Динамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 1 ч | 645 |
| 4 ч | 903 |
| 8 ч | 937 |
- Через 1 час645
- Через 6 часов937
- Всего сейчас937
A wise man is one who has learned to restrain his desires.The lowest level of life is to live only within the bounds of desire.Most people have many desires but little knowledge wisdom belongs to those who have much knowledge and few desires -Schopenhauer
23 нояб. – 24 нояб.+9 (0%)
| Дата | Подписчики |
|---|---|
| 23 нояб. 2026 г. | 26 617 |
| 24 нояб. 2026 г. | 26 626 |
По дню публикации
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 14 нояб. 2026 г. | 4 360 |
| 15 нояб. 2026 г. | 3 893 |
| 17 нояб. 2026 г. | 4 130 |
| 18 нояб. 2026 г. | 2 653 |
| 19 нояб. 2026 г. | 2 870 |
| 20 нояб. 2026 г. | 1 950 |
| 21 нояб. 2026 г. | 2 550 |
| 22 нояб. 2026 г. | 1 835 |
| 23 нояб. 2026 г. | 1 243 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 1 ч | 645 |
| 4 ч | 903 |
| 8 ч | 937 |
እነሆ ገፀ_በረከት የኔ ሴት ሙዚቀኛ ከመጣች ስንበትበት ብላለች ። እናም በነዚህ ሁለት አመታት ዉስጥ አልበም ካወጡ እንስት ዘፋኞች መካከል አበባዬን የሚያክል ሴት ሙዚቀኛ ማግኘት አልቻልኩም አበባ የነበራትን ቀለም ሳትለቅ ነዉ በዚህኛዉ አልበም የተገኘችዉ እና እኔ የማዉቀዉ አበባ መስከረም ላይ ነዉ ። አበባ ደሰለኝ ግን የኅዳር አበባ ሁና ነዉ የተገኘችዉ ። ከዚህ አልብም ዉስጥ በጣም የወደድኳቸዉ ትራኮች አሉ ግን አሁን የምጋብዛችሁ " ሰዉ እያለመደ " የተሰኘዉን ትራክ ይሆናል ። ሰዉ እያለመደ ጣዕሙ አይታወቅ የመኖር ትርጉሙ ካልሸመተ ወዳጅ ስሜ በፍቅር መቅረቡ እንግዲህ ታገሰዉ ልቤ አንተ መከረኛ እንደዚህ ናት አለም ይሄዉ አትሆን ለልከኛ እጨብጠዉ ጉሙን እይዘዉ ቸገረኝ አዬ ሰዉ እልና እኔስ ምኑን ለየኝ ....
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 1 ч | 670 |
| 4 ч | 927 |
| 8 ч | 963 |
Переслано из THE HUMANIST ROAD™
አብዛኛዉን ጊዜ ከእምነት ጋር በተያያዘ ከምጠየቃቸዉ ጥያቄዎች አንዱ ስለ ሞት ስታስብ ምን ይሰማሃል ፣ዘላለም አትኖርም፣ ሟች ነህ ! ቅብርጥሴ ስለዚህ የዘላለም ህይወት የሚሰጠዉን አካል ተከተል ጲሪሪም ጳራራም የሚሉ ማስፈራሪያ እና ዛቻ መሰለ ዓ.ነገሮችን ነዉ። ያዉ እንደማነኛዉም የሰዉ ልጅ(at least fully human በሆነዉ ጎኔ😁) ስለሞት ሳስብ uncertaintyዉ የስሜት መረበሽ ያደርስብኝ ይሆናል ያ የሚሆነዉ ግን ነገሮችን ከመጠናቸዉ በላይ አግዝፎ በመመልከት ነዉ። ሞትን መፍራት ወይ ከሞት ቡሃላ ስላለዉ እጣፋንታ መስጋት ተገቢ እና ተፈጥሯዊ ሆኖ ሳለ ፤ እንደ አንድ ተፈጥሯዊ የህይወት ዑደት ደሞ ከሱ ጋር ሰላም መፍጠር ያስፈልጋል። ይህ ማለት ግን ለእሱ እጅ መስጠት ማለት አይደለም። ይሄ ሁሉም ነገር ላይ የምትገብረዉ የህይወት መርሔ ነዉ። አንድ ነገር የመሆን እድሉ በጣም ጠባብ እና almost እንደማይሆን እያወቁ እንኳ ለመቀየር የመሞከር አባዜ። ይህም እንደምሞት አዉቃለዉ እና መሞት ችግር የለዉም ተፈጥሯዊ ነዉ የሚለዉን ተቀብሎ በተመሳሳይ ሰዓት ግን በህይወት እስካለሁ ላስቆመዉ እሰራለዉ የሚለዉን ወኔ መታጠቅ ነዉ። ሁሉንም ነገር የማረገዉም በዚህ መሰረት ነዉ። ሰዎች ድንቁርና dominant trait ነዉ፤ መልኩን እየቀያየረ ያለ እና የሚኖርም ነዉ ፤ ስለዚህ አንተ ለምን awareness ለመፍጠር ይሄን ያህል ትባዝናለህ ይሉኛል፤ ደሞም ልክ ናቸዉ በሀሳባቸዉም እስማማለሁ ግን ለእኔ ህይወት እሱ ነዉ። The struggle b/n the destiny. አዎ ድንቁርናን መቅረፍ የሚቻል አይመስልም እነሆ በሰዎች ታሪክ ዉስጥ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የማንነታችን አንድ ክፍል ነዉ እና ! ብሎ አምኖ at the same time ግን ሊጠፋ እንደሚችል ነገር መታገል። ህይወትን መኖር ማለት ልታረጓቸዉ ያሰባቿቸዉ ነገሮች odds against you እንደሆኑ እያወቃቹ "whatever" ብላቹ ማረግ የሚገባቹን የማረግ ጥበብ ነዉ። ብዙ ሰዎች ህይወት ይዛ ለምትመጣዉ uncertainty እጅ ይሰጣሉ፤ certainty ይሰጠኛል ብለዉ ወደሚያስቡት ነገር ሁሉም ይሮጣሉ። እኔ ግን ከ uncertaintyዉ ጋር ሰላምን እፈጥራለዉ፤አኖረዋለሁም! 