Кабинет
ሊያና ኬር Liyana Care 7755

ሊያና ኬር Liyana Care 7755

➮ የጤና ምክሮች 👨‍⚕️ ➮ ሀኪምዎን ያማክሩ7755 ➮ ቴሌሜዲስን 💉 ➮ በአይነቱ ለየት ያለ ሀክምና📱📲

Юзернейм
@ldhsethiopia
Категория
Медицина
Страна
ЭфиопияЭфиопия
Подписчики5 673
Просмотров на пост, 7 дн.66−58,6% к пред. 7 дн.
ERR1,16 %за 7 дней

Средние просмотры поста по дням

По дню публикации

Показать таблицей
ДатаПросмотров на пост
31 окт. 2026 г.314
7 нояб. 2026 г.252
18 нояб. 2026 г.160
25 нояб. 2026 г.66

Самые просматриваемые за месяц

  1. 01

    ❇️ የሪህ ወይም የጋውት (Gout)ህመም 🔴 ጋውት (Gout) ወይም ሪህ በመገጣጠሚያዎች ላይ ከፍተኛ ህመም፣ እብጠት እና ግትርነት የሚያስከትል የመገጣጠሚያ ህመም ዓይነት ሲሆን በብዛት የእግር አውራ ጣትን ያጠቃል፡፡ 🔷 ይህ ሪህ ሚከሰትው በሰውነት ውስጥ ያለው ዩሪክ አሲድ (uric acid) ከመጠን በላይ በመሆን በመገጣጠሚያዎች ላይ ሲጠራቀም/ክሪስታላይዝ ሲያደርግ የሚከሰት ነው፡፡ · ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ በብዛት ይታያል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት፡ 1️⃣ ኤስትሮጅን (Estrogen) በተባለው ሆርሞን ነው። ኤስትሮጅን ኩላሊት ላይ ዩሪክ አሲድን በሽንት በኩል በፍጥነትና በቀላሉ እንዲወገድ ያደርጋል፤ ስለዚህ ሴቶች ደግሞ ኤስትሮጅን ከወንዶች ይልቅ በብዛት ስላላቸው ነው፡፡ ደግሞም እድሜያቸው የገፋ ሴቶች ላይ ወይም ያረጡ ሴቶች ላይ የሪህ ተገላጭነታቸው ልክ እንደ ወንዶቹ ይሆናል ምክንያቱም የኤስትሮጅን መጠን ስለሚቀንስ ነው። 2️⃣ወንዶች ከሴቶች በላይ ዩሪክ አሲድን ስለሚያመርቱ ነው፡፡   🗯መንስኤዎች 🔵 በደም ውስጥ የዩሪክ አሲድ መብዛት (Hyperuricemia) ዋነኛው መንስኤ ነው። ይህም የዩሪክ አሲድ ከመጠን በላይ በመመረቱ ወይም ኩላሊት በትክክል ማስወገድ ባለመቻሉ ይከሰታል። 🎯ዋና ዋና ተጋላጭነቶች 🔔 ከመጠን በላይ ውፍረት፣ የደም ግፊት፣ የስኳር በሽታ፣ ስር የሰደደ የኩላሊት በሽታ እና የአልኮል ሱሰኝነት🍻 ናቸው። ስለዚህ ሁሉም ህሙማን ለእነዚህ ሁኔታዎች ምርመራ ሊደረግላቸው ይገባል። እንዲሁም ደግሞ በቤተሰብ ውስጥ የሪህ ታሪክ መኖር፡፡ 💥 ዋና ዋና ምልክቶች 🔸የሪህ ህመም በድንገት የሚነሳና ተደጋግሞ የሚመጣ ሲሆን፣ በሂደት የመገጣጠሚያ ህብረህዋሳትን (tissues) ሊጎዳ ይችላል። 📌ዋናው ምልክቱ ከፍተኛ የሆነ የመገጣጠሚያ ህመም ወይም ቁርጥማት ሲሆን🦵፣ ቦታው ሊያብጥና ቀለሙም ሊቀየር ይችላል። 🌙 ምልክቶቹ ብዙውን ጊዜ በሌሊት ስለሚጀምሩ እንቅልፍን ይረብሻሉ፤ የተጠቃው መገጣጠሚያም ሊያብጥ፣ ሊገታተር ወይም ሊሞቅ ይችላል። 📌ከአውራ ጣት በተጨማሪ ቁርጭምጭሚት፣ ጉልበት፣ ክርን💪፣ በእጅ አንጓ 🫳 ወይም በጣቶች🖖 ላይም ሊዳብር ይችላል። 📌አጣዳፊ🏃‍♂️‍➡️ የሪህ ህመም ከተነሳ ከ6 እስከ 12 ሰዓታት ባለው ጊዜ ውስጥ በጣም የሚበረታ ሲሆን፣ አብዛኛውን ጊዜ ከአንድ ሳምንት ገደማ በኋላ እፎይታ ይገኛል። ⚙️ ይህ ችግር በድንገት የሚጀምር አጣዳፊ (Acute) ወይም በተደጋጋሚ የሚከሰቱ እና ዘላቂ ምልክቶች ያሉት ሥር የሰደደ (Chronic) ሊሆን ይችላል።   💉የህክምና እና የመድኃኒት እንክብካቤ 📎 ሕክምናው በአብዛኛው በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን ያካትታል። እነዚህ መድኃኒቶች ምልክቶችን ለማከም፣ የወደፊት እብጠቶችን ለመከላከል እና ለመቀነስ ይረዳሉ። 💊የብግነትና ህመም ማስታገሻዎች (NSAIDs እና corticosteroids) እብጠትንና ህመምን ይቀንሳሉ። ሌሎች መድኃኒቶች ደግሞ የዩሪክ አሲድ ምርትን ይቀንሳሉ ወይም በኩላሊት ከሰውነት ውስጥ የማስወገድ ችሎታን ያሻሽላሉ። 🥗 የምግብ አጠቃቀም እና የህይወት ዘይቤ እንክብካቤ 🔰የምግብ ስርዓትን ማስተካከል ብቻውን ሪህን ለመቆጣጠር በቂ ባይሆንም፣ አስፈላጊና ለህመሙ መሻሻል በጣም ጠቀሜታ አለው፡፡ መገደብ ያለባቸው ምግቦች፡- 🥩ሥጋ (በቀይ ሥጋ ዓይነቶች መካከል ምንም ልዩነት የለም፡ የበሬ፣ በግ፣ የፍየል ሥጋ) 🍺 ቢራዎችን ጨምሮ የአልኮል መጠጦች (ቀይ ወይን በመጠኑ ዝቅተኛው አደጋ አለው) 🧋ከፍተኛ ስኳር የያዙ መጠጦች እና ምግቦች ሚበረታቱ ምግቦች፡- 🥛ወተት እና የወተት ተዋጽኦዎች 🥙ፍራፍሬዎች እና አትክልቶች 🥚እንቁላል 🧆ባቄላ፣ አተር፣ ሽምብራ ✳️ተጨማሪ አስፈላጊ ምክሮች: 🧍‍♂️ከመጠን በላይ ውፍረት ባላቸው ግለሰቦች ላይ ክብደት መቀነስ ይበረታታል፡፡ 🩺 በበሽታው የተያዙ ሁሉም ታካሚዎች ከፍተኛ የደም ግፊት፣ የስኳር በሽታ እና የደም ውስጥ ቅባት (dyslipidemia) መመርመር አለባቸው። ------------------------------------------------------- ለተጨማሪ መረጃ  ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448

