Переслано из Christ Life Reflection || የክርስቶስ ሕይወት ነጸብራቅ
❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓ ✨በቅርቡ ከተለቀቁ የመዝሙር አልበሞች ውስጥ የትኛው የመዝሙር አልበም እናድርሳቹ የምትፈልጉትን መርጣቹ የሚመጣላቹሁን መንፈሳዊ ቻናል ተቀላቀሉ
Открыть в TelegramПереслано из Christ Life Reflection || የክርስቶስ ሕይወት ነጸብራቅ
❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓ ✨በቅርቡ ከተለቀቁ የመዝሙር አልበሞች ውስጥ የትኛው የመዝሙር አልበም እናድርሳቹ የምትፈልጉትን መርጣቹ የሚመጣላቹሁን መንፈሳዊ ቻናል ተቀላቀሉ
Открыть в Telegram7 እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እመለከታለሁ፥ የመድኃኒቴንም አምላክ ተስፋ አደርጋለሁ፤ አምላኬም ይሰማኛል። * 8 ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ። * ት/ሚክ 7:7
Открыть в Telegramእንደገና ተነስ *-*-*-*-*-*-*-*-*-* በትጋት ውስጥ ነበርክ መውደቅ አልፈለክም ግና በማታውቀው ምክንያት መውደቅ አላቆምክም በድውይ ብትያዝ ሺ ብትታመምም ህይወት እንዲቀጥል መብላት አታቆምም መብላት ባትፈልግም ምን ባትሆን ደህና ታግለህ ትበላለህ ነገህ እንዲቃና መፀለይ ባትፈልግ መንፈስህ ተዳክሞ ህይወትህ ቢደክም ዳግም ባይመስልህም የምታየው ቆሞ ቃል ለማሰላሰል ባይኖርህ ፍላጎት መንፈሳዊ ስርዓት ማድረግህ አታቁም በቁም እንዳትሞት በቃ ወድቅያለው ዳግም አልነሳም ብለህ እንዳትቆርጥ ተስፋ ማረኝ ከምትልበት ከፀጋው ዙፋን ስር በፍፁም አትጥፋ በርትተህ እንደደከምክ ስትደክምም ለመበርታት በድጋሚ ተነስ በርከክ በልና ከቸሩ አባትህ የምህረት ልብስ ልበስ መፀለይ አታቁም ቃሉን ዙውትር አጥና ጠፍተህ ቢሆን እንኳን ምታመልከው አምላክ አለው እንደገና ✍ኤርሚያስ ክፍሌ react And Share @Kegetemku_leyesus
Открыть в Telegramአለምን አምኜ አለምን አምኜ አምላኬን ፈትኜ እንዲህ አድርግ ብዬ ከትዛዝ ባላነሰ ውርርድ ካላረከውማ ብዬ ፎክሬበት ከሰማይ ካልወረድክ መልሴ የዘገዬ የቀረ ሲመስለኝ ዓለም ደግሞ መጥታ ነይ እኔጋ ስትለኝ ባየው አንጋጥጬ ሰማይ ዝም ብሎአል ዓለም ደጃፌ ላይ ደስታ ሳቅ ክብር ተሰብስቦአል ታዲያ ያኔ ስለምነው ዝም ካለኝ ጩኼ ጩኼ ካልመለሰ ከሱ ጋራ እኔ ምን አለኝ ብዬ አለምን ተከትዬ ከቤት ወጣሁ በብር በወርቅ በመጠጡ ጮቤ ረገትኩ ማን እንደኔ ደስተኛ ማለት ጀመርኩ በከበቡኝ እልፍ ሰዎች ባሳዬችኝ ክብር ሰከርኩ መች ገብቶኝ በሰው ምሃል ለብቻዬ እንደቀረሁ መች አወቄ በሳኩ ቁጥር እልፍ ለቅሶ እንዳፈራሁ ዓለም ሆዬ በጉብዝናዬ ወራት ለአምላኬ ቃል እንዳልገዛ በ ብልጭልጭ ሽፍና ሬቱን በማር ቀብታ አጠፋችኝ እንደ ዋዛ እልፍ አበባ ይዛ አዱኛ ሰብስባ እንደከበበችኝ አበባው ሲረግፍ አዱኛው ሲደርቅ ባዶ አደረገችኝ እንዲህ ነበር ዓለም ከ እግዜር የለዬችኝ ግን እዉነት ሲገባኝ የዓለም ማንነት በልቤ ታወሰኝ ያ የአባቴ ቤት ሁሉ የሞላበት የምወደድበት እንደ ሎሌ ሳይሆን ልጅ የምሆንበት መጣሁ ወደ ደጅ ፈራ ተባ ብዬ ገና ከሩቅ ሲያየኝ እጆቹን ዘርግቶ እቅፍ አረገና ሳመኝ አባብዬ. ✍Tesfa Degu ✍✍ React And Share @Kegetemku_Ieyesus
Открыть в Telegramእምባ ለካስ ያምራል😭😭 እምባ ለካ ያምራል ሲታይ ያስደስታል ከ አይን እየወጣ ልብን የሚያፅናና ከምድር አርቆ ሚያስብል አየሱስ ና ለካስ ልቅሶ አለ ልብ ዉስጥ ሚገባ ስምህን እየጠራደግሞ ወደሌላው ረሃብን ሚያጋባ ስላንተ ሚለቀስ ፍቅርህ አይሎበት ክብርህ መገለጡ እጅግ እጅግ ናፍቆት ክብርህ ከላይ ወርዶ በምድር ላይ ከብዶ ትዉልድ ሁሉ አንተን አይቶ ጌትነትህን ሁሉም አዉቆ ማራናታ ማለታችን አንተን ናፍቀን የከበደ ያንተን ክብር ተመልክተን አንተን አንተን እንድንል ጌታ እየሱስ ያንን የጥንቱን ዘመን ክብር መልስ ደግሞ በኛ ዘመን ክብርህ ብቻ ይስራ ስምህን ብቻ ሰምቶ ፍጥረት ሁሉ አንተን ይፍራ. ✍✍✍Tesfa Degu✍✍✍ React And Share @Kegetemku_leyesus
Открыть в Telegramጊዜ የለንም እንጂ *-*-*-*-*-* ቃልህን ለመስማት፣ከእግርህ ስር መቀመጥ በመንፈስ ለመሞላት ለመዋል ለመስመጥ በምድራችን እንዲሆን የክብርህ ደመና ሪቫይቫል ሊሆን ዛሬም እንደገና መንፈስ ሲሰራ በልጆችህ ጎልቶ እኛ እንመኛለን ትጋታችን ጠፍቶ ጊዜ የለንም እንጂ ታውቃለህ ልባችን የተገለጠ ነው አንተ መውደዳችን የኑሮው ሁኔታ ባይለን ኖሮ ግድ ላንተ መገኘት ነው ምንሻው የነፍሳችን ውድ ቃልህ ማሰላሰል ስንፀልይ ለመዋል እኛ እንወዳለን ሁሉን ታውቀዋለህ ጌታ ሆይ ጊዜ የለን ጊዜ እኮ የለንም እንላለን ግብዞች ጊዜን የሚሻሙ አበጅተን ጣዖቶች ላንተ ቦታ የለንም ፍቅራችን ቀንሷል ደባል ጣዖታችን መኖርያ ቀልሷል ላንተ የለንም እንጂ ጊዜ እኮ አናጣም ለሳቅ ለጨዋታ በህይወታችን ላይ እየሆኑብን ነው ሚዲያዎች ጌታ ጊዜ የለኝም በዝቷል ለቃልህ እና ፀሎት ውድ የሆነው ጊዜ ለጠላቱ ሰጥቶት ላንተ ጊዜ ሳይሆን ያጣነው ፍቅር ነው አብልጠን እንድንወድህ ልባችን ፈውሰው ላንተ ያለኝ ፍቅር ስለጠፋ ከውስጤ ስለቀነሰብኝ ድምፅህን ማድመጤ ስለከበደብኝ ላንተ መገዛቴ በማይጠቅሙ ጣዖት ስለሞላ ቤቴ በዚህ ከቀጠልኩኝ ስለማልሆን ደህና ፍቅርህ በልቤ ይፍሰስ ዛሬም እንደገና ልቤን ፈውስልኝ ልውደድህ አብዝቼ ፊትህን ልፈልግ ደጆቼ ዘግቼ ጣዖቶች አይኑሩኝ አንተ ብቻ ግዛኝ ሌላ እስካያምረኝ በመንፈስህ ንካኝ ፍቅርህ ይንካኝ እንጂ የትም የሚባክን ብዙ ጊዜ አለኝ ልክ የወደድኩህ ቀን ሁሉን ነገር ትቼ ካንተ ጋር ነው ምገኝ ✍ኤርሚያስ ክፍሌ react And Share @Kegetemku_leyesus
Открыть в TelegramПереслано из Hebron Evangelical Ministry🔥
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟 ★እናቴን የምወዳትና የምኖርላት በቅርበት ስለማውቃት ነው፡፡ ይህም፦ የመጀመሪያው ማን እንደሆነች፣ ሲቀጥል ምን ያህል እንደምትወደኝና ለኔ ምን ያህል እንዳደረገች ስለማውቅ ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ የማደርገውን ሁሉ የማደርግላት ከፍቅር❤️ የተነሳና እንዲሁም ደስ😊 እያለኝ ነው፡፡ 👉ክርስትናም እንዲሁ ነው👈 ክርስትና የሚጀምረው ክርስቶስ ኢየሱስን ከማወቅ እና ለእኛ ካለው ፍቅር የተነሳ ምን ያህል ዋጋ እንደከፈለ እንዲሁም ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግስት እንዴት እንዳገባን ስንረዳ ነው፡፡ ይህ ሲገባን ነው ለእግዚአብሄር እንደሚገባ መኖር የምንጀምረው፡፡ ክርስትና ከስራ አይጀምርም ከእምነት እንጂ ፤ ነገር ግን እምነት ውስጥ ባለ ስራ ይገለጣል፡፡ (ያቆ 2፥26) አንድ ጊዜ ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ በተናገረው ምሣሌ ላስደግፍላችሁ፦ "አንድ ልብሱ የቆሸሸበት ሰው ልብሱን ለማፅዳት ብዙ ይታገላል ፣ የተቻለውንም ሁሉ አድርጎ ለማፅዳት ቢሞክርም ከልብሱ የበዛ ማደፍ የተነሳ ሊያፀዳ አልተቻለውም። በዚህ አጋጣሚ አንድ ሰው ሲታገል ያየውና የራሱን ንፁህ ልብስ ሰጥቶት፤ የእርሱን ቆሻሻውን ልብስ ያስወግደዋል፡፡" ከዚህ በሗላ ይህ ሰው👈......... ልብሱን ለማፅዳት መታገል ነው ያለበት🤔?ወይስ..... እንዳይቆሽሽበት ጥንቃቄ ማድረግ ነው ያለበት🤔🤔??? ምላሹ ግልፅ ነው🤗 👉 እንዳይቆሽሽ ጥንቃቄ ማድረግ ነው ያለበት! እንዳንረክስ ከሚያደርጉን ነገሮች ባለን ጥንቃቄ ስራችን ይገለጣል እንጂ ለፅድቅ ነው ብሎ መመፃደቅ በታላቁ አምላክ የተደረገልንን ታላቅ ስራ እንደማናናቅ ነው፡፡ ስለዚህ ክርስትና 1. ታላቅ አምላክ -እርሱን ስናውቅ (ቆላ 1፥15-20) 2. ታላቅ ስራ - በእርሱ የሆንነውንና