Кабинет

Посты канала አዝግ😂😁🤭

сначала новые

#12366Текст
Просмотры356−3%к среднему
Пересылки—
Реакции17
Комментарии—
#12362Фото
Просмотры466+27%к среднему
Пересылки—
Реакции8
Комментарии—
#12361Текст

ገና ስንተዋወቅ ስሜን ኤዱ ብዬ ነበር የነገርኩት። ሰው የነገሩትን አይደል የሚቀበለው እሺ ብሎ በኤዱ ተስማማ። አንድ ቀን መታወቂያዬን አውጥቼው ነው ስሜ እድል መሆኑን ያወቀው። "እድላዊት ነው ወይስ እድል ብቻ ነው" ግራ ተጋብቶ መታወቂያዬን ከእጁ መንጭቄ ወስጄ "የሰው ንብረት ዝም ብለህ ትወስዳለህ እንዴ?!" ብዬ ጥዬው ሄድኩ። ቤት ገብቼ ከተረጋጋሁ በኋላ ነው ምንም በማያውቀው እንደተመነቃቀርኩ የገባኝ። ምክንያቱም እድል የሚለው ስም እንደ እርግማን ተሸክሜው እንደምዞር አያውቅማ። እኔ የተወለድኩ ቀን እናቴ የምትወደው አባቴን በመኪና አደጋ ማጣቷን በኔ ማሳበቧን በምን ያውቃል። "ጦሰኛ! አንቺ ተወለድሽ ተብሎ ሲደወልለት እኮ ነው የመኪና ሲሳይ የሆነው ምነው አንቺንም ከሱ ጋር ቢወስድሽ?! ኖረሽ ምናረግሽልኝ? እንደፈለገ ቢጠምም እድሌ ይሄን ያህል ጠማማ መሆኑን ያየሁት ባንቺ ነው" ስባል ማደጌን በምን ያውቃል "እድላዊት አይደለም እድል ብቻ ነው" ብዬ አመጣጡንም ካስረዳሁት በኋላ " ብትነግሪኝ ታድያ ሌላ ቆንጆ ስም የምፈልግልሽን? ቆይ እሱን በደንብ እስካስብበት ኤዱ ይሁንልሽ" ብሎ ተስማማን ከዛ በኋላ ብዙ ወራቶች ክንፍ ብለን ቆይተን ለምሳ ተቀጣጥረን ለምን surprise አላደርገውም ብዬ መስርያ ቤቱ ሄድኩ። መስርያ ቤቱ ደርሼ የሱን ቢሮ ከፍቼ ልገባ ስል ጀርባውን ሰጥቶ ከባልደረባው ጋር ያወራል። ያለው ነገር ጆሮዬ ጥልቅ ሲል ባለሁበት ቆምኩ "...እድሌ እኮ ናት፣ የኔ እድል ሎተሪዬ በላት..." ጣልቃ ገብቶ "አታካብድ ባክህ" ይለዋል "ምን ታደርግ የት ታውቃታለህ። እንድታውቃትም አልፈልግም የኔ ብቻ በመሆኗ እድለኛ ነኝ። ገባህ አሁን እኮ እሷን ላገኝ ነው የምሄደው ታውቃለህ።" ሲለው "ባክህ አትጨቅጭቀኝ" ብሎ ጓደኛው ሲወጣ በር ላይ ተገጣጠምን። "ያው መጥታልሀለች እድልህ" ብሎ ሄደ እንደገባሁ ተጠምጥሜበት ሳበቃ "እድል በለኝ እሺ" አልኩት "አንቺ አልሰማሽም እንጂ ሁሌ እኮ እድሌ ነው የምልሽ" ከዛ በኋላ ስሜ በተጠራ ቁጥር የሚሰማኝ መሸማቀቅ በኩራት ተቀይሯል። አሁን እኔ የሱ በመሆኔ የሚኮራ ሰው አለ እየደጋገመ እድሌ ሲል የሚያፍር ሳይሆን ፈጣሪውን እኔ ስላለሁት የሚያመሰግን ሰው አለ። እንደዚህ ታሪኬም የስሜ ትርጉምም ይቀየራል ብሎ ማን አስቦ ነበር?

Открыть в Telegram
Просмотры384+5%к среднему
Пересылки—
Реакции12
Комментарии—