    Превью ссылки
    Просмотры358
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—
  2. 02

    ✳️ " የብርሃን" ሌባ ”👁 ❇️ ግላኮማ ምንድን ነው? 🔻 ግላኮማ የዓይንን ኦፕቲክ ነርቭ (Optic Nerve) በመጉዳት ለእይታ ማጣት ወይም ሙሉ ለሙሉ ለዓይን ብርሃን ማጣት የሚያጋልጥ በሽታ ነው። 📈 ጠቅላላ መረጃ 🔸 በግላኮማ በሽታ ከተያዙ ሰዎች መካከል ግማሾቹ በበሽታው መያዛቸውን አያውቁም፡፡ 🔸በአለም አቀፍ ደረጃ በሁለተኛ ደረጃ ከፍተኛ የዓይን ብርሃን ማጣትን የሚያስከትል በሽታ ነው ግላኮማ 🔸 በአብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ከሞራ (Cataract) ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ለዓይን ብርሃን ማጣት ዋነኛ ምክንያት ነው 🔸አፍሪካውያን ከነጮች ጋር ሲነፃፀሩ በግላኮማ (በተለይም በ Primary Open Angle Glaucoma) የመያዝ እድላቸው ከ 3 እስከ 4 እጥፍ የላቀ ነው። 🎯ኖርማል የዓይን ግፊት ሚባለው ከ10 እስከ 21mmHg ነው።   ⚠️ ለግላኮማ በሽታ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች እና መንስኤዎች   📍ማንኛውም ሰው በግላኮማ ሊያዝ ይችላል፤ ነገር ግን አንዳንዶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው፣ ከእነዚህም ውስጥ፡ 1️⃣🗜የዓይን ግፊት መጨመር (Intraocular Pressure - IOP)፦ ለብዙዎቹ የግላኮማ አይነቶች ዋነኛ የተጋላጭነት እና የመንስኤ ምክንያት ነው። የዓይን ግፊት መጠን እየጨመረ በሄደ ቁጥር በግላኮማ የመያዝ እድል ይጨምራል። የዓይን ግፊት  ከ20 እስከ 25 mmHg ክልል ውስጥ በሚሆንበት ጊዜ በግላኮማ ምክንያት ለዓይን ብርሃን ማጣት ከ14 እስከ 15 ዓመታት ሊወስድ ይችላል፡፡ ነገር ግን የዓይን ግፊት ከ 40 mmHg በላይ ከሆነ በጥቂት ወራት ውስጥ ለዓይን ብርሃን ማጣት ሊዳርግ ይችላል። ለ የዓይን ግፊት እንዲጨምር የሚያደርጉ ምክንያቶች፦ 1.  የዓይን ፈሳሽ ምርት መጨመር 2.  የዓይን ፈሳሽ መውጫ መንገድ መዘጋት ወይም መከልከል፦ ይህ በጣም የተለመደው መንስኤ ነው። 3.   የ ኤፒስክሌራል (Episcleral) ግፊት መጨመር፦ ከ 8 mmHg በላይ የ Episcleral venous ግፊት የሚፈጥር ማንኛውም የዓይን፣ የጭንቅላት ወይም ሌላ ሁኔታ የዓይን ግፊትን ሊጨምር ይችላል። 2️⃣👨‍🦳ዕድሜ፡- ከ 40 እስከ 70 ዓመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ የበሽታው ስርጭት 4% እስከ 5% ሲሆን፣ በ 80 ዓመት እድሜ አካባቢ ወደ 10%-15% ከፍ ይላል፤ ሆኖም በየትኛውም የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ሰዎችን ሊያጠቃ ይችላል፡፡ 3️⃣ 👥 የቤተሰብ ታሪክ፡- ከወላጆች አንዱ በግላኮማ ከተያዘ የልጆች ተጋላጭነት 5 እጥፍ ይጨምራል። ከወላጅ በተጨማሪ ወንድም ወይም እህት ከተያዙ ተጋላጭነቱ ወደ 9 እጥፍ ያድጋል፡፡ 4️⃣ 🍯 የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች። 5️⃣ 🧬 ዘር፡- ጥቁር ህዝቦች ከካውካሺያን (ነጮች) ጋር ሲነፃፀሩ በ Primary Open Angle Glaucoma (POAG) የመያዝ እድላቸው በ 4 እጥፍ የላቀ ነው 6️⃣💊መድሃኒቶች ፡ የስቴሮይድ (Steroid) መድኃኒቶችን መጠቀም፤ በተለይም በዓይን ጠብታ መልክ የሚወሰዱት ከፍተኛ ተጋላጭነት አላቸው። ዴክሳሜታሶን (Dexamethasone) በጣም ብርቱው የስቴሮይድ የዓይን ጠብታ ሲሆን፣ የመድኃኒቱ የጠብታ ብዛትና ድግግሞሽ በጨመረ ቁጥር ተጋላጭነቱ ይጨምራል።   🤒የሕመም ምልክቶች እና የሕክምና ግኝቶች 🧐ድንገተኛ ከፍተኛ የዓይን ህመም፣ የዓይን መቅላት እና ለብርሃን ተጋላጭ መሆን (Photophobia)። 🤢የማቅለሽለሽ፣ የማስታወክ እና የአንድ ጎን የጭንቅላት ህመም (Hemi-cranial headache)። 🫩የዕይታ በፍጥነት መቀነስ፣ ብዥታ (በጢስ የተሞላ ክፍል የመመልከት ያህል💨) እና በብርሃን ዙሪያ የቀስተደመና ከበብ🌈   🩺 ሕክምና 📌ግላኮማን ሙሉ በሙሉ ለመከላከል የሚታወቅ መንገድ ባይኖርም፣ ቀድሞ መመርመር እና ህክምና መጀመር የዓይን ብርሃን ማጣትን ለመከላከል ያለውን እድል ይጨምራል። 📌 በቅድመ ደረጃ በሽታውን ለማወቅ ብቸኛው መንገድ ዘወትር የዓይን ምርመራ ማድረግ ነው። 📌የግላኮማ ፋውንዴሽን (The Glaucoma Foundation) በ 40 ዓመት እድሜ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የመነሻ ምርመራ (Baseline test) እንዲደረግ ይመክራል። 📌ሐኪሙ የመነሻ ምርመራ ውጤቱን በመጠቀም ወደፊት የሚመጡ ለውጦችን ለመከታተል ይጠቀምበታል። እንደ ግለሰቡ የተጋላጭነት ደረጃ ሐኪሙ ምን ያህል ጊዜ የዓይን ምርመራ ማድረግ እንዳለበት ይመክራል 📌ግላኮማ በአይን ውስጥ ያለውን ግፊት ለመቀነስ በአይን ጠብታዎች፣ በአፍ የሚወሰድ መድኃኒት ወይም በቀዶ ጥገና (ወይም በተለያዩ የሕክምና ዓይነቶች) ይታከማል። እነዚህ ሕክምናዎች ዘላቂ የሆነ የእይታ መጥፋትን መከላከል ወይም ማዘግየት ይችላሉ። ------------------------------------------------------- ለተጨማሪ መረጃ  ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448

