዚህ ፍትሕ ማለት ሦስቱ ክፍሎች እያንዳንዳቸው የራሳቸውን ሥራ ሲሠሩ ሲሆን ኢፍትሐዊነት ደግሞ በሦስቱ ክፍሎች (ገንዘብ ሠሪዎች፣ አጋዥዎች፣ ጠባቂዎች) መካከል መለዋወጥና መግባት ለከተማ ከሁሉ የከፋ ጉዳት ማለት ነዉ። ነገር ግን ይላል ሶቅራጠስ "ይህንን እንደ ጸና እውነት አንቁጠረው" በግለሰብ ደረጃም ተመሳሳይ ሆኖ ከተገኘ ብቻ እንቀበለዋለን፤ ካልሆነ እንደገና ወደ ከተማ ተመልሰን እንመረምራለን። ሁለቱን እንደ እሳት ዱላዎች እርስ በርስ በማሻሸትም ፍትሕን እናበራለን። አንድ ትልቅና አንድ ትንሽ ነገር በአንድ ስም ከተጠሩ በዚያ ስም በሚጠሩበት ረገድ ተመሳሳይ ናቸው። ስለዚህ ፍትሐዊ ሰው ከፍትሐዊ ከተማ በፍትሕ ቅርጽ ረገድ አይለይም፤ ይመስለዋል እንጂ። ከተማዋ ፍትሐዊ ስትባል እያንዳንዱ ከሦስቱ ተፈጥሯዊ ክፍሎች የራሱን ሥራ ስለሠራ ነበር፤ ሌሎቹ ሦስት በጎነቶች (ጥበብ፣ ድፍረት፣ ራስን መግዛት) ደግሞ በእነዚህ ክፍሎች ሁኔታዎች ምክንያት ነበር። ስለዚህ ግለሰብም ተመሳሳይ ነገሮች በነብሱ ውስጥ ሊኖሩት ይገባል። "ነብስ እነዚህ ሦስት ዓይነት አላት ወይስ የላትም?" ፤ግላውኮንም "ጥንታዊው አባባል ያለው እውነት ሊኖር ይችላል ውብ የሆነ ሁሉ ከባድ ነው" ይላል።

Открыть в Telegram
Просмотры2 420−8%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—
#4199Текст

Переслано из HATETA Perspective

ፈረንሳዊው ጠንቋይ ኖርስተርዳም ወደፊት ከተነባያቸዉ ትንቢቶች መካከል በ20ኛዉ ክፍለዘመን ከወደ ምስራቅ አንድ አመፀኛ ሰዉ ይፈጠራል በማለት በትንቢቶቹ ዉስጥ ይገኛል ። ይህ ሰዉ ምናልባት ባግህዋን አለዛም ጋንድሂ ሊሆኑ ይችላሉ ይበልጥ ግን ለኦሾ ትንቢቱ የሚቀርብ ይመስለኛል ። ኦቸሪያ ፣ ባግህዋን ፣ ራጅናሽ በመጨረሻም ኦሾ በሚል ስም የሚታወቀዉ ከወደ ህንድ የተገኘዉ ብልጣብልጡ ብልህ ሰዉ ትንሽ ነገር ስለርሱ ማለት ወደድኩ! ምናልባትም አንዳንድ ሰዎች ፈላስፋ የሚሉት በእኔ እምነት ግን የአዲስ ሃይማኖት ሰባኪ እንደሆነ የምረዳዉ ይሄን ያልኩበት ምክንያትም ዞርባ + ቡድሃ ለነፍስህ ቡድሐን ለስጋህ ደግሞ ዞረባን ተከተል በማለት በሚታወቀዉ አስተምህሮዉ የአዲስ ሃይማኖት አስተማሪ እንደሆነ በዚህ ለመረዳት ነዉ የሞከርኩት ። ኦሾ ብልጥም ጅኔስም ብልጣብልጥም ነዉ በእኔ እምነት ምድር ላይ እንደነበሩ ነገስታቶች ( በሰማይ ያለዉ ንጉስ እንደ ኦሾ ተንደላቆ የሚኖር አይመስለኝም ምክንያቱም በቀን ዉስጥ ምን ያክል ሰዎች