«በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም መልአክ» በሰማያዊው መቅደስ፣ በነበልባል ዙፋን ፊት በክብርና በሞገስ የሚቆም፣ የፈጣሪን ቃል ሳይውል ሳያድር ለፍጥረታት የሚያደርስ ታላቅ መልአክ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ነው። ካህኑ ዘካርያስ በቤተ መቅደስ ዕጣን ሲያጥን በግርማ የተገለጠለትና «እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ» (ሉቃስ 1፥19) በማለት ማንነቱን ያወጀ ይህ ብርሃናዊ መልአክ፣ በሰማይና በምድር መካከል የምሕረትና የበረከት ድልድይ ሆኖ የሚያገለግል የልዑል ባለሟል ነው። ቅዱስ ገብርኤል የታላላቅ ምሥራቾች ሁሉ አብሳሪ ነው። የሰው ልጅ በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ተስፋ ቆርጦ በተቀመጠበት ዘመን፣ የድኅነት ጮራ ፈንጥቆ የመጣው በእርሱ አንደበት ነው። ለመካኗ ኤልሳቤጥ የመጥምቁ ዮሐንስን መወለድ ያበሰረ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ በናዝሬት ለምትኖር ለንጽሕት ድንግል ማርያም «ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ» በማለት የዓለም መድኃኒት የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን ሰው መሆን የነገረ የሰላም መልእክተኛ ነው። ዛሬም ቢሆን በሐዘን ለተሰበረ ልብ የደስታን፣ በጭንቀት ለተዋጠ ነፍስ የመጽናናትን ምሥራች ይዞ የሚመጣ ታማኝ አብሳሪ ነው። የእርሱ መገለጥ ሁልጊዜም ለሰው ልጆች ሰላምንና መረጋጋትን ያመጣል። የመላእክት ግርማ ለሰው ልጅ ዓይን አስፈሪ ቢሆንም፣ ቅዱስ ገብርኤል ግን በተገለጠባቸው ቦታዎች ሁሉ ቀዳሚ ቃሉ «አትፍራ» የሚል ነው። ለነቢዩ ዳንኤል ራእዩን ሲፈታለት፣ ለዘካርያስ በመቅደስ ሲታየው፣ ለእመቤታችንም ሲያበስራት ፍርሃታቸውን አርቆ ልባቸውን በሰማያዊ ሰላም አረጋግቷል። በዚህ ዓለም ውጣ ውረድና ማዕበል ውስጥ ለምትናወጥ ነፍስ፣ የቅዱስ ገብርኤል መገኘት የመንፈስ ዕረፍትና የልብ መረጋጋት ምንጭ ነው። አረጋጊ መልአክ ነውና። ቅዱስ ገብርኤል በስሙ ለሚጠሩትና በአማላጅነቱ ለሚታመኑት ሁሉ ፈጥኖ ደራሽ ነው። ነቢዩ ዳንኤል ስለ ሕዝቡ በጾምና በጸሎት ሲማልድ፣ ገና ጸሎቱን ሳይጨርስ ቅዱስ ገብርኤል «ፈጥኖ በርሮ» እንደደረሰለት ቅዱስ መጽሐፍ ይመሰክራል (ዳንኤል 9፥21)። በርቀት የማይገደብ፣ በጊዜ የማይታጠር ፈጣን ረዳት በመሆኑ፣ ችግርና መከራ ሲከብብ «ቅዱስ ገብርኤል ድረስልኝ» ተብሎ በተጠራ ቅጽበት ከራማ ፈጥኖ የሚወርድ የጭንቅ ቀን አለኝታ ነው።በተለይም ከነደደ እሳትና ከከበደ መከራ የሚያወጣ ኃያል ታዳጊ ነው። በባቢሎን ምድር ንጉሥ ናቡከደነፆር ላቆመው የወርቅ ምስል አንሰግድም በማለታቸው፣ ሰባት እጥፍ በነደደ የእሳት እቶን ውስጥ የተጣሉትን ሠለስቱ ደቂቅን (አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን) ከእሳቱ መካከል ወርዶ የታደጋቸው እርሱ ነው። የሚያቃጥለውን ነበልባል እንደ ጠዋት ጤዛ አቀዝቅዞ፣ እሳቱ ጠጉራቸውን እንኳ ሳይነካ በሰላም እንዲወጡ ያደረገ የእሳት ውስጥ ጠባቂ ነው። ዛሬም በሕይወታችን የሚነድደውን የፈተና፣ የበሽታና የመከራ እሳት በጸሎቱና በረድኤቱ የሚያጠፋልን ታላቅ መልአክ ነው። በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም መልአክ በመሆኑም ምልጃው የከበረና የሰመረ ነው። የሰው ልጆችን ጸሎት፣ እንባና ልመና እንደ ጣፋጭ ዕጣን አሳርጎ በልዑል ዙፋን ፊት ያቀርባል። ከፈጣሪ ዘንድ ምሕረትንና ይቅርታን የሚያሰጥ፣ የታመሙትን የሚፈውስ፣ የታሰሩትን የሚፈታ፣ የተጨነቁትን የሚያጽናና የምሕረት ባለሟል ነው። 🙏በብዙ መከራ፣በፈተና እሳት፣በሕመም እና በችግር ውስጥ ላለን ሁሉ ቅዱስ ገብርኤል ፈጥኖ በእግዚአብሔር ፊት ይቁምልን። የቆምኩት ገብርኤል ቆሞልኝ ነው ብለን ለመመስከር ያብቃን። 👉ይቀላቀሉ - @ephrem_views ናዝሬት -አዳማ-ኢትዮጵያ ✍️የኤፍሬም ዕይታዎች
Открыть в Telegram
የኤፍሬም እይታዎች (መ/ር)
በዚህ የቴሌግራም ገጽ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዶግማ፣ቀኖና እና ትውፊትን የጠበቁ ስርዓተ አምልኮና ትምሕርቶች ይቀርብበታል። ክርስቲያናዊ የሆኑ ማህበራዊ ጉዳዮችም ይነሱበታል። " ያየሁትን እናገራለሁ የሰማሁትን እመሰክራለሁ! "
Средние просмотры поста по дням
По дню публикации
Показать таблицей
| Дата | Просмотров на пост |
|---|---|
| 18 нояб. 2026 г. | 1 460 |
| 23 нояб. 2026 г. | 751 |
| 26 нояб. 2026 г. | 363 |
Самые просматриваемые за месяц
- 01Просмотры1,46 тыс.Пересылки—Реакции22Комментарии—
- 02Просмотры751Пересылки—Реакции31Комментарии—
- 03Просмотры363Пересылки—Реакции10Комментарии—
Новые посты
" ከነገ ሕዳር 15 ጀምሮ ጾመ ነቢያት(ገና) ጾም ይገባል።ዛሬ ቅበላ ነው። በጾሙ ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ በተሰበረ ልብ ወደ እግዚአብሔር ልናለቅስ ይገባል! መልካም የገና ጾም ይሁንልን
Открыть в Telegramየያዝከውን ቅርንጫፍ ልቀቅና በረከትህን ተቀበል! ++++++++++++ +++++++++++++++ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ በውኃ ላይ መራመድ ከፈለግክ፣ መጀመሪያ ከታንኳዋ መውጣት አለብህ። የእምነት ጉዞ የሚጀምረው ምቹ ከሆነው ስፍራ ወጥቶ የእግዚአብሔርን ቃል በመታመን ነው። አንተ ይህን በእምነት ስታደርግ የኢየሱስ አንድ ቃል "ና!"ብቻ የማዕበሉን ኃይል ሽሮ በውኃ ላይ ያራምድሀል። ጴጥሮስን በውሃ ላይ ያራመደው የውኃው መጠን መቀነስ ሳይሆን የጌታ ቃል ኃይል ነው። ጌታ አምኖ ከታንኳ መውጣቱ ነው። «እምነት ማለት ማዕበሉ የለም ብሎ መካድ ሳይሆን፣ በማዕበሉ መካከል ኢየሱስ እንዳለ ማመን ነው።» እውነተኛ እምነት በችግር ውስጥ ሆኖ የፈጣሪን ህልውና መመልከት ነው። ችግርህን ሳይሆን ከችግርህ በላይ የሆነው ክርስቶስን አሻግረህ ተመልከት። ጌታ ለመከተል ምቹ መንገድ አትፈልግ፣ከእርሱ ጋር ከሆንክ ወጀቡ እንደትቢያ የምትረማመድበት ጎዳና ነው። ዓይንህን ብቻ ከኢየሱስ ላይ አታንሳ«ዓይንህን ከኢየሱስ ላይ ስታነሳ፣ ማዕበሉ ካለው ወጀብ በላይ ገዝፎ ይታይሃል።» ጴጥሮስ መስጠም የጀመረው ነፋሱን ባየ ጊዜ እንጂ ኢየሱስን እያየ አልነበረም። የሚያሰጥምህ የማዕበሉ ጽናት ሳይሆን፣ ትኩረትህን ወደ ፍርሃትህ ማዞርህ ነው። ትኩረታችን ችግሩ ላይ ሲሆን እምነታችን ይዳከማል፤ ትኩረታችን መፍትሔ ሰጪው ላይ ሲሆን ግን እንጸናለን። የምንፀናው በእኛ አቅም ሳይሆን በጉልበታችን በኢየሱስ ነው። ፍርሃት የሚያንኳኳው በር ላይ ነው፤ ነፋሱ ቢበረታም፣ በኢየሱስ ፊት ምንም ዓይነት ኃይል የለውም። ጴጥሮስን አስታውሰው ያቺ «‘ጌታ ሆይ አድነኝ’>የምትል አጭር ጸሎት ሰማይን ሰንጥቃ የኢየሱስን እጅ ስትስብ። በጭንቀት ጊዜ ረጅም ንግግር አያስፈልግም፤ ከልብ የመነጨ አጭር የጸሎት ጥሪ በቂ ነው። ኢየሱስ ጴጥሮስ እስኪሰጥም አልጠበቀም ወዲያውኑ እጁን ዘረጋለት እንጂ። የእግዚአብሔር