Кабинет

Посты канала የህይወት ቃል / Word of life

сначала новые

#4870Текст

ቀን 294 ድምጹን ለመለየት ወደ እርሱ መጠጋት የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል - ዮሐንስ 9፤ ዮሐንስ 10፡1-21 ''በር ጠባቂው በሩን ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰማሉ። የራሱንም በጎች በየስማቸው እየጠራ ያወጣቸዋል። '' ዮሐንስ 10:3 “በጎቹ ድምፁን ይሰማሉ፤ እርሱም የራሱን በጎች በየስማቸው ይጠራቸዋል፤” ዮሐ. 10፡3 በእያንዳንዷ እርምጃችን ውስጥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ የምንችለው አካሄዳችንን ከእርሱ ጋር ያደረግን እንደሆን ብቻ ነው። ኢየሱስ ይህንን ሃሳብ በእረኛና በበጎች ምሳሌነት ሲያብራራው እንዲህ አለ፦ “በበሩ የሚገባ ግን እርሱ የበጎች እረኛ ነው፤ በር ጠባቂውም በሩን ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምጹን ይሰማሉ። የራሱንም በጎች በየስማቸው እየጠራ ያወጣቸዋል። የራሱ የሆኑትንም ሁሉ ካወጣ በኋላ ፊት ፊታቸው ይሄዳል፤ በጎቹም ድምጹን ስለሚያውቁ ይከተሉታል። እንግዳ የሆነውን ግን ድምጹን ስለማያውቁ ከእርሱ ይሸሻሉ እንጂ ፈጽሞ አይከተሉትም። . . . በጎቼ ድምጼን ይሰማሉ እኔ አውቃቸዋለሁ፤ እነርሱም ይከተሉኛል።” ዮሐ. 10፥2-5፣27። ልክ እንደ እነዚህ በጎች እኛም ከእረኛችን ጋር ያለን ቀረቤታ የጠበቀ ሲሆን ድምጹን የበለጠ እየለየን እንሄዳለን። ስለዚህ ጉዳይ ሳስብ አንድ ወንድም የሰጠው ሀሳብ አይረሳኝም። እንዲህ ነበር ያለው፦ “ሁለት ልጆች አሉኝ። በለጥ የሚለው ወንድ ሲሆን ሴቷ ደግሞ የእርሱ ተከታይ ገና አፏን በደንብ ያልፈታች ነበረች። ቀኑን ሙሉ ከቤት ርቄ በስራ ተጠምጄ ማታ ስገባ ትንሿ ልጄ ልታነጋግረኝ ፈልጋ ትቀርበኛለች። ሆኖም ግን የምትለውን ለማስተዋል ስለምቸገር ከመግባባት ይልቅ መደናቆር ይሆንብናል። ይሄን ጊዜ ተለቅ የሚለው ልጄ ‘አባዬ የምትልህ እኮ እንደዚህ ነው’ ይለኛል። የሚገርመው ደግሞ በእርግጥም የምትለኝ እንደዛ መሆኑ ነበር። ከዚያም ለምንድን ነው እኔ ሳይገባኝ እርሱ የገባው ብዬ ሳስብ የተረዳሁት ነገር ቢኖር፣ በሁለቱ መካከል ያለው ቅርርብ ልዩነት ማምጣቱን ነበር። እርሱ አብሯት ስለሚውል ለእኔ ትርጉም ያልሰጠኝ መንተባተብ ለእርሱ ግን የተሟላ ንግግር ሆነለት።” እኛም ከእግዚአብሔር ጋር በተቀራረብን ጊዜ ለሌላው ምንም ትርጉም የሌለውን የጌታን መልእክትና ቋንቋ በቀላሉ እንረዳለን። ፈቃዱን እንማርበታለን። እንዴት ያለ ድንቅ መረዳት ነው! “የራሱንም በጎች በየስማቸው እየጠራ ያወጣቸዋል” የሚለው መግለጫ ይህ መልካም እረኛችን ከእያንዳንዳችን ጋር የጠበቀ ሕብረት ማድረግ እንደሚፈልግ የሚያሳይ ነው። እርሱ በስማችን ያውቀናል። የእኛ ነገር ለእርሱ ታላቅ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው። በተጨማሪም ጌታችን ኢየሱስ በጎቹን ፊት ፊታቸው በመሄድ በፍቅር የሚመራቸው እንጂ በኋላ በዱላ የሚነዳቸው እንዳልሆነ ልብ ይሏል! ታዲያ በዘለዓለማዊ ፍቅሩ ወደ እርሱ ሲስበን እኛም ወደ እርሱ ተጠግተን፣ ድምጹን በመስማት በእያንዳንዱ እርምጃችን እርሱን መከተል ምኞታችን ሊሆን ይገባል። አባት ሆይ፣ ለእኛ ባለህ ታላቅ ፍቅር በግል የምታውቀን ወደ ራስህም ልታስጠጋን የምትፈልግ መልካም እረኛችን መሆንህን በመረዳት፣ እኛም ሁል ጊዜ ድምጽህን በመስማት ዱካህንም በመከተል ከአንተ ፈቃድ ጋር የተስማማ ህይወት መኖር እንድንችል በጸጋህ እርዳን። አሜን!

Открыть в Telegram
Просмотры192−55%к среднему
Пересылки—
Реакции17
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
6 ч104
15 ч192
  1. Через 6 часов104
  2. Всего сейчас192
#4869Фото
Просмотры172−60%к среднему
Пересылки—
Реакции6
Комментарии—
Динамика просмотровСкрыть динамику

Рост просмотров

Часов после публикации

Показать таблицей
Часов после публикацииПросмотры
0 ч0
6 ч96
15 ч172
  1. Через 6 часов96
  2. Всего сейчас172
#4868Текст

