Кабинет

Посты канала Dr. Eyob Mamo

сначала новые

#8412Фото
Просмотры2 500−51%к среднему
Пересылки—
Реакции24
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
6 ч2 080
9 ч2 500
  1. Через 6 часов2 080
  2. Всего сейчас2 500
#8411Текст

የማይፈራው ውሻ አንድ የሃገራችን ተወላጅ ወደ አውሮፓ ሃገር ሄዶ ብዙም ሳይቆይ አንድ ቀን በአንድ መናፈሻ አካባቢ ለመዝናናት በመዘዋወር ላይ እያለ ከአንዲት በዚያ ከምትዝናና ሴት ጋር የመጣ ውሻ ወደ እርሱ መጠጋቱን አይቶ ስለሰጋ ውሻውን ለማባረር ልክ ድንጋይ እንደሚያነሳ ሰው ጎንበስ አለ፡፡ እንቅስቃቄው ግን ለውሻው አልገባውም፡፡ አሁንም ደግሞ ጎንበስ በማለት ልክ ድንጋይ አንስቶ እንደሚወረውር ሰው ምልክትን አሳየው፡፡ አሁንም ውሻው አልገባውም፡፡ የዚህ ሁኔታ ጊደት ያልገባው ግን ሰውየው ብቻ አልነበረም፣ ይህ የሃገራችን ሰውም የውሻው ሁኔታ ሊገባው አልቻለም፡፡ “የሃገራችን ውሾች ገና የመጀመሪያዋን የእጃችንን ወይም የሰውነታችንን እንቅስቃሴ ሲያዩ ነው ጭራቸውን ቆልፈው በርረው የሚጠፉት፡፡ እነዚህ የምእራባውያን ውሾች ደግሞ ድፍረታቸው . . .” በማለት ሲያሰላስል ሁኔታውን ራቅ ብሎ ከተቀመጠበት ሲከታተል የነበረ ሌላ የእኛው ሃገር ሰው ጠጋ ብሎ፣ “የዚህ ሃገር ውሾች እኮ እንደዚያ ስላደረክ ምንም አይነት ምላሽ አይሰጡህም” አለው፡፡ በመቀጠልም፣ “አየህ፣ የሃገራችን ውሾች በመንገድ እንኳን የመሄድ ነጻነት የላቸውም፡፡ ያገኘ ሁሉ ድንጋይ እያነሳ ያባርራቸዋል፡፡ ስለዚህም ማንኛውንም የሰው እንቅስቃሴ ከድብደባና ከመባረር ጋር ነው የሚያዛምዱት፡፡ እዚህ ያሉት ውሾች ግን ይህም ያም ስለማያሳድዳቸው ተረጋግተው ነው የሚሄዱት”፡፡ ይህንን የዚህን ሰው ገጠመኝ እንደሰማሁ ትዝ ያለኝ የራሴውና የአንዳንዶች የሃገሬ ሰዎች ሁኔታ ነው፡፡ በግል ጉዳዩ ላይ ማንም ጣልቃ ሳይገባበት፣ ሰዎች እየተከታተሉ ክፉ ሳያስቡበትና ሳይሰሩበት፣ በሆነ ባልሆነ ሳያቆስሉት የኖረ ሰውና በተቃራኒው በየቀኑ እሱና የእሱ የሆነው ነገር ሁሉ ተነክቶና ስነ-ልቦናው ተደብድቦ የኖረ ሰው የአኗኗር ዘይቤያቸው አንድ ሊሆን አይችልም፡፡ ብዙ የተነካ ሰው ብዙ ይሸማቀቃል፣ ጠርጣራ ይሆናል፣ በሆነ ባልሆነው ይሸሻል፡፡ ከዚህ በፊት ሰዎች በብዙ አቅጣጫ የጎዱት ሰው የመኖር ድፍረቱን ይነጠቃል፡፡ ይህ ከአጉል ልምምድ የሚመጣ የፍርሃት ሕይወት መዘዙ ብዙ ነው፡፡ የሰዎችን ንግግር፣ ሁኔታና እንቅስቃሴ፣ “ምን ሊያደርጉብኝ ይሆን?” በሚል በማያፈናፍን የስጋት ሕይወት ውስጥ እንድንኖር ያደርገናል፡፡ ይህ አይነቱ የፍርሃት ህይወት ውስጥ ካለህ፣ ዘመንህን ሳታስበላ የማስተካከያ እርምጃ ውሰድ፡፡ 1. ከዚህ በፊት የጎዳህን ሰው የሚመስል ሰው ሁሉ ክፉ አይደለም፡፡ በፍቅረኛ ስለተጎዳህ እውነተኛ ፍቅረኛ የለም ማለት አይደለም፣ አለቃ ስለጎዳህ አለቆች ሁሉ ጨካኞች ናቸው ማለት አይደለም፡፡ የንግድ አጋርህ ስለጎዳህ ሁሉም ሰው እንዲያ ነው ማለት አይደለም፡፡ 2. ያለፈው ልምምድህ እንዲያስተምርህ እንጂ እንዲያስርህ አትፍቀድ፡፡ የደረሰብህን ክፉ ልምምድ ሁሉ ለወደፊት ከማን ጋር ምን ማድረግ እንደሚገባህ፣ ለምን አይነት ነገር ምን አይነት ጥበብ መጠቀም እንደሚገባ … ትምህርት አግኝበት እንጂ፣ “ሁለተኛ!” በሚል ጭፍን ውሳኔ አትታሰር፡፡ 3. የማይቀረውን የሕይወት እውነታ ተጋፈጥ፡፡ በዚህ ምድር ላይ ከጉዳት ነጻና አስተማማኝ ቦታ በፍጹም የለም፡፡ የትም ብትሄድ፣ ከማንም ሰው ጋር ብትገናኝ . . . አይነቱና በመጠኑ ይለያይ እንጂ ሰዎች ሁል ጊዜ ይጎዱሃል፡፡ ከስንቱ ሸሽተህና ተደብቀህ፣ ስንቱን የሕይወትና የስራ መስክ ትተህ ትዘልቀዋለህ? ጠንከር በል! በርታ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Открыть в Telegram
Просмотры2 140−58%к среднему
Пересылки—
Реакции38
Комментарии—
#8409Фото
Просмотры4 310−15%к среднему
Пересылки—
Реакции27
Комментарии—
#8408Текст

