Posts of አንቀጸ አድኅኖ Tube ዘማሪ አበጀ ጣሰው ኃይለ ገብርኤል
«በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል። ዳንኤል 12፥1 እንኳን አደረሳችሁ ❣️🙏ለሊቀ መልዐኩ ለቅዱስ ሚካኤል አመታዊ በዓል 🥰🙏
Open in Telegramበትሕትናው ልዕልናን ላገኘ፣ ለፍጥረታት ባለው ርኅራኄ የአምላክ እናትን ለሚመስል፣ የተቸገሩትን ፈጥኖ መርዳት ልማዱ ላደረገው፣ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ፣ ደግ እና ሰውን ወዳጅ ለሆነው መልአክ ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን። ቅዱሳን መላእክት በአንድ ኃጢአተኛ ወደ እግዚአብሔር መመለስ የሚደሰቱትን ያህል፣ ባልተመለሰው ኃጢአተኛ ደግሞ እንዲሁ ያዝናሉ። በአንዱ ኃጢአተኛ መመለስ የተሰማቸውን ደስታ ፈጣሪያቸውን በማመስገን እንደሚገልጹ፣ ባልተመለሰው ኃጥእ የተሰማቸውን ኃዘን ደግሞ አምላካቸውን "ማረው፣ ይቅር በለው" ብለው በመለመን ያሳያሉ። (ያዕ 5፥13) ቅዱስ ሚካኤል አሁን እንዴት እንደ ሆንን አይቶ ይዘንልን፣ አዝኖም ይለምንልን፣ ለምኖም ያስምረን!!!
Open in Telegramእነሆ፣ ከአቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ መንፈሳዊ ትምህርቶች የተወሰዱና በአማርኛ የተተረጎሙ ጥልቅ ሐሳቦች ናቸው። ለማስታወሻም ሆነ ለማጋራት ይጠቅማሉ። ✝️ 15 መንፈሳዊ ጥቅሶች 1. ስለ ትሕትና ራስህን ከሰዎች በላይ አታድርግ፤ ትሕትና የነፍስ ውበት ናት። 2. ስለ ፍቅር ወደ ፍቅር ጥልቀት ግባ፤ ፍቅር ፈጽሞ አትወድቅም። 3. ስለ ጸሎት ጸሎትህ ከአፍህ ብቻ ሳይሆን ከልብህ ይሁን፤ እግዚአብሔር የልብን ይመለከታል። 4. ስለ ይቅርታ የሰዎችን ጥፋት ከማስታወስ ይልቅ የራስህን ነፍስ መመርመር ጀምር። 5. ስለ መከራ በመከራ ጊዜ እግዚአብሔርን አትርሳ፤ በደስታም ጊዜ አትርሳው። 6. ስለ ንስሐ የንስሐ በር ለሚመለስ ሰው ሁልጊዜ ክፍት ነው። 7. ስለ ሰው ማክበር ሰውን በሀብቱ አትመዝነው፤ በሰውነቱ አክብረው። 8. ስለ እምነት እግዚአብሔርን እመን፤ የአንተ ጥበብ የማይደርስበትን እርሱ ያውቃል። 9. ስለ ልብ ውጫዊ ውበት ሰዎችን ያስደንቃል፤ የልብ ንጽሕና ግን እግዚአብሔርን ያስደስታል። 10. ስለ ትዕግሥት በትዕግሥት ጠብቅ፤ እግዚአብሔር የሚያደርገው ሁሉ በጥበብ ነው። 11. ስለ ምላስ ከመናገርህ በፊት አስብ፤ አንድ ቃል ልብን ሊፈውስም ሊያቆስልም ይችላል። 12. ስለ ዓለም የዓለምን ነገር ሁሉ ብታገኝ ነፍስህን ካጣህ ምን ትርፍ አለው? 13. ስለ በጎ ሥራ መልካም ሥራህን ለሰው ማሳየት አትፈልግ፤ ለእግዚአብሔር ብለህ አድርገው። 14. ስለ ሰላም ሰላምን ከሰዎች አትጠብቅ ብቻ፤ አንተም ለሰዎች የሰላም ምንጭ ሁን። 15. ስለ እግዚአብሔር ፍቅር እግዚአብሔር በሕይወትህ ውስጥ ከሁሉ በላይ ቦታ ይኑረው።
Open in Telegramወዳጄ ሆይ በሕይወትህ ውስጥ ከባድ ሐዘንና ድካም ሲገጥምህ፣ ሁሉ ነገር እንደተዘጋብህ አድርገህ አታስብ። ልክ ጨለማ ሲጠነክር የንጋት ብርሃን መቅረቡ እንደማይቀር፣ በነፍስ ውስጥ የሚሰማ ጥልቅ ድካምም ወደ አዲስ መታደስ የሚያመራ መንገድ ሊሆን ይችላል። ዋናው ነገር በሐዘን ጊዜ ራስን ላለማጣት እና ልብን በመራርነት ላለመዝጋት መጣር ነው። ዛሬ የምታፈስሰው እንባ በከንቱ አይቀርም፤ በፍቅርና በትዕግሥት የታለፈ ሐዘን የሰውን ልብ ያለሰልሳል፣ ለሌሎችም ይበልጥ እንድታዝንና እንድትረዳ ያደርግሃል። እናም ተወዳጆቼ ሐዘንን እንደ መጨረሻ ግድግዳ ሳይሆን፣ የሰውን ልብ የሚያለሰልስና ወደ ጥልቅ ርኅራኄ የሚያሸጋግር ጊዜ አድርጎ ያሳያል። ሐዘንን በመራርነት ሳይሆን በትዕግሥት ማለፍ የውስጥ ጥንካሬ ይሰጣል። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ✍️ / ዑራኤል
