📝"ጠንቋይ እና ዘራፊው አባት ፦ መልአከ ፀሐይ ሰናይ ባያብል" (የሰሚት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ) 👉በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን ላይ በስፋት እየታየ ያለው የውስጥ ፈተና ፣ መልኩን እየቀየረ ከቀን ቀን ፣ የቤተክርስቲያንን ቅድስና እና ክብር ለማሳጣት ከጳጳሳት ጀምሮ አገልጋዮች ላይ እየታየ ያለው ነውር የታከለበት ድፍረት በእውነት የምዕመኑን ልብ እየሰበረ ይገኛል ። 👉አሁንማ ፣ ከመለመዱ የተነሳ በነውር ጌጣቸው የታጀበው ሥራቸው ሲገለጥ ፣ ምንም የማይመስላቸው ፣ የሚዲያ ጫጫታ ለአንድ ሳምንት ነው በሚል ፣ ለአንድ ሳምንት ይደበቃሉ ከዛ ደረታቸውን ገልብጠው ይወጣሉ ፣ የድፍረታቸው ጥግ ሰማይ ደርሶል ። ሰሞኑን አይታችኃል ነውር ጌጡ የሽማግሌ ዱርዬ ዶኒ ተብዬው በአደባባይ ሲጨፍር ፣ ለሚመሩት ሕዝብ የማይጨነቁ መልሶ ሰንበት ሄዶ በድፍረት ቤተክርስቲያን አውደምሕረት ይቆማል ። 👉አሁን በአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሥር የሚገኙ አጥብያ አብያተክርስቲያናት በጥቂት ግለሰቦች ፣ ከፍተኛ የገንዘብ ምዝበራ ይከናወንባቸዋል ፣ ጠያቂም ተጠያቂም የለም ፣ ሰንሰለቱ ከታች እስከ ላይ በጥቅም የተያያዘ ነው ። 👉ይህ ግለሰብ መልአከ ፀሐይ ሰናይ ባያብል ቀደም ሲል ከነበረበት መገናኛ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን በርካታ ሚሊየን ገንዘብን ዘርፎ ፣ በአጥቢያው ካህናት እና ምዕመናን ክስ ተመስርቶበት መንግሥት ጋር ደርሶ የእነ አቡነ ሕርያቆስ አስተደር በግድይሌሽነት መረጃን ለመንግስት አካል ከመስጠት ይልቅ ሰውየውን አንስተው ሰሚት ቅዱስ ጊዮርጊስ መደቡት ፣ ይህ ነው እንግዲህ ጠያቂ ተጠያቂ አለመኖሩ ማስረጃው ፣ በልተህ ካበላህ በአራት ነጥብ። አፍ ታዘጋለህ ግን እስከ መቼ....? 👉አሁን በሰሚ ት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሥልጣኑን ተጠቅሞ ግብራአበሮቹን በመያዝ ቤተክርስቲያኒቱን እየመዘበሯት ይገኛሉ የደብሩ ዋና ፀሐፊ ኪሮስ አብርሃ ፣ የደብሩ ሂሣብ ክፍል አቢይ ገብረ ሚካኤል፣ የደብሩ ገንዘብ ቤት አቶ ታደለ አበበ በሰሚት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፣ ከእነዚህ ግለሰቦች ጋር በመሆን የገንዘብ ምዝበራው በቃላት አይገለጽም ይላሉ የቅርብ የመረጃ ምንጮቻችን 👉 በደብሩ ውስጥ ካሉት ተከራዮች የደብሩን የኪራዩን ገንዘብ ወደ ግል አካውንታቸው በማስገባት ከአንድ ሚልዮን አራት መቶ ሺህ ብር በላይ በማስረጃ የተደገፈ በምርመራ የተረጋገጠ ሆኖ እያለ የቦታ ኪራይ ጉዳይ ደብሩ ጨረታ የሚባል ፈጽሞ እንደማይታወቅ መረጃውን በፎቶ አስደግፈው ልከዋል ። ከላይ በዝርዝር የተገለጹት ከግለሰቦች ጋር በሚያደረጉት ድርድር ብቻ የሚፈፀም ውል እንጂ በፍፁም ህግ የሚባል እንደማይታወቅ ይናገራሉ ። 👉ይህ በእንዲህ እንዳለ ግለሰቡ ሲበዛ ነውረኛ ፣ ዐርብ እና እሮብ በጉባኤ ፋንታ የቅባ ቅዱስ መቀቢያ ቀን ብሎ ፣ የብዙ ባለ ትዳር ቤቶችን እያፈረሰ እንዳለ የአካባቢው ሰዎች ይናገራሉ ፣ መስተፋቅር እሰራለው ፣ የሀብት ድግምት እሰራለው ፣ እያለ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን ( private part) ጭምር ንቅሳት እነቅሳለው እያለ ብዙ ወጣቶችን ያስነወረ ወራዳ ባለጌ እንደሆነ ይመሰክራሉ ፣ ይህ ግለሰብ ታማሚ እንደሆነ ፣ የዕድሜ ማራዘሚያ እንደሚወስድም ይናገራሉ። ስለጤናው እግዚአብሔር ይማርህ ከማለት ሌላ ምን ይባላል ። 