Кабинет

Посты канала Munib Network

сначала новые

#16265Фото

የሐጅ ምዝገባ ማስታወቂያ ​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እንኳን ለ2019 ዓ.ል. (1448 ዓ.ሒ) የሐጅ ጉዞ በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል። ​የሳዑዲ ዓረቢያ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር ባካሄደው የአገልግሎት አፈጻጸም ውድድር ጠቅላይ ምክር ቤታችን ባለፈው ዓመት በሰጠው የላቀ አገልግሎት የዳይመንድ ደረጃ ተሸላሚ መሆኑ ይታወቃል። ​ዘንድሮም የትራንስፖርት፣ የምግብ፣ የማረፊያ ቦታ እና ሌሎች አገልግሎቶቹን ፈጣን፣ ተደራሽና ደረጃቸውን የጠበቁ ለማድረግ ከጨረታ አሸናፊ ድርጅቶች ጋር ስምምነት ተፈራርሟል። የምዝገባ ማዕከላትንም በቴክኖሎጂና በሰለጠኑ ባለሙያዎች በማደራጀት ምዝገባ እያከናወነ ይገኛል። ​በመሆኑም ለምዝገባ አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶችንና ቅድመ ሁኔታዎችን የምታሟሉ አማኞች ከታች በተዘረዘሩት የምዝገባ ማዕከላት በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ​ልብ ይበሉ!!! የዘንድሮው የሐጅ ጉዞ ምዝገባ ከታላቁ የረመዳን ወር በፊት ጥር 10 ቀን 2019 ዓ.ም (ሻዕባን 10 ቀን 1448 ዓ.ሒ) ይጠናቀቃል። ​ስለሆነም የሐጅ አዳ እቅድ (ኒያ) ያላችሁ ለሁሉም አገልግሎቶች የተወሰነውን ብር 827,000 (ስምንት መቶ ሀያ ሰባት ሺህ ብር) በክፈል በአቅራቢያችሁ በሚገኙ ማዕከላት እንድትመዘገቡ በድጋሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን። የምዝገባ ማዕከላት፡ 1. ​በአዲስ አበባ 2. ​በፊንፊኔ 3. ​ሮቤ 4. ​በጊኒር 5. ​በጅማ 6. ​በሀረር 7. ​በነገሌ 8. ​በአዳማ 9. ​በጊምቢ 10. ​በጭሮ 11. ​በፉሪ 12. ​በቡሌ ሆራ 13. ​በሞያሌ 14. ​በሻሸመኔ 15. ​በመቱ 16. ወራቤ 17. ​በሀረር 18. ​በሰመራ 19. ​በደሴ 20. በባህር ዳር 21. በከሚሴ 22. ​በጎንደር 23. ​በጋምቤላ 24. በአሶሳ 25. ​በመቐለ 26. ​በቴፒ 27. ​በሶዶ 28. ​በሐዋሳ 29. ​በጅግ ጅጋ 30. ​በጎዴይ 31. ​በሞያሌ 32. ​በዶሎ አዶ 33. ​በድሬደዋ ​ለበለጠ መረጃ፡ • ​በነጻ የስልክ መስመር፡ 9933 • ​የጠቅላይ ምክር ቤቱ ይፋዊ የትስስር ገጾች ​"የህይወት ዘመን ምኞትዎን እውን ለማድረግ በመመዝገብ ሰበብ ያድርሱ!" ​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት Munib_net

Открыть в Telegram
Просмотры1 0300%к среднему
Пересылки—
Реакции4
Комментарии—
#16260Текст
Просмотры4 730+359%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#16256Фото
Просмотры4 780+364%к среднему
Пересылки—
Реакции13
Комментарии—
#16251Фото
Просмотры4 250+313%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—
#16249Текст
Просмотры3 060+197%к среднему
Пересылки—
Реакции5
Комментарии—
#16248Текст
Просмотры3 020+193%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—
#16246Фото

ተማሪ ካሊድ በሽር ከስድስት መቶ 591 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ተማሪ ሆነ! በ2017 ዓ.ል የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 8.4 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ አምጥተዋል ብለዋል ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፡፡ 585 ሺህ 882 ተማሪዎች ፈተናውን መፈተናቸውንም አንስተዋል፡፡ፈተናውን ከወሰዱ 48,929 ተማሪዎች አልፈዋል። በ2017 ዓ.ሌ ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 8.4 ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ፡፡ ሚኒስትሩ የትምህርት ዘመኑን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን አስመልክተው መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ካስመዘገቡት መካከል የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች 5.2 በመቶ፣ ተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ደግሞ 11.4 በመቶ የ እንደሆኑ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠቅሰዋል፡፡ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡም በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 ፦ 591 ወንድ (ተማሪ ካሊድ በሽር) ከዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት፤ 579 ሴት ተማሪ ከብስራተ ገብርኤል ትምህርት ቤት ሲሆኑ በማህበራዊ ሳይንስ ፦562 ወንድ ከአምቦ ቦርዲግ ትምህርት ቤት ፤ 548 ከሴት ከሴንት ጆሴፍ ትምህርት መሆናቸውን ጠቅሰዋል በመግለጫቸው፡፡ በ2017 ዓ.ል የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 1 ሺህ 249 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ የ2017 ዓ.ል የትምህርት ዘመን ማጠናቀቂያን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳሉት 50 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን አሳልፈዋል። Munib_net

Открыть в Telegram
Просмотры6 310+513%к среднему
Пересылки—
Реакции35
Комментарии—
#16245Текст
Просмотры6 590+540%к среднему
Пересылки—
Реакции19
Комментарии—
#16241Фото
Просмотры7 810+658%к среднему
Пересылки—
Реакции14
Комментарии—