ቀን 293 አልፈርድብሽም የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል - ዮሐንስ 7-8 'እርሷም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንድም የለም” አለች። ኢየሱስም፣ “እኔም አልፈርድብሽም፤ በይ ሂጂ፤ ከእንግዲህ ግን ኀጢአት አትሥሪ” አላት።] ' ዮሐንስ 8:11 “ኢየሱስም፣ ‘እኔም አልፈርድብሽም፤ በይ ሂጂ፤ ከእንግዲህ ግን ኃጢአት አትሥሪ’ አላት።” ዮሐ. 8፡ 11 ይህች ሴት በምንዝር ኃጢአት እጅ ከፍንጅ ተይዛ በህጉ መሰረት በድንጋይ ሊወግሯት እየገፈታተሩ ወደ ቤተ መቅደሱ አደባባይ አመጧት። ለእርሷ ተገቢውን ቅጣት ከመስጠታቸው በፊት ግን በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንዲሉ ሊያጠምዱት የሚፈልጉትን ኢየሱስን እንዲህ ብለው ጠየቁት፦ “ መምህር ሆይ፣ ይህች ሴት ስታመነዝር ተያዘች፤ ሙሴም፣ እንደዚች ያሉ ሴቶች በድንጋይ እንዲወገሩ በሕጉ አዞናል፤ አንተስ ምን ትላለህ?” ዮሐ. 8:5። ኢየሱስ ግን ጎንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ይጽፍ ጀመር። በጥያቄ ሲወተውቱት ቀና ብሎ፣ “ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት እርሱ አስቀድሞ ድንጋይ ይወርውርባት” አላቸው። እንደ ገናም ጎንበስ ብሎ በምድር ላይ ጻፈ። ይህን እንደ ሰሙ፣ ከሽማግሌዎች ጀምሮ አንድ በአንድ ወጡ፤ ሴትዮዋም እዚያው ፊቱ እንደ ቆመች ኢየሱስ ብቻውን ቀረ። ኢየሱስም ቀና ብሎ፣ “አንቺ ሴት፣ ሰዎቹ የት ሄዱ? የፈረደብሽ የለምን?” አላት። እርሷም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንድም የለም” አለች። ኢየሱስም፣ “እኔም አልፈርድብሽም፤ በይ ሂጂ፤ ከእንግዲህ ግን ኃጢአት አትሥሪ” አላት። (ቁ 6-11)። በእርግጥም በዚያች አመንዝራ ላይ ለመፍረድ ሙሉ ስልጣን የነበረው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነበር። እርሱ ግን “እኔም አልፈርድብሽም” አላት። ይህንንም ያለው ለእርሷ እና ለዓለም ሁሉ ኃጢአት ደሙን በማፍሰስ ተገቢውን ቅጣት ሊከፍል ስለመጣ ነው። ጌታችን ኢየሱስ በራሱ ጽድቅ የዚህችን ኃጢአተኛ ሴት ገመና ሸፈነላት። ብልሹ ማንነቷን ጥላ አዲስ የህይወት ምዕራፍን እንድትጀምር ዕድል ሰጣት። በእርሱ የጽድቅ ካባ ተሸፍና፣ በጽድቅ ጎዳና እንድትመላለስ “ከእንግዲህ ግን ኃጢአት አትስሪ” ብሎ ሸኛት። እኛም ምናልባት እንደዚያች አመንዝራ በግልጽ ኃጢአት ውስጥ ወድቀን፣ ከገባንበት አዙሪት ውስጥ መውጣት አቅቶን ይሆን? እግዚአብሔር በኃጢአት ያደፈውን ማንነታችንን የሚያነጻ እና ነውራችንን የሚሸፍነውን ጽድቁን እነሆ ይለናል። ይህም ጽድቅ የተበረከተልትን በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው። “እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ለመፍረድ ሳይሆን፣ ዓለምን በእርሱ ለማዳን ነው። በእርሱ የሚያምን ሁሉ አይፈረድበትም፤ በእርሱ የማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ፣ አሁኑኑ ተፈርዶበታል።” ዮሐ 3:17 18። ዛሬ በእምነት ይህንን የእርሱን ጽድቅ ብንቀበል በእርግጥም ከፍርድ እናመልጣለን። እርሱ ካጸደቀን ደግሞ የሚከስሰን ማንም የለም። የከሳሻችንን የዲያቢሎስን አፍ ጥርቅም አድርጎ የሚዘጋልን ጽድቃችን የሆነው እግዚአብሔር ብቻ ነው። “እግዚአብሔር የመረጣቸውን የሚከስስ ማን ነው? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፤ ታዲያ የሚኰንን ማን ነው? የሞተው፣ እንዲሁም ከሞት የተነሣው፣ በእግዚአብሔር ቀኝ የተቀመጠው ክርስቶስ ኢየሱስ፣ ስለ እኛ ይማልዳል።” ሮሜ 8:33፣ 34 አባት ሆይ፣ የከሳሻችንን የዲያቢሎስን አፍ ልትዘጋ እና በልጅህ በክርስቶስ ኢየሱስ ጽድቅህን ልታለብሰን ዛሬም እጅህን ዘርግተን ስለምትጠራን እናመሰግንሃለን። እኛም ወደ እቅፍህ እንድንሮጥ በጽድቅህ እንድንሸፈን እና እንድንለወጥ እርዳን። አሜን!

Открыть в Telegram
Просмотры220−49%к среднему
Пересылки—
Реакции18
Комментарии—
#4866Текст

ቀን 292 ይቅር ተባባሉ የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል - ማቴዎስ 18 “ስለዚህ እያንዳንዳችሁ ወንድሞቻችሁን ከልባችሁ ይቅር ካላላችሁ፣ የሰማዩ አባቴም እንደዚሁ ያደርግባችኋል።” ማቴዎስ 18:35 አንዳንዴ በደረሰብን በደል እጅግ ከመጎዳታችን የተነሳ በጥልቅ ሃዘን እና ምሬት ተውጠን እንዲህ ስንል እንደመጣለን።“እርሱን ወይም እርሷን ይቅር ከምል ሰማይ ይቅርብኝ!” እርግጥ ነው፣ ይቅር ማለት ቀላል አይደለም። ያጠቁንን መበቀል፣ ከቻልን እጥፉን ካልሆነም ተመጣጣኙን ጥቃት ማድረስ ውስጣችን ይፈልጋል። ነገር ግን አፍቃሪ አምላካችን እኛ በበደልነው ጊዜ ለእኛ ያሳየው ምህረት እና ይቅርታ፣ እኛም እርስ በርሳችን አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖር ይቅር እንድንባባል ግድ ይለናል። ጌታችን ኢየሱስ ይህንን እውነት በማይረሳ ምሳሌ እንዲህ በማለት ነበር ያስተማረው:- “ስለዚህ መንግሥተ ሰማይ፣ በአገልጋዮቹ እጅ የነበረውን ሂሳብ ለመተሳሰብ የፈለገን ንጉሥ ትመስላለች። ሂሳቡን ማጣራት እንደ ጀመረም ዐሥር ሺህ ታላንት (በሚሊዮን የሚቆጠር ብር የሚያህል ነው) ዕዳ ያለበትን አንድ አገልጋይ አቀረቡለት። አገልጋዩም ያለበትን ዕዳ መክፈል ስላቃተው እርሱ ራሱ፣ ሚስቱ፣ ልጆቹና ንብረቱ ሁሉ ተሽጠው ዕዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ። በዚህ ጊዜ አገልጋዩ እግሩ ላይ ወድቆ፣ ‘ታገሰኝ፣ ያለብኝን ዕዳ ሁሉ እከፍልሃለሁ’ ሲል ለመነው። ጌታውም አዘነለትና ማረው፤ ዕዳውንም ትቶለት አሰናበተው። ያ አገልጋይ ከጌታው ፊት እንደ ወጣ አንድ መቶ ዲናር (ጥቂት ብር ያህል ነው) የእርሱ ዕዳ ያለበትን አገልጋይ ባልንጀራውን አግኝቶ እንቅ አድርጎ በመያዝ፣ ‘ያለብህን ዕዳ ክፈለኝ!’ አለው። ባልንጀራው አገልጋይም ከፊቱ ወድቆ፣ ‘ታገሠኝ እከፍልሃለሁ’ ብሎ ለመነው። ነገር ግን ሊታገሠው ፈቃደኛ ስላልነበረ፣ ያለበትን ዕዳ እስኪከፍለው ድረስ ወህኒ ቤት አስገባው። የሆነውን ነገር ያዩ ሌሎች አገልጋዮችም በጣም አዘኑ፤ ሄደውም ሁኔታውን በሙሉ ለጌታቸው ነገሩት። በዚህ ጊዜ ጌታው አገልጋዩን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ ‘አንተ ክፉ አገልጋይ፤ ስለ ለመንኸኝ ያን ሁሉ ዕዳ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ ማርሁህ አንተም ባልንጀራህን ልትምረው አይገባህም ነበርን?’ በቍጣም ያለበትን ዕዳ ከፍሎ እስኪጨርስ ድረስ ለአሳሪዎች አሳልፎ ሰጠው። ስለዚህ እያንዳንዳችሁ ወንድሞቻችሁን ከልባችሁ ይቅር ካላላችሁ፣ የሰማዩ አባቴም እንደዚሁ ያደርግባችኋል።” ማቴ 18: 23-35 በእርግጥም እጅግ ብዙ እዳ እንደነበረበት ተበዳሪ እኛም ፈጽሞ ራሳችንን ነጻ ልናወጣበት በማንችል የኃጢአት እዳ ውስጥ ተዘፍቀን ሳለ፣ ያንን ሁሉ እዳችንን በመስቀል ላይ ህይወቱን በመስጠት ጌታ ይቅር ብሎናል። ታዲያ በእኛ ላይ ደረሰብን የምንለው ጉዳት እኛ በአምላካችን ላይ ከፈጸምነው በደል ጋር ሲነጻጸር የሰማይና የምድር ያህል የተራራቀ መሆኑን ስንገነዘብ፣ ጌታ ይቅር እንዳለን እኛም ይቅር ለማለት ውስጣችን ይነሳሳል። እንግዲያውስ የይቅርታችን ምንጭ እና መስፈርት እኛ ራሳችን ከአምላካችን የተቀበልነው ይቅርታ ሊሆን ይገባል። ቂም ከመጥፎ ትዝታችን ጋር ሁል ጊዜ አቆራኝቶ የሚያኖረን ካቴና ሲሆን፣ ይቅርታ ግን ያንን ካቴና የመስበር እና እኛን ነጻ የማውጣት ኃይል አለው። ቂም ቁስላችንን ሁል ጊዜ እያመረቀዘ ስቃያችንን የሚጨምር ሲሆን፣ ይቅርታ ግን ፈዋሽ ኃይል አለው። ቂም የጎዳንን ለመውጋት ብለን ግን ስለቱን ወደ ራሳችን አዙረን የያዝነው ጩቤ ሲሆን፣ ይቅርታ ግን “የእሳት ፍም በራሱ” ላይ ለመከመር የሚያስችል ድንቅ መሣሪያ ነው (ሮሜ 12:20)። ይህንን በማስተዋል ቃሉ እንዲህ በማለት የሚያዘንን በህይወታችን ለመለማመድ ፈቃደኞች እንሁን። “እርስ በርሳችሁ ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ጌታ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ሌላውን ይቅር በሉ።” ቆላ. 3:13 አባት ሆይ፣ ይቅር ማለት ምን ያህል እንደሚከብደን አንተ ታውቃለህ። ነገር ግን አንተ እኛን አስቀድመህ ይቅር በማለት ልባችንን በፍቅርህ በማለስለስ እኛም ደግሞ እርስ በርሳችን አንተ ይቅር እንዳልከን እንደዚያው ይቅር እንድንባባል ስለ መራኸን እያመሰገንንህ ሁል ጊዜ ይህንን ይቅርታ በህይወታችን እንድንለማመድ በጸጋህ እርዳን። አሜን!