99 ለ 1 ቢመራኝ እንኳ ጨዋታዉ እስኪያበቃ ጨዋታዉን እቀጥላለሁ። ህይወት ማለት ይህ ነዉ ! ማሸነፍ ሳይሆን በህይወታቹ ልታረጉ የሚገባቹን ነገር በነፃነት ማረግ። ዉጤቱ ምንም ይሁን ምን። የሞት፣ስቅላት፣ግርፋት፣መገለል፣ድብደባ... ወዘተ ፍራቻ እና የእንዲ ቢሆንስ ሰንሰለት ሊያስራቹ አይገባም። አለም ልክ ተቦክቶ እንደተቀመጠ የሸክላ ጭቃ ለፈለጋቹት ነገር ለመበጀት ዝግጁ ናት፤ ጭቃዉን አንሱት፤እንዳሻቹም አቡኩት፤ እንደፈለጋቹም ጠፍጥፉት፤ በፈለጋቹት ቅርፅም አበጁት... ጭቃዉን ተጠበባቹበትም ተዋቹትም መድረቁ አይቀርም እና። ምናልባት በዛ ጭቃ እናንተን የሚመስል ልዩ ነገር ካስቀመጣቹ ግን በጭቃዉ ዉስጥ እናንተ ትታወሳላቹ ። አሁንም ማወቅ ያለባቹ ነገር መታወሱ ለናንተ ምንም አይሰራም ! ነገር ግን የህይወትን መኖር byproduct ሆኖ ስለሚመጣ ነዉ። ሞትን ማስቆም ብትችሉ እንኳ ዉበቱ ያለዉ ሞትን ማስቆም በመቻላቹ ዉስጥ ሳይሆን እሱን ልታስቆሙ በሄዳቹበት ጋራ እና ሸንተረር ፤ አቀበት እና ቁልቁለት ዉስጥ ነዉ። አንድ ልጅ ከመዳህ ወደ መራመድ በሚያረገዉ ጉዞ ላይ ትልቁ ኩነት መራመድ መቻሉ ሳይሆን መዉደቅ እና መነሳቱ መልሶም መጣሩ ነዉ ። so you gotta live life for the journey of it not for the destiny, The beauty of life is in its uncertainty ! ተፃፈ በፍጡር አብዝቶ ላሰበበት ተፈጥሮዉ።
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 2 ч | 511 |
| 4 ч | 742 |
| 7 ч | 891 |
| 24 ч | 1 830 |
◉ እሁድ ከረዘመባችሁ ➊ [ Ship of Theseus ፊልም] "Ship of Theseus" ፍልስፍናዊ ይዘት ያለው አስተካዥ ፊልም ነው። ርዕሱ በጥንታዊ ግሪክ ፍልስፍና ውስጥ ከሚገኘው «Ship of Theseus Paradox» የመጣ ነው። «If every component of the Ship of Theseus is replaced, is it still the same ship?» የሚለውን መሠረታዊ የለውጥ ጥያቄ ያነሳል። ፊልሙ በሦስት የተለያዩ ሰዎች ሕይወት ዙሪያ የሚሽከረከር ነው። ነገር ግን በሦስቱም ታሪኮች የምናየው የTheseus መርከብን መንፈስ ነው። ዓይኗ ሳያይ በድምፅና በንክኪ ዓለምን የምትረዳ...አሊያ የምትባል ፎቶግራፈር አለች። የዓይን ብሌን ንቅላት ተደርጎላት ማየት ስትጀምር ግን ነገሮች ይቀየራሉ። በሌላኛው በኩል በእንስሳት ላይ የሚደረግን ምርምር በጽኑ የሚቃወም መነኩሴ አለ። ድንገት ከባድ የጉበት በሽታ ይያዛል። ይህንግዜ ሕይወቱን ለማትረፍ የጉበት ንቅለ ተከላ ያስፈልገዋል። ሕይወቱን ለማቆየት በሚቃወማቸው መንገዶች ውስጥ ማለፍ ነበረበት። ደግሞ በሕገ-ወጥ የኩላሊት ዝውውር ውስጥ የተጎዳን ሰው ለማዳን የሚባክን ካራክተር አለላችሁ። በኋላ ራሱን ሲመረምር «እውን የማደርገው እርዳታ ሰዎችን ለማትረፍ አስቤ ነው ወይስ ራሴን እንደ በጎ አድራጊና ጻድቅ ለማየት?» ብሎ የሚጠይቅ። ሁሉም ሰው በሕይወቱ ውስጥ ድንገተኛ ሽግግር ሲገጥመው «እኔነቴ ምን ሆነ?» ብሎ እንደሚጠይቅ ያሳያሉ። የፊልሙ ገጸ-ባህሪያት በ moral ambiguity ውስጥ ቆመው የሚታገሉ ተራ ሰዎች ናቸው። አዘጋጁ ለተመልካቹ ቀጥተኛ መልስ ወይም መደምደሚያ ከመስጠት ይልቅ.... ጸጥ ያሉ ትዕይንቶችን በመጠቀም ተመልካቹ ራሱ እንዲያስብ ክፍት ቦታ ይተዋል። ➋ [የ Theseus መርከብ ታሪክና ጥያቄ] በጥንታዊ የግሪክ አፈ-ታሪክ Theseus የአቴንስ ጀግና ነበር። ከክሬት ደሴት በሕይወት ሲመለስ የተጠቀመባትን መርከብ... አቴናውያን ለመታሰቢያና ለክብር ወደብ ላይ አቁመው ይጠብቋት ነበር። ጊዜ እያለፈ ሲሄድ የመርከቧ የእንጨት ክፍሎች መበስበስ ጀመሩ። መርከቧ እንዳትፈርስና እንድትቆይ፣ ጠባቂዎቿ እያንዳንዱን የበሰበሰ እንጨት እያወጡ በአዲስ እንጨት መቀየር ጀመሩ። ከብዙ ዓመታት በኋላ፣ መርከቧ ስትቆረቆር የነበሩት እንጨቶች