    Превью ссылки
    Просмотры297
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—
  3. 03
    Просмотры271
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—
  4. 04
    Просмотры206
    Пересылки—
    Реакции—
    Комментарии—

Новые посты

#8224Превью ссылки

📣ማይግሬኔ ተነሳብኝ ወይም ማይግሬን አለብኝ ሲባል ሰመተዋል? 🧠 ስለ ማይግሬን (Migraine) 📌ማይግሬን ተራ የራስ ምታት ሳይሆን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴን፣ የሥራ እና የትምህርት ቀናትን በእጅጉ የሚያስተጓጉል የነርቭ ሥርዓት ሕመም ነው። ሕመሙ በቤተሰብ የመተላለፍ (የዘር ውርስ) ባህሪ ያለው ሲሆን፣ በሴቶች ላይ በብዛት ይከሰታል። ♦️የማይግሬን  ሕመም በሁለት ዋና ዋና ዓይነቶች ይከፈላል፡ ኦራ ያለው (Migraine with aura) እና ኦራ የሌለው (Migraine without aura)። በተጨማሪም በወር ውስጥ በሚታዩት ምልክቶች ቀናት ብዛት መሠረት በየጊዜው የሚመጣ (Episodic - ከ14 ቀን ያነሰ) እና ሥር የሰደደ (Chronic - በወር 15 ወይም ከዚያ በላይ ቀናት) ተብሎ ይመደባል። ⚠️ ዋና ዋና ምልክቶች 💥 ጽኑ የራስ ምታት: በአንድ ወይም በሁለቱም በኩል የሚወጋ/የሚመታ ኃይለኛ ሕመም። ☀️ 🔊 ለብርሃንና ድምፅ አላስፈላጊ ስሜታዊነት (Photophobia & Phonophobia): ብርሃንና ተራ ድምፅን መቋቋም አለመቻል። 🖐 ለትንሽ ንክኪ  በጣም ስሜታዊ መሆን (Allodynia): ፀጉር ሲበጠር ወይም ፊት ትራስ ሲነካ የሚሰማ ሕመም። 🤢 የማቅለሽለሽና የማስታወክ ስሜት። 💫 የአእምሮ ብዥታ (Brain fog)፣ የማዞር ስሜት፣ የአንገት መወጠር እና የጆሮ ዝም ብሎ መጮህ(Tinnitus)። ⏳ የማይግሬን 4 ደረጃዎች 1️⃣ ቅድመ-ምልክት (Prodrome): ከሕመሙ 1-2 ቀናት በፊት የሚታይ፤ የባህሪ/የሙድ ለውጥ፣ የምግብ ፍላጎት መጨመር፣ የጡንቻ መወጠር፣ የትኩረት ችግር፣ ድካም፣ ማዛጋት፣ ለመተኛት መቸገር፣ ለትንሽ ድምፅ በጣም ስሜታዊ መሆን እና ደጋግሞ መሸናት። 2️⃣ ኦራ (Aura): በጥቂት ሰዎች ላይ ከ5 ደቂቃ እስከ 1 ሰዓት የሚቆይ፤ የብርሃን ብልጭታዎችን ማየት፣ የእጅና እግር መደንዘዝ ወይም በብዙ አካላዊ ክፍሎች ላይ የመቆጥቆጥ ስሜት። 3️⃣ የራስ ምታት ደረጃ (Headache): ከጥቂት ሰዓታት እስከ 3 ቀናት (72 ሰዓታት) ሊቆይ የሚችል ጽኑ ምታት፤ ጨለማና ጸጥተኛ ቦታ መፈለግ። 4️⃣ ድህረ-ምልክት (Postdrome): ሕመሙ ካለፈ በኋላ የሚሰማ የሰውነት ድካም፣ የጡንቻ ቁስለት እና የማተኮር ችግር። 