Открыть в Telegram
Просмотры310−28%к среднему
Пересылки—
Реакции22
Комментарии—
#4864Текст

ቀን 291 በሰላም ኑሩ የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል - ማቴዎስ 17፤ ማርቆስ 9 “ጨው መልካም ነው፤ ነገር ግን ጨው ጨውነቱን ቢያጣ እንዴት መልሳችሁ ጣዕም እንዲኖረው ታደርጉታላችሁ? ጨው በውስጣችሁ ይኑራችሁ፤ እርስ በርሳችሁም ተስማሙ።” ማርቆስ 9:50 አስራ ሁለቱ የጌታ ደቀመዛሙርት በመንገድ እየሄዱ ሳለ በመካከላቸው አንድ አወዛጋቢ ጥያቄ ተነሳ። ጥያቄውም እንዲህ የሚል ነበር:- “ከሁሉ የሚበልጥ ማን ነው?” በቅርቡ ጌታቸው ምድራዊ ስልጣን እንደሚቆናጠጥ አስበው ነበርና ከፍተኛውን ሹመት ለማግኘት ሁሉም “እኔ ከሁሉም እበልጣለሁ” በማለት ተከራከሩ። ይህ አመለካከታቸው በመካከላቸው አንድነት፣ ፍቅር እና ሰላም እንዳይኖር አድርጎ ነበርና ጌታችን ኢየሱስ ይህንን አመለካከታቸውን አስወግደው በፍቅር እና በሰላም ለመኖር የሚያስችላቸውን ትምህርት ሰጣቸው። በመጀመሪያ “መጀመሪያ ለመሆን የሚፈልግ፣ ከሁሉ መጨረሻና የሁሉም አገልጋይ ይሁን” በማለት ስልጣን እና ክብር እነርሱ እንደሚያስቡት በሌላው ላይ መሰለጠን ሳይሆን ዝቅ ብሎ ማገልገል እንደሆነ ነገራቸው (ማር. 9:35)። በእርግጥም፣ የሰላም መደፍረስ እና የብዙ ግጭቶች መንስኤ በራስ ወዳድነት ሌሎችን ወደ ታች እየረገጥን እኛ ወደ ላይ ለመወጣጣት መፈለጋችን ነው። ያዕቆብ ይህ ራስ ወዳድነት የጠብ መንስኤ እንደሆነ ሲጽፍ እንዲህ ይላል:- “በእናንተ መካከል ያለው ጦርነትና ጠብ ከየት የመጣ ነው? በውስጣችሁ ከሚዋጉት ምኞታችሁ አይደለምን? ትመኛላችሁ፤ ነገር ግን አታገኙም። ትገድላላችሁ፤ በብርቱም ትመኛላችሁ፤ ልታገኙም አትችሉም። ትጣላላችሁ፤ ትዋጋላችሁ፤” ያዕ. 4:1፣3 በመቀጠልም ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን ለራሳቸው ከፍተኛ ስፍራን በመፈለግ በሚያደርጉት ትንቅንቅ ሌሎችን እንዳይጎዱ እንዲህ በማለት ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጣቸው:- “በእኔ ከሚያምኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ ከባድ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለዋል” ማር. 9:42። በእርግጥም፣ በራስ ወዳድነት ዓይናችን ሲታወር የራሳችንን ጥቅም ብቻ በማሳደድ በሌሎች ላይ ብዙ ጉዳት እናደርሳለን። በተለይም ጌታችን ታናናሽ በማለት የሚጠራቸውን ራሳቸውን መከላከል የማይችሉትን፣ በማህበረሰቡ ዘንድ ቦታ የማይሰጣቸውን እንጎዳለን። በጌታ ዓይን ግን ሁላችን ክቡር ዋጋ አለንና ይህ ድርጊታችን በቀላሉ እንደማይታይ ይህ ማስጠንቀቂያ ያስተምረናል። በመጨረሻም፣ ጌታችን ንግግሩን ሲደመድም “ጨው በውስጣችሁ ይኑራችሁ፣ እርስ በርሳችሁም ተስማምታችሁ በሰላም ኑሩ” አላቸው። በተለይ በዚያ ዘመን የጨው ዋና ጥቅም ምግቦችን ሳይበላሹ ማቆየት ነበር። እናም ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን በራስ ወዳድነት እርስ በርስ እየተሻኮቱ በሚለኩሱት እሳት ሌሎችን የሚያጠፉ ሳይሆን፣ ይልቁንም በፍቅርና በሰላም በመኖር፣ በበጎ ተጽእኖአቸው በዙሪያቸው ያሉትን ሰዎች ህይወት ከክፋት የሚጠብቁ እንዲሆኑ አስተማራቸው። ዛሬም ቢሆን በዓለማችን ሰላም ብርቅ የሆነውና በየቦታው ብዙ ወንጀል፣ ግጭትና ጦርነት ያለው ከራስ ወዳድነት የተነሳ ነው። “ሁሉም እኔ ከሁሉ እበልጣለሁ፣ ይሄ የሚገባኝ እኔ ነኝ” ብሎ ሲያስብ ያን ጊዜ ትልቁን ጫካ የምታቃጥለው ትንሽዋ የራስ ወዳድነት እሳት ትለኮሳለች። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ደቀ መዛርሙርቱን የጠራው ወደ ዓለምም የላከው፣ እነርሱም እርስ በርስ በመጠላለፍ እንዲህ ያለውን እሳት እንዲለኩሱ ሳይሆን፣ ይልቁንም በያሉበት ማእዘን “የምድር ጨው” እንዲሆኑ፣ ጌታ እነርሱን በወደደበት የራሱን በማይፈልግ ፍቅር ተዋድደው፣ በሰላም በመኖር ሰላምን እንዲያመጡ ነው። እኛም የእርሱ ተከታዮች ነን የምንል የተጠራነው ለዚህ ነው። ነገር ግን ህይወታችን የሚያሳየው ከዚህ ተቃራኒውን ከሆነ፣ በስግብግብነት፣ በዘረኝነት፣ በራስ ወዳድነት “ከሁሉ የምበልጥ እኔ ነኝ” የሚለው አመለካከት ከወረሰን፣ ጨውነታችንን ያጣን ወደ ውጪ ልንወረወር እና በመንገድም እንደ ድንጋይ ልንረገጥ የሚገባን እንሆናለን። ለዚህ ነው ጌታችን “ጨው ይኑራችሁ፣ እርስ በርሳችሁም ተስማምታችሁ በሰላም ኑሩ” የሚለን። አባት ሆይ፣ በቃል እንደተናገርኸን የፍቅርህን ጨው በውስጣችን እንድታኖርልን እኛም በዚያ ፍቅር ተዋድደን የአንተን ሰላም በመለማመድ እንዲሁም ሰላምን ለሌሎችን በማካፈል፣ የአንተ የሰላሙ መስፍን ደቀ መዛሙርት መሆናችን በዚህ እንዲታወቅ እርዳን። አሜን!