ከብርታታችሁ ጀምሩ! ስንቶቻችሁ የእኔ አይነት የልጅነት ልምምድ እንዳላችሁ ባላውቅም፣ አንድ የማልረሳውን ልምምድ፣ ምናባትም እናንተም የተለማመዳችሁትን ነገር ላስታውሳች፡፡ የተለያዩ የፈተና ውጤቶችን እቤት ይዘን ስንመጣ አብዛኛውን ጊዜ የወላጆቻችንን ትኩረት የሚስበው ዝቅተኛ ውጤት ያገኘንበት የትምህርት ዘርፍ ነው፡፡ ጥሩ ውጤት ላገኘንበት የትምህርት ዘርፍ ከምናገኘው ምስጋና ወይም አድንቆት ይልቅ አናሳ ውጤት ላገኘንበት ዘርፍ የምናገኘው ወቀሳውና ማስጠንቀቂያው ይበዛል፡፡ ይህ ልምምድ ብርታታችን ላይ ከማተኮርና እሱን ከማሳደግ ይልቅ ደካማ ጎናችን ላይ በማተኮር እንድንታገል ሳናውቀው አእምሮአችንን አሳምኖታል፡፡ ስለሆነም ቀድሞውኑ ያታገለን ነገር ላይ እንደገና ስንታገል፣ ቀለል ያለንንና የሚሳካልንን ችላ እንልና የዚህ አቀራረባችን ተጽእኖው ሁለቱንም ይዟቸው ይወርዳል፡፡ ያታገለን፣ የከበደንና አልሆን ያለን ነገር ላይ የማተኮር ሁኔታ በራሱ ምንም ችግር የለውም ካላችሁና ከሰራላችሁ በዚያው ቀጥሉበት፡፡ ነገር ግን ሁል ጊዜ መጀመር የሚገባንና ተገቢውን ትኩረት ልንሰጠው የሚገባን ብርቱ ጎናችን እንደሆነ ዛሬ ላስታውሳችሁ፡፡ ከብርቱ ጎናችሁ መጀመር . . . 1. በምታገኙት የመጀመሪያ ስኬት የመነሳሳትንና ለከበዳችሁ ነገር ድፍረት የማግኘትን አቋም ይሰጣችኋል፤ 2. በደካማ ጎናችሁ ላይ ሳይሆን በብርቱ ጎናችሁ ላይ የምትገነቡበትን መሰረት ጠንካራ ይጥልላችኋል፤ 3. አብዛኛውን አቅማችሁን በብርታታችሁ ላይ በመገንባት፣ የተረፈውን ደግሞ ያታገላችሁ ላይ በመስራት እያደጋችሁ እንድትሄዱ መንገዱን ይጠርግላችኋል፡፡ ማንኛውንም ነገር ስትጀምሩ ብርቱ በሆናችሁበትና በሚሳካላችሁ ነገር ጀምሩ፡፡ ስሌቱ እንዲህ ነው፡- 80 በመቶ ጥረታችሁን በብርታታችሁ ላይ እና በሚሳካላችሁ ላይ አሳልፉ፤ 20 በመቶውን ጥረታችሁን ደግሞ ያታገላችሁን ነገር ለማዳበር ተጠቀሙበት፡፡ ማሳሰቢያ ለወላጆች፡- ልጆቻችሁ የሚሳካላቸውን፣ ጥሩ ውጤት የሚያመጡበትንና የሚያጓጓቸውን ነገር ለዩላቸውና እሱን ከማድነቅ ጀምሩ፡፡ እሱን አድርጋችሁ በማበረታታት ካጠገባችኋቸው በኋላ ቀስ በቀስ ደከም ያሉበት ነገር ላይ እንዲሰሩ አደፋፍሯቸው፡፡ ልጆች በዝንባሌና በሚሳካላቸው ነገር ይለያያሉ እንጂ “ጎበዝና ደደብ” በሚል ጎራ አይለያዩም፡፡ የጉብዝና ዘርፋችን ይለያያል እንጂ ሁላችን ጎበዝ ነን!!! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Открыть в Telegram
Просмотры4 080−19%к среднему
Пересылки—
Реакции44
Комментарии—
#8406Текст

የማቆም ውሳኔ አንድ የጀመራችሁት ነገር በፍጹም እንደማያስቀጥላችሁ እያወቃችሁ ለውጥ ማምጣት ካቃታችሁ . . . እንዲሁም ከአንድ ሰው ጋር ያላችሁ ግንኙነት ፍጹም ጤና ቢስ እንደሆነና እንደማያዛልቃችሁ እያወቃችሁት ደንዝዛችሁ እንደቀራችሁ ከተሰማችሁ፣ ችግራችሁ ነገሩን የማቆም ከመሆኑ ይልቅ አዲስ ነገር የመጀመር ጉዳይ እንደሆነ አትዘንጉ፡፡ 1. እንደገና የመጀመር ፍርሃት አንድን ነገር እንደገና የመጀመር ፍርሃት ካለብን አሁን ያለውና አላስኬድ ያለውን ነገር ማቆም እንዳለብን እያወቅነው እንኳን ያንን ማድረግ ያስቸግረናል፡፡ ሆኖም፣ የተበላሸ ነገር ይዞ የመቀጠል ሁኔታ ረጅም ርቀት የሚሄድን ችግር ይዞ እንደሚጠብቀን እናስታውስ፡፡ 2. ግራ መጋባት አንድን ነገር ማቆም እንዳለብን ብቻ አውቀን ያንን ካቆምን በኋላ ምን እንደምንጀምር ካላወቅነውና ግራ ከገባን ሁኔታው አስፈሪ ያደርገዋል፡፡ እዚህ ጋር ማስታወስ ያለብን ነገር ቢኖር አንድን ነገር ስናቆም በቶሎ ሌላ ነገር መጀመር እንደሌለብን ነው፡፡ በተለይም ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት እንዳቆምን ወዲያው ሌላ መጀመር እንዳለብን ማሰብ ወደሌላ አስቸጋሪ ግንኙነት ውስጥ እንድንገባ ሊያሳስተን ይችላል፡፡ 3. ጊዜ እንዳባከንን መሰማት አንድ ነገር አላስኬድ ሲለንና ማቆም ስንፈልግ፣ አንዳንድ ጊዜ የሚቆጨን በዚያ ነገር ላይ እስካሁን ያሳለፍነው (ያባከንነው) ጊዜ ነው፡፡ “ይህንን ያህል አመት ቆይቼ” እንላለን፣ ልክ በቁጭት ከተነሳን አሁን ያለው ነገር ይለወጥ ይመስል፡፡ አንድ ነገር ፈጽሞ እንደማያስኬደን ካወቅን በኋላ ብዙ ጊዜ አቃጥያለሁ ብሎ ማሰብ በማይሰራ ነገር ላይ ሌላ ተጨማሪ ጊዜ በመቃጠል ወደፊት ለሚቆየን የከፋ ጸጸት ራስን ማዘጋጀት ማለት ነው፡፡ አስታውሱ . . . • አዲስ የሚተክለውን ነገር በሚገባ ያወቀ ሰው አሮጌውን መንቀል አያስቸግረውም፡፡ • አዲስ የሚገነባው ነገር የገባው ሰው አሮጌውን ማፍረስ አይከብደውም፡፡ • አዲስ የሚጀምረውን ነገር የተረዳ ሰው አሮጌውን ማቋረጥ አያዳግተውም፡፡ ችግራችን አቅጣጫን ያለማወቅ እንደሆነ ተገንዝበን ስለነገው ጉዟችን ግልጽ የሆነ እይታን ስናዳብር በፊት ያስቸገረን ነገር ምን ያህል ቀላል እንደሆነ እንደርስበታለን፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Открыть в Telegram
Просмотры5 650+12%к среднему
Пересылки—
Реакции82
Комментарии—
#8404Фото
Просмотры5 840+16%к среднему
Пересылки—
Реакции121
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
65 ч5 780
67 ч5 840
  1. Всего сейчас5 840
#8403Текст