አንድም ሳይቀሩ በሙሉ ተቀይረው በአዲስ ተተኩ። በዚህ ጊዜ መሠረታዊው ጥያቄ ተነሳ... «ሁሉም ክፍሎቿ ተቀይረው በአዲስ ከተተኩ በኋላ፣ ይህች መርከብ አሁንም እውን የ Theseus መርከብ ናት ወይንስ ሌላ አዲስ መርከብ ሆናለች?» የTheseus መርከብ ታሪክ የሰው ልጅ ሕይወቱን እንዲፈክር የሚያስገድድ ጥያቄን ነው የሚያነሳው። በሰውነታችን ውስጥ ያሉ cells፣ ሐሳቦቻችን፣ እምነቶቻችንና ልምዶቻችን በጊዜ ሂደት ይቀየራሉ፣ ይታደሳሉ። የዛሬ 10 ዓመት የነበርኩት ሰው እና የዛሬው እኔነቴ ለየቅል ናቸው። የምር እኔ የምለው ማንነቴ የቱን ነው ብዬ እጠይቅና «ያኔ ያለፍኩት እኔ ነኝ፣ ዛሬም ያለሁት እኔ ነኝ» ብዬ እመልሳለሁ። የሰው ልጅ ሁሌ በለውጥ ሂደት ውስጥ ነው። የሰው ልጅ የተጠናቀቀ ፍጡር ነው ብዬ አላምንም። በመሰራት ላይ ያለን ያላለቅን ፍጡሮች ነን። ትናንት በጽኑ ያመንኩበት ነገር ዛሬ በሌላ ዓይን ላየው እችላለሁ። የቀድሞው «እኔ» ሲሞት አዲሱ «እኔ» ይወለዳል። ይህ ለውጥ ክህደት አይመስለኝም። የተፈጥሮ ሕግ ነውና። ውሃ ካልፈሰሰ እንደሚበላሸው፤ የሰው ልጅም እንደዛ ነው። ፊልሙም እንዲህ ያሳስባል! ©Mesoud
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 41 ч | 2 380 |
| 68 ч | 2 720 |
ግላውኮንም ሶቅራጠስን እንዲህ ሲል ያስታዉሰዋል... ሌላውን ሁሉ እስማማለሁ፤ ምንም እንኳ ጠቃሚ ጥቅሞችን ጨምሬ ልናገር ብችልም (ሴቶችም አብረው ቢዋጉ ማንም ሊያሸንፋቸው አይችልም)። ነገር ግን ይህ ሕገ መንግሥት ሊፈፀም ይችላል ወይ፣ እንዴት? ይሄንን ይህ ሁሉ ጊዜ ዘልለኸዋል። ይለዋል። ሶቅራጠስ "ሦስተኛውና ከሁሉ የላቀዉ ማዕበል እየመጣብኝ ነው" ይላል። ቀጥሎም... ፍትሕ ምን እንደሆነ ስንፈልግ ዓላማችን ሞዴል (ምሳሌ /paradigm) ማግኘት ነበር ፤ ፍጹም ፍትሐዊው ሰው ምን እንደሚመስል (ቢኖር)፣ ከዚያ ወደ እሱ የቀረበ ሰው ዕጣውም ወደ እሱ እንደሚቀርብ ለማየት ነዉ። ሰው እንደዚህ ሊኖር እንደሚችል ማሳየት ዓላማችን አልነበረም። አንድ ሰዓሊ ውብ ሰውን በፍጹም መልክ ቢስል፣ ነገር ግን እንደዚህ ያለ ሰው ሊኖር እንደሚችል ማሳየት ባይችል ከሠዓሊነቱ አይቀንስም። እኛም በንግግር የጥሩ ከተማ ሞዴል ሠርተናል። ሁሉም ነገር በንግግር በተገለጸው መንገድ በትክክል ሊፈጸም ይችላል? ተግባር ከንግግር ይልቅ እውነትን ያነሰ ይይዛል። ስለዚህ ማሳየት ያለብን የተገለጸው ከተማ በተቻለ መጠን የቀረበ ሊሆን የሚችልበትን መንገድ ነው። በዘመናችን ከተሞች ምን እንደሚከለክል፣ ወደዚህ ሕገ መንግሥት ለመድረስ ሊደረግ የሚችለው ትንሹ ለውጥ (አንድ፣ ካልሆነ ሁለት፣ ካልሆነ ጥቂት) ምን እንደሆነ እናሳያለን። ይላል። ሶቅራጠስም በማከል ፈላስፎች በከተሞቻቸው እንደ ነገሥታት እስካልገዙ ወይም ዛሬ ነገሥታትና መሪዎች የሚባሉት እውነተኛና በቂ ፈላስፎች ሆነው የፖለቲካ ሥልጣንና ፍልስፍና እስካልተዋሐዱ እና ዛሬ አንዱን ብቻ የሚከተሉ ብዙ ተፈጥሮዎች በግድ እስካልተቀላቀሉ ድረስ ከተሞች ከክፋት ዕረፍት አያገኙም፤ የሰው ልጅም አያገኝም፤ እኛ የገለፅነው ሕገ መንግሥትም በተቻለ መጠን አይወለድም፣ የፀሐይም ብርሃን አያይም። ይላል። ሶቅራጠስም ይህን ለመናገር ለረዥም ጊዜ ያመነታበትን ምክንያት ሲገልፅ... ይህ በጣም የማይታመን ይመስላል፤ ከዚህ ሌላ ከተማ ደስታ (በግልም በሕዝብም) የለም ማለት ነውና። ግላዉኮንም ማስጠንቀቂያ ቢጤ ይሰጠዋል...ብዙ ታዋቂ ሰዎች ካባቸውን አውልቀው የደረሰውን መሣሪያ ይዘው ሊያጠቁህ ይሮጣሉ፤ ራስህን በክርክር ካልተከላከልክ በዚህ ፌዝህ ትቀጣለህም።ይለዋል። በመቀጠል ስቅራጠስ እነዚህን ተቃዋሚዎች ለመቋቋም "ፈላስፋ" ማን እንደሆነ መግለጽ አለብን፤ አንዳንዶች በተፈጥሯቸው ለፍልስፍናና ለመምራት የተሠሩ፣ ሌሎች ደግሞ መከተል የሚገባቸው መሆኑን ማሳየት አለብን ይላል። አንድ ነገር እንወዳለን ስንል የተወሰነውን ክፍል ሳይሆን ሙሉውን እንወዳለን እያልን ነዉ። ለምሳሌ... ወጣት ወዳጅ ወንድ ልጅ በሁሉም ባሕርዩ ምክንያት ያገኛል (አፍንጫው ዘለግ ያለ "ንጉሣዊ"፣ ደፍጣጣ "ቆንጆ"፣ ጥቁር "ወንዳወንድ"፣ የገርጣ "የአማልክት ልጅ")፤ የወይን ወዳጆችም ማንኛውንም ወይን ይወዳሉ፤ ክብር ወዳጆች ጄኔራል ካልሆኑ ሻለቃ ይሆናሉ ክብርን በሙሉ ይመኛሉና። ስለዚህ ፈላስፋ ጥበብን በሙሉ የሚመኝ፣ ሁሉንም ዓይነት ትምህርት በደስታ የሚቀምስና የማይጠግብ ሰው ነው። "የሚመርጥ" ተማሪ (በተለይ ወጣት) ፈላስፋ አይደለም። ልክ ምግብ የሚመርጥ ሰው የተራበ ወይም