💥 ሕመሙን የሚያቀሰቅሱ ምክንያቶች 😨ዛል/ጭንቀት (Stress) ወይም ከጭንቀት በኋላ የሚመጣ እፎይታ።  😴 የእንቅልፍ መዛባት (በቂ አለመተኛት ወይም አብዝቶ መተኛት)። 💧 የሰውነት ውሃ እጥረት (Dehydration)። 🌧 የአየር ንብረትና የከባቢ አየር ጫና (Barometric pressure) ለውጥ። 💡 🔊 ከፍተኛ ብርሃን፣ ጮክ ያለ ድምፅ እና የሽቶ/ጽዳት ዕቃዎች ሽታ። 🍷 💊 የተወሰኑ ምግቦች፣ የአልኮል መጠጦች እና የመድኃኒት አጠቃቀም (የጽንስ መከላከያና የሕመም ማስታገሻዎችን አብዝቶ መጠቀም)። 🚨 የማይግሬን ሕመም ተጋላጭነት መንስኤዎች 📌ማይግሬን  በማንኛውም ሰው ላይ ሊከሰት ቢችልም፣ ከተወሰኑ ተፈጥሯዊና ባዮሎጂያዊ ሁኔታዎች ጋር ተያይዞ በስፋት ይስተዋላል። ዋና ዋናዎቹ የተጋላጭነት መንስኤዎች የሚከተሉት ናቸው፡ 🧬 የዘር ውርስ እና ጄኔቲክስ: ማይግሬን በቤተሰብ የመተላለፍ ከፍተኛ ባህሪ ያለው የነርቭ ሕመም ነው። 👩 ፆታ: ሴቶች ከወንዶች ይልቅ በማይግሬን ሕመም የመጠቃት ዕድላቸው በእጅጉ የጎላ ነው። ይህም በዋናነት በሰውነት ውስጥ ካለው የኤስትሮጅን (Estrogen) ሆርሞን ለውጦች ጋር የተያያዘ ነው። 🩸 የሆርሞን ለውጦች እና ወርሃዊ ዑደት: ሴቶች ከወርሃዊ የደም አበባ (Menstruation) በፊት ወይም በኋላ ባሉት ቀናት የኤስትሮጅን መጠን በመቀነሱ ምክንያት ለማይግሬን  ሕመም ይጋለጣሉ። በተጨማሪም የፅንስ መከላከያና የሆርሞን ምትክ መድኃኒቶች ሕመሙን ሊያባብሱት ይችላሉ። 👶 👨 ዕድሜ : አብዛኞቹ በማይግሬን የሚያዙ ሰዎች የመጀመሪያውን የሕመም ስሜት የሚያስተናግዱት ከ40 ዓመት ዕድሜ በፊት ነው። ሆኖም ማይግሬን በሕፃንነት ወይም በልጅነት ጨምሮ በማንኛውም የዕድሜ ክልል ውስጥ ሊጀምር ይችላል። 🛡 መከላከያና ሕክምና 📓 የሕመም ማስታወሻ (Headache diary) መያዝ: ሕመሙን የሚያቀሰቅሱ ሁኔታዎችን መዝግቦ መለየትና ማስወገድ። • 🏃‍♂️ የአኗኗር ዘይቤ ማሻሻያ: በቂ እንቅልፍ፣ መደበኛ የምግብ ሰዓትና መደበኛ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ። 💊 የመድኃኒት ሕክምና: ሕመሙ ሲነሳ ምልክቶችን የሚያስታግሱ ወይም የሕመሙን መደጋገምና ጽኑነት የሚከላከሉ መድኃኒቶችን በሐኪም ትዕዛዝ መጠቀም። ------------------------------------------------------- ለተጨማሪ መረጃ  ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448

Открыть в Telegram
Просмотры67−66%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#8222Превью ссылки

