Переслано из Wondimu D.
📢 የ1ኛ ሩብ ዓመት ማጠቃለያ ፈተናን በተመለከተ ለወላጆች የተላለፈ ማሳሰቢያ: 📢 🏛️ውድ የማርክ ዩዝ አካዳሚ ወላጆች እና አሳዳጊዎች፤🏛️ እንደምን ሰነበታችሁ! 👋 የልጆቻችንን የትምህርት ጉዞ ውጤታማ ለማድረግ ከትምህርት ቤታችን ጎን በመቆም እያደረጋችሁት ያለው ድጋፍ ትምህርት ቤታችንን እንዲሁም ተማሪዎቻችንን ስኬታማ እና ተሸላሚ ስላደረገው ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን ከወዲሁ እናቀርባለን።🙏🙏🙏 ቀደም ብሎ በተላለፈው የፈተና መርሐ ግብር መልእክት መሠረት፣ የ1ኛ ሩብ ዓመት ማጠቃለያ ፈተና ከነገ ሰኞ ጀምሮ እስከ መጪው ሐሙስ ድረስ የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል። 🗓️ የፈተናው ሂደት በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ይረዳ ዘንድ፣ የሚከተሉትን ወሳኝ ጉዳዮች በድጋሚ ለማስታወስና ተጨማሪ መልእክቶችን ለማሳወቅ እንወዳለን፡- ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 1️⃣ የፈተና መርሐ ግብርን በተመለከተ 🗓️ 🔹 ፈተናው ከሰኞ እስከ ሐሙስ ባሉት ቀናት ውስጥ ቀደም ብሎ በተለጠፈውና ለወላጆች በተላከው መርሐ ግብር መሠረት ይካሄዳል። 🔹 ተማሪዎች በፈተና ቀናት በሰዓቱ ትምህርት ቤት እንዲገኙ ⏰ አስፈላጊውን ክትትል እንድታደርጉ እናሳስባለን። 🔹 ማንኛውም ተማሪ ያለ በቂና አሳማኝ ምክንያት ከፈተና መቅረት አይቻልም። 🚫 ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 2️⃣ ለፈተና የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በተመለከት ✏️🖊️ 🔹 የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተናው የሚሆን የHB እርሳስ ✏️ እና ሰማያዊ እስክሪብቶ 🖊️ ይዘው መምጣት ይኖርባቸዋል። 🔹 ሌሎች ተማሪዎች እስክሪብቶ 🖊️ ይዘው መምጣት የሚጠበቅባቸው ሲሆን፣ እርሳስ መያዝ ግን እንደ አማራጭ ነው። 🔹 ተማሪዎች ከቤት ከመውጣታቸው በፊት ለፈተናው የሚያስፈልጓቸውን ቁሳቁሶች እንዲሁም ደብተራቸውን 🎒📓 መያዛቸውን እንድታረጋግጡ እንጠይቃለን። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 3️⃣ የምግብ ሁኔታን በተመለከተ 🍱 🔹 ከመደበኛ ክፍለ ጊዜ በኋላ በሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት (After-Class Program) የሚማሩ ተማሪዎች እንዲሁም ሁሉም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ምሳ 🍱 ይዘው መምጣት አለባቸው። 🔹 የማጠናከሪያ ትምህርት የማይማሩ እና የ6ኛ ወይም የ8ኛ ክፍል ተማሪ ያልሆኑ ሌሎች ተማሪዎች ግን ምሳ ይዘው መምጣት አይጠበቅባቸውም። 🚫🍱 ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 4️⃣ በፈተና ቀናት (ከሰኞ እስከ ሐሙስ) የመውጫ ሰዓት እና የማጠናከሪያ መርሐ ግብርን በተመለከተ 🕕 🔹 በፈተና ቀናት ፈተናው ከቀኑ 6፡30 ላይ ይጠናቀቃል። በመሆኑም በማጠናከሪያ ትምህርት የማይሳተፉ ተማሪዎችን ከቀኑ 6፡30 ላይ 🕡 መጥታችሁ መውሰድ ትችላላችሁ። 🔹 ሐሙስ ዕለት ከመደበኛ ሰዓት በኋላ የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት (After-Class Program) ለሁሉም ተማሪዎች የማይኖር ሲሆን ልጅዎን 6:00 🕕 መጥተው መዉሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 5️⃣ ዓርብ ዕለት የፈተና ወረቀት መመለሻ መሆኑን በተመለከተ 📄✅ 🔹 ዓርብ ዕለት የፈተና ወረቀቶች ለተማሪዎች መምህራን የሚመልሱበትና የእርማት ችግር ካለ የሚስተካከልበት ቀን ነው። 📝 🔹 በመሆኑም ከፈተና እርማት እና ዉጤት ጋር በተያያዘ የሚመጡ ጥያቄዎች ከዚ ቀን ዉጭ ተቀባይነት አይኖራቸውም:: ⚠️ 🔹 በዚህ ዕለት ሁሉም ተማሪዎች ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ 🕕 ወደ ቤታቸው ስለሚመለሱ፣ ወላጆች በተጠቀሰው ሰዓት ልጆቻችሁን እንድትወስዱ በአክብሮት እናሳውቃለን። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 6️⃣ በፈተና ወቅት ከወላጆች የሚጠበቅ ድጋፍና ክትትልን በተመለከተ 👨👩👧👦❤️ ተማሪዎች ፈተናቸውን በተረጋጋ መንፈስና በከፍተኛ ውጤት እንዲያጠናቅቁ የወላጆች ሚና እጅግ የላቀ ነው። በመሆኑም፡- ✅ በቤት ውስጥ ጸጥ ያለና ለጥናት ምቹ የሆነ ሁኔታ በመፍጠር እንዲያጠኑ ያድርጓቸው። 📚🤫 ✅ በቂ እንቅልፍ እንዲያገኙ 😴 ቀደም ብለው ትምህርት ቤት እንዲገኙ ያድርጉ። ✅ የፈተና ሕግና ደንቦችን እንዲያከብሩና ከማንኛውም ዓይነት ኩረጃ ስርቆት እንዲርቁ በቤት ውስጥ ምክር ይስጡ። ⚖️🚫 ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📌 በመጨረሻም:- ⚠️ ከላይ የተዘረዘሩትን ማሳሰቢያዎች ችላ በማለት ለሚፈጠሩ ችግሮች ኃላፊነቱን የማንወስድ መሆኑን ከወዲሁ እንገልፃለን:: 💳 ወርሐዊ መደበኛ እንዲሁም የAfter class ክፍያ ያልፈፀማችሁ ወላጆች በአስቸኳይ ክፍያውን ይፈፅሙ:: 📞 ከፈተናው ጋር በተያያዘ ማንኛውም ጉዳይ ካጋጠመ ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር በፍጥነት እንድታሳውቁ እየጠየቅን፣ ለተማሪዎቻችን በሙሉ መልካም የፈተና ጊዜ እንመኛለን! 🌟🍀 🏫 የማርክ ዩዝ አካዳሚ አስተዳደር
Открыть в Telegram