ምግብ ወዳድ ሳይሆን ምግብ መራጭ እንደሆነ ሁሉ። ግላውኮን በዚህ ላይ ተቃዉሞን ያነሳል፤ እንደዚያ ከሆነ የማየት ወዳጆች (ሁሉንም ትርዒት የሚወዱ) እና የመስማት ወዳጆች (ጆሮአቸው በኮንትራት እንደተከራየ ሰው የዳዮኒሶስ በዓሎችን ሁሉ የሚዞሩ) ፈላስፎች ይሆናሉ? ሶቅራጠስ "አይደሉም፤ እነሱ ፈላስፎችን ይመስላሉ።" እውነተኛዎቹ "እውነትን የማየት ወዳጆች" ናቸው። ውብና አስቀያሚ ተቃራኒዎች ስለሆኑ ሁለት ናቸው፤ እያንዳንዳቸው ደግሞ አንድ ናቸው። ፍትሐዊ/ኢፍትሐዊ፣ መልካም/መጥፎ እና ሁሉም ቅርጾች (forms) እንዲሁ እያንዳንዳቸው በራሳቸዉ አንድ ናቸዉ፤ ነገር ግን ከድርጊቶችና ከአካላት፣ እንዲሁም እርስ በርስ ስለሚዛመዱ ብዙ ሆነው ይታያሉ።ይለዋል። በመቀጠል እነኚህ ፈላስፋ መሳዮች እና እዉነተኛ ፈላስፎች በምን እንደሚለዩ ይገልፅለታል... ፈላስፋ መሳዮች ውብ ድምፆችን፣ ቀለሞችን፣ ቅርጾችንና ከእነሱ የተሠሩ ነገሮችን ይወዳሉ ፤ እዉነተኛ ፈላስፎች ግን ውብ ነገሮችን ብቻ ሳይሆን ውበትን ራሱን ማየትና መውደድ ይችላሉ። ፈላስፋ መሳዮች ሐሳባቸው የውበትን ተፈጥሮ ማየት አይችልም። እዉነተኛ ፈላስፎች ግን ውበትን ራሱን በራሱ ማየት ይችላሉ፤ እንዲህ ያሉ ሰዎችም ጥቂት ናቸው። ፈላስፋ መሳዮች በውብ ነገሮች ያምናሉ፤ በውበት ራሱ ግን አያምኑም፤ ወደ እሱ የሚመራቸውንም መከተል አይችሉም፤ ሕልም ውስጥ ናቸው(ምስልን ከራሱ ነገር ጋር የሚያምታታ ሰው ሕልም እያለመ ነውና)። እዉነተኛ ፈላስፋዎች ግን ውበትን ራሱንና የሚሳተፉበትን ነገሮች ሁለቱንም ያያሉ፤ አያምታቱም፤ ነቅተዋል። ፈላስፋ መሳዮች አስተያየት እና እምነት አላቸው። እዉነተኛ ፈላስፋዎች ግን ዕውቀት አላቸው። አማኝ የሆነ ሰው ተቆጥቶ ቢከራከር እንዴት እናሳምነዋለን? ሶቅራጠስ በገርነት ይጠይቃል። ለራሱም ጥያቄ መልስ ይሰጣል... የሚያውቅ ሰው አንድን ነገር ያውቃል። ያ ነገር ያለ (is) ወይ የሌለ (is not) ነዉ።ያለ፣ የሌለን ነገር ማወቅ አይቻልም። ስለዚህ ሙሉ በሙሉ ያለ ነገር ሙሉ በሙሉ የዕውቀት ዓላማ ነው፤ በምንም መንገድ የሌለ ነገር የድንቁርና ዓላማ ነው። ሁለቱም "ያለ" እና "የሌለ" የሆነ ነገር ቢኖር በንጹሕ መኖርና በንጹሕ አለመኖር መካከል ይሆናል፤ ለእሱም በዕውቀትና በድንቁርና መካከል የሆነ ነገር ያስፈልጋል። እምነት (belief) ከዕውቀት የተለየ "ሃይል" ነው፤ ኃይሎች የሚለዩት በሚመለከቱት ነገርና በሚያደርጉት ነው። ዕውቀት የማይሳሳት፣ እምነት ደሞ የሚሳሳት ስለሆነ ሁለቱ የተለዩ ናቸው። የተለዩ ሃይሎች የተለዩ ነገሮችን ይመለከታሉ፤ ዕውቀት "ያለውን" ስለሚመለከት የእምነት ዓላማ ሌላ ነገር መሆን አለበት። እምነት "የሌለን" ማመን አይችልም (ምንም የማያምን ሰው የለም፤ የሌለ ማለት "ምንም" ማለት ነው)። ስለዚህ እምነት ዕውቀትም ድንቁርናም አይደለም፤ ከዕውቀት ያነሰ ከድንቁርናም የበለጠ እና በመካከላቸው የሚገኝ ነው። ስለዚህ ሁለቱም "ያሉ" እና "የሌሉ" ሊባሉ የሚችሉ ነገሮች የአስተያየት ዓላማ ናቸው። ብዙ ውብ ነገሮችን የሚወደውን ሰው "ከብዙ ውብ ነገሮች ውስጥ አስቀያሚ ሆኖ የማይታይ አለ? ከፍትሐዊዎች ውስጥ ኢፍትሐዊ ሆኖ የማይታይስ?" ብለን ብንጠይቀዉ ሁሉም ተቃራኒ ሆነው እንደሚታዩ መቀበል አለበት። እጥፍ የሆኑ ነገሮች ግማሽም ናቸው፤ ትልቅ፣ ትንሽ፣ ቀላል፣ ከባድ የምንላቸው ከተቃራኒያቸው ባልተናነሰ መልኩ ናቸው። እነዚህ ድግግሞሽ ውስጥ ያሉ ነገሮች እንደ ድግስ ላይ እንቆቅልሾች አጠራጣሪ ናቸው። "ያሉ ወይም የሌሉ፣ ሁለቱም ወይም አንዳቸው" ብሎ መያዝ አይቻልም። ስለዚህ የብዙኃኑ በውበትና በሌሎችም ላይ ያላቸው ብዙ ልማዳዊ ደንቦች በ"የሌለ" እና "ንጹሕ ያለ" መካከል የሚንከባለል ነው። ይቀጥላል... ምንጭ፤ከላይ ከተያያዘዉ መፅሀፍ(Republic) ከገፅ 227 እስከ ገፅ 282
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 45 ч | 2 380 |
| 67 ч | 2 670 |