Open in TelegramForwarded from ♱ ባሕራን ♱ [ ʙᴀʜɪʀᴀɴ ]
🕊 🌺 🕊 🌸 ቅዱሳን ፫፻፲፰ ቱ ሊቃውንት ! 🌸 🕊 🌺 🕊 [ እንኳን ለአበው ቅዱሳን ፫፻፲፰ ቱ ሊቃውንት" ዓመታዊ የጉባኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ] ❝ ቤተ ክርስቲያንን በብዙዎች ቍልፎች [ መቀርቀሪያዎች ] ያጸኗት ለኾኑ ፤ ከከንፈሮቻቸው ምንጮችና የወንዞች ፈሳሽ የሚፈስስ ፣ በሥላሴ ተወጋጋኞች [ተባባሪዎች] ለኾኑ ሕግን ለደነገጉ ሃይማኖታቸው ለቀና ለሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ ሊቃውንት ሰላምታ ይገባል። ❞ [ ተአምኆ ቅዱሳን ] ▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬ “ማኅበረ በኵር እለ በኒቅያ ተጋብኡ፤ በኒቅያ ቃለ ሃይማኖት ወሰኑ ወሠርዑ፤ እንበለ ሕጸት ሥላሴ አርትዑ። [ በኒቅያ የተሰበሰቡ የበኵር ጌታ ማኅበር፤ በኒቅያ የሃይማኖትን ቃል ወስነው ሥርዐትን [ቀኖናን] ሠሩ፤ ያለ አካላት ጕድለትም ሦስትነትን አቅናኑ፡፡ ] [ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያው ሃይማኖታዊ ምስጢርን የሚመግቡ፣ ሃይማኖትን ገልጠው ያብራሩ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ሊቃውንት፣ በጉባኤያቸው የኑፋቄ ሕንጻን አፈረሱ፣ መናፈቃንንም አስወገዱ፡፡ የሐዲስ ኪዳን ሙሽሪት ቤተክርስቲያንን ማሕሌታይ ነቢይዋ ሰሎሞን በማሕሌተ ትንቢት እንዳመሰገናት መጠን፣ በሳኔር የፊት ርዝማኔ ዋሊያዎች ታዩ፤ የኒቂያ ጉባኤ [አንድነት] ሰዎች በቅድስት ሀገር ኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖትን አቅናኑ ] [ ቅዱስ ያሬድ ] 🌸 🌸 ††† ✟ 𝐎𝐑𝐓𝐇𝐎𝐃𝐎𝐗Y ✟ 🕊 💖 🕊
Open in Telegramአምላከ ቅዱሳን ሊቃውንት በጸሎታቸው እኛንም: ቤተ ክርስቲያናችንንም ከክፉ ጠላት ይጠብቅልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን:: 🕊 [ † ኅዳር ፱ [ 9 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱሳን ፫፻፲፰ ቱ ሊቃውንት ፪. ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ ፫. ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ፬. አባ ይስሐቅ ሊቀ ጳጳሳት ፭. ሊቁ አካለ ወልድ [ † ወርሐዊ በዓላት ] ፩. አባ በርሱማ ሶርያዊ [ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት] ፪. አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ፫. የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን ፬. አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ ፭. ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ " እውነት እላቹሃለሁ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል:: በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል:: ደግሞ እላቹሃለሁ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል:: ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና::" † [ማቴ.፲፰፥፲፰] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ] † † † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖 🕊 💖