Открыть в Telegram
Просмотры346−19%к среднему
Пересылки—
Реакции19
Комментарии—
#4862Текст

ቀን 290 ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ግን ነፍሱን ቢያጎድል የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል - ማቴዎስ 16፤ ማርቆስ 8፤ ሉቃስ 9፡18-27 ''ሰው ዓለሙ ሁሉ የርሱ ቢሆንና ነፍሱን ቢያጠፋ ምን ይጠቅመዋል? '' ማርቆስ 8:36 ጌታችን ኢየሱስ እርሱ የሚሰጠን የዘለዓለም ህይወት በዓለም ያለውን ነገር ሁሉ አግኝቶ ያንን ህይወት ከማጣት ይልቅ ልንመርጠው የሚገባን መሆኑን ሲያስተር እንዲህ የሚል ጥያቄ ጠየቀ፦ “ሰው ዓለሙ ሁሉ የእርሱ ቢሆንና ነፍሱን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል?” ማር. 8:36 በእርግጥም የክርስቲያኖችን ተስፋ እጅግ የከበረና ተወዳዳሪ የሌለው ነው። ጌታችን ኢየሱስ የሰጠን ተስፋ ስንሞት አንዲት ሽራፊ ሳንቲም ይዘን የማንሄደውን የተትረፈረፈ ምድራዊ ንዋይ አይደለም። ስልጣን፣ ዝና፣ እውቀት እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገው ብዙዎች ብዙ ይደክማሉ። ይሁን እንጂ የተመኙትን ሲያገኙ ከመርካት ይልቅ ይበልጥ በጥማት የሚሰቃዩ ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። አዎ፣ ጌታችን ኢየሱስ የሰጠን ተስፋ ግን ከእነዚህ ሁሉ ለየት ያለ ሲሆን፣ እርሱም የዘለዓለም ህይወት ነው። እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈው፦ “ይህ እርሱ የሰጠን ተስፋ የዘለዓለም ህይወት ነው።” 1 ዮሐ. 2፡25 የዚህ ተስፋ ባለቤት ለመሆን ደግሞ መስፈርቱ አንድ ብቻ ነው። ይሄውም “አህዛብ ሁሉ በስሙ ተስፋ ያደርጋሉ” በተባለለት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ሙሉ በሙሉ እምነታችንን ማድረግ ነው። የሚከተሉት ጥቅሶች ይህንን እውነት ፍንትው አድርገው ያሳዩናል። “ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት ሰጣቸው።” ዮሐ. 1:12 “ይኸውም በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ህይወት እንዲኖረው ነው።” ዮሐ. 3:15 “በወልድ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ህይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቊጣ በላዩ ይሆናል እንጂ ህይወትን አያይም።” ዮሐ. 3: 36 “የአባቴ ፈቃድ ወልድን አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ህይወት እንዲኖረው ነው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።” ዮሐ. 6:40 “እኔ የዘለዓለም ህይወት እሰጣቸዋለሁ፤ ከቶ አይጠፉም፤ ከእጄም ሊነጥቃቸው የሚችል ማንም የለም።” ዮሐ. 10:28 የዘለዓለም ህይወት ተስፋ የሰጠንን ይህንን ድንቅ አፍቃሪ አምላክ በማሰብ፣ በአታላዩ በዲያቢሎስ የሚቀርብልንን “ለእኔ ብትሰግድልኝ፣ ዓለምን ሁሉ እሰጥሃለሁ” በሚለው የፈተና ወጥመድ ከመያዝ እናመልጣለን። እንዲሁም፣ በሕይወት ጎዳና በሚያጋጥሙን በተለያዩ ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎች ላይ ድልን መቀዳጀት እንችላለን። ለታላቅ እና እጅግ የከበረ ርስት የተጠራን የዘለዓለም ህይወት ተስፋ ያለን የእግዚአብሔር ውድ ልጆች መሆናችንን አምነን እንኑር። አባት ሆይ፣ ተወዳዳሪ የሌለውን የከበረ ስጦታ የዘለዓለም ህይወትን በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስላበረከትክልን እያመሰገንንህ፣ ዓለምን ለማትረፍ ነፍሳችንን በሚያሳጣን ጎዳና እንዳሄድ በዚህ የዘለዓለም ህይወት ተስፋ ላይ እኛም ተስፋችንን በመጣል በማንኛውም ፈታኝ እና ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ አንተን ምርጫችን እንድናደርግ እርዳን። አሜን!

Открыть в Telegram
Просмотры476+11%к среднему
Пересылки—
Реакции19
Комментарии—
#4860Текст