ሶቅራጠስ አራቱን አንጃነላሹ አገዛዞች ለመግለፅ ሲዘጋጅ ፖሌማርኮስ የአዴይማንቶስን ልብስ ጎትቶ በጆሮው አንድ ነገር ሹክ አለው፤ አዴይማንቶስም "አንለቅህም!" ብሎ ጮኸ ምክንያቱም ሶቅራጠስ ስለ ሴቶችና ልጆች በጋራ መጠቀም(ጓደኞች ሁሉንም በጋራ ይጋራሉ) ብሎ በቀላሉ አልፎ ሄዷል። እነሱም ይህ ሕገ መንግሥቱ ትክክል መሆን አለመሆኑን ሁሉ ይወስናል ብለው ያስባሉ ስለዚህ እንዴት እንደሚደረግ፣ ልጆች እንዴት እንደሚወለዱና እንደሚያድጉ ማብራራት አለበት።ግላውኮንም በዚህ ጣልቃ ይገባል፤ ትራስማኮስም "የሁላችንም ውሳኔ ነው" ይላል። ሶቅራጠስ በማማረር ቅላፄ "ብዙ ክርክር እየቀሰቀሳችሁ ነው፤ ለዚህ ነበር ርዕሱን ዝም ያልኩት።ይላቸዋል። ትራስማኮስም መለስ አርጎ እዚህ የመጡት ክርክር ለመስማት እንጂ ብረት ለማቅለጥ እንዳልሆነ ይነግረዋል። ሶቅራጠስም አንድ ጥያቄ ያቀርብላቸዋል ...ጠባቂ ውሾች ሴቶችና ወንዶች ሲሆኑ፣ ሴቶቹ ከወንዶቹ ጋር መጠበቅና ማደን ላይ ይሳተፋሉ ወይስ ቡችላ በመውለድና በማሳደግ ምክንያት በቤት ይቀራሉ? ግላውኮን "ሁሉንም ይጋራሉ፤ ሴቶችን ግን እንደ ደካማ፣ ወንዶችን እንደ ጠንካራ እንጠቀማለን" ይላል። ከዚያ ሶቅራጠስ ይቀጥላል፤ እንስሳትን ለተመሳሳይ ሥራ ስንጠቀም ተመሳሳይ ትምህርት መስጠት አለብን፤ ስለዚህ ሴቶችም ሙዚቃ፣ የአካል ሥልጠናና ወታደራዊ ሥልጠና ይማራሉ፤ በተመሳሳይ ሥራዎችም ይመደባሉ። ሴቶች (ወጣትም አዛውንትም) ከወንዶች ጋር በአካል ማሠልጠኛ ቦታ ልብስ አልባሳቸውን አውልቀው (ወይም ያለ ካባ) ሲሠለጥኑ ማየት በአሁኑ ሁኔታ አስቂኝ ይሆናል። ግሪኮች በጥንት ወንዶች ራቁታቸውን መታየትን እንደ አሳፋሪና አስቂኝ ይቆጥሩት ነበር፤ ቀርጤሳውያንና ከዚያ ስፓርታውያን ጂምናዚየም ሲጀምሩ ኮሜዲ ጸሐፊዎች አሾፉባቸው። ነገር ግን አዲሱ ልማድ የተሻለ መሆኑ ሲታወቅ ሳቁ ጠፋ። ስለዚህ ከመጥፎና ከሞኝነት ሌላ ነገርን አስቂኝ የሚያደርግ ወይም ከመልካም ሌላ የውበት መለኪያ የሚወስድ ሰው ሞኝ ነው።አላቸዉ። ሶቅራጠስ በመቀጠል ሌላ ሊነሳ የምችለዉን ተቃዉሞ ይጠቅሳል... ከተማ ስንመሠርት እያንዳንዱ በተፈጥሮው የሚስማማውን አንድ ሥራ ይሥራ ብለን ተስማምተን ነበር። ሴትና ወንድ በተፈጥሮ በጣም የተለያዩ ናቸው፤ ታዲያ ተመሳሳይ ሥራ እንዲሠሩ መናገራችሁ ራሳችሁን አይቃረንም? ግላውኮንም ወዲያውኑ ለጥያቄዉ መልስ ያጣለታል። ሶቅራጠስ ግን "ትንሽ ገንዳ ይሁን ወይም ታላቅ ባሕር፣ መዋኘት ግድ ነው" ይላል ዶልፊን እስኪያድነን እንጠብቃለን በማለት የኦሪዮንን ታሪክ ያሳታዉሳቸዋል። በመቀጠልም የጥያቄዉን አጣብቂኝ ወደ መፍታት ይሻገራል... የተቃዋሚው ክርክር በቃል ጨዋታ (eristic) እንጂ በትክክለኛ ተቃርኖ (dialectic) ላይ የተመሰረት አይደለም፤ ምክንያቱም "የተለያየ ተፈጥሮ" ስንል የትኛውን ልዩነት እንደምንመለከት አልመረመርንም። ለምሳሌ መላጦች ጫማ ሠሪ ከሆኑ ረጅም ፀጉር ያላቸው ጫማ ሠሪ መሆን የለባቸውም ልንል እንችላለን? ይህ አስቂኝ ነው፤ ምክንያቱም የምንመለከተው ከሥራው ጋር የሚዛመደውን ልዩነት ብቻ ነው። በሌላ ምሳሌም ብናይ ለሕክምና ተስማሚ ነብስ ያላት ሴትና ወንድ ተመሳሳይ ተፈጥሮ አላቸው፤ ሀኪም እና አናጢ (ሁለቱም ወንዶች ቢሆኑ እራሱ) ግን የተለያየ ተፈጥሮ አላቸው። ሴቷ የምትወልደው፣ ወንዱ የሚያስወልደዉ ልዩነት ብቻ ከሆነ ለከተማ አስተዳደር ሥራዎች ሴት ከወንድ እንደምትለይ እስካሁን አልተረጋገጠም። ለአንድ ሥራ በተፈጥሮ የተስማማ ማለት በቀላሉ ይማራል፣ ከትንሽ ትምህርት ብዙ ያገኛል፣ አካሉ አእምሮውን ያገለግላል ለማለት ነዉ እንጂ በእነዚህ ነገሮች ወንዱ ሁልጊዜ ከሴቷ ይበልጣል፤ሁሉም ሥራ ውስጥ (መሸመንና ምግብ ማብሰልንም ጨምሮ ግላውኮን "ብዙ ሴቶች ከብዙ ወንዶች በብዙ ነገር ይሻላሉ" ይላል፤ በአጠቃላይ ግን እውነት ነው)። ስለዚህ ለከተማ አስተዳደር የሚያገለግል ሥራ በሴትነት ምክንያት ለሴት ወይም በወንድነት ምክንያት ለወንድ የሚመደብ የለም፤ ተፈጥሯዊ ችሎታዎች በሁለቱም ፆታዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ይሰራጫሉ፤ ሴት በሁሉም ሥራ ልትሳተፍ ትችላለች፣ ግን ለሁሉም ዓላማ ከወንድ ደካማ ናት። አንዲት ሴት ለሕክምና ተስማሚ ነች፣ ሌላዋ አይደለችም፤ አንዲት ለሙዚቃ፣ ሌላዋ አይደለችም፤ አንዲት ለአካል ሥልጠናና ለጦርነት፣ ሌላዋ ጦር ጠል ነች፤ አንዲት ፈላስፋ (ጥበብ ወዳድ)፣ ሌላዋ ጥበብ ጠል (misosopher)፤ አንዲት ስሜታዊ፣ ሌላዋ ስሜት የለሽ። ስለዚህ ጠባቂ ለመሆን የተስማማች ሴትም የማትስማማም አለች፤ ተስማሚዎቹ ከወንድ ጠባቂዎች ጋር በተፈጥሮ ዝምድና ያላቸው ናቸው፣ ከወንዶቹ ጋር አብረው መኖርና መጠበቅ አለባቸው። ይህ ሕግ ሊሆን የሚችል ነው ነገር ግን ከተፈጥሮ ጋር የሚስማማ ሲሆን ብቻ። ለከተማ ምርጥ ወንዶችና ምርጥ ሴቶች እንዲኖሩ ከማረግ የተሻለ ነገር የለም፤ የሙዚቃና የአካል ሥልጠና ድብልቅ ይህንን ያደርጋል። ስለዚህ ሴት ጠባቂዎች "በጎነትን እንደ ካባ ይለብሳሉ" በጦርነትና በጥበቃ ይሳተፋሉ፤ ነገር ግን በሴትነት ደካማነት ምክንያት ቀለል ያሉ ሥራዎች ይሰጣቸዋል። ሴቶች ለሚጠቅም