የተደረገልንን ስናውቅ (ቆላ 2፥9-23) 3. ታላቅ ኑሮ- ለእርሱ የሚመጥን ኑሮ ስንኖር ነው፡፡(ቆላስይስ 3 ፤ 4፥1-2) ክርስትናችን በእነዚህ ቅደም ተከተል ካልሆነ በቀር ፍሬአልባ ፣ የማስመሠልና የግዳጅ ነው የሚሆንብን፡፡( እናትህን ሳታውቃት ውደዳትና ኑርላት ማለት በርግጥ ይከብዳል፡፡ ምንም እናትህ እንኳን ብትሆን አብረሃት ካልኖርክና ካላወቃት ምክንያታዊ ፍቅር አይኖርህም፡፡ ነገር ግን አብረሃት ከኖርክ በደንብ ታውቃታለህ ፤ ማንም ስላለህ ሳይሆን ደስ እያለህ ትወዳታለህ ደስ እያለህም ትኖርላታለህ፡፡ ክርስትናም ልክ እንዲሁ ነው፡፡ ያመንከውንና ያወቅከውን እግዚአብሔር ስትኖርለት ለእርሱ በመኖር ውስጥ በሚገጥሙህ በማናቸውም ውጣ ውረዶች ደስተኛ ትሆናለህ😊 ምክንያቱም ያመንከውን ታውቀዋለህ😎፡፡(ቆላ 1፥24 ፤ ሐዋ 5፥41) ያላወከውን እግዚአብሔር በምን ሒሳብ ትወደዋለህ?😱 በምንስ ሁኔታ ትኖርለታለህ?🤔) እግዚአብሔርን እንወደዋለን እንላለን ግን አንወደውም ፣ እናውቀዋለን እንላለን ግን አናውቀውም ፣ በአንደበታችን እናከብረዋለን ግን ከልባችን አይደለም፡፡ ከዚህም የተነሳ እኛና ክርስትናችን ለየቅል ናቸው፡፡🙅♂ ስለዚህ እግዚአብሔርን እንወቀው እናውቀውም ዘንድ እንፈልግ ፤ <እርሱ ያለምክንያት ወዶናልና እኛ ደግሞ በምክንያት እንውደደው> " እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።" (1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:19) ✍በረከት ተስፋዬ 👇Join to channal 👇 https://t.me/Holiness_unto_lord
Открыть в Telegramአልጥፋ ከስርህ ጠዋት ሆነ ማታ በቀንና ሌሊት ስትጠራኝ እንድገኝ ዘወትር አንተ ፊት መገኛዬ ይሁን ሁሌም ከእግርህ ስር አልጥፋ ከፊትህ አምላኬ እግዚአብሔር. የልብህን ሃሳብ ፈቃድ ሁሉ አውቄ ላንተ እንድኖርልህ ይህን ዓለም ንቄ ሁነኝ መዋያዬ መጥቼ የማርፍበት ሁሉን እረስቼ አንተን ምሰማበት. በቃ ኢየሱሴ አልጥፋ ከስርህ ወዳንተ ቀርቤ ይበልጡን እንዳውቅህ አንተን ተጠግቶ ዓለምን ያቀለለ አለቅህም ብሎ የሙጥኝ ያለ መዋያ ማደሪያው ክብርህ ውስጥ ነውና አልጥፋ ከስርህ ልወቅህ እንደገና. ልውደደው ቃልህን ሕይወት የሆነውን ቀድሜ እንድገኝ ይህን ክፉ ዘመን ስትጠራኝ ነቅቼ ተናገር እንድልህ አስተምረኝ ጌታ አልጥፋ ከስርህ. ✍️ሃና መኮንን @kegetemku_leyesus