ምሕረትና እርዳታ ከውድቀታችን በላይ ፈጣን ነው። «መስጠም ስትጀምር እንኳ እምነትህ ቢጎድል፣ የኢየሱስ እጅ ግን ከአንተ አይርቅም።» የእኛ እምነት ቢዋዥቅም የእርሱ ታማኝነትና አዳኝነት ግን አይለወጥም። ለዚህ ምሳሌ የሚሆነን የዚያ መንገደኛ ሰው ታሪክ ነው። አንድ ወደ ተራራ የሚጓዥ ሰው በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሲጓዝ በድንገት መንገዱን ስቶ ወደ ጥልቅ ገደል ይወድቃል። ገደሉ ውስጥ ገብቶ ከመሞቱ በፊት በአጋጣሚ በገደሉ አፋፍ ላይ የበቀለ አንድ የእንጨት ቅርንጫፍ በእጁ ጨብጦ ይይዛል። ሰውየው በጨለማው ውስጥ ምን ያህል ጥልቀት እንዳለ ስለማያውቅ በከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ ሆኖ «ጌታ ሆይ እባክህ አድነኝ!» እያለ አምርሮ ይጸልያል። በዚህ ጊዜ ከሰማይ «ታምነኛለህን?» የሚል ድምፅ ይሰማል። ሰውየውም «አዎ ጌታ ሆይ ሙሉ በሙሉ አምንሃለሁ» ብሎ ይመልሳል።የሰማው ያ ድምጽም መልሶ «እንግዲያውስ የያዝከውን ቅርንጫፍ ልቀቀው» ይለዋል። ሰውየው ግን ቅርንጫፉን ከለቀቀ ወድቆ የሚሞት ስለመሰለው በፍርሃት ተውጦ ቅርንጫፉን ይበልጥ አጥብቆ ይይዛል። ተደጋጋሚ ቢነግረውም በንግግሩ "አምንሃለው" ያለው ያ ሰው ተግባሩ ግን አለማመን ሆነ። ሊያስተምረው ስለፈለገ ጌታ ሌሊቱን ሙሉ በብርድና በፍርሃት ሲንቀጠቀጥ ካደረ በኋላ ንጋት ላይ ፀሐይ ስትወጣ አካባቢውን ሲያይ... ሰውየው የያዘው ቅርንጫፍ ከመሬት ሁለት ጫማ (ግማሽ ሜትር) ያህል ብቻ ከፍ ብሎ እንደነበር ይመለከታል። ጌታን አምኖ የያዘውን ቅርጫፍ ቢለቅ ከችግሩ ተላቆ ጉዞውን ይቀጥል ነበር። ብዙዎቻችን ጌታ እንድለቀው የሚፈልገው ብዙ ቅርጫፍ በሕይወታችን አለ ግን "ጌታ ሆይ አድነኝ " ብለን ብንጠይቀው ሊያድነን መጥቶ የያዝነውን ቅርጫፍ ልቀቁ ሲለን መልቀቅ አንፈልግም።" አንተንም አምናለሁ፣ የያዝኩትን ቅርጫፍ አምናለሁ"ነው ድርጊታችን። ብዙዎቻችን በጸለይነው ልክ፣ባለቀስነው ልክ፣በጠበቅነው ልክ ከጌታ ዘንድ በረከት ያልተቀበልነው በረከት የምንቀበልበት እጅ ልንለቀው የሚገባንን ቅርጫፍ በመያዙ ነው። ያ ከጌታ በረከት መቀበል የሚገባው እጅ የማይጠቅመውን ነገር መልቀቅ ስላልፈለገ ብዙ በረከቶች በሕይወታችን አመለጡን። ንስሐ እንዳንገባ፣ሥጋውና ደሙን እንዳንቀበል ያደረገን ያንን ቅርንጫፍ መቼ ይሆን ለቀን መልካሙን የሕይወት ጎዳና መጓዝ የምንጀምረው። አንተ/አንቺ መልቀቅ ያልቻልከው ቅርጫፍ በሕይወትህ/ሽ ምንድነው ? ✍️Ephrem Habtemariam (የኤፍሬም እይታዎች ) ሕዳር 9- ሞጆ - ኢትዮጵያ -
Открыть в Telegram"እናታችን ኪዳነ ምኅረት ሆይ! በአርሲ በግፍ ለሚታረዱት ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን በተገባልሽ የምሕረት ቃል ኪዳንሽ ፈጥነሽ ድረስላቸው። ለቅሶአቸውን ወደ ደስታ፣ መከራቸውን ወደ ሰላም ለውጪላቸው፣ ክንድሽን ዘርጊላቸው። ድንግል ሆይ በስደትሽ ወራት ስለተቀበልሽው መከራ ብለሽ በቀያቸው ስለተሰደዱት ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢ😭አሜን!" ✍️ @ephrem_views ..
Открыть в Telegram📌#ትኩረት_በአርሲ_ላሉ_ኦርቶዶክሳውያን ! ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና አላማው ክርስትያኖችን በሁለተናዊ ደኅንነት መጠበቅ ነው። ክቡር የሆነው የሰው ልጅ በሃይማኖቱ ምክንያት እየተገደለ ቅዱስ ሲኖዶስ ስለሌላ አጀንዳ መወያየት የለበትም። ለሌሎቹ ሁሉም አጀንዶች ለሰው ናቸው። ስለዚህ ከሁሉም የሰው ሕይወት ይቀድማል። ትኩረት ለአርሲ ክርስትያኖች ! ✍️ @ephrem_views ..
Открыть в Telegramየተሳትፎ ጥያቄ ! 📌ከእግዚአብሔር ጋር ስላለን ግንኙነት (ኅብረት) 1.በቀን ውስጥ ለጸሎትና ለቃለ እግዚአብሔር የምሰጠው ጊዜ ከማኅበራዊ ሚዲያ (Social Media) ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል ነው? 2.እግዚአብሔርን የምፈልገው በችግርና በጭንቀት ጊዜ ብቻ ነው ወይስ በደስታዬም ጭምር? 3.በቅድስት ቤተክርስቲያን የምገኘው ልማድ ስለሆነ ነው ወይስ ከፈጣሪዬ ጋር ለመገናኘት ባለኝ እውነተኛ ናፍቆት? 👉ሁላችሁም ተሳተፉ።አንዱ ከሌላኛው መልስ ብዙ ሰው ይማራል። ✍️ የኤፍሬም ዕይታዎች @ephrem_Views 👆የቴሌግራም አድራሻ👆👆
Открыть в Telegramመናኙ ሃኪም ! ............. ....... በአዲስአበባ የፎቅ ጫካ ውስጥ እልፍኛቸውን ዋሻ ያደረጉ፣ ኃጢያት በበረታበት ከተማ በምናኔ የሚኖሩ፣ በትትልቅ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው እየሰሩ ገንዘብ፣ዝናንና ክብርን ንቀው የተቸገሩት ለመርዳት የሚሰሩ፤ ዓለምና አምሮቷን ንቀው ግርማ ሌሊቱን ጸብዓ አጋንንቱን ታግሰው በበረሃ ከሚኖሩ ባህታውያን ያላነሰ የቅድስና ሕይወት ላይ የደረሱ ስውር ባሕታውያን ብዙ ወንድምና እህቶች በየከተማው ያሉባት ሀገር ናት ኢትዮጵያ። ጊዜው ቢረዝምም በአንድ ወቅት ለጊዜው ስማቸውን የማልጠቅሳቸው በገዳም የሚኖሩ አንድ ትልቅ አባት ያጫወቱኝን ታሪክ በአጭሩ ላውጋችሁ። "ልጄ በአንድ ወቅት ወደ ገዳሙ የመጣ አንድ ወንድም ያጫወተኝ ታሪክ ልንገርህ....." ነገሩ ወዲህ ነው በአዲስአባ የሚኖርና በአንድ ታዋቂ ሃኪም ቤት ተቀጥሮ የሚሰራ አንድ ዶክተር ነበር። ይህ ሃኪም በሙያው አንቱ የተባለ የታፈረና የተከበረ ሃኪም ነው። ብዙ ሕመምተኞችን አምላኩን አጋዥ በማድረግ የፈወሰ ጎበዝ ሃኪም ነበር። ቤተሰቡ ጥሩ ገቢ ያላቸው በመሆኑ የሚኖረው ከቤተሰቡ ጋር በአንድ ቤት ነበር። በሚሰራበት መስሪያ ቤት ከትሕትናው፣ከእርጋተውና ከጠንካራ ሰራተኛነቱ በተጓዳኝ በሁለት ነገር የስራ ባልደረብቹ ያስታውሱታል። 1ኛ ሁልጊዜ ሽክ ብሎ ሙሉ የሱፍ ልብ ለብሶ ወደ ስራ ገበታው በመምጣቱና። 2ኛ "ለጤናዬ የሚስማማኝን ቤት በልቼና ጠጥቼ ስለመጣሁ አልበላም" በሚለው ንግግሩ። ከቤተሰቡ ጋር ሲኖርም ማንም የማይገባበት የራሱ ክፍል ቤት ነበረው። ቤተሰቡም "በሕይወት እያለን አግብተህ ፣ወልደህ ከብደህ እንይህ " ሲሉትም " አምላክ ሲፈቅድ" ከማለት ውጪ አይመልስም ነበር። የሚገርመው ይህ ሰው ሳይታመም በድንገት ያርፋል። ቤተሰቡም ይደናገጣል። እንግዲህ ጉዳዩ ከዚህ በሗላ ነው የታወቀው። ገናዦች መጥተው ገላውን ለማጠብ ልብሱን ሲያወልቁ " ቅንአተ ዮሐንስ " ታጥቆ መላ ሰውነቱን በሰንሰለት አስሮ ያገኙታል። የጆቹ መዳፎች ጠቋቁረው፣ ጉልበቱም ገርጦ፣ ሰንሰለቱም በሰውነቱ ላይ መስመር ሰርቶ ይመለከታሉ። በመገረም አዲስ ነገር ቢሆንባቸው " ምንድን ነው" ብለው ቤተሰቡን ይጠቃሉ። ቤተሰቡም "ኸረ እኛም አናውቅም ከብዙ ጊዜ በሗላ ክፍሉ ብንገባ የጥራጥሬ አይነት በፌስታል ተቋጥሮ ከበሶና ከስኳር ጋር አገኘን። ክፍሉም እንደምትመለከቱት የጸሎት ቤት ነው የሚመስለው።