Account

Posts of Wolkite University muslim student jema

newest first

#3545Photo

📢 አስደሳች ዜና ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፍሬሽ ተማሪዎች በሙሉ! የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማአ የአካዳሚ ጉዳይ ክፍል፣ ባለፉት ዓመታት በተሳካ ሁኔታ ሲያከናውነው የቆየውን የፍሬሽ ተማሪዎች የትምህርት ድጋፍ (TUTORIAL) ፕሮግራም፣ በዚህ ዓመትም ይዘቱን በማሻሻልና ከተማሪዎች ፍላጎት እና የትምህርት ሁኔታ ጋር በማጣጣም ለማካሄድ ተዘጋጅቷል። ይህ ፕሮግራም፦ 📚 በትምህርታችሁ ላይ ጥልቅ ግንዛቤ እንድታገኙ፣ 📝 ለፈተናዎች በተሻለ ሁኔታ እንድትዘጋጁ፣ 🎯 የትምህርት ጉዞአችሁን በመተማመንና በስኬት እንድትጀምሩ፣ 🤝 ከተማሪ ጓደኞቻችሁ ጋር በመማማርና በመደጋገፍ የተሻለ ውጤት እንድታመጡ ይረዳችኋል። ስለሆነም ሁላችሁም ይህንን ውድ ዕድል በመጠቀም በፕሮግራሙ ላይ በንቃትና በተከታታይ እንድትሳተፉ በአክብሮት እንጋብዛችኋለን። 📍 ቦታ: አንሳር መስጂድ      ኮርስ:Psychology 🕒 ሰዓት:  ቅዳሜ ጠዋት 2:30 📌 አዘጋጅ: የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማአ – የአካዳሚ ጉዳይ ክፍል ለምታውቁት ተማሪ አጋሩ!!

Open in Telegram
Views181−53%vs avg
Forwards—
Reactions4
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
8 h93
28 h181
  1. After 24 hours181
  2. Total to date181
#3543Text