ነገር ሲሠለጥኑ የሚስቅ ሰው "ያልበሰለ የጥበብ ፍሬ" እየነጠቀ ነው፤ ምክንያቱም "የሚጠቅመው ውብ፣ የሚጎዳው አስቀያሚ" ነው። ሶቅራጠስም አንድ ማዕበል እንዳስወገደ ይናገራል፤ ግላውኮን ግን "ትንሽ ማዕበል አይደለም" ይላል ፤ ሶቅራጠስም "ቀጣዩን ስታይ ይህ ትንሽ ይመስልሃል" ይለዋል። በመቀጠል ሕጉን ሲያስረዳ ሁሉም ሴቶች ከሁሉም ወንዶች ጋር በጋራ ይሆናሉ፤ አንድ ሴትና አንድ ወንድ በግል ጋብቻ አብረው አይኖሩም፤ ልጆችም በጋራ ይሆናሉ፤ ወላጅ ልጁን፣ ልጅ ወላጁን አያውቅም። ግላውኮን ይህ "ከመጀመሪያው ይልቅ ይበልጥ አጠራጣሪ" እንደሆነ ይናገራል በጥቅሙም ሆነ በመቻሉ። ሶቅራጠስ ግን የመቻል ጥያቄውን ለጊዜው እንዲተው ይለምናል፤ እንደ ሰነፍ ብቻውን በእግር ሲሄድ ለሚያስበው ምኞት በሐሳብ እንደሚደሰት ሰው፣ ከተፈጸመ ገዥዎች እንዴት እንደሚያደራጁትና ለከተማ እንደሚጠቅም ብቻ ይመረምራል። ሴትና ወንድ ጠባቂዎች በጋራ መኖሪያ፣ በጋራ ምግብ፣ በጋራ ሥልጠና ስለሚኖሩ ወደ ግብረ ሥጋ ግንኙነት "በተፈጥሮ ግዴታ" (erotic necessity) ይነሳሳሉ። ነገር ግን ያልተመራ ግንኙነት ከደስተኞች ከተማ ጋር አይስማማም፤ ስለዚህ ጋብቻዎች "በተቻለ መጠን ቅዱስ" ይሆናሉ፤ ቅዱስ ማለት ጠቃሚ ማለት ነው። ሶቅራጠስ በእርባታ ምሳሌም ይመስለዋል፤ ግላውኮንን ስለ አደን ውሾቹና ስለ ወፎቹ ይጠይቃል። ከምርጦቹ ብቻ፣ በወጣትነት ዘመናቸው የሚራቡ ስለሆኑ፣ እንዲህ ካልሆነ ዘሩ ይባባሳል። ሰው ከዚህ የተለየ ካልሆነ ገዥዎች እጅግ ጥሩ መሆን አለባቸው።"መድኃኒት" ሆኖ ዉሸት ሊሆን የሚችል ቀደም ብለን እንዳልነው፤ ውሸትና ማታለል ለገዥዎች እንደ መድኃኒት ጠቃሚ ነው። ምርጦቹ ከምርጦቹ ጋር እንዲጣመሩ፣ ዝቅተኛዎቹ እንዲገደቡ፤ ይህ ሁሉ ከገዥዎች በቀር ማንም ሳያውቅ መከናወን አለበት። በዚህም መሰረት ዝርዝር ሕጉ.... በጋብቻ ወቅት በገዥዎች ሥርዓት የተወሰኑ በዓላትና መሥዋዕቶች ይደረጋሉ፤ ባለቅኔዎች ለጋብቻዎች መዝሙር ይጽፋሉ፤ የጋብቻዎች ቁጥር በገዥዎች ይወሰናል (ከጦርነት፣ ከበሽታ ጋር ተመጣጥኖ የወንዶች ቁጥር እንዲቆይ)። ከዛ በተጨማሪ ብልሃተኛ ዕጣ አወጣጦች ይቋቋማሉ፤ ዝቅተኛ ሰው ገዥዎችን ሳይሆን ዕድልን እንዲወቅስ።በጦርነትና በሌሎች የጥበቃ አገልግሎቶች ጥሩ የሆኑ ወጣቶች ከሌሎች ሽልማቶች በተጨማሪ ከሴቶች ጋር ለመሆን ተጨማሪ ዕድል ያገኛሉ፤ ብዙ ልጆች ከእነሱ እንዲወለዱ።ልጆች ከተወለዱ በኋላ በዚህ ኃላፊነት በተሾሙ ባለሥልጣኖች (ወንድም ሴትም) ይወሰዳሉ፤ የጥሩ ወላጆች ልጆች በከተማዋ በተለየ ክፍል ወደሚገኝ "የሕፃናት ማሳደጊያ" ለልዩ ሞግዚቶች ይሰጣሉ፤ የዝቅተኛ ወላጆች ልጆችና የአካል ጉድለት ያለባቸው ሕፃናት በምስጢራዊና ባልታወቀ ቦታ ይደበቃሉ። እናቶች ወተት ሲሞላ ወደ ማሳደጊያው ይመጣሉ፤ ማንም እናት ልጇን እንዳታውቅ የተለያዩ ዘዴዎች ይተገበራሉ፤ ወተት ካነሰ ሌሎች ሴቶች ያጠባሉ፤ የሌሊት ሥራ ለሞግዚቶች ይሰጣል።ሴት ለከተማ ከ20 እስከ 40 ዓመት፤ ወንድ ከሩጫ ጥንካሬው ጫፍ በኋላ እስከ 55 ዓመት ድረስ ያገለግላል። ከዚህ ዕድሜ ውጭ ወይም ገዥዎች ሳያጣምሩ የተወለደ ልጅ "ሕገ ወጥ፣ ያልተፈቀደ፣ ርኩስ" ተብሎ ይቆጠራል (ያለ መሥዋዕትና ጸሎት በጨለማ የተወለደ ተደርጎ ይታሰባል)። ከዕድሜ ገደብ በኋላ ወንዶችና ሴቶች ከተወሰነ የቅርብ ዘመድ (ሴት ልጅ፣ እናት፣ የልጅ ልጅ፣ የእናት ዘር፣ ወዘተ) በስተቀር ከማንም ጋር ሊሆኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን እርግዝና ቢፈጠር ልጁ እንዳይወለድ ወይም ከተወለደ እንዳያድግ ማዘዝ ይገባል። ማን ማን እንደሆነ እንዴት ያውቃሉ? ይላል ግላዉኮኝ ሶቅራጠስም፣ አያውቁም። ከጋብቻው ቀን በኋላ በ7ኛውና በ10ኛው ወር የተወለዱትን ሁሉ "ልጆቼ" ይሏቸዋል፤ እነሱም "አባቴ፣እናቴ" ይሏቸዋል። የእነዚህ ልጆች ልጆች "የልጅ ልጆች" ፣ የእሱ ቡድን "አያቶች" ይባላሉ፤ ከአንድ ወቅት የተወለዱት "ወንድሞችና እህቶች" ይባላሉ፤ ስለዚህ እርስ በርስ ከመጋባት ይታቀባሉ። ሆኖም ዕጣው ቢያወጣና የዴልፊ ቄስ ቢፈቅድ ወንድም ከእህት ጋር እንዲሆን ሕጉ ይፈቅዳል። ብሎ ይመልሳል። ለከተማ ትልቁ ክፋት የሚበታትናትና ከአንድ ወደ ብዙ የሚያደርጋት ነገር ነዉ፤ ትልቁ መልካም ደግሞ የሚያስተሳስራትና አንድ የሚያደርጋት ነው። ደስታና ሥቃይን በጋራ ማካፈል ያስተሳስራል፤ "የእኔ" እና "የእኔ አይደለም" የሚሉትን ቃላት በአንድነት መጠቀም አለመቻል ይበትናል። ለምሳሌ አንድ ሰው ጣቱን ቢጎዳ መላው ሰውነት (አካልና ነብስ በአንድ ሥርዓት በገዥው ክፍል ሥር የተሳሰሩ) በአንድነት ሥቃዩን ይሰማሉ፤ "ሰዉየዉ ይሠቃያል" ይባላል። የተሻለውም ከተማ ተመሳሳይ ነው ፤ ማንኛውም ዜጋ ደስታ ወይም ሥቃይ ሲያጋጥመው መላው ከተማ "የእኔ ነዉ" ይላል። በሌሎች ከተሞች ገዥዎች ተገዥዎችን "ባሪያዎች" ፣ ተገዥዎች ገዥዎችን "ጌቶች" ይላሉ። በእኛ ከተማ ተገዥዎች ገዥዎችን "አዳኞች/ጠባቂዎችና አጋዥዎች"፣ ገዥዎች ተገዥዎችን "ደመወዝ ከፋዮችና አስተናጋጆች" ይሏቸዋል፤ ገዥዎች እርስ በርስ "አብሮ ጠባቂዎች" ይባባላሉ።