Открыть в Telegram..........እኔ እንዳልናገር ተናገረኝ ብዬ ወዳንተ መጥቼ በፀሎቴ መሃል ድምፆችን ሰምቼ ያንተ እየመሰለኝ እኔ እንዳልናገር ጩኸቶች በዝተው እንዳልደናገር በዝምታህ አዉራኝ ለኔ ያን ጊዜ ነው ያንተ ድምፅ ሚሰማኝ ያንተ ድምፅ ብቻ በዝምታ አዉሪ በወሬዎች መሃል እዉነት ተናጋሪ ለነፍስ ጥያቄ መልስን የሚያመጣ በሥራት ያሉትን ነፃ የሚያወጣ በዝምታ ሚጮህ ከሁሉ አብልጦ ሰላምን ይሰጣል ከጩኸቶች በልጦ:: ✍✍በ ተስፋ ደጉ ✍✍ Joni and Share @Kegetemku-leyesus
Открыть в Telegram........የመስቀሉ ሥራ ታላቅ ተጋድሎ ከጨለማ ጋራ በመስቀል ተሰራ የአብ ድንቅ ስራ ልጁን ለፍቅር ልኮ የሰው መልክ አልብሶ ሲገረፍ ታሰር ሲሰቀልም ታግሶ ቅዱሱን ሲያረክሱት ብለው የተረገመ በእንጨት ሲሰቀል እርግማን አከተመ ያኔ ለታ ነበር ጎልጎታ የቻለው የአለምን መድህን በእንጨት ሲሸከመው እሱ ነው ታሪኩ የመስቀል ዋጋው በራስ ቅል ጎልጎታ ለአለም የታየው መስቀል ከተባለ መስቀል ሚታወሰው እንጨቱ መች ነውና በእጁ የተሰራው ሚስጥሩ ይሄ ነው የመስቀል ቅሉ በእንጨት ላይ ወጥቶ ጌታ መሰቀሉ ዋጋው ዉድ ነው የመስቀሉ ስራ ተሸካሚው ሳይሆን በላዩ ላይ ወጥቶ ጨለማን አበራ ጉልበታም ነው መስቀል ጌታ የወጣበት ከግዑዙ ሳይሆን ታሪክ ተሰራበት ይነገር ለአለም ይሰበክ መስቀሉ ከእንጨቱ ሳይን የወጣውን ተቀበሉ ባልታወቀ ነበር ባይሰቀል ጌታ ባላመለኩ ነበር ለመስቀል ስሞታ አትሳቱ ኑ ሚስጥር ላውጋችሁ የመስቀሉ ጌታ እሱ ነው ሀይላችሁ ✍✍✍በጌታሁን አናሞ✍✍✍ https://t.me/kegetemku_leyesus
Открыть в Telegramየማንሰራራት አመት *-*-*-*-*-*-*-* ሰላም የአባቴ ብሩካን እንዴት ከረማቹ ? በብዙ ተጠፋፋን አይደል ጌታ እረድቶን ዛሬ ተገናኝተናል ከእንግዲህ አልጠፋም ከረፈደም ቢሆን ልበላቹ ለኢዲሱ አመት 2019 እንኳን አደረሳቹ ሰሞኑ በውስጤ የከበደ ሀሳብ ላካፍላቹ " ከዚህ በኋላ የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩት አሕዛብ ሁሉ ጌታን ይፈልጉ ዘንድ እመለሳለሁ፥ የወደቀችውንም የዳዊትን ድንኳን እንደ ገና እሠራታለሁ፥ ፍራሽዋንም እንደ ገና እሠራታለሁ እንደ ገናም አቆማታለሁ ይላል ይህን የሚያደርግ ጌታ።" (የሐዋርያት ሥራ 15:16-17) ኢሄ አመት ለእኔ የማንሰራራት አመት ይሆናል ብዬ ጀምርያለው ማንሰራራት ማለት ሙሉ የነበረ ነገር በተለያየ ምክንያት ጎድሎ ወደ ሙሉነቱ ሲመለስ የከሰረ መልሶ ትርፋማ ሲሆን የታመመ ወደ ጤንነት ሲመለስ እና መሰል ጉዳዮች ማንሰራራት ማለት እንችላለን 2018 አመት ሙሉ ትኩረቴም ጉልበቴም ሀሳቤ ለ ወደ ስራ አድርጌ መንፈሳዊ ነገሬ ፀሎት የእግዚአብሔር ቃል ጥናት አገልግሎት መንፈሳዊ ግለቴ የቀነሰበት አመት ነበር። እንደምታውቁት በ2018 ብዙ ቀን ላይቭ ፕሮግራም