📝 Before writing your answers, you MUST include: A. Full Name B. Department C. Year of Study D. Declaration: "Wallahi, I did not use any AI (ChatGPT, Google, or other social media) to answer these questions." 👉Use this Bot for Answers @WKUMSJ_dawah_bot 1. የ«ሚን ኡሱል ዓቂደቲ አህሊሱና ወልጀማዐ» ኪታብ ደራሲ ማን ናቸው? ١. من هو مؤلف كتاب «من أصول عقيدة أهل السنة والجماعة»؟ A) ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን / الشيخ صالح بن فوزان الفوزان B) ኢማም አል-ቡኻሪይ / الإمام البخاري C) ኢብኑል ጀውዚይ / ابن الجوزي D) ሸይኽ ኢብኑ ባዝ / الشيخ ابن باز 2. «አህሊሱና ወልጀማዐ» ውስጥ «አል-ጀማዐ» ማለት ምን ማለት ነው? ٢. ما معنى «الجماعة» في اسم أهل السنة والجماعة؟ A) በሐቅ ላይ መሰባሰብና አለመለያየት / اجتماعهم على الحق وعدم تفرقهم B) በአንድ ቦታ መኖር / اجتماعهم في مكان واحد C) በስሜት መሰባሰብ / اجتماعهم على الأهواء D) የመሪዎቻቸውን ስም መያዝ / الانتساب لقادتهم 3. መላእክት ከምን ተፈጠሩ? ٣. مِمَّ خُلِقت الملائكة؟ A) ከእሳት / من نار B) ከአፈር / من طين C) ከውሃ / من ماء D) ከብርሃን (ኑር) / من نور 4. ስለ ቁርኣን የአህሊሱና ወልጀማዐ እምነት ምንድን ነው? ٤. ما عقيدة أهل السنة والجماعة في القرآن الكريم؟ A) ፍጡር ነው / مخلوق B) የአላህ ቃል ነው እንጂ ፍጡር አይደለም / كلام الله منزل غير مخلوق C) መልእክቱ ብቻ የአላህ ቃል ነው፤ ፊደላቱ ግን ፍጡር ናቸው / معانيه غير مخلوقة وحروفه مخلوقة D) የጅብሪል ቃል ነው / كلام جبريل 5. «ሰው ምርጫና ፍላጎት የለውም፤ ተገዶ ይሰራል» የሚለው የጥመት አንጃ ማን ነው? ٥. من هي الفرقة التي تقول إن العبد مجبر على أفعاله وليس له اختيار؟ A) ቀደሪያ / القدرية B) ሙርጂአ / المرجئة C) ኸዋሪጅ / الخوارج D) ጀብሪያ / الجبرية 6. በአህሊሱና አስተምህሮ «ኢማን» ምንድን ነው? ٦. ما هو الإيمان عند أهل السنة والجماعة؟ A) በልብ ማመን ብቻ / اعتقاد بالقلب فقط B) በምላስ መናገር ብቻ / قول باللسان فقط C) ቃል፣ ስራ እና እምነት ሲሆን ይጨምራል ይቀንሳል / قول وعمل واعتقاد يزيد بالطاعة وينقص بالمعصية D) ስራ ብቻ ነው፤ አይጨምርም / عمل فقط لا يزيد ولا ينقص 7. «ወንጀል ከኢማን ጋር ምንም አይጎዳም» የሚሉት እነማን ናቸው? ٧. من القائلون: «لا يضر مع الإيمان معصية»؟ A) ኸዋሪጅ / الخوارج B) ሙዕተዚላ / المعتزلة C) ጀህሚያ / الجهمية D) ሙርጂአ / المرجئة 8. ከሺርክ በታች የሆነ ትልቅ ወንጀል (ከባኢር) የሰራ ሙስሊም ምን ይባላል? ٨. ما حكم مرتكب الكبيرة التي دون الشرك عند أهل السنة؟ A) ካፊር / كافر B) ሙሉ ሙእሚን / مؤمن كامل الإيمان C) ፋሲቅ (አመጸኛ) እና ኢማኑ የጎደለበት / فاسق ناقص الإيمان وتحت المشيئة D) ሙናፊቅ / منافق 9. የሙስሊም መሪዎችን መታዘዝ የሚቆመው መቼ ነው? ٩. متى لا تجوز طاعة ولاة أمور المسلمين؟ A) ወንጀልን ሲያዙ (ማዕሲያ) / إذا أمروا بمعصية B) ሲታመሙ / إذا مرضوا C) ሲያረጁ / إذا كبروا في السن D) ሲጓዙ / إذا سافروا 10. ከነቢዩ (ﷺ) በኋላ በቅደም ተከተል የመጡት አራቱ ኸሊፋዎች እነማን ናቸው? ١٠. ما الترتيب الصحيح للخلفاء الراشدين بعد النبي ﷺ؟ A) አቡበክር፣ ዑስማን፣ ዑመር፣ ዐሊይ B) ዑመር፣ አቡበክር፣ ዑስማን፣ ዐሊይ C) አቡበክር፣ ዑመር፣ ዑስማን፣ ዐሊይ D) አቡበክር፣ ዑመር፣ ዐሊይ፣ ዑስማን 11. ከራማተል አውሊያእን (የጻድቃን ድንቅ ክስተት) የካዱት አንጃዎች እነማን ናቸው? ١١. من الذين أنكروا كرامات الأولياء؟ A) ኸዋሪጅ እና ራፊዷ / الخوارج والرافضة B) ሙዕተዚላ እና ጀህሚያ / المعتزلة والجهمية C) ሙርጂአ እና ቀደሪያ / المرجئة والقدرية D) ሶፊያ እና ፈላሲፋ / الصوفية والفلاسفة 12. አህሊሱና በአለመግባባት ጊዜ ነገሮችን ወደ ምን ይመልሳሉ? ١٢. إلى أي شيء يرد أهل السنة ما اختلف فيه الناس؟ A) ወደ ሱና ብቻ / إلى السنة فقط B) ወደ ቁርኣንና ሱና / إلى كتاب الله وسنة رسوله ﷺ C) ወደ ባህል / إلى العادات D) ወደ ቁርኣን ብቻ / إلى كتاب الله فقط

Open in Telegram
Views169−56%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
#3542Text
Views136−65%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#3541Text
Views135−65%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#3538Photo

