Account

Posts of Zeraf Books

newest first

#17790Photo
Views509−6%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#17788Photo
Views577+6%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#17787Photo
Views587+8%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#17772Photo

📖 የብ/ጄ ታደሰ ብሩ ስልክ ጥሪ ከሰላምታዬ በኋላ <ጌታዬ ምን ልታዘዝ?> አልኳቸው። እርሳቸውም ''ሪቮልሽኑ እየተጧጧፈ እያለ አንተ ከቤትህ ምን ትሰራለህ? ከቢሮህ ደውዬ አጥቼህ ተረኛው ነው ስልክህን የሰጠኝ: እኔማ የሚረዳ ነገር ካለ ልምጣ ወይ ለማለት ነበር የደወልኩልህ'' አሉኝ። ልምጣ ወይ ያሉት ባይገባኝም እንደቀልድ ወሰድኩትና በሳቅ ብቻ ዝም ብዬ አለፍኩት : 'ጌታዬ እኔ በዋልኩበት ቦታ የኑሮ ችግር አድማ እንጂ ሪቮልሽኑ ገና መታየት አልጀመረም ነበር አልኳቸው: "እንዴ እውነት ነው አልሰማህም?'' አሉኝ: ከእንቅስቃሴው ሁኔታ ከባድ ነገር እንደሚከተል ጠርጥሬያለሁ: ነገር ግን እስካሁን ምንም የማውቀው ነገር የለም: በእርስዎ በኩል የሰሙት ካለ ቢያካፍሉኝ ደስ ይለኛል አልኳቸው: ''እንዴ ጦሩ እኮ የሲቪል ባለሥልጣኖችን ከየቤታቸው እየሄደና እየያዘ ወደ አራተኛ ክ/ጦር እያስገባ እያሠራቸው ነው: ከታሠረባቸው ቤተሰብ አንዱ ደውሎ ሃዘኑን አካፍሎኛል'' አሉኝ: ጌታዬ ለመሆኑ ስለሩቮልዩሽኑ ዓለማና ማንስ እንደሚያንቀሳቅሰው የሚያውቁት ነገር አለ አልኳቸው: ''እኔማ አንዱም አንተ ነህ ሲሉ ሰምቼ ነው እንጂ ምንም የማውቀው ነገር የለም'' አሉኝ: አዬ ጌታዬ እርስዎም ሆኑ እኔ እንድናውቅ ቢፈለግ ኖሮ ቀድም ብሎ ይነገረን ነበር: ሳንፈልግ ለማወቅ አጥብቆ ማንኳኳት ደጃች ለጥይበሉ ባስከፈቱት በር መግባትን ያመጣልና ዝም ብለን ማዳመጡ ይሻላል ስላቸው ሳቅ ፈነቀላቸው: እውነትህን ነው፣ የገፋ ነገር ከመጣ እንደዋወል ተባብለን በዚሁ ዘጋን። °°°° 📖 “ትግል አያቆምም” ጸሐፊ : ዮሴፍ ያዘው (ሻለቃ) የህትመት ዘመን : 2007 የገፅ ብዛት : 285 ~ Inbox @Zerafb To Order. Shipping Worldwide 🇺🇸🇨🇦🇩🇪🇷🇺🇫🇷🇬🇧🇰🇷🇮🇹~🌎 & Delivering Locally.

Open in Telegram
Views645+19%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—