አምላኩን የሚፈራ ጠንካራ ክርስቲያን አንደ ሆነ ልጃችንን እናውቃለን አንዲህ አይነት ሕይወት እንዳለው ግን አናውቅም " በማለት ይመልሳሉ። በስፍራው የተገኙ ጓደኞቹም ይህንን ሲመለከቱ " ለካ ጓደኛችን ባሕታዊ ነበር። ሙሉ ልብስ በከረባት ሁሌ ለብሶ የሚመጣው ለካ በውስጥ የደበቀውን የምናኒ ልቡሱን እዳናይና እንዳንጠረጥረው ነው። ለካ ምግብ ቤት በልቼ መጥቻለው የሚለን "የእርሱ ምግብ ቆሎና በሶ ነበር።" ብለው ተላቀሱ። በምናኔ ሕይወቱ እጅግ ተደነቁ። ይኸውልህ ልጄ "ሁለተኛው በጣም ያስደነቀኝ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተፈጠረው ነገር ነበር። " ማን የተገኘ ይምስልዃል ?" አሉኝ በተመስጦ እያዳመጥኳቸው መሆኔን ተገንዝበው። ኸረ ምኑን አውቄ አባቴ። አልኳቸው " የተገኙትማ አይናቸው የፈረጠ፣እግራቸው የተቆረጠ፣ ዓይነ ስውራን፣ ጧሪ ቀባሪ የሌላቸው አረጋውያን ከየት መጡ ሳይባል ከቀባሪ ዘመድ አዝመድ በቁጥር በልጠው። የለቅሶ እሩምታ ያዘንቡ ጀመር። " ወይኔ አባቴ" " ከእንግዲህ ማን ያክመኛል " የማትጠየፈኝ አንተ ነበርክ " ሕይወቴን፣ ልጄን ማን ነጠቀኝ" ለማን ጥለኸን ሄድክ "የሚሉ የለቅሶ ድምጾች ተበራከቱ። ቤተሰቡም የሰፈሩ ሰዎችና ጓደኞቹም በተፈጠረው ነገር ተደነቁ። " እነ ማናቸው " በሚል.. ከመሃል አንድ ሰው ጠርተው ሲጠይቁ ያገኙት መልስ። እጅግ ልብ የሚነካ ነበር።" በትርፍ ሰዓቱ ሳይቀር እየሰራ የሚያስተዳድራቸው፣ የሚንከባከባቸው፣የሚጦራቸው፣ ፍቅር የሚሰጣቸው ሰዎች እንደሆኑ ይሰማሉ ። ይኼንን ከሃኪሙና ከእነዚህ ሰዎች በቀር ማንም አያውቅም ነበር። የሚደንቀው በአንድ ቤት አብረውት የሚኖሩ የገዛ ወላጆቹ እንኳን ስለ እርሱ የምናኔ ሕይወት አያውቁም ነበር። ታዲያ ከዚህ በላይ የምናኔ ሕይወት ወዴት አለ ? በመሃል ከተማ በአዲስአበባ እንዲህ ያለ የቅድስና ሕይወትን መኖር እንዴት አያስገርም አያስደንቅ ልጄ። መናኝ በበረሃና በገዳም ብቻ ሳይሆን በከተማም አለ። ታሪኩን ከሰማሁት የዘገየ ቢሆንም ሁሌ ስለሚደንቀኝ ነው ያጫወትኩህ።" በማለት የነገሩኝ ታሪክ ዛሬ በልቤ ውስጥ ይታወሰኛል። የሰው ልጅን ክፋት፣ ተንኮል፣ጸብ፣ክርክር፣ መገፋፋትና መጠላላት ስመለከት ሁልጊዜ ይኼንን አስታውሰዋለሁ። እኔ ኃጢያተኛውና በደለኛው ብቻ ሳይሆን ይህች ዓለም የከተማ ባሕታውያን የሚኖሩባትም ዓለም ናትና በዚህ እጸናለሁ። እጽናናለሁ። ያለንበት ሁኔታና ቦታ፣ የሰዎችን ክፋትና ተንኮል እየዘረዘርን ከመውቀስና ከማማረር እኛ ራሳችንን በማረምና በማስተካከል ኃጢአት በበዛበት ከተማ " እንዴት ከእግዚአብሔር ጋር መኖር እንደምንችል እናስብ" መንፈሳዊነት ረቂቅ ነው። መንፈሳዊነት ጥልቅ ነው። መንፈሳዊ ሰው እርሱ ሁሉን ይመረምራል። እርሱ ግን በማንም አይመረመርም። የክርስቶስ ልብ አለውና። የሃኪሙ ታሪክም የሚያስረዳን ይኼንኑ ነው። ❤ልዑል አምላክ ለሁላችን ለጽድቅ የመነነ ልብ ያድለን። Telegram 👉 @ephrem_views ......... ✍️ ኤፍሬም ሀብተ ማርያም (መ/ር) አዳማ -ኢትዮጵያ
Открыть в Telegram📌ወደ አንድ ቋት መሰብሰብ ካልተቻለ ወይም ጊዜ የሚወስድ ከሆነ በአንድ አካባቢ ያሉ አቢያተክርስቲያናት ገንዘባቸውን በአንድ ቋት አድርገው ወይም በጋራ የሚሰሩበት ሕግና ሥርዓት መዘርጋት። በ45ኛው ሠበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ በተለይም በጠቅላይ ቤተክርስቲያን ደረጃ አሁን ላይ እየታዩ ያሉ ለውጦች፤የአዲስአበባ ሀገረ ሰብከት ሰው ተኮር እቅድ፣በአንዳንድ ሀገረ ስብከቶች የታዩ ጥረቶች በተሻለ ሁኔታ ለውጥ እንዲያመጡ ከተፈለ ይህ ጉዳይ ይታሰብበት ዘንድ ይህን የውስጥ ቁጭቴንና የግል