ቀን 289 ኤፍታህ የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል - ማቴዎስ 15፤ ማርቆስ 7 'ወደ ሰማይም ተመልክቶ ቃተተና፣ “ኤፍታህ!” አለው፤ ይኸውም፣ “ተከፈት” ማለት ነው። ማርቆስ 7:34 ጌታችን ኢየሱስ የእኛን ሥጋ ለብሶ በምድር ላይ ሲመላለስ አብዛኛውን የአገልግሎቱን ጊዜ ያሳለፈው ሕሙማንን በመፈወስ ነበር። ከብዙ ተአምራቱ ደግሞ የተወሰኑት ዘርዘር ተደርገው የተጻፉ ሲሆን ከእነዚህ መካከል በማርቆስ ወንጌል መስማት እና መናገር የማይችልን ሰው ጌታችን እንዴት እንደፈወሰው እናነባለን። በመጀመሪያ ጌታችን ሰውየውን ከሕዝቡ ለይቶ ወሰደው (ቁ. 33)። ቀጥሎም በቅድሚያ ጆሮውን ከዚያም ምላሱን በእጆቹ ዳሰሰ። ከዚያም “ወደ ሰማይም ተመልክቶ ቃተተና፣ ‘ኤፍታህ!’ አለው፤ ይኸውም፣ ‘ተከፈት’ ማለት ነው። ወዲያውም ጆሮዎቹ ተከፈቱ፤ ምላሱም ተፈትቶ አጥርቶ መናገር ጀመረ።” (ቁ. 34፣ 35)። በእርግጥም ይህ የጌታችን ተአምር እርሱ ሁሉን ቻይ መሆኑን የሚያሳይ የአምላክነቱ ማሳያ ነበር። ‘ሕዝቡም ከመጠን በላይ በመደነቅ፣ “ያደረገው ሁሉ ጥሩ ነው፤ ደንቈሮዎች እንዲሰሙ፣ ድዳዎች እንዲናገሩ እንኳ አድርጓል’ አሉ።” (ቁ. 37) ይህንን የጌታችንን ተአምራት ይበልጥ ጠጋ ብለን ስንመረምር ደግሞ ከአካላዊው ፈውስ ባለፈ እርሱ ሊሰጠን ስለ የሚችለው መንፈሳዊ ፈውስ ትልቅን ትምህርት እናገኛለን። ምንም እንኳን ከአካላችን ጋር በተገናኘ የጆሮ እና ምላስ ችግር ባይኖርብንም ነገር ግን መንፈሳዊ ጆሮአችንና ምላሳችን የተቆለፈብን ስንቶች እንሆን? እንዲህ ባለው መንፈሳዊ በሽታ ስለተያዙ ሰዎች ሲናገር ኢየሱስ እንዲህ ይላል፦ “የሕዝቡ ልብ ደንድኗልና፤ ጆሯቸውም አይሰማም፤” (ማቴ. 13:15)። ጆሯችን የእግዚአብሔርን ፈቃድ የማይሰማ ከሆነ ደግሞ ምላሳችን የእርሱን ክብር ለመናገር የማይችል ይሆናል። ለዚህ ነው የጌታችንን የፈውስ ቀደም ተከተል ስንመለከት በመጀመሪያ ጆሮአችንን ቀጥሎም አንደበታችንን የሚፈውስልን። ዛሬም ቢሆን ይሄ ጌታ የተደፈኑ መንፈሳዊ ጆሮዎቻችንን እና የተቆለፉ አንደበቶቻችንን “ኤፍታህ” ብሎ ሊከፍታቸው ይችላል። ይህንን ለማድረግም ልክ ይህንን ደንቆሮና ዲዳ ሰው ከሕዝቡ ለይቶ እንደ ወሰደው እኛንም በግላችን በጓዳችን ሊያገኘን ይፈልጋል። ትኩረታችንን ከእርሱ ላይ እንድናነሳ ካደረጉን ነገሮች ዞር አድርጎ በትክክል የእርሱን ድምጽ እንድንሰማ እና የእርሱንም ክብር አጥርተን እንድንናገር በቅዱስ መንፈሱ ሊሞላን ይሻል። እንግዲያውስ ይህንን መለኮታዊ መንፈሳዊ ፈውስ ለመለማመድ ከጌታችን ጋር የግል ጊዜ እንውሰድ። ድምጹን ለመስማት እና ፈቃዱን ለመረዳት ከልባችን እንፈልግ። በመጨረሻ፣ በዚህ የፈውስ ታሪክ ላይ ጌታችን እንደቃተተ ተጽፎልናል። ይህ የሚያሳያው ደግሞ ለእኛ አካላዊም ሆነ መንፈሳዊ ፈውስን ለመስጠት እርሱ ከጨለማው ሠራዊት ጋር ብርቱ ትግልን እንደሚያደርግ ነው። ይህ ትግል ጌታችንን እንዲቃትት ያደረገው ዐቅም አንሶት ሳይሆን ነገር ግን የእኛን የምርጫ ነጻነት ተጋፍቶ ምንም ማድረግ ስለማይችል ነው። በእርግጥ እርሱ እኛን ለማዳን ከእርሱ ዘንድ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ሁሉ የሚከፍል አፍቃሪ አምላክ ነው። አባት ሆይ፣ ዛሬም ድምጽህን መስማት ተስኗቸው የተደፈኑትን መንፈሳዊ ጆሮዎቻችንን እንዲሁም ክብርህን ለመናገር ያቃታቸውን የተቆለፉ አንደበቶቻችንን “ኤፍታህ” ብለህ እንድትከፍትልን እንጸልያለን። አሜን!

Открыть в Telegram
Просмотры513+20%к среднему
Пересылки—
Реакции18
Комментарии—
#4858Текст

ቀን 288 ወደ ማን እንሄዳለን? የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል - ዮሐንስ 6 ''ስምዖን ጴጥሮስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ጌታ ሆይ፤ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤ '' ዮሐንስ 6:68 ጌታችን ኢየሱስ በአምስት ትንንሽ የገብስ እንጀራ እና ሁለት ትንንሽ ዓሣ አምስት ሺህ ያህል ወንዶችንና ከእነርሱ ጋር የነበሩትን ሴቶችና ሕጻናትን የመመገብን ታላቅ ተዓምር ሰራ። ታዲያ በማግስቱ በዚህ ምገባ ላይ ተሳታፊ የነበሩት ብዙ ሰዎች እርሱን ፍለጋ ብዙ ደክመው ባገኙት ጊዜ፣ ጌታችን ለየት ያለ አቀባበል አደረገላቸው። እነርሱ እንደጠበቁት ዛሬም እንደትላንቱ ነጻ የምግብ ዕደላ አልነበረም። ይልቁንም ተበልቶ መልሶ የሚያስርበውን፣ ምድራዊ ኑሮአችንን እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ብቻ ለማቆየት የሚያስችለውን እንጀራ ሳይሆን ሌላ ዓይነት እንጀራን አቀረበላቸው። ይህ እንጀራ ለዓለም የዘለዓለም ህይወት የሚሰጥ ከሰማይ የሚወርድ የእግዚአብሔር እንጀራ ነው (ዮሐ 6፡ 33)። በመቀጠልም ይህ የሕይወት እንጀራ እርሱ እንደሆነ እንዲህ በማለት ደጋግሞ ነገራቸው፦ “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፤ በእኔም የሚያምን ፈጽሞ አይጠማም።” ዮሐ. 6:35 “የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ።” (ቁ. 48) “ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ማንም ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘለዓለም ይኖራል፤ ይህም እንጀራ፣ ለዓለም ህይወት እንዲሆን የምሰጠው ሥጋዬ ነው።” (ቁ. 51) ይህንን የሕይወት እንጀራ ለመመገብ የሚቻለው ደግሞ የእርሱን ሥጋ በመብላት እና ደሙን በመጠጣት እንደሆነ ጌታችን ኢየሱስ ተናገረ (ቁ. 53-55)። ይህ ንግግሩ ግን ብዙ አድማጮቹን አስጨነቃቸው። ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ እነርሱ ጌታን ፍለጋ የመጡት ሆዳቸውን ለመሙላት እንጂ ከዚያ ያለፈ ምንም አይነት ሕብረት ከእርሱ ጋር ለማድረግ ስላልነበረ ነው። “ደሙን መጠጣት እና ሥጋውን መብላት” በጥሬ ትርጉሙ የሚስተዋል ሳይሆን የሕይወት እንጀራ የሆነውን የክርስቶስን ቃል በእምነት ተቀብሎ በዚያ በመኖር ከእርሱ ጋር ሕብረት ማድረግን የሚያመለክት ነው። ይህንን ለማድረግ ያልፈለጉ ሁሉ ወደ ኋላ ተመለሱ፦ “ከዚህም በኋላ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ፤ ከዚያም ወዲያ አልተከተሉትም።” ዮሐ. 6፡66 ይህን ጊዜ፣ ማንንም አስገድዶ ወይም አወናብዶ ተከታዩ ማድረግ የማይፈልገው ይህ አፍቃሪ ጌታ ወደ አስራ ሁለቱ ዘወር ብሎ እንዲህ አላቸው ፦ “እናንተም ደግሞ መሄድ ትፈልጋላችሁ?” “ስምዖን ጴጥሮስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ ‘ጌታ ሆይ፤ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘለዓለም ህይወት ቃል አለህ፤ አንተ አንድያ የእግዚአብሔር ቅዱስ እንደ ሆንህ አምነናል፤ ዐውቀናልም።’” (ቁ. 68፣ 69)። እዚህ ላይ ቆም ብለን ራሳችንን እንዲህ ብለን እንጠይቅ፦ “የእኔስ ምላሽ ምን ይሆን?” ጌታ ኢየሱስን የምፈልገው ለምድራዊ ጥቅም ብቻ ነው ወይስ በእርሱ ዘንድ የዘለዓለም የሕይወት ቃል እንዳለ አስተውየ፣ ያንን ቃል ዕለት ዕለት እየተመገብኩ ነው?” አባት ሆይ፣ አንተ ብቻ ከሰማይ የምትሰጠውን የሕይወት እንጀራ፣ ይኼውም የዘለዓለም የሕይወት ቃል ዕለት ዕለት በእምነት በመመገብ ከአንተ ጋር የጠበቀ ሕብረት እንዲኖረን በጸጋህ እርዳን። አሜን!