እንደሚሞቱ እና ለፍርድ እንደሚቀመጥ ሳስብ እረፍት እና ተዝናኖት ያለዉ ስለማይመስለኝ ነዉ ) ተንደላቆ የኖረ የላቀ እንክብካቤ እየተደረገለት የኖረ ግለሰብ ነዉ ። ባግህዋን ምናልባትም ከክርስቶስ እና ከመሀመድ በኋላ ከተነሱ አደገኛ ሰዎች መካከል አንዱ ነዉ ። የታላቅነቱ ምንጭ የሚመስለኝም ያለ ፍርሃት እነርሱን በመዝለፍ እና መሬት ላይ በመደቅደቅ በዓለም ላይ የታወቀ ይመስለኛል ። የኦሾን አንደበተ ርትዑነት እዚህ ላይ መካድ አልችልም ምክንያቱም ይህ ሰዉ ሲናገር ጣቶቹን ወደ ሰማይ በማመልከት እና በእርጋታ የሚነገርበት መንገድ አስደናቂ ነዉ ። በንግግርቹም የአያሌዎችን ልብ ሰልቧል በንግግሮቹም ብዙዎች ተከትለዉታል ከእግሩም ስር ወድቀዋል ባርከንም ብለዉታል በሚሄድበትም ተከትለዉታል ሁለ ነገራችዉንም አሳልፈዉ ሰጥተዉታል በምላሹ ግን ያተረፉት ድህነት እና ስቃይን ነበር ። በእኔ አመለካከት እዉነተኛ ጠቢብ ወደ ራሳቸዉ የአዕምሮ ጎዳ ይመራቸዋል እንጂ ወደ ራሱ አስተሳሰበብ አይመራም! ኦሾ በህይወት እያለ የፃፋቸዉ ሁለት መፅሐፍት ብቻ ናቸዉ ( ምናልባትም የተለየ መረጃ ያላችሁ ለማስተካከል ክፍት ነኝ ) ከዛ ዉጭ ንግግሮቹ ተቀድተዉ ከስድስት መቶ በሚበልጡ መፅሐፍቶች ተጠርዘዉ በመላዉ ዓለም ተበትነዋል ። በንግግሮቹ ዉስጥ ስለ ወሲብ ፣ ስለ ጋብቻ ፣ ስለ ሴትነት ፣ ስለ ሃይማኖት ፣ ስለ ማህበረሰብ ፣ ስለ ወንድ ( ወንድን እንዲያዉም ትምክህተኛ ተባዕት ነዉ የሚለዉ ) ስለ ፖለቲካ ፣ ስለ ሳይንስ ፣ ስለ ስነ_ልቦና (በእኔ እምነት ስለ ስነ ልቦና የቀረበ ሰዉ ይመስለኛል ) ፣ ስለ ፍልስፍና ፣ ስለ ጦርነት ፣ ስለ ባህል .... ሁሉንም ባካተተ መልኩ የሚደቀድቀዉንም እየደቀደቀ የሚያሞግሰዉንም እያሞገሰ በመፅሐፍቶቹ ተካተዉ ይገኛሉ ። ኦሾ ስለ በኢትዮጵያ ዉስጥ ስለሚገኙ ሰዎችም ተናግሯል ኢትዮጵያ ዉስጥ ሄጄ ስለ ሜዲቴሽን አላስተምርም እዛ ከሄድኩ ይገሉኛል ብሏል ምናልባትም ልንገድለዉ እንችል ይሆናል አላዉቅም ይሄን ያልኩበት ምክንያት የኦሾን መፅሐፍ አታንብቡ ታብዳላችሁ እየተባለ ይወራል አንዳንድ ለጋ ወጣቶችም የእሱን መፅሐፍ አንብቤ ነዉ ያበድኩት የሚሉም አሉ ያሳዝናል ወንድሜም ሆነ እህቴ የኦሾ መፅሐፍ አያሳብድም ምናልባትም የአዕምሮ እክል ገጥሟችሁ ከሆነ ሂዳችሁ ባለሙያዎች ጋር ታዩ እሺ! እንጂ እንደምትሉት የእርሱ መፅሐፍ ካሳበዳችሁ ወይም ያበዳችሁ ካላችሁ የትኛዉ መፅሐፍ እንዳሳበዳችሁ ጠቁሙኝ እና እኔም ልቀላቀላችሁ! በመጨረሻም ያላችሁን ልንገራችሁ እና ሀሣቤን ልቋጭ ምክንያቱም የዚህ ግለሰብ ታሪክ ተወርቶ አያልቅም አስፈላጊ እና መሳጭ ከሆነ በሌላ ዙር እንመለስበታለን ። ግን እናተ ለዚህ ግለስብ ምን ዓይነት አመለካከት እንዳላችሁ ሀሳባችሁን አስቀምጡ ... እንዳላችሁ ፦ ወሲብ በምታደርጉበት ወቅት ደነሱ እጣን አጫጭሱ ታጣባችሁ ታጥናችሁ ቅረቡ ምክንያቱም ይሄን ካደረጋችሁ ወደ መለኮት ከፍ ትላላችሁ እግዚአብሔርንም በጨረፍታ ትመለከቱትታላችሁ በዛ ቅፅበት የተፀነሰዉ ህፃንም የተደበተ አይሆንም ወደዚህ ምድር ሲመጣም ብሩህ እና የተደሰተ ሆኖ ይመጣል ብሏቹኋል ።

Открыть в Telegram
Просмотры2 670+1%к среднему
Пересылки—
Реакции29
Комментарии—
#4197Фото
Просмотры4 130+56%к среднему
Пересылки—
Реакции59
Комментарии—
#4196Текст

Переслано из HATETA Perspective

ማታ አንድ ድሮ የተፃፈ የታሪክ መፅሐፍ ላነብ ስገልጥ ( አሁን የሚፃፉት ዉስጥም አይጠፋም ) ገና ከመቅድሙ " ኢትዮጵያ ታብፅሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር " የሚል ጥቅስ አነበብኩ ። በተለይ የታሪክ እና አንዳንድ የግጥም መፅሕፍትን ሳነብ እነዚህን አምስት ቃላት ደጋግሜ በማግኘቴ እየተሰላቸሁ ነዉ ። ይሄ የኢትዮጵያ እጅ መዘርጋት ነገር በመደጋገሙ ምክንያት የመደጋገሙን ዋቤነት መጠየቅ ግድ ሆነብኝ መደጋገሙ ምን ማለት ነዉ ? ከክርስቶስ ልደት በፊት የተፃፈ የብሉይ መፅሐፍ በሙሉ ልብነት እጅ ስለመዘርጋታችን ይነግረናል ወይም የፈጣሪ ቃል ነኝ በሚል ትዕቢት ወደፊት መዘርጋታችን እንደማይቀር ይተነብያል ። በመጀመሪያ መዘርጋት ምንድነዉ ? መፀለይ ? መለመን ? መለገስ ? መለመን ከሆነ እስካሁን ምን እየለመንን ነዉ ? በእኔ በእኔ ፈጣሪ በቸርነቱ በመጀመሪያዉ ልመናችን ላይ ሁሉን ሰጥቶናል ብዬ አምናለሁ ። ካልህነ ቸሩ እግዚአብሔር የምንለዉ መግለጫችን እንደያጥር እጠይቃለሁ ። ሚሊዮኖች ዐርብ ዕሮብ እንፆማለንና ይሄ ቸር የተባለዉ ፈጣሪ ይሄን ሁሉ ዘመን እጇን እንደዘረጋች አገሪቷን ሜዳ ላይ ብቻዋን እንድትሰቃይ ይተዋታል ብዬ አላምንም ። ግን አሁንም መዝሙረ ዳዊትን ያነበቡ ያ እጃችሁን "እየዘረጋችሁ ነዉ " ይሉናልና እጠይቃለሁ ። ለምን ብለን አሁን እንዘረጋለን ? የኛን አገር ብቻ መርጠዉ ዘርጊ ያደረጉዋት እነማን ናቸዉ ? እስከመቼስ ነዉ የምንዘረገዉ ? እኛ ጉራ የምናደርግበት ጥቅስ የሆነ ወጥመድነት የሚኖርበት አይመስልሽም ሽዋዬ ? ይሄ ለእኔ የአለማብቃቱ ነገር የእጅ ዝርጋታዉን ሤረኛ እና አሳዛኝ ያደርገዋል ። ወይስ እንደዉ ዘመን ዘመን አለዉ መዘርጊያዉና መሰብሰቢያዉ ? ወይስ እያረፈች ነዉ አገራችን እጇን የምትዘረገዉ ? እና ግን ደራሲዉ ወይም ይሄ " ዳዊት " የተባለዉ ነጋሢ አዝማሪ እረፍት ማድረጓን ሳይጠቅስ ለምን በበገናዉ አላዘነባት ? ምናለ ከወደዳት በአንዱ ምዕዛል ትንሽ እረፍት ባበጀላት ? ይህችን አገር አይወዳትምን ? የመዘርጋታችን መቆሚያ ቀኑ አልተነገረንምና እንዲሁ ለዕልፍ ዘመን ሳናርፍ ይሄን ደብዛዛ ጥቅስ የታሪካችንና የኑሮአችን ዕጣ መተርጎሚያ አድርገነዉ እንባዝናለን ። ኢትዮጵያ ጠይም ፣ ቀጭን ፣ ደረታም ፣ አጥንታም ፣ ዞማምና ዐይነ ትላልቅ የአማርናንዋን ቆንጅ ንግስት ነፈርቲትን የመሰለች ወይዘሮ ናት ። እና ይሄን ሁሉ ያልገባንን ያህል ዘመን ይህቺ ዉብ ሳታቆም እጆቿን ለመዘርጋት ክንዶ አይችልም እላለሁ ። ሲመስለኝ ብትዘረጋ እንኳን ታንጎራጉራለች ። ያ እንጉርጉሮ በምሳሌ ተለዉጦና በቃላት ተደልሆ ልመና እንዳይባልባት አንገቷን ሰብራ የፈጣሪን እግር እግር እያየች እሱ ብቻ እንዲሰማ አድርጋ 'ኧረ አታስቸግረኝ ጌታዬ ፣ ከዚህ ጥቅስ ልገላገል' ማለቷ አይቀርም ። ደሞ የኢትዮጵያ እጅ የማርያም እጅ ነዉ ። የእናቱ እጅ ነዉ ። እና ሩህሩህ ነዉና እንደ እናቱ እንደዉ ስገምት ይሄን እጅ ፈጣሪ ስሞ ወደ መሬት ከመለሰዉ እጅግ ከረመ ። ታዲያ ግን አሁን ድረስ 'ዘርግተዋለች' ለምን ይሉናል ? የወደዱን አስመስለዉ በግርማ ምገሳም መፅሐፍና በሃይማኖት ጋርደዉ መለማመጥ ፤ ልመናና ባዝኖ መቅረትን ሊያስተምሩን ነዉ ? አምላክ ሰዉን ሲፈጥረዉ 'ሠርተህ ፣ጥረህ ፣ ግረህ ብላ' አለዉ እንጂ 'ዕድሜ ልክህን እጅህን ወደ እኔ ዘርግተህ ኑር' አላለዉም ። ገና የአገሪቷ ስም እዛ መፅሐፍ ዉስጥ ተጠራና ምን ይጠበስ ? ደሞስ የተጠራዉ ሺህ ጊዜ ሆኖ ብልጣብልጦች በአርትኦት 50 ካደረጉትስ ? ወይስ 'መዘርጋት' ሌላ ትርጉም አለዉ ? ከቃላት ዕዉቀት በመነሳት 'ታበፅሕ' በግዕዝ ቋንቋ 'ታደርሳለች' ማለት ነዉ እንጂ 'ትዘረጋለች' ማለት አይደለም የሚሉም አሉ ። ማን ማንን ሊያምታታ ነዉ 'ታደርሳለች' የሚለዉን 'ትዘረጋለች' ብሎ ተርጉሞ ወደ ለማኝ የለወጠን ? ይሄ 'ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር' ሌላ የታባ መልካ ነገር ዘሏል?..... ያልተብራሩ ጥቅሶች ሕዝቦች ሆይ ያልተነገረላቸዉ አቆርቋዥ ናቸዉ ። መዝመረ ሄላም ገፅ 180 #አዳም_ረታ

Открыть в Telegram
