Переслано из Abu Imran Muhammed Mekonn
💧 ኢልያስ አህመድ እንዲህ ይላል፦ «ሰዎች ብዙ እንኳን አይደሉም፤ በነገራችን ላይ ያው ጥቂት ሰዎች ይህ ነገር አልጣማቸውም። ለዚህ ያመጡት ምንም ዓይነት በእውቀት ላይ የተመሠረተ ምላሽ የለም...» ✅ መልስ ፦ በንግግሩ የሐቅ መለኪያ ብዛት መሆኑን ሊነግረን ይቃጣዋል። ይህ ነጥብ ግልፅ ስለሆነ ልለፈው። ከዛ ጥቂት ሰዎች አልጣማቸውም ይላል ማለትም የነሱና ኢኽዋንዮችን ዝምድና መሆኑ ነው። ምነው ኢልያስ? እንደት ባጢል ይጥማል? አዎ ለሀቅ ባለቤቶች ባጢል አይሰማቸውም። አይፈልጉትምም። ግን ለሱ የምር ጥሞት ይሆን? ከበሰበሰው የኢኽዋን አንጃ መደበር እንደት ይጥማል? በምን ሚዛን? ትናንት እኮ ለአንተም አይጥምህም ነበር። ዛሬ ላይ አጣጣምከውንጂ? ✅ ሌላው ከጉጠት ያገጠጠው ንግግር «ለዚህ ያመጡት ምንም ዓይነት በእውቀት ላይ የተመሠረተ ምላሽ የለም» ይሄ ከባዱ ውሸትና ቅጥፈት ነው። ማነው ይህንን የሚቀበለው? ስለማስረጃ ሲወራ ትንሽ አይሰቀጥጣችሁም? ስንትና ስንት ማስረጃዎች አሉ ግን የሚቀበል የለም። => "ከቢድዓ ባለቤቶች ጋር በዲን ጉዳይ ላይ መተባበርን፣ ከእነርሱ ጋር በባጢል ላይ መሰባሰብንና የተሳሳተ እምነታቸውን መደገፍን የሚያስጠነቅቁ በርካታ የቁርኣን አንቀጾች አሉ።" እስኪ ጥቂት አንቀፆችን እንጥቀስ፦ سورة الأنعام: 68 وَإِذَا رَأَيْتَ الَّذِينَ يَخُوضُونَ فِي آيَاتِنَا فَأَعْرِضْ عَنْهُمْ حَتَّىٰ يَخُوضُوا فِي حَدِيثٍ غَيْرِهِ ۚ وَإِمَّا يُنْسِيَنَّكَ الشَّيْطَانُ فَلَا تَقْعُدْ بَعْدَ الذِّكْرَىٰ مَعَ الْقَوْمِ الظَّالِمِينَ በአንቀጾቻችን ውስጥ የሚገቡትን (በባጢል የሚከራከሩትን) ባየህ ጊዜ ወደ ሌላ ንግግር እስኪገቡ ድረስ ከእነርሱ ዞር በል። ከተረሳህም በኋላ ካስታወስክ ከበደለኞቹ ሕዝቦች ጋር አትቀመጥ። سورة هود: 113 وَلَا تَرْكَنُوا إِلَى الَّذِينَ ظَلَمُوا فَتَمَسَّكُمُ النَّارُ وَمَا لَكُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ مِنْ أَوْلِيَاءَ ثُمَّ لَا تُنْصَرُونَ ወደእነዚያ የበደሉት አትዘንበሉ፤ እሳትም ትነካችኋለች። سورة المائدة: 2 وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ በመልካምነትና በጥንቁቅነት ላይ ተተባበሩ፤ በኃጢአትና በጥቃት ላይ ግን አትተባበሩ። سورة النساء: 140 وَقَدْ نَزَّلَ عَلَيْكُمْ فِي الْكِتَابِ أَنْ إِذَا سَمِعْتُمْ آيَاتِ اللَّهِ يُكْفَرُ بِهَا وَيُسْتَهْزَأُ بِهَا فَلَا تَقْعُدُوا مَعَهُمْ حَتَّىٰ يَخُوضُوا فِي حَدِيثٍ غَيْرِهِ ۚ إِنَّكُمْ إِذًا مِثْلُهُمْ በአላህ አንቀጾች ሲካድባቸውና ሲያላግጡባቸው ስትሰሙ ወደ ሌላ ንግግር እስኪገቡ ድረስ ከእነርሱ ጋር አትቀመጡ። እናንተም ያን ጊዜ እንደነርሱ ትሆናላችሁ። سورة الأنعام: 116 وَإِنْ تُطِعْ أَكْثَرَ مَنْ فِي الْأَرْضِ يُضِلُّوكَ عَنْ سَبِيلِ اللَّهِ ۚ إِنْ يَتَّبِعُونَ إِلَّا الظَّنَّ وَإِنْ هُمْ إِلَّا يَخْرُصُونَ በምድር ላይ ካሉት አብዛኞቹን ብትታዘዝ ከአላህ መንገድ ያሳስቱሃል። سورة النساء: 115 وَمَنْ يُشَاقِقِ الرَّسُولَ مِنْ بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ الْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِ جَهَنَّمَ ۖ وَسَاءَتْ مَصِيرًا ቅኑ መንገድ ከተገለጠለት በኋላ ከመልእክተኛው የሚጣላና ከሙእሚኖች መንገድ ሌላን የሚከተል ሰው ወደ መረጠው እንመራዋለን። سورة آل عمران: 103 وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا ሁላችሁም በአላህ ገመድ በጋራ ያዙ፤ አትከፋፈሉም። ሐቅን ለሚፈልግ በቂ ማስረጃዎች ናቸው ወይስ ቁርኣን ውስጥ «ከቢድዓ ባለቤት ጋር አትቀመጡ» በሚል ቃል በቀጥታ የመጣ አንቀጽ የሚፈለገው? በጥቅሉ በባጢል ላይ አለመተባበርን፣ ከሐቅ የሚያርቁ ሰዎችን አለመከተልንና ከአላህ አንቀጾች ጋር የሚያላግጡ ሰዎችን አለመቀመጥን የሚያስተምሩ በቂ ማስረጃ ናቸው። ➩ እንዲህ ይላል፦ የሆኑ ስብስቦችን የስህተት አካሄድ ለመከላከል ብለን በቁርአንና በሐዲሥ የጸደቁ ትክክለኛ እውነታዎችን ከሩቅ መሸሽ አያስፈልግም። ✅ መልስ፦ በእውነት ከሩቅ እየሸሻችሁ ያላችሁት እናንተ ናችሁ! አላህ አውቆ አጥፊ ከሚባሉት ከመካተት ይጠብቀን! በሩቁ እየሸሻችሁ ያላችሁት እናንተው ከመሆናችሁ ጋር ሌሎችን ለመክሰስ በመሞከር ሌላ ጥፋት ትገባላችሁ። አስቸጋሪ ነገር ... አይነገር ሆነባችሁ ⁉️ ወይስ የቢድዓ ባለቤት የሚለው ከፋይላችሁ ጠፋ! ሁሉም ሀቅ ላይ ነው። ሁላችንም ሙስሊሞች ነን ወደሚለው የኢኽዋን መንሃጅ ልብሳችሁ ሆነ? ውይ ይቅርታ ለካ ኢኽዋን ሆናችኋል! እ ያ ዳ መ ጣ ች ሁ 👇👇👇 https://t.me/AbuImranAselefy/12436
Открыть в Telegram