📢 ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለምትገቡ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ! 🌙 እንኳን ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በሰላም መጣችሁ! ውድ ሙስሊም እህትና ወንድሞቻችን! የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማዓ በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ወደ ዩኒቨርሲቲያችን ለምትገቡ አዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 21 እና 22 መሆናቸውን እያሳወቀ፣ እናንተን በእስላማዊ ፍቅር፣ በወንድማማችነትና በእንክብካቤ ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል። ❤️ እናንተ ብቻችሁን አይደላችሁም! ከደም በላይ የሚያገናኘን የኢስላም ወንድማማችነት ትስስር አለን። ዩኒቨርሲቲ አዲስ ጉዞ፣ አዲስ ልምድና አዲስ ፈተና ቢሆንም በአንድነት እንደጋገፋለን። ስለሆነም ማንኛውንም መረጃ፣ ምክር ወይም እገዛ በምትፈልጉበት ጊዜ ከሚከተሉት የጀማዓው ኃላፊዎች ጋር በመገናኘት እገዛ ማግኘት ትችላላችሁ። 📞 የመገኛ ስልክ ቁጥሮች 🔹 አሚር ሁሴን – የጀማዓው አሚር 📱 0955783551 🔹 አብዱሰላም – ምክትል አሚር 📱 0926356562 🔹 መንሱር አወል – የአካዳሚ ዘርፍ አሚር 📱 0943590777 🔹 አብዱልዋሂድ – Afaan Oromoo 📱 0905820421 🌸 ለአዲስ ሙስሊም እህቶቻችን ልዩ መልዕክት! ውድ እህቶቻችን፣ የምትፈልጉትን መረጃና እገዛ ለማግኘት ከላይ በተጠቀሱት ወንድሞች በኩል የሴት ተወካዮችን ማግኘት ትችላላችሁ። 📲 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ https://t.me/wkumuslims ━━━━━━━━━━━━━━━━ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማዓ

Open in Telegram
Views965+149%vs avg
Forwards—
Reactions7
Comments—
#3537Text
Views265−32%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
47 h252
67 h265
  1. Total to date265
#3535Photo
Views371−4%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#3531Photo
Views600+55%vs avg
Forwards—
Reactions11
Comments—
#3530Photo
Views469+21%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#3528Text