የመጽሐፍ አጻጻፍ ጥበብና ዘዴ (The Art and Techniques of Book Writing) የቡድን ኮቺንግ (Group Coaching) መጽሐፍ በመጻፍ ማስተላለፍ የምትፈልጉት መልእክት ካለና ሃሳባችሁን አዋቅራችሁ እንዴት ለህትመት ማብቃት እንዳለባችሁ ተጨማሪ ስልጠና እና መመሪያ ከፈለጋችሁ ይህ የቡድን ኮቺንግ ሊጠቅማችሁ ይችላል፡፡ ይህ ፕሮግራም የቡድን ሥልጠናንና የግል ኮቺንግን ያቀናጀ (Hybrid) የመጽሐፍ አጻጻፍ የኮቺንግ ፕሮግራም ነው፡፡ ማለትም የግሩፕ ስልጠናን እና በግል የሚደረግ ኮቺንግን የቀላቀለ አቀራረብ ነው፡፡ የ online የቡድን ሥልጠና፦ ስለ መጽሐፍ አጻጻፍ መርሆዎች፣ ዘዴዎችና ሂደቶች በ online በቡድን መሰልጠን። የግል (individual) ኮቺንግ፦ የ online ስልጠናው ሲጠናቀቅ ተሳታፊዎች በየራሳቸው የመጽሐፍ ፕሮጀክት ላይ ተመስርተው የግል እገዛና መመሪያ ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ በአካል ወይም በ online ማግኘት። ይህ የቡድን ኮቺንጉ የሚሰጠው ከ10 እስከ 15 ለሚሆኑ ሰዎች ብቻ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው ሰልጣኞች ከዶ/ር ኢዮብ ጋር በግል የማሳለፍ እድል እንዲያገኙ ነው፡፡ የቡድን ሥልጠና (Telegram Live Training) ቀን 📖        የሚቆይበት ጊዜ፦ ሁለት ሳምንታት 📖        የሥልጠና ቀናት፦ ሰኞ እና ሮብ (ሰኞ ሕዳር 21 እና ሮብ ሕዳር 23 እንዲሁም ሰኞ ሕዳር 28 እና ሮብ ሕዳር 30 - 2019) 📖        ሰዓት፦ ከምሽቱ 2:00 እስከ 3:30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር) 📖        የሥልጠና መንገድ፦ Telegram Live 📖        የሥልጠና ብዛት፦ በጠቅላላ አራት ክፍለ ጊዜዎች የግል ኮቺንግ (Individual Coaching Sessions) 📖        ይህ ክፍል እያንዳንዱ ተሳታፊ በራሱ የመጽሐፍ ፕሮጀክት ላይ ተመስርቶ የግል መመሪያና እገዛ የሚያገኝበት ነው። 📖        ተሳታፊዎች እንደ ምርጫቸው ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር በአካል ወይም በTelegram/ስልክ በመገናኘት ኮቺንጉን ያገኛሉ። የቀጠሮ ቀንና ሰዓትም በግል ስምምነት ይወሰናል። 📖        እያንዳንዱ ተሳታፊ በሦስት ሳምንታት ውስጥ ሦስት የአንድ ሰዓት የግል ኮቺንግ ክፍለ ጊዜዎችን ያገኛል። በዚህ coaching ለመሳተፍ፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡ Thank You!

Открыть в Telegram
Просмотры6 480+28%к среднему
Пересылки—
Реакции41
Комментарии—
#8401Фото

ችግር ካለ መፍትሄ አለ! ሁለት ጓደኛሞች ቀለል ባለ የቁምጣና የቲሸርት አለባበስ ሆነው በአንድ ጫካ ውስጥ ዘና እያሉና እየተጫወቱ ይሄዳሉ፡፡ በድንገት አንዱ ጠያቂ ሌላኛው መላሽ የሆኑበት ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ ጠያቂ፡- “አሁን አንበሳ ቢመጣብህ ምን ታደርጋለህ?” መላሽ፡- “ሽጉጤን አውጥቼ ግንባሩን ነዋ የምለው”፡፡ ጠያቂ፡- “እንዴ! ሽጉጡን ደሞ ከየት አመጣኸው?” መላሽ፡- “አንተስ አንበሳውን ከየት አመጣኸው?” የዚህ በልጅነታችን እንሰማቸው የነበሩትን ታሪኮች የሚመሰለው ታሪክ አስተማሪ ነጥብ፡- ለሚመጣው ለማንኛውም ችግር መፍትሄ አለው! አንዳንድ ሰዎች አመለካከታቸው ሁሉ አሁን “አንበሳ ቢመጣብኝስ” የሚል አይነት ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ሁል ጊዜ የሚታያቸው የሚመጣው “አንበሳ” ነው፡፡ ስለሆነም ሁል ጊዜ በፍርሃት፣ በስጋትና ገና ለገና አንድ ችግር ይመጣ ይሆናል በሚል ጠርጣራነት ነው የሚኖሩት፡፡ የዚህ ተቃራኒ ሰዎች በማንኛውም ሰዓት ችግር ሊከሰት እንደሚችል ያውቃሉ፤ ነገር ግን ለእያንዳንዱ ለሚመጣው ችግር መፍትሄ የማምጣት ብቃትም እንዳላቸው ያምናሉ፡፡ ስለዚህ ገና ለገና ችግር ይመጣል ብለው ከመዝናናት፣ ከመግባባት፣ ከመስራት፣ ከመውጣት፣ አዳዲሲ ነገር ከመጀመር . . . አይመለሱም፡፡ ገደል ካለ፣ ድልድይ አለ! በሽታ ካለ፣ መድሃኒት አለ! ጠላት ካለ፣ ወዳጅ አለ! መውደቅ ካለ፣ መነሳት አለ! ሁል ጊዜ ራእይህንና ተልእኮህ መንገድ ላይ ሊቆም የሚመጣ ችግር ካለ መፍትሄም አለ! ስለዚህ፣ ገና ለገና ችግር ይመጣል ብለህ ከመንገድህ አትገታ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Открыть в Telegram
Просмотры5 610+11%к среднему
Пересылки—
Реакции100
Комментарии—
#8394Текст
Просмотры6 720+33%к среднему
Пересылки—
Реакции61
Комментарии—
#8393Фото
Просмотры6 470+28%к среднему
Пересылки—
Реакции48
Комментарии—