✳️አልማዝ ባለጭራ፣ Shingles (herpes zoster) ምንድን ነው? 📌 የአልማዝ ባለጭራ ቫሪሴላ ዞስተር(varicella-zoster virus, VZV) በተባለ ቫይረስ የሚመጣና ከባድ የማቃጠል ስሜት ያለው የቁስል ሽፍታ የሚያስከትል የቆዳ ህመም ነው፡፡   🔷ህመሙ የሚከሰተው ቀደም ብሎ ኩፍኝ (Chickenpox) አጋጥሞን የነበረ ከሆነ እና ቫይረሱ (VZV) በሰውነታችን ተደብቆ ቆይቶ ልክ የበሽታ መከላከል አቅማችን ሲቀንስ እንደገና በሚቀሰቀስበት ወቅት ነው።   🔆 ተጋላጭነት   🔰ማኛውም ሰው በኩፍኝ (Chickenpox) የተያዘ ሰው አልማዝ ባለጭራ(herpes zoster) ሊይዘው ይችላል፡፡ በተለይ ደግሞ እድሚያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ላይ በብዛት ይገጥማል ምክንያቱም በሽታ የመከላከል አቅማቸው ስለሚቀንስ ነው፡፡   🌀 የአልማዝ ባለጭራ ተጋላጭነትን ሊጨምሩ የሚችሉ ሌሎች ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡   📍የተዳከመ የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅም፦ እንደ ኤችአይቪ ኤድስ፣ ካንሰር ፣ የአካል ክፍሎች ንቅለ ተከላ እና እንዲሁም የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅምን የሚቀንሱ  መድኃኒቶች ተጋላጭነቱን ሊጨምሩ ይችላሉ።   📍ውጥረት፦ ከፍተኛ የውጥረት ጊዜያት የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅምን ለጊዜው ሊያዳክሙት ይችላሉ፤ ይህም የአልማዝ ባለጭራ ህመም እንዲከሰት ሊያነሳሳ ይችላል።   📍የተወሰኑ የጤና እክሎች፦ እንደ የስኳር በሽታ፣ ሥር የሰደደ የኩላሊት በሽታ እና የሳንባ በሽታ ያሉ ሁኔታዎች አደጋውን ሊጨምሩ ይችላሉ።   🔎 ዋና ዋና ምልክቶች    🔻ሽፍታው ከመውጣቱ በፊት በቆዳ ላይ የሚሰማ ከባድ የመውጋት፣ የማቃጠል ወይም የመቆርቆር ህመም። 🔻በሰውነት በአንድ በኩል ብቻ የሚወጣ ፈሳሽ የያዘ ሽፍታ ወይም አረፋ። 🔻ትኩሳት፣ የራስ ምታት እና የድካም ስሜት። 🚨 ማስታወሻ፡ ሽፍታው በዓይን አካባቢ ከተከሰተ አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ያስፈልጋል   👥 እንዴት ይተላለፋል?   🧩 አልማዝ ባለጭራ(herpes zoster) በራሱ ከሰው ወደ ሰው ባይተላለፍም፣ በውሃ የቋጠሩት እብጠቶች ፈሳሽ አማካኝነት ቫይረሱን ከዚህ በፊት ኩፍኝ (Chickenpox) ላልያዛቸው ወይም ክትባቱን ላልወሰዱ ሰዎች ሊያስተላልፍ ይችላል። ሆኖም እነዚያ ሰዎች የሚይዛቸው ኩፍኝ (Chickenpox) እንጂ አልማዝ ባለጭራ(herpes zoster) አይደለም፤ እብጠቶቹ አንዴ ከደረቁና ቅርፊት ካወጡ በኋላም የመተላለፍ ዕድሉ እጅግ አነስተኛ ነው። 🩺 ሕክምና 💊አልማዝ ባለጭራ(herpes zoster) ዋነኛ ሕክምና እንደ አሳይክሎቪር (acyclovir) ያሉ የፀረ-ቫይረስ መድኃኒቶችን (antiviral medications) መውሰድ ነው፤ እነዚህ መድኃኒቶች የሚከተሉትን ጥቅሞች ይሰጣሉ፦   🔸የበሽታውን ክብደት እና የሚቆይበትን ጊዜ ለመቀነስ 🔸የጤና እክሎች (complications) የመከሰት ዕድሉን ለመቀነስ ⚠️የፀረ-ቫይረስ መድኃኒቶች ይበልጥ ውጤታማ የሚሆኑት ሽፍታው ከታየ በ72 ሰዓታት ውስጥ መወሰድ ከጀመሩ ነው። ሌሎች የሕክምና አማራጮች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦ 🙂የሕመም ማስታገሻዎች፦ ያለ ሐኪም ትዕዛዝ የሚገዙ እንደ አይቡፕሮፌን (ibuprofen) ወይም ፓራሲታሞል/ (paracetamol) ያሉ የሕመም ማስታገሻዎች ሕመሙን ለመቆጣጠር ይረዳሉ። 🧴የካላሚን ሎሽን (Calamine lotion) ወይም ሰውነትን ማቀዝቀዝ (cool compresses)፦ እነዚህ ቆዳን ለማለስለስና ማሳከክን ለማስታገስ ይረዳሉ። 🧼ሽፍታውን በንጽሕና እና በደረቁ መያዝ፦ ይህ ተጨማሪ የባክቴሪያ ኢንፌክሽኖችን ለመከላከል ይረዳል።   ♨️የጤና እክሎች ✅ የአልማዝ ባለጭራ(herpes zoster)በጣም የተለመደው የጤና እክል ፖስትሄርፔቲክ ኒውራልጂያ (Postherpetic Neuralgia - PHN) ሲሆን፤ ይህም ሽፍታው ከዳነ በኋላ እንኳን ለወራት ወይም ለዓመታት ሊቆይ የሚችል የማያቋርጥ የነርቭ ሕመም ነው። ይህ ሕመም ከባድ እና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴን የሚያስተጓጉል (አቅም የሚያሳጣ) ሊሆን ይችላል። 💉ኩፍኝ (Chickenpox)ክትባት እና አልማዝ ባለጭራ(herpes zoster)  🖇 ኩፍኝ (Chickenpox)ክትባት (የቫሪሴላ ክትባት) በዕድሜ እየገፉ ሲሄዱ የአልማዝ ባለጭራ(herpes zoster) በሽታ የመያዝ አደጋን ሊቀንስ ይችላል። 🔖የኩፍኝ (Chickenpox) ክትባት የተዳከመ የቫሪሴላ-ዞስተር ቫይረስ (VZV) ስሪት ይይዛል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት የኩፍኝ (Chickenpox ክትባት የወሰዱ ልጆች በተፈጥሮው ኩፍኝ (Chickenpox) ከያዛቸው ልጆች ጋር ሲወዳደሩ ለአልማዝ ባለጭራ(herpes zoster) የመጋለጥ ዕድላቸው በከፍተኛ ሁኔታ አነስተኛ ነው። ------------------------------------------------------- ለተጨማሪ መረጃ  ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448

Открыть в Telegram
Просмотры176−11%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#8218Превью ссылки