ሁሉም ዘመድ ነው። ጠባቂ የተገናኘውን ሁሉ እንደ ወንድም፣ እህት፣ አባት፣ እናት፣ ልጅ ወይም የዘር ሐረግ አባል አድርጎ ይቆጥራል፤ ስሞቹ ብቻ ሳይሆኑ ተግባሮቹም (አክብሮት፣ እንክብካቤ፣ መታዘዝ) ይከተላሉ ፤ አለበለዚያ በአማልክትና በሰዎች ፊት ያልፀደቀ ይባላል። በዚህም ክስና ቅሬታዎች ይጠፋሉ (ከሰውነታቸው ሌላ የግል ንብረት ስለሌላቸው)፤ በሀብትና በቤተሰብ ምክንያት የሚነሣ ጥል አይኖርም። እኩዮች እርስ በርስ እራሳቸውን መከላከል ይችላሉ (ለአካል ብቃት ይጠቅማል፣ ስሜታዊ ቁጣ ወደ ከባድ ጥል እንዳያድግ ይረዳል)፤ ታናናሾች አዛውንቶችን በፍርሃትና በአፍረት ያስተናግዳሉ። በዚህ የህይወት መንገድም ሀብታሞችን ማሞካሸት፣ ልጆችን የማሳደግ ጭንቀት፣ ለቤተሰብ ወጪ ገንዘብ ማግኘት፣ ብድርና ዕዳ የመሳሰሉ ነገሮች አይኖሩባቸዉም። በዚህ የአኗኗር ዘይቤም ጠባቂዎች "ከሁሉ የተባረከው" ከሆነው የኦሊምፒክ አሸናፊዎች ሕይወት የበለጠ ደስተኛ ሆነው ይኖራሉ፤ ምክንያቱም ድላቸው መላውን ከተማ ማዳን ነው፤ ኑሯቸውም ከሕዝብ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ይሸፈናል፤ በሞታቸው ጊዜም ክብር ያለዉ ቀብር ያገኛሉ። ስለዚህ የአዴይማንቶስ ቀደም ብሎ የነበረው ተቃውሞ ( ጠባቂዎች ደስተኛ አይደሉም) ተመልሷል ፤ ዓላማው ከተማዋን በሙሉ ደስተኛ ማረግ ነበር። ጠባቂ በተገባ ኑሮው ካልረካ ሁሉን ለራሱ ለመውሰድ ቢሞክር የሄሲዮድን አባባል "ግማሹ ከሙሉው ይበልጣል" የሚለውን እውነትነት ይማራል። ሶቅራጠስ እዛዉ ላይ በማከል ይጠይቃል ሴቶች ከወንዶች ጋር በትምህርት፣ በልጆችና በጥበቃ ይሳተፉ፤ በከተማ ቢቆዩም በጦርነት ቢወጡ አብረው እንደ ውሾች ይጠብቁና ያድኑ ፤ ይህ ከተፈጥሯቸው ጋር የሚስማማ እንጂ የሚቃረን አይደለም ግላውኮንም "እስማማለሁ" ይላል። የሚቀረው ለሰው ልጆችም ይቻላል ወይ፣ እንዴትስ ይሆናል? የሚለው ነው። ሴቶችና ወንዶች አብረው ወደ ጦርነት ይሄዳሉ፤ ልጆችም ከብቃታቸው በኋላ አብረው ይወሰዳሉ ፤ ልክ የሸክላ ሠሪ ልጆች ሸክላ ከመንካታቸው በፊት ረዥም ጊዜ እንደሚያዩና እንደሚረዱ። ማንኛውም እንስሳ በልጆቹ ፊት በተሻለ ይዋጋል። ግላውኮን አደጋውን ይጠቅሳል (ሽንፈት ቢመጣ ልጆችም ይሞታሉ)፤ ሶቅራጠስ ሁሉንም አደጋ ማስወገድ አይቻልም፤ ዋጋ ያለው አደጋ ብቻ መወሰድ አለበት ይላል። ስለዚህ አባቶች አደገኛ ዘመቻዎችን ያውቃሉ፤ ጥሩ መሪዎች ይሾማሉ፤ ልጆች በፈጣን ፈረሶች ላይ ተጭነዉ አስፈላጊ ሲሆን እንዲሸሹ ይደረጋል። የሚከተሉት የጦር ሕጎችም ይወጣሉ... ቦታውን ትቶ የሸሸ ወይም ጋሻ የጣለ ፈሪ ወደ ሙያተኛ ወይም ገበሬ ደረጃ ዝቅ ይደረጋል። በጠላት በሕይወት የተያዘ ለአጥቂዎቹ እንደ ምርኮ ይሰጣል። በጦርነቱ ጀግንነትን ያሳየ ደሞ አብሮ የሚዘምቱ ወጣቶችና ልጆች ዘውድ ያደርጉለታል፤ እጁን ይጨብጣሉ፤ ማንም እሱ መሳም የሚፈልገውን ሰው ሊከለክል አይችልም፤ ይህም ለሌሎች አርአያ ይሆናል። ያ ደፋር ሰው ለጋብቻም ተጨማሪ ዕድል ያገኛል። በመሥዋዕትና ግብዣዎች የክብር መቀመጫ፣ የምርጥ ሥጋ ቁራጭና የተሞላ ጽዋ ይሰጠዋል። ያማረ እና በክብር የተንቆጠቆጠ ቀብር ይደረግለታል "የወርቅ ዘር" ነው ተብሎም ይታወጃል፤ በሄሲዮድ መሠረት ከሞቱ በኋላ "በምድር የሚኖሩ ንጹሕ ዳይሞኖች" (ከክፋት ጠባቂዎች) ይሆናሉ፤ የአምላክ (አፖሎ) መመሪያ ተከትለው ይቀበራሉ፤ መቃብራቸው የዳይሞን መቃብር ተደርጎ ይመለካል። ተመሳሳይ ክብር በሕይወት ዘመኑ በጣም ጥሩ ሆኖ ለታወቀ ሰው ሞት ይሰጣል። ሌላም ተጨማሪ ሕግ ይወጣል እሱም ከጠላቶቻችን ጋር የምንተዳደርበት ነዉ ሕጉም ይሄን ይመስላል... ባርነትን በተመለከተ ግሪክ ግሪክን አይገዛም፤ ሌሎች ግሪኮችም እንዳያደርጉ ይመከራሉ (ግሪኮች ወደ ባዕዳን እንዲዞሩ)፤ ከጠላት አስክሬን ላይም ከጦር መሣሪያ በስተቀር ማንኛውም ነገር አይወሰድም (አልያ ግን ለስግብግብነትና ፈሪዎችን ሰበብ የሚሰጥ ነው፤ አስከሬንን እንደ ጠላት መቁጠር ትንሽ አእምሮነትና "ሴትነት" ነው፣ ድንጋይ በጣለው ሰው