Открыть в Telegram
Просмотры537+25%к среднему
Пересылки—
Реакции23
Комментарии—
#4856Текст

ቀን 287 "ጌታ ሆይ፣ አድነኝ!" የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል - ማቴዎስ 14፤ ማርቆስ 6፤ ሉቃስ 9:1-17 ''ነገር ግን የነፋሱን ኀይል ባየ ጊዜ ፈራ፤ መስጠምም ሲጀምር፣ “ጌታ ሆይ፤ አድነኝ!” ብሎ ጮኸ። '' ማቴዎስ 14:30 በውሃ ላይ መራመድ በራሱ አንድ ትልቅ ተአምር ሲሆን፣ በውሃ ላይ የምትንሳፈፈውን ጀልባ እንኳን ሊያሰምጥ እየተገለባበጠ ባለ ማዕበል ላይ መራመድ ግን ከተአምርም ተአምር ነው! ጌታችን በማእበሉ ላይ እየተረማመደ ልትሰምጥ ባለችው ታንኳቸው ውስጥ ወዳሉት በጭንቀት እና በፍርሃት ወደ ተሞሉት ደቀመዛሙርቱ ሲመጣ፣ የሚያዩትን ማመን አቅቷቸው የበለጠ ፈሩ። ያን ጊዜ ነበር "እኔ ነኝ፣ አትፍሩ" ያላቸው። እኛንም ባስጨነቀን በማኛውም ወጀብ ላይ መራመድ የሚችለው ጌታ "እኔ ነኝ፣ አትፍሩ" ይለናል። “በምድር ላይ ከሚሆነው ነገር የተነሳ፣ የሰዎች ልቦች በፍርሃት ምክንያት ይወድቃሉ። ነገር ግን በእግዚአብሔር የሚያምኑ ሁሉ በወጀቡ መካከል እንዲህ የሚለውን ድምጹን ይሰማሉ:- ‘እኔ ነኝ፣ አትፍሩ’” Signs of the Times October 9 1901. አባት ሆይ፣ በእርግጥም አንተ አስጨናቂውን ወጀብ መረማመጃ የምታደርግና ልጆችህን ለመታደግ የምትፈጥን አባት ነህና ስምህ የተመሰገነ ይሁን። በአንተ ላይ መታመናችንን እንድናደርግ እርዳን። አሜን! ጴጥሮስ ከጀባው ወርዶ በብርቱ ንፋስ እየተገለባበጠ ባለው ወጀብ ላይ መራመድ የቻለው፣ ዓይኑን፣ "ና" ብሎ በጠራው፣ በማእበሉና በወጀቡ ጌታ ኢየሱስ ላይ በማድረጉ ነበር። ነገር ግን ዓይኑን ከዚህ ጌታ ላይ አንስቶ የነፋሱን ኃይል ባየ ጊዜ ፈራ፣ መስጠምም ጀመረ። በሌላ አነጋገር፣ ሂደቱ በእነዚህ አራት "መ"ዎች ሊቀመጥ ይችላል - መንቀል፣ መመልከት፣ መፍራት፣ መስጠም:- 1) ዓይንን ከጌታ ላይ "መንቀል፣" 2) የነፋሱን ኃይል "መመልከት፣" 3) ከነፋሱ ኃይል የተነሳ "መፍራት፣" 4) ከእምነት ማጣት የተነሳ "መስጠም!" ይህንን ወደ ጥፋት የመንደርደር ጉዞ ያስቆመው ታዲያ የጴጥሮስ 5ኛው መ - "መጮህ" ነበር። "ጌታ ሆይ፣ አድነኝ!" ጌታም ወዲያውኑ እጁን ዘርግቶ ያዘው። "ወዲያው ደረሰለት!" ስሙ ይባረክ! እኛም ዓይናችንን ከጌታ ላይ ነቅለን፣ የተከበብነበትን የሚያስፈራ ነገር በማየት፣ እምነታችን በፍርሃት ተውጦ፣ እየሰጠምን ከሆነ፣ እንደ ጴጥሮስ እንዲህ ብለን እንጩህ - "ጌታ ሆይ፣ አድነኝ!" እርሱም ፈጥኖ ይደርስልናል። ከተዋጥንበት ፍርሃትም አውጥቶ በእምነት ውስጣችንን ይሞላዋል። ከዚያም ዓይናችንን በእርሱ ላይ ተክለን ጉዟችንን እንቀጥል። አባት ሆይ፣ አንተ ብቻ ከሰማይ የምትሰጠውን የሕይወት እንጀራ፣ ይኼውም የዘለዓለም የሕይወት ቃል ዕለት ዕለት በእምነት በመመገብ ከአንተ ጋር የጠበቀ ሕብረት እንዲኖረን በጸጋህ እርዳን። አሜን!

Открыть в Telegram
Просмотры560+30%к среднему
Пересылки—
Реакции17
Комментарии—
#4854Текст