✳️ " የብርሃን" ሌባ ”👁 ❇️ ግላኮማ ምንድን ነው? 🔻 ግላኮማ የዓይንን ኦፕቲክ ነርቭ (Optic Nerve) በመጉዳት ለእይታ ማጣት ወይም ሙሉ ለሙሉ ለዓይን ብርሃን ማጣት የሚያጋልጥ በሽታ ነው። 📈 ጠቅላላ መረጃ 🔸 በግላኮማ በሽታ ከተያዙ ሰዎች መካከል ግማሾቹ በበሽታው መያዛቸውን አያውቁም፡፡ 🔸በአለም አቀፍ ደረጃ በሁለተኛ ደረጃ ከፍተኛ የዓይን ብርሃን ማጣትን የሚያስከትል በሽታ ነው ግላኮማ 🔸 በአብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት ከሞራ (Cataract) ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ለዓይን ብርሃን ማጣት ዋነኛ ምክንያት ነው 🔸አፍሪካውያን ከነጮች ጋር ሲነፃፀሩ በግላኮማ (በተለይም በ Primary Open Angle Glaucoma) የመያዝ እድላቸው ከ 3 እስከ 4 እጥፍ የላቀ ነው። 🎯ኖርማል የዓይን ግፊት ሚባለው ከ10 እስከ 21mmHg ነው።   ⚠️ ለግላኮማ በሽታ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች እና መንስኤዎች   📍ማንኛውም ሰው በግላኮማ ሊያዝ ይችላል፤ ነገር ግን አንዳንዶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው፣ ከእነዚህም ውስጥ፡ 1️⃣🗜የዓይን ግፊት መጨመር (Intraocular Pressure - IOP)፦ ለብዙዎቹ የግላኮማ አይነቶች ዋነኛ የተጋላጭነት እና የመንስኤ ምክንያት ነው። የዓይን ግፊት መጠን እየጨመረ በሄደ ቁጥር በግላኮማ የመያዝ እድል ይጨምራል። የዓይን ግፊት  ከ20 እስከ 25 mmHg ክልል ውስጥ በሚሆንበት ጊዜ በግላኮማ ምክንያት ለዓይን ብርሃን ማጣት ከ14 እስከ 15 ዓመታት ሊወስድ ይችላል፡፡ ነገር ግን የዓይን ግፊት ከ 40 mmHg በላይ ከሆነ በጥቂት ወራት ውስጥ ለዓይን ብርሃን ማጣት ሊዳርግ ይችላል። ለ የዓይን ግፊት እንዲጨምር የሚያደርጉ ምክንያቶች፦ 1.  የዓይን ፈሳሽ ምርት መጨመር 2.  የዓይን ፈሳሽ መውጫ መንገድ መዘጋት ወይም መከልከል፦ ይህ በጣም የተለመደው መንስኤ ነው። 3.   የ ኤፒስክሌራል (Episcleral) ግፊት መጨመር፦ ከ 8 mmHg በላይ የ Episcleral venous ግፊት የሚፈጥር ማንኛውም የዓይን፣ የጭንቅላት ወይም ሌላ ሁኔታ የዓይን ግፊትን ሊጨምር ይችላል። 2️⃣👨‍🦳ዕድሜ፡- ከ 40 እስከ 70 ዓመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ የበሽታው ስርጭት 4% እስከ 5% ሲሆን፣ በ 80 ዓመት እድሜ አካባቢ ወደ 10%-15% ከፍ ይላል፤ ሆኖም በየትኛውም የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ሰዎችን ሊያጠቃ ይችላል፡፡ 3️⃣ 👥 የቤተሰብ ታሪክ፡- ከወላጆች አንዱ በግላኮማ ከተያዘ የልጆች ተጋላጭነት 5 እጥፍ ይጨምራል። ከወላጅ በተጨማሪ ወንድም ወይም እህት ከተያዙ ተጋላጭነቱ ወደ 9 እጥፍ ያድጋል፡፡ 4️⃣ 🍯 የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች። 5️⃣ 🧬 ዘር፡- ጥቁር ህዝቦች ከካውካሺያን (ነጮች) ጋር ሲነፃፀሩ በ Primary Open Angle Glaucoma (POAG) የመያዝ እድላቸው በ 4 እጥፍ የላቀ ነው 6️⃣💊መድሃኒቶች ፡ የስቴሮይድ (Steroid) መድኃኒቶችን መጠቀም፤ በተለይም በዓይን ጠብታ መልክ የሚወሰዱት ከፍተኛ ተጋላጭነት አላቸው። ዴክሳሜታሶን (Dexamethasone) በጣም ብርቱው የስቴሮይድ የዓይን ጠብታ ሲሆን፣ የመድኃኒቱ የጠብታ ብዛትና ድግግሞሽ በጨመረ ቁጥር ተጋላጭነቱ ይጨምራል።   🤒የሕመም ምልክቶች እና የሕክምና ግኝቶች 🧐ድንገተኛ ከፍተኛ የዓይን ህመም፣ የዓይን መቅላት እና ለብርሃን ተጋላጭ መሆን (Photophobia)። 🤢የማቅለሽለሽ፣ የማስታወክ እና የአንድ ጎን የጭንቅላት ህመም (Hemi-cranial headache)። 🫩የዕይታ በፍጥነት መቀነስ፣ ብዥታ (በጢስ የተሞላ ክፍል የመመልከት ያህል💨) እና በብርሃን ዙሪያ የቀስተደመና ከበብ🌈   🩺 ሕክምና 📌ግላኮማን ሙሉ በሙሉ ለመከላከል የሚታወቅ መንገድ ባይኖርም፣ ቀድሞ መመርመር እና ህክምና መጀመር የዓይን ብርሃን ማጣትን ለመከላከል ያለውን እድል ይጨምራል። 📌 በቅድመ ደረጃ በሽታውን ለማወቅ ብቸኛው መንገድ ዘወትር የዓይን ምርመራ ማድረግ ነው። 📌የግላኮማ ፋውንዴሽን (The Glaucoma Foundation) በ 40 ዓመት እድሜ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የመነሻ ምርመራ (Baseline test) እንዲደረግ ይመክራል። 📌ሐኪሙ የመነሻ ምርመራ ውጤቱን በመጠቀም ወደፊት የሚመጡ ለውጦችን ለመከታተል ይጠቀምበታል። እንደ ግለሰቡ የተጋላጭነት ደረጃ ሐኪሙ ምን ያህል ጊዜ የዓይን ምርመራ ማድረግ እንዳለበት ይመክራል 📌ግላኮማ በአይን ውስጥ ያለውን ግፊት ለመቀነስ በአይን ጠብታዎች፣ በአፍ የሚወሰድ መድኃኒት ወይም በቀዶ ጥገና (ወይም በተለያዩ የሕክምና ዓይነቶች) ይታከማል። እነዚህ ሕክምናዎች ዘላቂ የሆነ የእይታ መጥፋትን መከላከል ወይም ማዘግየት ይችላሉ። ------------------------------------------------------- ለተጨማሪ መረጃ  ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448

Открыть в Telegram
Просмотры297+50%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#8216Превью ссылки

❇️ የሪህ ወይም የጋውት (Gout)ህመም 🔴 ጋውት (Gout) ወይም ሪህ በመገጣጠሚያዎች ላይ ከፍተኛ ህመም፣ እብጠት እና ግትርነት የሚያስከትል የመገጣጠሚያ ህመም ዓይነት ሲሆን በብዛት የእግር አውራ ጣትን ያጠቃል፡፡ 🔷 ይህ ሪህ ሚከሰትው በሰውነት ውስጥ ያለው ዩሪክ አሲድ (uric acid) ከመጠን በላይ በመሆን በመገጣጠሚያዎች ላይ ሲጠራቀም/ክሪስታላይዝ ሲያደርግ የሚከሰት ነው፡፡ · ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ በብዛት ይታያል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት፡ 1️⃣ ኤስትሮጅን (Estrogen) በተባለው ሆርሞን ነው። ኤስትሮጅን ኩላሊት ላይ ዩሪክ አሲድን በሽንት በኩል በፍጥነትና በቀላሉ እንዲወገድ ያደርጋል፤ ስለዚህ ሴቶች ደግሞ ኤስትሮጅን ከወንዶች ይልቅ በብዛት ስላላቸው ነው፡፡ ደግሞም እድሜያቸው የገፋ ሴቶች ላይ ወይም ያረጡ ሴቶች ላይ የሪህ ተገላጭነታቸው ልክ እንደ ወንዶቹ ይሆናል ምክንያቱም የኤስትሮጅን መጠን ስለሚቀንስ ነው። 2️⃣ወንዶች ከሴቶች በላይ ዩሪክ አሲድን ስለሚያመርቱ ነው፡፡   🗯መንስኤዎች 🔵 በደም ውስጥ የዩሪክ አሲድ መብዛት (Hyperuricemia) ዋነኛው መንስኤ ነው። ይህም የዩሪክ አሲድ ከመጠን በላይ በመመረቱ ወይም ኩላሊት በትክክል ማስወገድ ባለመቻሉ ይከሰታል። 🎯ዋና ዋና ተጋላጭነቶች 🔔 ከመጠን በላይ ውፍረት፣ የደም ግፊት፣ የስኳር በሽታ፣ ስር የሰደደ የኩላሊት በሽታ እና የአልኮል ሱሰኝነት🍻 ናቸው። ስለዚህ ሁሉም ህሙማን ለእነዚህ ሁኔታዎች ምርመራ ሊደረግላቸው ይገባል። እንዲሁም ደግሞ በቤተሰብ ውስጥ የሪህ ታሪክ መኖር፡፡ 💥 ዋና ዋና ምልክቶች 🔸የሪህ ህመም በድንገት የሚነሳና ተደጋግሞ የሚመጣ ሲሆን፣ በሂደት የመገጣጠሚያ ህብረህዋሳትን (tissues) ሊጎዳ ይችላል። 📌ዋናው ምልክቱ ከፍተኛ የሆነ የመገጣጠሚያ ህመም ወይም ቁርጥማት ሲሆን🦵፣ ቦታው ሊያብጥና ቀለሙም ሊቀየር ይችላል። 🌙 ምልክቶቹ ብዙውን ጊዜ በሌሊት ስለሚጀምሩ እንቅልፍን ይረብሻሉ፤ የተጠቃው መገጣጠሚያም ሊያብጥ፣ ሊገታተር ወይም ሊሞቅ ይችላል። 📌ከአውራ ጣት በተጨማሪ ቁርጭምጭሚት፣ ጉልበት፣ ክርን💪፣ በእጅ አንጓ 🫳 ወይም በጣቶች🖖 ላይም ሊዳብር ይችላል። 📌አጣዳፊ🏃‍♂️‍➡️ የሪህ ህመም ከተነሳ ከ6 እስከ 12 ሰዓታት ባለው ጊዜ ውስጥ በጣም የሚበረታ ሲሆን፣ አብዛኛውን ጊዜ ከአንድ ሳምንት ገደማ በኋላ እፎይታ ይገኛል። ⚙️ ይህ ችግር በድንገት የሚጀምር አጣዳፊ (Acute) ወይም በተደጋጋሚ የሚከሰቱ እና ዘላቂ ምልክቶች ያሉት ሥር የሰደደ (Chronic) ሊሆን ይችላል።   💉የህክምና እና የመድኃኒት እንክብካቤ 📎 ሕክምናው በአብዛኛው በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን ያካትታል። እነዚህ መድኃኒቶች ምልክቶችን ለማከም፣ የወደፊት እብጠቶችን ለመከላከል እና ለመቀነስ ይረዳሉ። 💊የብግነትና ህመም ማስታገሻዎች (NSAIDs እና corticosteroids) እብጠትንና ህመምን ይቀንሳሉ። ሌሎች መድኃኒቶች ደግሞ የዩሪክ አሲድ ምርትን ይቀንሳሉ ወይም በኩላሊት ከሰውነት ውስጥ የማስወገድ ችሎታን ያሻሽላሉ። 🥗 የምግብ አጠቃቀም እና የህይወት ዘይቤ እንክብካቤ 🔰የምግብ ስርዓትን ማስተካከል ብቻውን ሪህን ለመቆጣጠር በቂ ባይሆንም፣ አስፈላጊና ለህመሙ መሻሻል በጣም ጠቀሜታ አለው፡፡ መገደብ ያለባቸው ምግቦች፡- 🥩ሥጋ (በቀይ ሥጋ ዓይነቶች መካከል ምንም ልዩነት የለም፡ የበሬ፣ በግ፣ የፍየል ሥጋ) 🍺 ቢራዎችን ጨምሮ የአልኮል መጠጦች (ቀይ ወይን በመጠኑ ዝቅተኛው አደጋ አለው) 🧋ከፍተኛ ስኳር የያዙ መጠጦች እና ምግቦች ሚበረታቱ ምግቦች፡- 🥛ወተት እና የወተት ተዋጽኦዎች 🥙ፍራፍሬዎች እና አትክልቶች 🥚እንቁላል 🧆ባቄላ፣ አተር፣ ሽምብራ ✳️ተጨማሪ አስፈላጊ ምክሮች: 🧍‍♂️ከመጠን በላይ ውፍረት ባላቸው ግለሰቦች ላይ ክብደት መቀነስ ይበረታታል፡፡ 🩺 በበሽታው የተያዙ ሁሉም ታካሚዎች ከፍተኛ የደም ግፊት፣ የስኳር በሽታ እና የደም ውስጥ ቅባት (dyslipidemia) መመርመር አለባቸው። ------------------------------------------------------- ለተጨማሪ መረጃ  ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448