Open in Telegramተወዳጆች ሆይ! እግዚአብሔር ፈጽመን ካልካድነው በስተቀር፣ የትኛውም ጥልቅ ውስጥ ብንሆን ጥበቃውንና ቸርነቱን ከቶ አያቆምም! ይህ ማለት ግን ኃጢአታችንን ይወደዋል ማለት አይደለም። አንዳንዴ ኃጢአት እየሠራን እግዚአብሔር መልካም ሲያደርግልን፣ ሰይጣን «እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ወዶልን ነው ወይም በኃጢአታችን እንድንጸና ፈቅዶልን ነው» በማለት ሞኝና ግዴለሽ አድርጎሊያሳየን ይሞክራል። ነገር ግን እግዚአብሔር መልካም የሚያደርግልን ኃጢአታችንን ወዶልን አይደለም፤ ይልቅስ፡ 👉እንድናድግና እንድንለወጥ ስለሚፈልግ፤ 👉ድካማችንንና የተሰበርንበትንም ሐዲድ ስለሚያውቅ፤ ከጨለማችን በላይ ሆኖም እንኳ ታላቁን ቸርነቱንና ስጦታውን ለእኛ ከሰማይ ማየቱን አያቆምም። ይህ የርኅራኄና የይቅርታ ሥራ የእግዚአብሔር የአባትነት ባሕርይው ነው! እርሱ አባት በመሆኑ፣ ልጆቹ በድካም ውስጥም ቢወድቁ ከፈጣሪነቱና ከርኅራኄው የተነሣ ይመግበናል፣ ይጠብቀናል፤ ዋናው ዓላማው ግን ከኃጢአታችን ተመልሰን በእርሱ ፊት ንጹሐን እንድንሆን ነው። እግዚአብሔር የማይለወጥ አባትነቱንና ቸርነቱን አብዝቶ ይባርክልን! ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን
Open in Telegramዘመኔ በከንቱ እንዳይፈፀም መልካም እንድሰራ እርዳኝ መድኃኒዓለም ሀጥያቴ በዝቶብኝ መቆም አቅቶኛል በቤት ዉስጥ ልጣል ሠላም ይሻለኛል ድንገት ስትጠራኝ ግራ እንዳይገባኝ በህይወት ዘመኔ ለንስሀ አብቃኝ አንተ የወሰንከዉ እድሜዬ ሲያበቃ ለነፍሴ የሚቆም አድለኝ ጠበቃ /2/ በሞት ሳልገታ ሳይደክም ጉልበቴ እንደምትወደው ልኑር መድሀኒቴ በሰማይ መንግሥትህ አስበኝ አደራ አቁመኝ በቀኝህ ከቅዱሳን ጋራ /2/ በጎ ማድረግ ስወድ መስራት ያቅተኛል የሥጋዬ ፍቃድ እንቅፋት ሆኖኛል ከሀጥያት እስራት አምላኬ ፍታኝ ሕግህን ልጠብቅ በቃልህ አፅናኝ /2/
Open in Telegramሀበ ማርያም ድንግል ሀበ ማርያም ድንግል በእንተ ፍልሰተ ዐፅሙ ጸለየ እንዘ ይብል ጊዮርጊስ ቀዲሙ ምስለ ፍልሰትኪ ደምርኒ እሙ ከሥጋ ፈቃድ ለመራቅ ወደ ርስት ሀገር ለመድረስ /2/ ርግበ ገሊላዋ ማርያም ኦፈ ከራዲዮን ጊዮርጊስ /2/ በመከራ ጌጦ ተሸልሞ የግፍ ጽዋን ለሚቀምስ /2/ እመ ሰማዕታት ማርያም መክብበ ሰማዕት ጊዮርጊስ /2/ ሰባ ነገስታት ፊት ቆሞ ስቃይ መከራን ቢታገስ /2/ ቀጸላ መንግስቱ ማርያም የጽጌ አክሊል ለጊዮርጊስ /2/ ከድራጎን አፍ ለመትረፍ ከደል ነሺዎች ለመድረስ /2/ የመለኮት ዙፋን ማርያም ባለ ነጭ ፈረስ ጊዮርጊስ /2/ በነፍስ ዝለን እንዳንወድቅ ከክብራችንም እንዳንረግፍ /2/ አፍጣኒተ ረድኤት ማርያም ፍጡነ ረድኤት ጊዮርጊስ /2/ ሥዕሏ ከሥዕሉ ጋር ባንድ ተስሎ የሚቀድስ /2/ ሰዋሰወ ነፍስ ማርያም ተንከተመ ድሂን ጊዮርጊስ /2/ ፍልሰት ሕሊና እንድንገኝ የሀገር አንድነት እንዳይፈርስ /2/ የአሥራት ርስት ናት ለማርያም ገበዘ ኢትዮጵያ ጊዮርጊስ /2 አዲስ ዝማሬ ሀበ ማርያም ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች •➢ ሼር // SHARE @zemarAbeje21 @zemarAbeje21 @zemarAbeje21 👆👆ይ🀄️ላ🀄️ሉን 👍 ✅ ❌ ✍️ ˡᶦᵏᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
Open in Telegram"ኃጥእ ነኝ ማለት ብቻ እውነተኛ ትህትና እንዳይደለ በእውነት እናገራለሁ፤ እውነተኛ ትህትናስ ትሩፋት መስራት ነው፡፡ 🙏 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያጋሩ 🔄 ሼር 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄 ╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀| ✧══╮ https://t.me/zemarAbeje21 ╰══✧•ೋ✧๑♡๑✧ ✧══╯
Open in Telegram