ሳይሆን በድንጋዩ እንደሚናደድ ውሻ ይመስላል) ፤ የግሪክ መሣሪያዎች ወደ መቅደስ አይቀርቡም (ጎሳን ማርከስ ስለሆነ) ፤ የግሪክ መሬት አይወድምም፣ ቤቶች አይቃጠሉም፤ የዓመቱ ሰብል ብቻ ይወሰዳል። ከጥፋተኞች ጥቂቶች ብቻ ይቀጣሉ ፤ አብዛኛው ነዋሪ ወዳጅ ነው። ሶቅራጠስም ሁለቱን ይለያል፤ "ጦርነት" ከባዕድ ጋር የሚደረግ ጠላትነት፣ "አንጃነት" (faction) ከራስ ዘመድ ጋር የሚደረግ ነዉ። ግሪኮች ለራሳቸው ዘመዶች፣ ለባዕዳን ደግሞ ባዕድ ናቸው። ግሪክ ከባዕዳን ጋር ስትዋጋ ጦርነት፤ ግሪክ ከግሪክ ጋር ስትዋጋ ግን "ግሪክ ታማለች፣ ወደ አንጃነት ተከፍላለች" ነው የሚባለው። የእኛ ከተማ ግሪክ ስለሆነች ዜጎቿ ግሪኮችን የሚወዱ ናቸው፤ ከግሪኮች ጋር ያላቸውን ግጭት "አንጃነት" እንጂ "ጦርነት" አይሉትም፤ ዓላማቸውም እርቅ ነው፤ ጠላቶቻቸውንም እንደ "አስተካካዮች" እንጂ እንደ ጠላቶች አይቀጡም።
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 45 ч | 1 930 |
| 67 ч | 2 260 |
Переслано из HATETA Perspective
እርግጥ ነዉ ከላይ የሚታየዉ ስዕል በመስታዉት ዉስጥ የሚታየዉ የወጣቷ ልጅ ምስል ነፀብራቅ አደለም ይልቁንም የአስቃያሚ አሮጊት ምስል ነዉ የሚታየዉ ። እኔ ስለዚህ panting ለማዉራት አይደለም ይልቁንም ወጣት ስለሆንሽዉ እና ስለ ወጣቷ ልጃገረድ ለማዉራት ነዉ ፍላጎቴ ምን መሰለሽ girl ወጣት ነሽ ምናልባትም እንደ ፀደይ አበባ ነሽ እናም ምን ያክል ወጣትነትሽን እየተደሰትሽበት ነዉ ? ማደረግ የምትፈልጊዉንስ ምን ያክል እያደረግሽ ነዉ ? ምን ያክል ከድሪቶ ባህል እና ከሃይማኖት ትብታብ ነፃ ነሽ ? ከማህበረሰቡ አሉታዊ ተፅዕኖ ምን ያክልስ ተላቀሻል ? ኢትዮጵያ ዉስጥ እየኖርሽ ከነዚህ ሁሉ ተፅእኖዎች ምን ያክል ነፃ እንደሆንሽ እርግጠኛ አደለሁም! እናም ይሄን ልነግርሽ እፈልጋለሁ ምናልባትም እድለኛ ሆነሽ በወጣትነሽ ካልሞትሽ ከላይ እንዳለችዉ የወጣቷ ልጅ ምስል ነፀብራቅ እንደሆነችዉ አስቀያሚ ፣ ጨቃጭቃ ፣ነገረኛ ፣ ተራጋሚ ፣ ማድቤት ( ኪችን ) ተቀምጣ በወጣትነቷ ያላደረገችዉን እያሰበች የምትፀፀት ... ብቻ ብዙ አይነት ልትሆኝ እንደምትችይ ከወዲሁ ላስታዉስሽ እፈልጋለሁ! ስለዚህም ወጣቷ ሆይ እልሻለሁ ለማግባት ከመወሰንሽ በፊት ምን ያክል በወሲብ ዘና እንደሚያደርግሽ አረጋግጭ ከነጠረቀኝ በኋላ ትቶኝ ቢሂደስ የሚለዉን እርግፍ አድርገሽ እርሽዉ በምላሹ አንቺም ካልተሰማማሽ ከዚህ ልትሄድልኝ ይገባል በይዉ ዘና ካላደረገሽ ምናባቱን ያደርግልሻልና! ምናልባትም በዙሪያሽ የማለልሽለት ወንድ ካለ እና የምትወጂዉ ከሆነ እንዲነጭሽ ፍቀጅለት ( ግን ጆከር እንዳያሲዝሽ ተጠነቀቂ ) ሰሞኑን አንድ ትሬንድ እየተመለከትኩ ነበር በግልፅ ለመናገር ያክል በቀልድ መስሎ የቀረብ ግን ከጀርባ የሆነ ዓይነት አመፅ የያዘ ይመስላል በታሪክ ዉስጥ እንዲህ በቀልድ እና በምፀት የቀረቡ ሀሳቦች ናቸዉ ወደ እዉነተኛ አብዮት የተቀየሩት በግሌ ትሬንዱ ይቀጥል ብያለሁ! እናም ወጣቷ ሆይ የሚያስደስትሽን ነገር ለማድረግ የማነንም ፈቃድ አትብቂ ወግ ባህል አስጠባቂ ነኝ የሚለዉንም እርሽዉ ምክንያቱም የሀገሪቱ ባህል ከተሸረሸረ ሰንበትበት ብሏል የምዕራቡን ዓለም ባህል በሯን በርግዳ ካስገባችም ቆይታለች ስለዚህ ባህል ወግ አስጠባቂ ነኝ የሚሉ አጫፋሪዎችን እርሻቸዉ ። የሃይማኖት ሰባኪዎችን ቀሳዉስቶችን ፣ ኡስታዞችን ፣ ፓስተሮችን እርሻቸዉ እነሱ ህይወትን በምላዕት እንዳትኖሪ የሚያደርጉ እንቅፋቶች ናቸዉ ። ሀገሪቱም እንደምታያት ሺት የሆነች ሀገር ሁናለች ። ስለዚህም ወጣቷ ሆይ እኔም እልሻለሁ ሃይማኖት ፣ ባህል ፣ ብሔር ፣ ነገድ ሳይገድብሽ የሚያስደስትሽን ነገር እያደረግሽ ኑሪ ከዛም ያ አስቀያሚነት አሮጊትነት ቢመጣ አንዳች ፀፀትም ሆነ ድንጋጤ አይሰማሽም!
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 62 ч | 1 960 |
| 67 ч | 2 030 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 62 ч | 1 830 |
| 67 ч | 1 870 |
MIIRA JECHOOTA@miira_jechootaЦитаты38 тыс.
ጥቀርሻ🧠🗣@tkershaЦитаты1,34 тыс.
قناة | علي آل حوّاء@ali_hawwaЦитаты27,3 тыс.
مستِ مغموم.@mastemaqmomЦитаты25,8 тыс.
off@offmemzЦитаты25,8 тыс.
Neo@yekerankЦитаты27,5 тыс.