⛓ ከ700 ዓመት በፊት “ሙስሊሙ አዲያ” በጨካኙ ዐፄ አምደፂዮን ተወሮ ነበር❗️               بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيم ምሳሌ የታሪክ ትምህርት ፦ 《 وَلَوْ شِئْنَا لَرَفَعْنَٰهُ بِهَا وَلَٰكِنَّهُۥٓ أَخْلَدَ إِلَى ٱلْأَرْضِ وَٱتَّبَعَ هَوَىٰهُ فَمَثَلُهُۥ كَمَثَلِ ٱلْكَلْبِ إِن تَحْمِلْ عَلَيْهِ يَلْهَثْ أَوْ تَتْرُكْهُ يَلْهَث ذَّٰلِكَ مَثَلُ ٱلْقَوْمِ ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا فَٱقْصُصِ ٱلْقَصَصَ لَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ 》(الأعراف),  176 (( “ በሻንም ኖሮ በእርሷ ከፍ ባደረግነው ነበር፡፡ እርሱ ግን ወደ ምድር ተዘነበለ፡፡ ፍላጎቱንም ተከተለ፡፡ ብጤውም ብታባርረው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ ወይም ብትተወው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ እንደ ኾነ ውሻ ነው፡፡ ይህ የእነዚያ በአንቀጾቻችን ያስተባበሉት ሕዝቦች ምሳሌ ነው፡፡ ያስተነትኑም ዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው፡፡ ” )) አል–አዕራፍ 176 አዎ ! ሐቀኛው አምላክ እንዳለው ታሪካቸውን ሳይሆን ታሪካችንን እንተርክላቸው … ሐቅን በመተዋችን የተነሳ ልክ እንደነሱ በሚያለከልክ ውሻ እንዳንመሰል ዘንዳ ወደ ምንመከረው እውነት እንመለስ !!! በት/ቤት ውስጥ ከታች ታዳጊ እፃናት ጀምሮ  እስከ ትልቁ የትምህርት ተቋም በካፊሮች ተፅኖ ውስጥ ወድቀው በመማቀቅ ላይ ነው ያሉት … በመማሪያ ክፍል ውስጥ ታሪክን ማወቅ ከአከባቢ ይጀምራል… በሚል መርዝ የተለወሰበት ሴራ "ትምርታዊ ጉዞ" የሚል ስያሜ ይሰጠውና የነብዩንና የሰሓባዎቻቸውን ታሪክ በቅጡ እንዳያውቅ በወላጆቹ አስገዳጅነት ት/ቤት የተወረወረው “የኢስላም ትውልድ” የኢስላም ጠላት የሆኑ ከሃዲያን አፄዎችን የግፍ ገድል አጣፍጠው ታሪክክ … ይሉታል። ሰማይና ምድር በፍትሕ የቆሙበትን የኢስላም ታሪክ ከክርስቶስ ከመሐመድ ልደት በፊት በኋላ እያሉ የእስልምናን አመጣጥ በተዛባ እይታ ለተማሪዎቹ ይግቷቸዋል። የእስልምና ምልክትና መገለጫ የሆኑ ነገሮችን ባጠቃላይ ፦ “ሒጃብ” ታሪክን ያላገናዘብ ተፅኖና ነፃነት ገፈፋ ፣ አፈና…፤ “ሶላት” የዕድገት ፍጥነት ገደብን ወደ ኋላ የሚጎትትና የመማር ማስተማር ሂደትን የሚያዛባ ፤ ፍትሓዊ ስርዓተ–ገደብ የተደረገለትን "ጋብቻ" የሴት ልጅ መብትን መግፈፍና ማስገደድ በማለት ባጠቃላይ የእስልምና አስተምሮን የኋልዮሽ እንጂ ከዘመን ጋር የማይሄድ ጎታታ ጨለምተኛ አድርጎ በመሳል ማነወር… እነሱ የመስቀል ጦርነት ብለው በሚልዮን የሚቆጠር ንፁሐንን ደም በግፍ ያፈሰሱበትን ፤ የአረር መስጂዶችን ወደ ቤተ–ክርስቲያንነት የቀየሩበትን ፤ ሙስሊም እናቶቻችንን… ቆርጠው ገደል የከተቱበትን ፤ ወንዶቻችንን አስገድደው ያስጠመቁበትን ፤ በግፍ ያቃጠሉት መስጂድና ያነደዱት ቁርኣን ታሪክ ደብቀው “የግራኝ አህመድን” የነፃነት ጥያቄና ፍትሕን የማስፈን ትግል … እንደሚያስፈራ አውሬ ስሎ ሙስሊሞችን በዕምነታቸው ፍትሓዊነት ላይ ጥርጣሬ እንዲኖራቸው ማድረግ… ከዚህም ባለፈ የእስልምና መንፈሳዊና ታሪካዊ ስርጭትን በዓለም ህዝብ ሀንገት ላይ በተሳለ ስለት ነው እዚህ ያደረሰው የሚለው ድብቅ የታሪክ ሸፍጥ የሙስሊም ታዳጊዎችና ወጣቶች “ግን ለምን ? ” እያሉ እውነተኛውን የእስልምና ታሪክ ከምንጩ የሚያገኙበትን ስፍራ እንዳይመለከቱ አውረዋቸው እንደ ተጠመደ በሬ እነሱ በፈለጉት አቅጣጫ ወደ ፊት ብቻ አርገው አስቀሩሃቸው !!! ተጠያቂው ማነው !? አዎ !  