ምልከታዬን በልጅነት መንፈስ ለማንሳት ወደድኩ። በሐዋርያት መንበር እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለቤተክርስቲያን የሾማችሁ ብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና የቤተክርስቲያን መሪዎች ሁሉ ይህን ጉዳይ በአጽንኦት ታዩት ዘንድ በታላቅ አክብሮትና ትሕትና እጠይቃለሁ። ምክንያቱም የቤተክርስቲያን ገንዘብ በባንክ እየበሰበሰ አገልጋዮች በኑሮ ውድነት የሚሰቃዩበት፣ ምእመናን ሥራ አጥተው የሚባክኑበት ዘመን ሊያበቃ ይገባልና! ሀብታችንን ወደ አንድ በማምጣት፣ ወደ ምርታማ ኢንዱስትሪዎች በመግባት የራሳችንን የኢኮኖሚ ነጻነት ልናረጋግጥ ይገባል። ጊዜው አሁን ነው፤ ካልሠራንበት በሀገራችን ባለው ከፍተኛ የዋጋ ንረት (Inflation) ምክንያት፣ በባንክ ዝም ብሎ የተቀመጠ ገንዘብ በየቀኑ የመግዛት ዓቅሙ እየሞተ ፤እኛም ዳቦ ጨብጠን እየተራብን መቀጠል ሊኖርብን ይችላልና። ስለዚ የቤተክርስቲያን የፋይናንስ ሥርዓቱን የበለጠ በማዘመን በራሷ ልጆች የኢኮኖሚ ነጻነቷን ያረጋገጠች ቤተክርስቲያን ትኖረን ዘንድ እንስራ። ✍️ ኤፍሬም ሀብተ ማርያም (ሰባኬ ወንጌል) (የኤፍሬም እይታዎች ) ጥቅም 7/2019 ዓም.
Открыть в Telegram#ይድረስ_ለቅዱስ_ሲኖዶስ +======== =======+ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሀገርና የታሪክ ምሰሶ፣ የቅርስና የጥበብ ምንጭ ናት። ነገር ግን ይህች ታላቅ ተቋም የሺህ ዓመታት እድሜዋንና ታሪኳን በማይመጥን ዛሬም ድረስ "ከልመና" እና ከዕርዳታ ባልተላቀቀ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ ትገኛለች። አሁን ላይ ከቀድሞ የተሻለ የፋይናንስ ሥርዓት ለመዝርጋት ጥረት ቢደረግም ነገር ግን አሁንም ብዙ ይቀራል። በራሱ የተጀመረው ጥረት ቢደነቅም። እውነታው ቤተክርስቲያናችን በዓለም መድረክ ካሉ ሌሎች እህት አብያተ ክርስቲያናት ጋር እኩል ተወዳዳሪ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪና ተባባሪ መሆን የምትችለው የውስጥ የኢኮኖሚ ጥንካሬዋን ስትገነባ ብቻ ነው። መንፈሳዊ ልዕልና ያለ ኢኮኖሚ ነፃነት መቼም ሙሉ ሊሆን አይችልም። ቤተክርስቲያን ራሷን ችላ፣ ግዙፍ የንግድ ተቋማትን፣ የማምረቻ ፋብሪካዎችንና የግብርና ኢንዱስትሪዎችን መገንባት ስትጀምር ያንጊዜ መንፈሳዊ ተልዕኮዋን ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት በነጻነት ማስፈጸም ትችላለች። ይህም ብቻ ሳይሆን ከልመና ተላቃ፣ በኢኮኖሚ ራሷን ችላ ትልልቅ የንግድ ተቋማትንና ፋብሪካዎችን በመገንባት ከአገልጋዮች ባሻገር ለምእመናን ልጆቿ የሥራ ዕድል መፍጠር የምትችልበት ሁኔታም ይፈጠራል። ከትላንት እሰከ ዛሬ በየአጥቢያው የተከፈተው የልመና ስልት፣ በየመንገዱ የምንዘረጋው እጅና፣ታቦት አቁመን የሰበሰብነው ገንዘብ ዘመኑን በሚመጥን አዲስ የፋይናንስ ሥርዓት ካልተተካና መፍትሔ ላይ ካልሰራን ሲቆም የፋይናንስ ሥርዐታችን እንደሚቆም መገንዘብ ይገበናል። ይህን ካልተረዳንና ካልነቃን ራሳችንንም በኢኮኖሚ ካልቻልን፣ ተቋማዊ ሉዓላዊነታችን ከዛሬ በበለጠ ነገ በሌሎች እጅ መውደቁ አይቀሬ ነው። 📌 ታዲያ ይህንን የፋይናንስ ሥርዓታችንን ወደ ተሻለ ኢኮኖሚ መር የፋይናንስ ሥርዓት ለመለወጥ ምን እናድርግ? 1.