ቀን 286 ርግብና እባብ የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል - ማቴዎስ 9-10 '“እንግዲህ፣ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልኆች እንደ ርግብ የዋሃን ሁኑ። '' ማቴዎስ 10:16 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ለመጀመሪያ ወደ መስክ ሥራ ሲልካቸው፣ የእስራኤል ቤት ወደ ሆኑት ወደ ጠፉት በጎች በመሄድ “መንግስተ ሰማያት ቀርባለች” ብለው እንዲሰብኩ አዘዛቸው። ከዚህ በተጨማሪም ይህንን ተልእኮ አንግበው ሲወጡ የሚሄዱት በጠላት በዲያቢሎስ ቁጥጥር ስር ወዳሉት ነውና የሚገጥማቸው ብዙ አስቸጋሪ ፈተና እንደሚኖር የሚያውቀው ጌታችን እንዲህ በማለት አሳሰባቸው። “እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ” ተኩላዎች በጎችን አድነው ለመብላት እንደሚፈልጉ ሁሉ፣ የጌታ የኢየሱስ የሆነውን ሁሉ ሁል ጊዜ ለማጥቃት እና ለማጥፋት ተግቶ የሚሰራ፣ ከመጀመሪያ ጀምሮ ነፍስ ገዳይ የሆነ ጠላት አለን። እርሱም የቀደመው እባብ የተባለው ሰይጣን ነው። ታዲያ የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋት የተሰጠንን ተልእኮ ለመፈጸም ስንወጣ ይህንን ጠንቅቀን በመረዳት በተኩላዎች መካከል እንደሚሄዱ በጎች መሆናችንን ልናስተውል ይገባል። በመቀጠልም ጌታችን የተከበብንበትን አደገኛ ሁናቴ ካሳየን በኋላ፣ “እንደ እባብ ብልሆች፣ እንደ ርግብ ደግሞ የዋሆች ሁኑ” ብሎ ያዝዘናል። ብዙ ጊዜ እነዚህን ሁለቱን ባህርያት ሚዛን በጠበቀ መልኩ ተላብሶ መኖር ሲሳነን ይስተዋላል። አንዳንዶቻችን ርግቧን በእባብ በማስበላት ብልህነታችን ከየዋህነታችን እጅግ በዝቶ በተንኮል ስራ ውስጥ እንተበተባለን። ብልህነት - የዋህነት = ተንኮለኝነት ምንም እንኳን ተንኮለኛ በሆነ ጠላት ዒላማ ውስጥ ብንሆንም፣ እግዚአብሔር ግን ሥራው በተንኮል እንዲሰራ አይፈልግም። ይልቁንም ልጆቹ የዋህነት በተሞላ ብልህነት የተሞሉ እንዲሆኑ ይፈልጋል። ሁለተኛው ሚዛን ስተን የምንወድቅበት ጉድጓድ ደግሞ “እንደ እባብ ብልህ ሁኑ” የተባልነውን ትተን እንደ ርግብ የዋህ በመሆን ብቻ ስንበር ነው። ብልህነት የጎደው የዋህነት ሞኝነት፣ ጅልነት፣ ቂልነት ነው። የዋህነት - ብልህነት = ጅልነት ብዙዎች የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋት ቀናኢ ሆነው፣ ብልህነት በጎደለው የዋህነት በሚያደርጉት ጥረት፣ አላስፈላጊ ስደትን፣ መከራን እና ችግርን በራሳቸው ላይ አምጥተዋል። ለምሳሌ ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ ምስክርነታቸው በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ሊሆን እንደሚገባ ማንም ሰው ሊያስተናግዳቸው ወይም የሚናገሩትን ሊሰማ ፈቃደኛ ባይሆን የእግራቸውን ትቢያ አራግፈው ከዚያ ዞር እንዲሉ እንጂ፣ በክርክርና በንትርክ ወደ አላስፈላጊ ግጭት ውስጥ እንዳይገቡ ነግሯቸዋል። ይሁን እንጂ ይህንን ምክር በመዘንጋት ብልህነት በጎደለው የዋህነት ፈቃደኞች ካልሆኑ ሰዎች ጋር በመከራከር ጉዳት እንዲያደርሱብን ብናደርግ ያ ጅልነት ነው። እንግዲያውስ፣ ጌታችን የሰጠንን ተልእኮ በስኬታማ ሁኔታ ለመወጣት በተኩላዎች መካከል የተላክን በጎች መሆናችንን በማስተዋል፣ በዙሪያችን ያለውን አደጋ በትክክል በመረዳት እንደ እባብ ብልህ እንደ ርግብ ደግሞ የዋህ በመሆን የእርሱን ምሪት መከተል ያስፈልገናል። አባት ሆይ፣ በቃልህ ውስጥ የሰጠከንን ምሪት በመከተል በየዋህነት በተሞላ ብልህነት የሰጠኸንን ስራ እንድንሰራ ፣ መንግስትህንም እንድናሰፋ እና ብዙዎችን ከሰይጣን ጭቆና ወደ መንግስትህ እንድናመጣ በጸጋህ እርዳን። አሜን!

Открыть в Telegram
Просмотры774+80%к среднему
Пересылки—
Реакции15
Комментарии—
#4852Текст

ቀን 285 እመን እንጂ አትፍራ የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል - ማቴዎስ 8፡ 14-34፤ ማርቆስ 4-5 ''ኢየሱስ ግን ሰዎቹ የተናገሩትን ችላ በማለት የምኵራቡን አለቃ፣ “እመን ብቻ እንጂ አትፍራ፤” አለው። '' ማርቆስ 5:36 ይበልጥ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ስንወስን ችግሮቻችን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ተፋፍመውብን ግራ ተጋብተን ይሆን? በማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 5 ላይ ኢያኢሮስ የተባለ የምኩራብ አለቃ ልጁ በጠና ታምማበት፣ እርዳታን ፍለጋ ወደ ኢየሱስ እንደ መጣ እናነባለን። የምኩራብ አለቃ እንደ መሆኑ እንደ እርሱ ያሉት ሌሎች የአይሁድ መሪዎች የሚንቁትን እና የሚያሳድዱትን ኢየሱስን ፍለጋ መምጣት ለእርሱ ቀላል አልነበረም። ሆኖም ግን የሌሎችን ሰዎች ተጽእኖ ሁሉ አሸንፎ፣ ኢየሱስ ልጄን ሊያድንልኝ ይችላል በሚል እምነት ወደ እርሱ መጣ። ጌታም የኢያኢሮስን ልጅ ለመፈውስ ጉዞ ጀመረ። ይሁን እንጂ፣ ብዙ ህዝብ እያጨናነቀው ስለ ነበረ፣ ኢያኢሮስ በተመኘው ፍጥነት ሊጓዝ አልቻለም። በሞትና በህይወት መካከል የተዋት የልጁ ስቃይ በፊቱ ድቅን እያለበት ኢያኢሮስ በብዙ ተጨነቀ። ይባስ ብሎ፣ ጌታችን ኢየሱስ ጉዞውን አቁሞ፣ "ማነው የነካኝ?" በማለት ግራ የሚያጋባ ጥያቄን አነሳ። በእርግጥም ብዙ ሰው እየተጋፋው ነበርና ጥያቄው ግራ የሚያጋባ ነበር። ይሁን እንጂ፣ አስራ ሁለት ዓመት ደም ሲፈስሳት የነበረች ሴት ጨርቁን ብቻ ብነካ እድናለሁ በማለት በእምነት ነክታው ስለ ተፈወሰች ነበር ጌታ ይህንን ጥያቄ የጠየቀው። ሴቲቱም ወደ ፊት መጥታ ታሪኳን ሁሉ መዘርዘር ጀመረች። ይሄ ሁሉ ሲሆን ታዲያ፣ የኢያኢሮስ ትእግስት እና እምነት ትልቅ ፈተና ውስጥ ወደቀ። የልጁን በጠና መታመም እያሰበ፣ ከመዘግየታቸው የተነሳ የፈራው እንዳይደርስ ትልቅ ስጋት ገባው። ይሁን እንጂ፣ የፈራው አልቀረም፣ ከእርሱ ቤት የተላከ መልክተኛ፣ "መምህሩን አታድክመው፣ ልጅህ ሞታለች" የሚል መልእክት ይዞ ከተፍ አለ። አዎ፣ ኢያኢሮስ ምንም እንኳን ዋጋ ከፍሎ በጌታ ቢያምንም ለልጁም መፍትሔን ለማግኘት ተመኝቶ የነበረም ቢሆን፣ አሁን ግን ተስፋው ተሟጠጠ። ኢየሱስ ግን፣ "እመን እንጂ፣ አትፍራ" አለው። ይህ ለኢያኢሮስ ከባድ ፈተና ነበር። ወደ ቤቱም በተቃረቡ ጊዜ በብላቴናይቱ ሞት ምክንያት ሲያለቅሱ የነበሩትን ሰዎች ክርስቶስ እንዲህ አላቸው:- "ብላቴናዪቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም" ይህ የሚገርም ንግግር የጌታን ብርቱ ኃይል የሚያውጅ ነበር። በሰው ዘንድ ተስፋ የተቆረጠበት እና ፈጽሞ የማይቻል ፣ እንደ ሞት ያለው ነገር ለእርሱ ግን እንደ እንቅልፍ መሆኑን ያወጀበት ቃል ነው። ለእኛ እንደ ሞት የከበደን ነገር ለእርሱ ግን እንደ እንቅልፍ የሚታይ ነው። በመጨረሻ የኢያኢሮስ አልነጋ ያለ ሌሊት ነጋ። ጌታ በሰዓቱ ደርሶ ነገሮችን ሁሉ ውብ አድርጎ ሰራ። እኛም ዛሬ ችግሮቻችንን ይዘን ወደ ጌታ ስንቀርብ የኢያኢሮስ ችግር እንደተባባሰ፣ የእኛም ችግር ሊባባስ ይችላል። የታመመው ሊሞት ይችላል። ነገር ግን ሞትን እንደ እንቅልፍ የሚቆጥረው ጌታ የሞተውን ነገራችንን ነፍስ ሊዘራበት ይችላልና "እመን እንጂ አትፍራ" ሲለን እንስማው። አባት ሆይ፣ እኛም እንደ ኢያኢሮስ ወደ አንተ እርዳታን ፍለጋ ስንጮህ ችግራችን ሲባባስብን፣ የዘገየህ ሲመስለን፣ "እመን እንጂ አትፍራ" የሚለውን ድምጽህን እንድታሰማን፣ በአንተም ላይ ተስፋችን እንዲጸናልን በጸጋህ እርዳን። አሜን!