Просмотры4 130+56%к среднему
Пересылки—
Реакции20
Комментарии—
#4194Фото
Просмотры3 860+46%к среднему
Пересылки—
Реакции30
Комментарии—
#4193Текст

አስክሊፒዮስ(የህክምና አማልክት ነዉ) ሕክምናን ለልጆቹ ያላስተማረው ከድንቁርና አይደለም ይልቁንም በሥርዓት በተደራጀች ከተማ እያንዳንዱ ሰው የራሱ ሥራ አለው፣ ማንም ዕድሜ ልኩን ለመታመምና ለመታከም ጊዜ የለውም ብሎ ስላወቀ ነው። ሕክምናን የፈጠረው በተፈጥሮና በልማድ ጤናማ አካል ላላቸው ግን የተወሰነ በሽታ ላለባቸው ሰዎች ነው፤ በመድኃኒት ወይም በቀዶ ሕክምና በሽታውን አስወገደ፣ ከዚያ መደበኛ አኗኗራቸውን አዘዘ። በበሽታ የተሞላ አካል ላላቸው ሰዎች ሕይወታቸውን በረዥም ሥቃይ ለማራዘም እና ተመሳሳይ ልጆች እንዲወልዱ ለማድረግ አልሞከረም። መደበኛ ኑሮ መኖር ለማይችል ሰው ለራሱም ለከተማውም አይጠቅምም ብሎ ሕክምና አልሰጠም። የአስክሊፒዮስ ልጆች በትሮይ ጦርነት በሜኔላዎስ ቁስል ደሙን ጠጥተው ለስላሳ መድኃኒት ብቻ ሲቀቡ፣ ከዚያ በኋላ ምግብና መጠጥ አላዘዙም። ፎኪሊዴስ "ኑሮ ሲኖርህ በጎነትን ተለማመድ" ብሏል። ግን ለሰውነት ከመጠን ያለፈ እንክብካቤ፣ቤት አስተዳደርን፣ ወታደራዊ አገልግሎትንና የፖለቲካ ሥራን እንዲሁም ማንኛውንም ትምህርት፣ አስተሳሰብና ፍልስፍናዊ ማሰላሰልን እንደሚያደናቅፍ ግላውኮንም ይቀበላል። አስክሊፒዮስ በወርቅ ተገዝቶ ሊሞት የተቃረበ ሀብታም ሰው ስለፈወሰ በመብረቅ ተመታ ይላሉ። ይህንንም በቅድሙ  መርሁ መሰረት ሶቅራጠስ አይቀበለዉም፤ ምክንያቱም የአምላክ ልጅ ከሆነ በገንዘብ አይሸነገልም፤በገንዘብ ከተሸነገለ ደሞ የአምላክ ልጅ አይደለም። ይሄን ጊዜ ግላውኮን... በከተማችን ጥሩ ሐኪሞችና ጥሩ ዳኞች ያስፈልጉናል አይደል? ጥሩ ሐኪም ብዙ ጤነኛና የታመሙ ሰዎችን የተመለከተ፣ ጥሩ ዳኛም ከብዙ ባሕርይ ካላቸው ሰዎች ጋር የተገናኘ ነው ይላል። ሶቅራጠስ ግን ሁለቱ ጥያቄዎች አንድ ዓይነት አይደሉም ይላል... ጥሩ ሀኪም አካልን በአካል ሳይሆን በነብስ ያክማል ፤ ከልጅነት ጀምሮ ከብዙ የታመሙ አካላት ጋር ቢቆይ፣ ራሱም ሁሉንም በሽታ ቢያገኝና በተፈጥሮው በጣም ጤነኛ ባይሆን ይበልጥ ብልህ ይሆናል። ጥሩ ዳኛ ግን ነብስን በነብስ ይገዛል ፤ ከልጅነት ጀምሮ ከመጥፎ ነብሳት ጋር ማደግና በኢፍትሐዊነት መጠመድ የለበትም፤ በውስጡ ኢፍትሐዊነትን የማያውቅ መሆን አለበት ፤ አዛውንት እና "ዘግይቶ ተማሪ" መሆን አለበት። ኢፍትሐዊነት ምን እንደሆነ ከራሱ ነብስ ሳይሆን በሌሎች ነብስ እንደ ባዕድ ነገር የሚያውቅ መሆን አለበት፤ በወጣትነታቸው ግን ተላላ ስለሚመስሉ ኢፍትሐዊ ሰዎች በቀላሉ ያታልሏቸዋል እነሆ በውስጣቸው የመጥፎ ባሕርይ ምሳሌ የላቸዉምና። ይላል። ሕክምናና ዳኝነት ጥሩ አካልና ነብስ ያላቸውን ዜጎች ይንከባከባሉ፤ አካላቸው በተፈጥሮ ጤነኛ ያልሆነውን እንዲሞት ይፈቅዳሉ፤ ነብሳቸው በተፈጥሮ ሊታከም በማይችል ሁኔታ መጥፎ የሆኑትን ደግሞ ራሳቸው ይገድላሉ !። ግላውኮንም ይህ ለተቀበሉትም ለከተማዋም የተሻለ እንደሆነ ይስማማል። ቀጥሎም ይቺን የምናብ ከተማ ማን ይገዛል ለሚለዉ ስቅራጠስ አዛውንቶች ይገዛሉ፣ ወጣቶች ይገዛሉ፤ ገዥዎች ከጠባቂዎች ምርጦቹ ማለትም ከተማዋን በመጠበቅ የተሻለ ዕውቀትና ችሎታ ያላቸው እና ለከተማዋ የሚያስቡ መሆን አለባቸዉ። ሰው ከሁሉ የሚያስብለት የሚወደውን ነው፤ የሚወደውም ለእሱና ለራሱ አንድ ዓይነት ጥቅም እንደሚሰጥ ሲያስብ ነው። እሱ ሲሳካለት ራሱም እንደሚሳካለት ሲያምን ነዉ። ስለዚህ ከጠባቂዎች ለከተማዋ ጥቅም ነው ብለው የሚያምኑትን በሕይወታቸው ሙሉ ለማድረግ በጣም የሚያዘነብሉትን እንመርጣለን። ይላል። ሶቅራጠስ ጠቃሚ ውሸቶችን ሲያነሳ ቆይቷል፤ አሁን "አንድ የተከበረ ውሸት" (a single noble lie) እንዴት እንደሚፈጠር ይጠይቃል፤ በተቻለ መጠን ገዥዎቹን ራሳቸውን የሚያሳምን፤ ካልተቻለ የቀረውን ከተማ የሚያሳምን መሆን አለበት። "የፊንቄ ተረት" ይለዋል፤ ባለቅኔዎች እንደሚሉት ብዙ ቦታዎች የሆነ ነገር ነው፤ በዘመናችን አልሆነም፣ ሊሆንም አይችልም፤ ሰዎችን ለማሳመን ብዙ ሥራ ይጠይቃል። ሶቅራጠስ ድፍረትና ቃላት ከየት እንደሚያገኝ እንደማያውቅ ይናገራል፤ ግላውኮንም "ለዚህ ነው ቀደም ብለህ ያፈርከው" ይለዋል። ሶቅራጠስም ተረቱን ይቀጥላል... ዜጎች የተሰጣቸው አስተዳደግና ትምህርት ሁሉ እንደ ሕልም ነበር፤ እውነታው ግን እነሱና መሣሪያዎቻቸው በምድር ውስጥ ተሠርተውና ተመግበው ነበር፤ ሲጠናቀቁ እናታቸው ምድር ወደ ላይ ላከቻቸው። ስለዚህ ለምድሪቱ መጠበቅና ማሰብ አለባቸው፣ ሌሎችን ዜጎች "ከምድር የተወለዱ ወንድሞቻቸው" አድርገው መቁጠር አለባቸዉ። ሁላችሁም ወንድማማቾች ናችሁ፤ ነገር ግን አምላክ ሲሠራችሁ ለመግዛት የሚችሉት ላይ ወርቅ፣ በአጋዥዎች ላይ ብር፣ በገበሬዎችና በሌሎች ሙያተኞች ላይ ብረትና ነሐስ ቀላቅሏል። ልጆች በአብዛኛው እንደ ወላጆቻቸው ይሆናሉ፤ ዝምድና ስላላችሁ ግን አልፎ አልፎ ከወርቅ ወላጅ የብር ልጅ፣ ከብር ወላጅ የወርቅ ልጅ ይወለዳል።