የመግዛት አቅሙ እየተዳከመ የሚገኘውን በባንክ የተከማቸውን በቢሊዮን የሚገመት ገንዘብ ስራ ላይ ማዋል! ቤተክህነቱ የኢኮኖሚ ነጻነትንና ግልጽ የሆነ አሰራርን በማስፈን፣የክትትልና የቁጥጥር መስመሮችን በመዘርጋት በባንክ ያለ የቤተክርስቲያን ገንዘብ በቀጥታ ወደ ስራ ላይ እንዲውል መደረግ አለበት። እታች ካለው አጥቢያ እስከ ጠቅላይ ቤተክህነት ባሉ መዋቅሮች ውስጥ በሚሊዮንና በቢሊዮን የሚቆጠሩ የቤተክርስቲያን ገንዘቦች በተለያዩ ባንኮች ውስጥ በዝግ አካውንት (Fixed Deposit) ወይም በተንቀሳቃሽ ሒሳብ ተቀምጠው ይገኛሉ። ይህንን ገንዘብ ሥራ ላይ አለማዋል ትልቅ ኪሳራ መሆኑን ብዙ ሰው ሲያነሳውና በመድረኮቻችን ሲነገር አላይም። ለጥቂት ወራት ከሚከፈል ደሞዝና የሥራ ማስኪጃ በቀር ሁሉም ገንዘብ ስራ ላይ ካልዋለ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ ሁኔታ እየከሰረች ነው። ምክንያቱም በሀገራችን ባለው ከፍተኛ የዋጋ ንረት (Inflation) ምክንያት፣ በባንክ ዝም ብሎ የተቀመጠ ገንዘብ በየቀኑ የመግዛት ዓቅሙ እየሞተ ስለሚሄድ። 📌ይህንን በምሳሌ ላስረዳ:-ለአብነት ያህል፣ በዓመት በአማካይ 25% የዋጋ ንረት ቢኖር፣ ዛሬ በባንክ የተቀመጠ 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን) ብር ተቀማጭ ያለው አንድ ደብር በሂደት የሚደርስበትን የዓቅም መዳከም እንመልከት፦ ዝርዝር የሒሳብ ቀመሩን ትተን ውጤቱን እንመልከት። 📌በባንክ ደብተሩ ላይ 1,000 000 ሚሊዮን ያለው ደብር በዓመት በአማካይ 25% የዋጋ ንረት ቢኖር በሀገራችን የ5 ዓመታት ጉዞ (ደረጃ በደረጃ ስሌት) እንመልከት ገንዘቡ ሥራ ላይ ሳይውል በየዓመቱ በ0.75 እየተባዛ ለ5 ዓመታት ሲሄድ የሚደርስበት ኪሳራ ተመልከቱ፦ 📌ዛሬ (ዓመት 0)፦ 1 ደብር 1,000,000 ብር አለው እንበል። 1ኛ ዓመት ማጠናቀቂያ፦ 1,000,000 × 0.75 = 750,000 ብር ይኖረዋል። 2ኛ ዓመት ማጠናቀቂያ፦ 750,000 × 0.75 = 562,500 ብር ይሆናል የመግዛት አቅሙ። 3ኛ ዓመት ማጠናቀቂያ፦ 562,500 × 0.75 = 421,875 ብር ይሆናል የመግዛት አቅሙ። 4ኛ ዓመት ማጠናቀቂያ፦ 421,875 × 0.75 = 316,406 ብር ይሆናል የመግዛት አቅሙ። 5ኛ ዓመት ማጠናቀቂያ፦ 316,406 × 0.75 = 237,304 ብር ተመልከቱ ከ5 ዓመት በኋላ በባንክ ደብተራችን ላይ 1 ሚሊዮን ብር የሚል ቁጥር ቢኖርም፣ በትክክለኛው ገበያ ላይ መግዛት የሚችለው ዛሬ በ237,304 ብር ሊገዛ የሚችለውን ዕቃ ብቻ ነው። ይህም ማለት ከ76% በላይ ዓቅሙን አጥቷል ማለት ነው! ቤተክርስቲያን ገንዘብ ስታስቀምጥ ምን ያህል እየከሰረች እንደ ሆነ ልብ በሉ። ስለዚህ ምን እናድርግ ? መልሱ 2ኛ ላይ ነው። 2.የተበታተነውን የፋይናንስ ሥርዓት ወደ አንድ ቋት ማምጣት! በየአጥቢያውና በየገዳማቱ የተበታተነው የቤተክርስቲያን ገንዘብ በተናጠል ሲታይ አነስተኛ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ይህ አጠቃላይ ሀብት በጠቅላይ ቤተክህነት ወደ አንድ ማዕከላዊ ቋት (Single Pool) ቢሰበሰብና በባለሙያዎች የሚመራ የኢንቨስትመንት ተቋም ቢቋቋም፣ ቤተክርስቲያን በአጭር ጊዜ ውስጥ የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብት የሚቀይሩ ታላላቅ ኢንተርፕራይዞችን መገንባት ትችላለች። ስለዚህ አጠቃላይ የቤተክርስቲያን ገንዘብ ወደ አንድ ቋት ተሰብስቦ ተሻጋሪ የኢኮኖሚ ሥራዎች መሠራት አለበት። በአፋጣኝ ከአጥቢያ እስከ ጠቅላይ ቤተክህነት የተሰብሰው ገንዘብ በተጠና መልኩ:- ሀ.