HTU College of Distance and online education
Holy Trinity University, College of Distance Theological Education for Ethiopian Orthodox Tewahido Church members only.
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры3,26 тыс.Пересылки—Реакции36Комментарии—
- 02Просмотры3,14 тыс.Пересылки—Реакции17Комментарии—
- 03Просмотры3,05 тыс.Пересылки—Реакции17Комментарии—
Новые посты
Переслано из የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት-Holy Trinity University PR
ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በድሬደዋ ሀገረ ስብከት! (ቅ.ሥ.ዩ. ኅዳር 2፣ 2019 ዓ.ም) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠውን ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት በማድረግ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እና ትውልድን በመንፈሳዊነትና በዕውቀት የሚያገለግሉ አገልጋዮችንና ምዕመናንን ለማፍራት፣ የነገረ መለኮት ትምህርትን ለማስፋፋት በዋናው ግቢ በመደበኛ፣ በማታ እና በሳምንቱ መጨረሻ እንዲሁም በርቀትና በይነ-መረብ ትምህርት መርሐ ግብር በመጀመሪያ ዲግሪና ሁለተኛ ዲግሪ ከ7,500 በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል። የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት እያሳየ ካለው ሁለንተናዊ ተቋማዊ እድገት በተጨማሪ የኦርቶዶክሳዊ ነገረ መለኮት ትምህርትን በዓለም አቀፍና በሀገር ውስጥ ተደራሽ ለማድረግ በያዘው ዕቅድ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ጉባኤ የርቀት እና በይነ-መረብ ትምህርት ኮሌጅ ከዚህ ቀደም በወላይታ እና ጅማ አኅጉረ ስብከት ከከፈታቸው የርቀት ትምህርት ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ማዕከላት በተጨማሪ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በድሬደዋ፣ በደሴ፣ በባህር ዳር እና በአዳማ አጥንቶ አዳዲስ ቅርንጫፍ ማዕከላት እንዲከፈቱ ውሳኔ አስተላልፏል። በዚህም ውሳኔ መሠረት የርቀት እና በይነ-መረብ ትምህርት ኮሌጅ በቅርቡ በይፋ ምዝገባ የሚጀመርበት የደሴ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ማዕከል እንደተጠበቀ ሆኖ በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሳባ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በከፈተው የርቀት ትምህርት ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ማዕከል በዛሬው ዕለት 02/03/2019 ዓ.ም የኮሌጁ ዲን በተገኙበት በይፋ ማስጀመሩን አስታውቋል። ከኮሌጁ ያገኘነው ቀዳሚ መረጃ እንደሚያሳየው የቅርንጫፍ ማዕከላቱ እየተከፈቱና እየተስፋፉ ያሉት በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር) የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት፣ የደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባታዊ ቡራኬና የሥራ መመሪያ ሰጪነት ነው።
Открыть в Telegram