የሚል ነበር። አምላክም ለነዋሪዎቹ እንደዚህ ያዛል፤ በልጆቻቸው ነብስ ውስጥ ያለውን የብረት ድብልቅ ከሁሉ በላይ መጠበቅ አለባችሁ። ልጃቹ በብረት ወይም በነሐስ ተቀላቅሎ ቢወለድ በምንም መንገድ ሊራሩለት አይገባም፤ ለተፈጥሮው የሚስማማ ክብር ሰጥተው ወደ ገበሬዎችና ሙያተኞች ያስወጡታል። ከእነሱ ልጅ ወርቅ ወይም ብር ያለው ከተገኘ ክብር ተሰጥቶት ወደ ጠባቂዎች ወይም አጋዥዎች ይወሰዳሉ። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግን ከተማዋ ብረት ወይም ነሐስ ጠባቂ ካላት ትጠፋለች። ከተረቱ በኋላ ሶቅራጠስ ምድራዊ ልጆች መሣሪያ አስታጥቀው ከገዥዎቻቸው ጋር ወደ ከተማዋ ምርጥ ቦታ ሰፈር እንዲመሠርቱ ይመራል፤ ከዚያ በከተማዋ ውስጥ ሕጎችን የማይታዘዝ ማንኛውንም ሰው በቀላሉ መቆጣጠር ወይም እንደ ተኩላ መንጋ የሚያጠቃ የውጭ ጠላትን እንዲመክት መደረግ አለበትም ይላል። ከዚያ መስዋዕት ከፍለው ማረፊያ ይሠራሉ። ትምህርት ብቻ በቂ እንዳልሆነም ሶቅራጠስ ያስጠነቅቃል ፤ መኖሪያና ንብረትም ከጥሩ ጠባቂነት የማይከለክሉና በዜጎች ላይ ክፋትን የማያበረታቱ መሆን አለባቸው። ሕጉም እንደሚከተለዉ መሆን አለበት ይላል... ከሚያስፈልገው በላይ የግል ንብረት ማንም አይኖረውም። መኖሪያና ማከማቻ ቤቶች ሁሉም በፈለገው ጊዜ ሊገባበት የሚችል ክፍት ይሆናሉ። አስፈላጊውን ምግብ ከሌሎች ዜጎች እንደ ጠባቂነት ደመወዝ ይቀበላሉ፤ መጠኑ በዓመቱ መጨረሻ ሳያንስና ሳይተርፍ እንዲወሰን ይደረጋል። የጋራ ማዕድ ቤቶች በየሰፈሩ እንደ ወታደር አብረው ይኖራሉ። መለኮታዊ ወርቅና ብር በነብሳቸው ውስጥ ከአማልክት እንደ ቋሚ ስጦታ አላቸው ስለዚህ የሰው ወርቅ አያስፈልጋቸውም። ወርቅና ብር መንካት፣ ከእነሱ ጋር በአንድ ጣሪያ መኖር፣ እንደ ጌጥ መልበስ፣ ከወርቅ/ብር ጽዋ መጠጣት በመለኮታዊ ሕግ ተከልክሏል። ሶቅራጠስም በዚህ መንገድ ራሳቸውንም ከተማዋንም ያድናሉ። ግን የግል መሬት፣ ቤትና ገንዘብ ካገኙ የቤት አስተዳዳሪዎችና ገበሬዎች ይሆናሉ እንጂ ጠባቂዎች አይሆኑም፤ የዜጎች ወዳጅ ሳይሆን ጠላት ጌቶች ለመሆን ይቃጣሉ።በሕይወታቸዉ ሙሉ ሲጠሉና ሲጠሉ፣ ሲያሴሩና ሲሴስኑ፣ ከውጭ ጠላቶች የበለጠ አደገኛ የዉስጥ ጠላቶች ይሆናሉ። ስለዚህ ይህ እንደ ሕግ ይደነገግ ይለዋል ፤ግላውኮንም ይስማማል። ይቀጥላል... ምንጭ፤ ከላይ ከተያያዘዉ መፅሀፍ (Republic) ከገፅ 128 እስከ 176

Открыть в Telegram
Просмотры4 360+65%к среднему
Пересылки—
Реакции25
Комментарии—