አላደረግንም ሪከርድ ተደርጎ የሚለቀቁት ትምህርቶች እየተለቀቁ አልነበረም በዚህ አመት ግን ከእኔ ጋር አብረን ጌታ እንፈልጋለን ቅዳሜ ቅዳሜ ላይቭ ገብተን እንፀልያለን የእግዚአብሔር ቃል እንማራለን። የሐዋረያት ስራ 15:16 የወደቀችው የዳዊት ድንኳን እንደገና አነሳታለው ይላል። የወደቀው የዳዊት ድንኳን ምን አይነት ነበር? አምልኮ የማይቋረጥበት አህዛብ እንኳን ገብተው ፀሎት ሚያደርጉበት እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ ሚደረግበት ነበር እና እግዚአብሔር ኢሄን ድንኳን በምንድነው መልሶ ሚሰራው ካላቹ መንፈሱ በመላክ የማይቋረጥ አምልኮ እንዲደረግ በሰዎች ውስጥ እሳት በመቆስቆስ ያነቃቃል አህዛብ በኢየሱስ ክርስቶስ በተሰራው ስራ የጥሉ ግድግዳ ስለ ፈረሰ ወደ እግዚአብሔር እንዲገቡና ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት እንዲያደርጉ ያደርጋል የልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ መልክ በእኛ በመግለጥ እግዚአብሔር አብ እንዲከበር ያደርጋል። እናም መንፈሱ ሲመጣ የወደቀ የዳዊት ድንኳን ይነሳል። አምልኮ እንደገና ያንሰራራል እንደገና ወደ ከፍታው ይመለሳል። በኢየሱስ ስም በዚህ አመት እንዲህ ይሆናል። ከመንፈሱ ቅዱስ የተነሳ መንፈሳዊ ህይወታቸው የደከመ እንደገና ይታደሳል። ስራቹ የከሰረ ከመንፈሱ የተነሳ እንደገና ወደ ትርፍማነት ይመለሳል። የታመመ በኢየሱስ ስም መፈወስ ይሆናል ዘንድሮ ለእኔና ለአንተ/ለአንቺ መበርታት ይሆናል መነሳት ይሆናል ማንሰራራት ይሆናል ተባረኩ ✍ኤርሚያስ ክፍሌ join and share👇👇 @Kegetemku_leyesus
Открыть в Telegramጣፍጥልኝ ዮሴፍ አስቻለው -New Album ሰምቼ ያልጠገብኩት መዝሙር ▷ ▸@Kegetemku_leyesus◂ ◁ ▷ @kegetemku_leyesus◁ △Join Us△
Открыть в Telegramፍቅር ያዘኝ ፍቅር ያዘኝ ከእየሱሴ መዳኛ ሁኗል ለነፍሴ የወደደበት መዉደድ ፍቅሩን ይገልፃል ያፈሰሰው ደሙ ከኃጢያት ያነጻናል ከሱ ነው በፍቅር መያዜ ነፍስ አስካይቀርልኝ በመስቀል ሙቶ ነው መዉደዱን ያሳየኝ ኧረ ስለሱማ መግለጫ ቃላቶች ያጥሩኛል የእዉነት የሚያፈቅር ከወዴት ይገኛል ፍቅር ታየ ባደባባይ እርቃን ዋለ ለኔ ሊታይ ከ አባቱ ሊያስታርቀኝ ክብሩን ጥሎ ሂወት ሰጠኝ ገባሁ ሰማይ ከአብ ፊት ያለ ከልካይ እኔ ስቆም የሱ ደም ነው ለኔ ሚታይ አብ አቀፈኝ ወራሽ ሆንኩኝ የመንግስቱ ፅድቄ ሆነኝ ጌታ አየሱስ የናዝሬቱ ለዚህ እኮ ነው መሽነፌ ለሱ ፍቅር ተገዛሁኝ ከሱ ዉጪ ሁሉም ይቅር ✍✍Tesfa Degu ✍✍ Joni and share @Kegetemku le yesus
