Динамика просмотровСкрыть динамику
Рост просмотров
Часов после публикации
Показать таблицей
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 123 |
| 4 ч | 343 |
| 27 ч | 628 |
- Через 1 час123
- Через 6 часов343
- Через 24 часа628
- Всего сейчас628
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 123 |
| 4 ч | 343 |
| 27 ч | 628 |
የደረጃ 1 ተተኪ መምህራን ሥልጠናምዝገባ ለደረጃ አንድ ተተኪ መምህራን የመመልመያ መስፈርቶች!👇👇👇 1. በአለማዊ ትምህርቱ አስረኛ ክፍል የጨረሰ 2. በሰ/ት/ቤት የካልዓይ ወይም የ8ኛ ክፍል የጨረሰ:: 3. ቅዳሜ እና እሁድ ከ 8-11 ሠአት ትምህርት፣ አገልግሎት፣ ሥራ፣ የሌለው 4. ትምህርቱን ሲጨርስ ለማገልገል ፍቃደኛ የሆነ እና አንደበተ ርቱዕ የሆነ። 5. ፀባዩ እና መንፈሳዊነቱ በሰንበት ትምህርት ቤቱ የተመከረለት። 6. ሁለቱንም ፆታ (ወንድ እና ሴት) 7. የመግቢያ ፈተናውን ከ75% በላይ የሚያመጣ። ለመመዝገብ ፡ 0920054286 ላይ በአስቸኳይ ቴክስት ሜሴጅ ብቻ ይላኩ። አዘጋጅ ፡ ማህበረ ቅዱሳን
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 1 ч | 232 |
| 5 ч | 381 |
| 28 ч | 579 |
Часов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 8 ч | 206 |
| 26 ч | 731 |
"ለሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በሙሉ ማስታወቂያ ስራ መስራት ለሚፈልግ ስልጠና ስለሚሰጥ ፍላጎቱ ያላችሁ ልጆች እንድት መዘገቡ" በ 0964013892 በቴሌግራም ቻናል ኢንቦክስ አርጉልን። " @EwketBirhan24
Открыть в TelegramЧасов после публикации
| Часов после публикации | Просмотры |
|---|---|
| 0 ч | 0 |
| 24 ч | 610 |
| 70 ч | 910 |
ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ታህሳስ 19 ቀን የሚከበረውን የሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል አስመልክቶ ወደ ደብረ ኃይል ቁልቢ ቅዱስገብርኤል ገዳም ምዝገባ ጀምረናል። ለበለጠ መረጃ +251913498421 +251934505253 ይደውሉ። አዘጋጅ፦ እውቀት ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ጉዞ ክፍል
Открыть в Telegramየበጎ አድራጎት ክፍል እሁድ ህዳር 20 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት ከቅዳሴ በኋላ ወደ መቄዶንያ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል ጉዞ አዘጋጅቷል። እርሶም በጉዞው ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ እየጋበዝን በእለቱ በምግባረ ሰናይ የተሰበሰበውን ልብስ ይዘን ስለምንሄድ በምትችሉበት ቀን ጉዞ ክፍል አጠገብ ያለው ልብስ ማስቀመጫ ክፍል በመሄድ ልብስ በመምረጥ እንድታግዙን በማክበር እንጠይቃለን። የሚያስፈልጉ ነገሮች የልብስ፣ የገላ እና የእቃ ሳሙና ማንኛውንም ሳሙና ብቻ ይዛችሁ መምጣት ይቻላል “ትራንስፖርት በነፃ ነው”
Открыть в Telegramየማጽናኛ_መርኃግብር የሰንበት ት/ቤታችን አባል የሆነው ወንድማችን አሚናዳብ ወንድም ዕረፍት ምክንያት በማድረግ ነገ ማክሰኞ ህዳር 15/ 2019 ዓ.ም የማጽናኛ መርኃ ግብር 12:00 ሰዓት በቤቱ የሚደረግ ይሆናል። ስለሆነም ቤ/ክ ተገናኝተን እንሄዳለን። ሰዓት ይከበር! አድራሻ፦ ኳስ ሜዳ ለቤተሰቦቹ መጽናናትን እንመኛለን! እውቀት ብርሃን ሰንበት ት/ቤት