የኢንዱስትሪ ዞን መገንባት፦ ቤተክርስቲያን የራሷን የሲሚንቶ፣ የጨርቃጨርቅ፣ የመድኃኒትና የቴክኖሎጂ ግዙፍ ፋብሪካዎችን የያዘ ሀገራዊ ፕሮጀክት የሆነ የኢንደስትሪ ዞን መገንባት። ለ.ከሸማችነት ወደ አምራችነት የሚየደርሱ ስራዎችን መስራት፦ ለምሳሌ -ግብርናና ማኑፋክቸሪንግ ስራዎች ላይ መስራት። -ለቅዱሳት መካናት የሚያስፈልጉ ንዋያተ ቅድሳትንና አልባሳትን እንኳ ከውጭ ሀገር በዶላር ከመግዛት ተላቀን፣ ራሳችን አምርተን ለዓለም የምናስተዋውቅበትን ዓቅም መፍጠር ። ተበታትኖ በባንክ የመግዛት አቅሙ እየወደ ያለው ሳንቲም ተሰብስቦ ወደ ግዙፍ ካፒታል ካልተቀየረ፣ ድህነታችንን በገዛ እጃችን እያራዘምን ነው የምንቆየው። 📌ይህ ከሆነ በገጠርም በከተማም ያለችው ቤተክርስቲያን ያለምንም የኢኮኖሚ ችግር መገልገል ትችላለች። 3.ለአገልግሎት እና ለምእመናን የሥራ እድል መፍጠር ዛሬ ሀገሪቱን እያናወጠ ያለው የኑሮ ውድነት የቤተክርስቲያንን ደጅ እያንኳኳ ነው። ሌሊትና ቀን በቅፅረ ቤተክርስቲያን የሚተጉ ካህናትና ዲያቆናት ማዕዳቸው ሲጎድል፣ የሰንበት ትምህርት ቤትና ማኅበራት ወጣት ምእመናን ልጆቿ ተስፋ ጨልሞ በሥራ አጥነት ለጭንቀትና ለድብርት ሲዳረጉ፤በዓለም ያሉ ልጆቿም በሱስ ጎዳና ሲባክኑ ማየት የተለመደ ነው። ይህ ካልተፈታ ቤተክርስቲያን ነገ ታረካቢ ትውልድ መፍጠር አትችልም። ስለዚህ መፍትሄው ምንድነው ? 📌የሥራ ዕድል መፍጠር (Job Creation)፦ ይህንን ለማድረግ ቤተክርስቲያን በአስቸኳይ ወደ ሰፊ የግብርናና አግሮ-ኢንዱስትሪ ልማት መግባት አለባት። በዚህም ለአገልጋዮቿም ሆነ ለምእመናን በቂ የሥራ እድል መፍጠር ትችላለች። 📌 በቴክኖሎጂ፣ በማምረቻና በንግድ ዘርፎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ወጣቱን ከስደትና ከሱስ መታደግ። 📌 ኦርቶዶክሳዊ የቢዝነስ ተቋማትን ወጥነት ባለውና በተጠና መልኩ በየአጥቢያው መገንባት። 📌ለአገልጋዮችም ሆነ ለምእመናን የባንክ ብድር ማመቻቸት። ጠንክረው እንዲሰሩ የሥልጠና መድረኮችን መፍጠር። 👇ከታች ይቀጥላል ❗️ 👇👇👇👇
Открыть в Telegram- ገራፊውን የሚፈውስ ቁስል -ለገዳዩ ሕይወት የሚሰጥ ሞት - ለሚንቁት ክብር የሆነ ውርደት - በጦር የወጋውን ሰው ዓይን የሚያበራ ደም መድኃኔዓለም 🙏 ✍️ @ephrem_views ...
Открыть в TelegramСвязи
Похожие каналы
አቤል ተፈራ በላይ@abellteferaРелигия2,86 тыс.
ቢብሊካ ኢትዮጵያ (Biblica Ethiopia)@ethbiblicaРелигия2,83 тыс.
Catholic Web News Network@catholicbРелигия2,83 тыс.
GRACE LIFE COMMUNITY CHURCH@gracelifecommunitychurchРелигия2,82 тыс.
Fursaan Media@fursaan_mediaРелигия2,81 тыс.
የአንዋር መስጂድ ደርሶች@anwardersРелигия2,97 тыс.
AL-RISALA HUMANITY CENTER@alrisala1Религия2,78 тыс.
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 🇪🇹@orthodox_tewahedo23Религия2,78 тыс.