Открыть в Telegramቶሎ ና አባ ኢየሱስ የኔ ሙሽራ በሰማይ ያለኸው ቤቴን ልትሰራ እመጣለሁ ብለህ ያኔ የነገርከኝ በክብር ታጅበህ እኔን ልትወስደኝ መቼ ይሆን ጌታ ቀኑ የምትመጣበት ፊትለፊት ካንተ ጋር ምንተያይበት. ትዝ ይልሃል አባ ያኔ ቃል ስትገባ የሐዋርያቱ ነፍስ በሃዘን ተከባ ወላጅ እንደሌላቸው አልተዋችሁም ብለህ ስትነግራቸው እንደምትመጣ ዳግም የመምጣትህን ዜና ለዓለም እያወሩ አመታትን አልፈው ዘመን ተሻገሩ. ይኸው በኔም ዘመን ዜናው ይነገራል የመምጣትህ ጉዳይ በብዙ ይወራል በሰሜን በደቡብ በምዕራብ በምስራቅ ሕፃን ወጣቱ ከትንሽ እስከ ትልቅ በሁሉም አቅጣጫ ስላንተ ይሰማል የመምጣትህ ተስፋ በልባችን ገብቷል. አባ ኢየሱስ የኔ አባት ነፍሴን ከዓለም ወስደህ የራስህ ያረካት እጅግ ናፍቅያለሁ ፊትህን እስካየው የተወጋ እጅህን በእጄ ልይዘው. ይህን ከንቱ ዓለም ለዘላለም ትቼ ዘላለም ለመኖር አንተ ውስጥ ገብቼ ስትመጣ ለማየት ጓጉቻለሁና ሙሽራዬ ኢየሱስ እባክህ ቶሎ ና. ✍️ሃና መኮንን @kegetemku_leyesus
Открыть в Telegramልብ ስጠኝ ልብ ስጠኝ አባ አንተን የሚፈራ በሄደበት ሁሉ ስምህን የሚጠራ በቃልህ ተመክሮ ለፈቃድህ የሚኖር አንተን ለማስደሰት ዘወትር የሚጥር ልብ ስጠኝ አንተ የምትወደውን ልትሰራ ስትመጣ ላንተ ሚገኘውን. ሰው ሁሉ ፈቃዱን በሚፈፅምበት ካንተ ሃሳብ ርቆ ጠፍቶ በሄደበት በፈጠርከው ፍጥረት እጅግ ተፀፅተህ ልታጠፋ ስትል ሁሉንም ፈፅመህ ላንተ እንደተገኘ ኖህ ተለይቶ ራሱን ለፈቃድህ ሃሳብ አስገዝቶ ልብ ስጠኝ ጌታ አንተ ምታርፍበት ከሰማይ ስታየው ምትደሰትበት. ልብ ስጠኝ ልብ ስጠኝ አባ እንደ ዳዊት ያለ ሙሉ ማንነቱን አንተ ላይ የጣለ ፈቃድ እና ሃሳቡን ቃልህ ውስጥ ሰውሮ ከሚጠፋው ይልቅ አንተ ላይ አተኩሮ የልቡን ረሃብ ናፍቆቱን ሳይቀንስ አንተ ላይ ጀምሮ አንተ ላይ ሚጨርስ አባ ልብ ስጠኝ ያንተ የሆነውን ከምድር ሳይሆን አንተ ጋር ያለውን. ልብ ስጠኝ አባ አንተን የሚሰማ እሺ ብሎ ሚታዘዝ አንዳች ሳያቅማማ ለፈቃድህ መፈፀሚያ ዕቃ ሚሆንልህ በህይወት መንገዱ አንተን የሚያሳይህ ልብ ስጠኝ አባ ከክፋት የራቀ ድምፅህን አጥርቶ ለይቶ ያወቀ. አባ መንፈስ ቅዱስ ልብ ስጠኝ ዛሬም አንተን የሚመስል ሁሉንም የሚወድ ትልቅ ትንሽ ሳይል አንተን የሚሰማ ካንተ የተማረ ከስርህ ሳይጠፋ እዛው ውሎ ያደረ ለልብህ ሃሳብ ዘወትር የነቃ ትውልድን በቃልህ መክሮ የሚያነቃ አባ ልብ ስጠኝ ቆራጥ የጀገነ መገኛ ሰፈሩ ክብርህ ውስጥ የሆነ. ✍️ሃና መኮንን @kegetemku_leyesus
Открыть в Telegram