Открыть в Telegram
Просмотры358+81%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—
#8214Превью ссылки

🔴 ኩፍኝ (Measles) 🔷ኩፍኝ በኩፍኝ ቫይረስ የሚከሰት፣ በክትባት መከላከል የሚቻል እና በከፍተኛ ሁኔታ የሚተላለፍ ህመም ነው። 🦠 ምልክቶቹ እንዴት ይከሰታሉ 🔅ቫይረሱ በአፍ 👄፣ በአፍንጫ 👃 ወይም በአይን 👁 በኩል ገብቶ በሳንባ 🫁 እና በደም አማካኝነት ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ይሰራጫል። እናም ቫይረሱ ወደ ቆዳ ሲደርስ የኩፍኝ ሽፍታ ምልክት ያስከትላል። ወደ ሳንባ ሲደርስ የሳንባ ምች ያደርሳል 🫁። 🧠ወደ አንጎል ሲደርስ የአንጎል እብጠት ያደርሳል እናም ወዘተ... 🔄 እንዴት ይስፋፋል? 🔅በሽታው ተላላፊ ነው። የሲዲሲ (CDC) ዘገባ እንደሚያመለክተው አንድ ሰው ሽፍታው ከታየ ከ4 ቀናት በፊት እና ከታየ ከ4 ቀናት በኋላ ቫይረሱን ማስተላለፍ ይችላል ⏱️። 🔘ኢንፌክሽኑ በሚከተሉት መንገዶች ይተላለፋል 🤝 ኩፍኝ ካለበት ሰው ጋር አካላዊ ግንኙነት 🤧 ኩፍኝ ካለበት ሰው ጋር ሲሳል ወይም ሲያስነጥስ በአቅራቢያ መሆን 🛑 ቫይረሱ ያለበትን ቦታ ነክተው ከዚያም ጣቶችን ወደ አፍ ውስጥ በማስገባት ወይም አፍንጫን ወይም አይንን በማሸት 👁 አንድ ሰው ካሳለ ወይም ካስነጠሰ በኋላ ቫይረሱ በአየር ላይ ለ2 ሰዓታት ያህል ንቁ ሆኖ ይቆያል 💨። 🔅አንድ ሰው ኩፍኝ ካለበት፣ በሽታ የመከላከል አቅም ከሌለው ወይም ክትባቱን ካልወሰደ በስተቀር እስከ 90% ለሚሆኑ ሰዎች ሊያስተላልፈው ይችላል 📈። 🧑‍🤝‍🧑ኩፍኝ ሰዎችን ብቻ ነው የሚያጠቃው ። 🚫🐾 ማንኛውም የእንስሳት ዝርያ ሊያስተላልፈው አይችልም ። 🩺 ዋና ዋና ምልክቶች 🌡 ከፍተኛ ትኩሳት፣ የአፍንጫ ፈሳሽ፣ ሳል 😷፣ የአይን መቅላት እና የአፍ ውስጥ ነጠብጣቦች (Koplik's spots) ይታያሉ። ✨ ከጥቂት ቀናት በኋላ በሰውነት ላይ የሚሰራጭ የቆዳ ሽፍታ ይወጣል። ⚠️ የሚያስከትላቸው የጤና ጉዳቶች 🫁 የሳንባ ምች (bronchopneumonia)፣ 👂 የጆሮ ኢንፌክሽን፣ ህመሙ የምግብ ፍላጎትን ስለሚቀንስ የምግብ እጥረት (risk of malnutrition) 🍽 ያመጣል እና እስከ ማየት ማጣት የሚያደርስ የአይን ቁስለትን ያስከትላል 👁‍🗨። 🧠 በ 1,000 ታካሚዎች ውስጥ በ 1 ሰው ላይ ገዳይ ሊሆን የሚችል የአንጎል እብጠት ሊያመጣ ይችላል። 🛡 መከላከያ እና ሕክምና 💉 መከላከያ: ዋናውና አስተማማኙ መንገድ የኩፍኝ ክትባት መከተብ እና ከታመመ ሰው ጋር የሚደረግ ንክኪን ማስወገድ ነው። 💊 ሕክምና: የታመመውን ሰው መለየት 🛏፣ በቂ ፈሳሽና አልሚ ምግብ መስጠት 🥣፣ በሕክምና ትዕዛዝ የሚሰጡ የቪታሚን ኤ (Vitamin A) መውሰድ 💊፣ የትኩሳት ማስታገሻ (Paracetamol) 🌡 እና የአይን ቅባት መጠቀምን ያካትታል። ------------------------------------------------------- ለተጨማሪ መረጃ  ወደ 7755 በመደወል ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡📲ቴሌግራም፡ @ldhsethiopia መተግበሪያችን: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.liyanadigitalhealth.liyanacare https://apps.apple.com/us/app/liyana-care/id1572231448

Открыть в Telegram
Просмотры338+71%к среднему
Пересылки—
Реакции—
Комментарии—

Все посты

Связи