ታሪክ ይፍረደን !!! ብለን ግን ዝም አንልም የሚሰማን ብናጣም ትውልድን የማንቃት አላፊነት አለብን !!! «… لِّيَهْلِكَ مَنْ هَلَكَ عَنۢ بَيِّنَةٍ وَيَحْيَىٰ مَنْ حَىَّ عَنۢ بَيِّنَةٍ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَسَمِيعٌ عَلِيمٌ» (الأنفال) 42 (( " …ግን አላህ ሊሠራው የሚገባውን ነገር ሊፈጽም የሚጠፋ ሰው ከአስረጅ በኋላ እንዲጠፋ ሕያው የሚኾንም ሰው ከአስረጅ በኋላ ሕያው እንዲኾን… ፡፡ አላህም በእርግጥ ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡ " )) [አል–አንፋል 42] አዎ ! እናንተ ለዚህ ጥፋትና… እውነተኛውን የኢስላም ታሪክን ለማዛባት ራሳቹንና ልጆቻቹን ገንዘባቹን ፣ ጊዜያቹን ጭምር ሳይቀር አሟጣቹ በመስጠት እንደ የድርሻቹ በመወጣት ትብብር እያረጋቹ መሆኑን ቆም ብላቹ በመገንዘብ አላህ ዘንድ ከሚያስጠይቃቹ አደገኛ ስህተት ለራሳቹ ስትሉ በፍጥነት ተመለሱ !! በማለት ለሀገራችን ዑለማዎች ፣ ለሁስታዞች ፣ እንዲሁም ለወላጆችና ለወጣቶች ጥሪዬን አቀርባለሁ ! ሙስሊም ወገኖቼ ሆይ ! እስቲ በጣም በጥቂቱ በአንድ አላህ በማመናቸው ብቻ ካልካዳቹ በሚል አስገዳጅ የዐፄዎች ግፍ ደማቸው ፈሶ ስለ ቀራውና ስለ ተረሳው … አሳቃቂ የሙስሊሞች ታሪክ በስሱ ላውጋቹ !!! አሁን ላይ እኛ ባንፈልገውም (ታሪኩ) የሚፈልገን ቀን ይመጣ ይሆናል ! እኛ የመቶ ዓመታት ዘመን ተሻጋሪ የአማኝ እህት ወንድሞቻችን ዕምባ…መጥረግ ቢያቅተን ቢያቅተን የነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) “ሱና” የሙጥኝ በማለትና “ዱዓ” በማድረግ ልናስባቸው ሲገባን "በምን አገባኝ” ስሜት የውለታቸውን ተጋድሎ ረስተን ደማቸውን ጠጥተው ካልረኩ አረመኔ ከሃዲያን ጋር ወደጅነታችን ደርቷል ! ያንን ሁሉ የዘመናት የግፍ ታሪክ ገልብጠን የ"ነገስታቶቻችን" አኩሪ ታሪክ በሚል ቅኝት የልጆቻችንን ስነ–ልቦና አንጥፈን የ3000 ዓመት የውሸት ትርክት አዙሪት እንዲሆንባቸው ከአፀደ እፃናት ጀምሮ እስከ ዩንቨሪስቲ እያስጋትናቸው እንገኛለን !!! የአማኞችን ታሪክ በግፍ ከተቀበረበት አውጥተን ፍትሕን ማስፈን አቅቶን… የጨካኝ ግፈኞችን ታሪክ ማጣፈጫ ቀባብተን እንደ ገደል ማሚቱ እናስተጋባለን !!! ታላቁ ነብይ እንዳሉት ፦ የትንሳሔ ዕለትም አብረናቸው እንዳንቀሰቀስ ያስፈራልናል !!! አላህ ሆይ ከወዳጆችህ ጋር ወዳጅ አድርገን !!! አሚን ! «ሳናውቀው ቀርተን ይሆን…» እስቲ ልጆቻችን ት/ቤት የሚማሩት የማንን ታሪክ ነው ! አማኝ አባት እናቶቻችን በግድ ጠምቀው በማስቆረብ መስቀል ያሸከሙሃቸውን ሴይጣን ነገስታቶች ታሪክ እንደሆነ ለምልከታ ያህል ከማይገፋው ግፋቸው ውስጥ እጅግ በጣም ጥቂቱን እንመልከት ፦ በ1314 ዐፄ አምደፂሆን በሰሜን ነገሰ በ1316/7 በተ/ሀብት የበለፀገችውን የዳሞትን ግዛት በመውረር ወደ ግዛቱ ጨመረ በዚሑ ጊዜ የሙስሊም ሐገር የሆነችውን ሀዲያን አጠቃ ! ህዝቡንም ማረከ ! ሀይቅ ገዳም በተገኘው ጥንታዊ ፅሁፍ አምደፂሆን ስለ አገኘው ድሉ እንዲህ ብሎ ነበር ፦ “የቅዱሥ እስጢፋኖሥንና የአባቴን ክርሥቶስ ተስፋና ፀሎት በማመን ወደ ጦርነት ሄድኩ ! እ/ብሄር ሁሉንም የዳሞት ሕዝቦች በእጄ ሰጠኝ ወንዱንም ሴቱንም ወደ ሌላ ቦታ አጋዝኩዋቸው ! ከዚያ እ/ብሔር ሁሉንም የሀድያ ሕዝብ ሴት ወንዱን ሠጠኝ ! እነርሱንም ወደ ሌላ ቦታ አጋዝኩዋቸው !!! ዐፄ አምደፂሆን ሙስሊሞችን በሀይል ከወረረ በዋላ እንዲህ ነበር ያለው … 📌ድብልቅልቁ የትምህርት ዓለም ዋይታ በእውነተኛው የኢስላም ብርሃን ሲፈታ📌 ከሚለው ተከታታይ ፅሁፍ የተወሰደ።

Open in Telegram
Views579+49%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#3523Text
Views526+36%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—