Открыть в Telegram
Просмотры770+79%к среднему
Пересылки—
Реакции25
Комментарии—
#4850Текст

ቀን 284 የሰናፍጭ ዘር ምሳሌ የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል - ማቴዎስ 13፤ ሉቃስ 8 'ሌላ ምሳሌ እንዲህ ሲል ነገራቸው፤ “መንግሥተ ሰማይ አንድ ሰው ወስዶ በዕርሻው ቦታ የዘራትን የሰናፍጭ ዘር ትመስላለች። የሰናፍጭ ዘር ከሌሎች ሁሉ ያነሰች ብትሆንም፣ ስታድግ ግን ከአትክልት ሁሉ በልጣ፣ የሰማይ ወፎች መጥተው በቅርንጫፎቿ ላይ እስኪያርፉ ድረስ ዛፍ ትሆናለች።” ' ማቴዎስ 13:31-32 ጌታችን ይህንን ምሳሌ በሚያስተምር ጊዜ ከአድማጮቹ መካከል አብዛኞቹ ስለ እግዚአብሔር መንግስት እንደገና የመመስረት ተስፋ የሚያውቁ ነበሩ። እንዲሁም ይህ የእግዚአብሔር መንግስት የሚመጣው መንግስታትን ሁሉ ገለባብጦ ነው ብለው ያስቡ ነበር። ወደዚህ ድምዳሜ ያደረሳቸው ደግሞ አንዳንድ ትንቢቶችን በትክክል አለመረዳታቸው እንደሆነ ማወቅ ይኖርብናል። ታዲያ ጌታችን ኢየሱስ እንዲህ ያለን የተሳሳተ መረዳት ለማረም ፣ አስቀድሞ ተስፋ የተሰጠችው የእግዚአብሔር መንግስት እንዴት እንደምትቋቋም እና እንደምታድግ በዚህ ምሳሌ አጋዥነት በግልጽ አስተማረ። በምሳሌውም ብዙዎች ይጠባበቁት እንደነበረው የእግዚአብሔር መንግስት ከሰማይ እሳትን በማውረድ መንግስታትን በማፈራረስ ከጅምሩ አንስቶ ታላቅ ሆና የምትገለጥ ሳትሆን ይልቁንም አነሳሷ እንደሰናፍጭ ዘር ታናሽ እንደሚሆን አስረዳ። ምንም እንኳን መንግስቱ አነሳሷ ላይ ታናሽ ትምሰል እንጂ በሂደት ግን እያደገችና እየሰፋች በመሄድ እንደ ሰናፍጭ ተክል እጅግ ታላቅ እንደምትሆን ጨምሮ ገለጸ። በእርግጥም የእግዚአብሔርን መንግስት ይመሰርት ዘንድ የተገለጠውን ኢየሱስን ከአወላለዱ አንስተን እስከ መስቀል ሞቱ ስንከተለው፣ እንደዚያች የሰናፍጭ ዘር አንሶ ሊታየን ይችላል። ሆኖም ግን እግዚአብሔር በዘመናት መካከል ብዙዎችን ከዲያቢሎስ የጨለማ ግዛት በመታደግ ወደ ልጁ መንግስት በማሻገር ይህንን መንግስት አሳደገው (ቆላ. 1፡13)። የእግዚአብሔር መንግስት እያደገች እና እየሰፋች ቢሆንም በእድገቷ ገና ከፍጻሜ አልደረሰችም። በማቴዎስ 24፡14 ላይ “ይህ የመንግስት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል ከዚያም መጨረሻው ይመጣል” ብሎ ጌታ በተናገረው መሰረት ወደዚህ መንግስት እንዲገቡ ለሁሉም ጥሪ ከተደረገ በኋላ የመንግስቱ እድገት ያበቃል። በዚያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ዳግም ይመጣል። የሚመጣበትም ዓላማ ተቀናቃኝ ኃይላትን በአፉ እስትንፋስ በመጠራረግ ለአንዴና ለዘለዓለም መንግስቱን ለማጽናት ነው። በቅርብ ጌታችን ኢየሱስ ተመልሶ ይመጣል ፤ ደግሞም ምጻቱ መቃረቡን ምልክቶች እያሳዩን ነው። በመጀመሪያው መገለጹ እንደ ሰናፍጭ ዘር ዘርቷት የሄደውን መንግስቱን በዳግም ምጽአቱ ሁሉን የምትጠቀልል ሊያደርጋት ጌታ ይገለጣል። ናብከደነጾር ባየው ህልም ላይ ትንሿ ድንጋይ ምድርን እንደሞላች (ዳን. 2፡ 44) ሁሉ በዳግም ምጽአቱም በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ዙፋኑን ከፍ አድርጎ ለማንሰራፋት የፈለገው ዲያቢሎስ ወደ እሳቱ ባህር ይጣልና (ራዕይ 20፤10) የእግዚአብሔር አገዛዝ እንደገና በምድር ላይ በሙላት ይንሰራፋል። የጨለማው መንግስት ተወግዶ የእግዚአብሔር መንግስት ሙሉ ለሙሉ በምድር ላይ ሲመሰረት “የእግዚአብሔርና የበጉ ዙፋን በከተማይቱ ውስጥ ይሆናል” (ራዕይ 22፤3) የተባለው ተስፋ ይፈጸማል። በአጭሩ የእግዚአብሔር መንግስት አነሳሷ ታናሽ ቢመስልም በስተመጨረሻ ግን የሰይጣንን መንግስት ድምጥማጡን አጥፍታ ምድርን እንደምትሞላ ምሳሌው ያስረዳል። አባት ሆይ፣ እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት በታናሽ ጅማሬ በመሰረትከው የጸጋህ መንግስት ውስጥ በእምነት ባለድርሻዎች እንድንሆን በጸጋህ አርዳን። አሜን!

Открыть в Telegram
Просмотры650+51%к среднему
Пересылки—
Реакции22
Комментарии—