Открыть в Telegramምዕመናን የደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም እና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራልን የልማት ስፈራዎች በማገዝ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ ቀረበ፡፡ የደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም እና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል የተመሰረተበትን 50ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ግቢውን የማስዋብና ለስብከተ ወንጌል እና ልዩልዩ ሀይማኖታዊ መርሀግብሮች ምቹ የማድረግ ስራ ለማከናወን የሚያስችል የልማት ስራ ህዳር2 ቀን 2019 ዓ.ም ተጀምሯል፡፡ የልማት ስራውን ያስጀመሩት የካቴድራሉ ዋና አስተዳዳሪ መልአከ ኃይል ቆሞስ አባ ተክለብርሃን ደስታ እንዳስታወቁት የልማት ስራው የካቴድራሉን አጥር ማጠር፡ የመሬት ንጣፍ ስራ፡ ተጨማሪ የመብራት መስመር ዝርጋታ፡ የምእመናን መቀመጫ ስፍራዎች እና የመኪና ማቆምያ ስፍራ ግንባታን ያካተተ ነው፡፡ ይህ የልማት ስራ ምእመናን የተለያዩ አገልግሎቶችን በምቹ ሁኔታ እንዲካፈሉ አሰተዋፅኦ እንደሚኖረውም ገልፀዋል፡፡ ምእመናን የልማት ስራውን በሚችሉት መንገድ በመደገፍ የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
Открыть в Telegramምስጋና ለተከታታይ ለአምስት ሳምንታት የማሕሌተ ጽጌ ወረብ ወደ እናንተ በዩቲዩብ ቻናላችን ስናደርስ ቆይተናል። የሰንበት ትምህርት ቤታችን ሚዲያ ክፍል እድገትና ለተከናወኑት አበይት ስራዎች ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና እናቀርባለን ። ለመምህራችን የኔታ ትዕግስቱ: አምስቱን ሳምንታት ሙሉ አብረውን በመሆን፣ ወረብ በማቅረብ እና ከጎናችን በመቆም ላደረጉት ትልቅ ድጋፍና እገዛ ከልብ እናመሰግናለን። እግዚአብሔር አምላክ ረጅም እድሜ ከሙሉ ጤንነት ጋር እግዚአብሔር አምላክ እንዲሰጥልን እንመኛለን። ለወንድማችን ፊላ ፒክቸር በመጨረሻው የማሕሌተ ጽጌ ወረብ ቀረጻ ላይ ላደረገልን ትብብርና እጅግ የላቀ ምስጋናችን እናቀርባለን ። የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና ተከታዮች: ስራዎቻችንን በመከታተል፣ አስተያየት በመስጠትና በማበረታታት ሁልጊዜም አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን። ለቀጣይ ስራዎች የበለጠ እንድንተጋ አስተያየታችሁን እና ድጋፋችሁን እንዳትለዩን በአክብሮት እንጠይቃለን። የእውቀት ብርሃን የመረጃና ውስጥ ግንኙነት ክፍል ሚዲያ
Открыть в Telegramቀለማት የሚነጋገሩበት፣ ግጥሞች ከዜማ ጋር የሚዛመዱበት እና ትረካዎች የልብን ትርታ የሚያዳምጡበት ልዩ የምሽት ማዕድ ተዘርግቷል። ከዕለት ተዕለት ውዥንብር ወጣ ብለን፣ በስነ-ጥበብ ውበት ታጅበን የጥበብን ድምጽ የምንሰማበት ይህ ድንቅ ምሽት ያመልጥዎ! 📍 መቼ? ማክሰኞ ምሽት ☕ ና፣ የጥበብን ጣዕም አብረን እንቋደስ!
Открыть в Telegram🌹🌹🌹🌹🌹 የመጨረሻውን ማሕሌተ ጽጌ ኑ አብረን እናመስግን 🌹🌹🌹🌹 https://youtu.be/eKLJPni7og0?si=jgjyauJvQUggpz32
Открыть в Telegramበምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ እንዳቶ ቀበሌ ከተገደሉት መካከል እስካሁን የ34 ኦርቶዶክሳውያን አስክሬን መገኘቱ ተሰማ። ከምእመናን በተጨማሪ ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም የሚፈጸመውን ጥቃት ለማስቆም ወደ አካባቢው እየሄዱ የነበሩ የመንግሥት የጸጥታ አካላት የጥቃት ሰለባ መሆናቸው ታውቋል። ( MK TV ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ) በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ እንዳቶ ቀበሌ የምእመናን ግድያ የጀመረው ከጥር 21ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን ዛሬም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ያሉ ምእመናን የዛሬውን ግድያ ከቀድሞው ጋር ወደ ኋላ መለስ ብለው ያስታውሳሉ። ሮቤ ወረዳ እንደቶ ቀበሌ ከሸርካ ወረዳ ጋር አዋሳኝ ስሆን ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም በሸርካ ወረዳ እንደተፈጸመው አሰቃቂ ጥቃት ሁሉ ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም በእንዳቶ ቀበሌ ከማለዳው 11 ሰዓት ጀምሮ ጥቃት መፈጸሙን ምእመናን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቮዥን መረጃ አድርሰዋል። እንደመረጃ ሰጭዎቻችን ታጣቂዎች በፈጸሙት በዚህ ድንገተኛ ጥቃት ይህንን ዜና እስከምንዘግብበት ጊዜ ድረስ ከሟቾች መካከል የ34 ኦርቶዶክሳውያን አስክሬን በእንደቶ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መሰብሰቡን አሳውቀዋል። የሟቾች ቁጥርም እንደሚያሻቅብ ተጠቁሟል።
Открыть в Telegram