👉የኢዲስ አበባ ሀገረስብከት ጽ/ቤት ይህንን ጉዳይ እንዴት ያያዋል ፣ እስከ መቼ በዚህ ልክ አጥበያ አብያተክርስቲያናት እየተመዘበሩ ይቀጥላል ፣ ይህ እንደማሳያ ሆነ እንጂ አብዛኛ አጥቢያዎች በተመሳሳይ ምዝበራ ይፈጸምባቸዋል ፦ ጠያቂው ማን ነው ? ጽ/ቤቱ ምንድን ነው የሚሰራው ? 👉የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ጽ/ቤትግ በአስቸኳይ አጣሪ ልኮ በገለልተኛ አካል ሁኔታውን ማጣራት አለበት ፣ ሌላውን መረጃ ይቀጥላል .. 📍ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ
Open in TelegramPosts of ኢትዮ ቱንቢ ሚዲያ Ethio Tunbi (Official)
በማኅበረ ቅዱሳን እና በዶንኪ ቲዩብ ትብብር በአርሲ ጥቃት ለተጎዱ ወገኖች የ2.76 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ። ማኅበረ ቅዱሳን በአርሲ የተለያዩ ወረዳዎች በሃይማኖት ተኮር ጥቃት ለተፈናቀሉ እንዲሁም በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት “አለሁ እኔ ለወገኔ” በሚል መሪ ቃል ድጋፍ እያሰባሰበ መሆኑ ይታወቃል ። በዚህም መሠረት ከኮሜዲያን እሸቱ መለሰ (ዶንኪ ቲዩብ) ጋር በመሆን ኅዳር 12 ቀን በካናዳ ሀገር በlive በተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ ከተገኘ ገቢ የመጀመሪያ ዙር ድጋፍ በአርሲ ዞን መርቲ ወረዳ ከተለያዩ ቀበሌዎች ተፈናቅለው በአቦምሳ ከተማ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል። በድጋፉ ወቅትም የማኅበረ ቅዱሳን ተወካዮችን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ያስረከቡ ሲሆን፣ ለዚህ ድጋፍም 2.76 ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጓል። ይህ ድጋፍ ከዚህ በፊት በአርሲ ዞን በሽርካ ወረዳ ከተደረገው ቀጥሎ ለ2ኛ ዙር የተደረገ ሲሆን፣ በቀጣይነትም መሰል የድጋፍ ተግባራትም ተመሳሳይ ጉዳት እና ድርቅ ባለባቸው ቦታዎች ሁሉ በቅርቡ እንደሚደረጉ ተገልጿል። ማኅበረ ቅዱሳን በአርሲና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የድጋፍ ጥሪውን ተቀብለው ለደገፉ አካላት ሁሉ ምስጋናውን እያቀረበ አሁንም ከችግሩ ስፋት አንጻር ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያሳስባል።
Open in Telegram#Koore በደቡብ ኢትዮጵያ፣ ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ጀሎ ቀበሌ ትናንት ረብዕ ከቀኑ 7፡00 እስከ ምሽቱ 1፡00 ድረስ በቆየ የታጣቂዎች ጥቃት አንድ ሰው ሲገደል ቢያንስ 12 ሰዎች መቁሰላቸውን እና ቀደም ሲል ተፈናቅለው በቀበሌው ተጠልለው የነበሩ ነዋሪዎችም ዳግም ተፈናቅለው ወደ ኬሌ ከተማ መግባታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶቼ በለ ሬድዮ ጣቢያ ገልጸዋል። ነዋሪዎቹ የክልሉ አድማ በታኝ አባላት ከሕዝቡ ጋር በመተባበር የታጣቂዎቹን እንቅስቃሴ ባይገታ ኖሮ የከፋ ጉዳት ይከሰት ነበር ብለዋል። የኮሬ ዞን ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰባክ ሰሎሞን በበኩላቸው ጥቃቱን የፈጸሙት ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ የተሻገሩ «ሸኔ» በማለት የጠሯቸው ታጣቂዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። የፀጥታ ኃይሎች እስከ ምሽት በመከላከል የተከፈተውን ጥቃት መመለሳቸውን የገለጹት ኃላፊው፣ " በእኛ በኩል የሞቱም የቆሰሉም አሉ " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል። ዛሬ በነበረው የፓርላማ ውሎ፥ አወቀ ሃምዛዬ (ዶ/ር) ፥ ስለ ሀገሪቱ ሰብዓዊ መብት እና የፀጥታ ሁኔታ ጥያቄ ባቀረቡበት ወቅት የኮሬ ሕዝብን ጉዳይ በልዩ ትኩረት አንስተዋል። ሕዝቡ በኢትዮጵያ ታሪክ ሰምቶትም ሆነ አይቶት በማያውቀው ሁኔታ ላለፉት 11 ዓመታት በፅንፈኛ ታጣቂዎች እየተወረረ ህልውናው አደጋ ላይ መውደቁን ተናግረዋል። " ጉዳዩ በተደጋጋሚ ጊዜ ለም/ቤቱ እንዲሁም ለኢትዮጵያ መንግሥት ቢቀርብም ወረራው ከትላንት በስቲያም፣ ትላንትም ሆነ ዛሬ መቀጠሉን " ጠቅሰው፣ " የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ የተሰማሩ የክልሉ የፀጥታ አካላትም አላስፈላጊ መስዋዕትነት እየከፈሉና እየሞቱ መሆኑን " አስረድተዋል። " ይህ አነስተኛ ቁጥር ያለው የኮሬ ሕዝብ ለ11 ዓመታት በተከታታይ እየተወረረና እየተጨፈጨፈ ህልውናው አደጋ ላይ ወድቆ መንግሥት ጉዳዩን ቸል ያለው ለምንድን ነው ? የዚህ ሕዝብ የወደፊት ተስፋና ዕጣ ፈንታ ምንድን ነው ? " ሲሉ የጠየቁት የምክር ቤት አባሉ፣ የኮሬ ሕዝብ አሳሳቢ የህልውና አደጋና በተጠቀሱት አካባቢዎች ያሉ የሰላምና የጸጥታ ችግሮች አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው አሳስበዋል። ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
Open in Telegram8 እስረኞች ወደ «ታንከር» የቅጣት ቦታ መዛወራቸውን ቤተሰቦቻቸውና ጠበቃቸው ገለጹ። በቃሊቲና ቂሊንጦ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ 8 እስረኞች «ታንከር» ወደተባለ የቅጣት ቦታ መዛወራቸውን ቤተሰቦቻቸውና ጠበቃቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። እስረኞቹ ፦ - አቶ ዮሐንስ ቧያሌው፣ - ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ - አቶ እስክንድር ሽፈራው፣ - ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ - ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ፣ - ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም፣ - አቶ መለሰ ቸሩ እና መንበረ አለሙ ናቸው። አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የታሳሪ ቤተሰብ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፤ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት የማረሚያ ቤቱ አካል አቶ ዮሐንስ ከክፍላቸው እንዲወጡ ጠይቀዋቸው ነበር። ለምን እንደሚወጡ ሲጠይቁም «ከላይ የተሰጠ ትዕዛዝ ነው» የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ገልጿል። አቶ ዮሐንስ ለደህንነታቸው በመስጋት መጀመሪያ ለመውጣት ፈቃደኛ ባይሆኑም፣ ሰኞ ጠዋት በኃይል እንደሚያስወጧቸው ከተነገራቸው በኋላ ወጥተው ወደ «ታንከር» መወሰዳቸውን የታሰሪ ቤተሰብ ተናግረዋል። አቶ ዮሐንስ ከጤና ጋር በተያያዘ ቀዝቃዛ እንዳይመገቡ ለማሞቂያነት እንዲጠቀሙ ፍርድ ቤት የፈቀደላቸው እቃዎች ወደ ተቀየሩበት ቦታ ይዘው እንዳይገቡ መከልከላቸውን አመልክተዋል። በተመሳሳይ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ መንበረ አለሙ እና እስክንድር ሽፈራው ከክፍሎቻቸው ለመውጣት እንዳመነቱና ጉዳት እንዳይደርስባቸው በመስጋት መውጣታቸውን ገልጸዋል። እስረኞቹ የተወሰዱበት ክፍል ጠባብ እንደሆነ፣ ከስምንት በላይ ሰዎች በአንድ ቦታ ተጣበው ያሉበት ፤ በቂ ብርሃን እንደሌለው ቤተሰቡ አስረድቷል። ይህም በእስረኞቹ ጤና ላይ ስጋት እንደፈጠረ ተገልጿል። ይህ ትዕዛዝ ሰጠ የተባለው " የበላይ " የተባለው አካል ማንነው ? መንግስትስ ያውቀዋል ? የሚል ጥያቄ ያነሱት የታሳሪ ቤተሰብ መፍትሄ እንዲጥ ጠይቀዋል። የእስረኞቹ ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት፣ ሰባቱ እስረኞች ሕዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም.፣ አቶ ዮሐንስ ደግሞ ሕዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም. ወደ «ታንከር» ተወስደዋል። ጠበቃው እንዳሉት፣ እስረኞቹ ቀደም ሲል በቦታው ያለውን ሁኔታ በተመለከተ የሕግ ሂደት አካሂደው ነበር። የዐቃቤ ሕግ ባለሙያዎች ቦታውን በአካል ከጎበኙ በኋላ እስረኞቹ ከዚያ ቦታ እንዲወጡ መደረጉንም አስታውሰዋል። አቶ ዮሐንስ አሁንም ጉዳዩን ለፍርድ ቤት ማቅረባቸውን ጠበቃው ገልጸዋል። እንደ ጠበቃው ገለጻ፣ አቶ ዮሐንስ ሕዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም. በችሎት ቀርበው፣ በሌሊት ከክፍላቸው ወጥተው ወደ «ታንከር» / ቅጣት ቤት እንዲገቡ መጠየቃቸውንና ከዚህ ቀደም በፍርድ ቤት የተሰጠውን ትዕዛዝ በመጥቀስ ከመንግስት የስራ ሰዓትና ቀን ውጭ ወዴትም እንደማይሄዱ፣ ማረሚያ ቤቱም የፈለገውን እርምጃ መውሰድ እንደሚችል በመግለጽ እንደተቃወሙ ለችሎቱ አብራርተዋል። ጠበቃው እንዳሉት፣ ፍርድ ቤቱ ቀደም ሲል የሰጠው ትዕዛዝ ለምን እንደተጣሰ ለመመርመር ተነጋግሯል። ሆኖም ከዳኞቹ አንዱ በሕመም ምክንያት ባለመገኘታቸው፣ የችሎቱ ሙሉ አባላት ሳይገኙ ውሳኔ መስጠት እንዳልተቻለ ገልጸዋል። ዳኛው ከተመለሱ በኋላ ጉዳዩ እንደሚታይ እንደተነገራቸውም አክለዋል። የታሳሪ ቤተሰብ በበኩላቸው፤ የጎደለው ዳኛ ወደ ስራው እንደተመለሰ " ተነጋግረን በጠበቃችሁ በኩል ቀጠሮ እንሰጣለን ነው " ያለው እንጅ የቀጠሮው ቀን አልታወቀም ሲሉ ተናግረዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
Open in Telegramቤታችንን ጥለን ውጭ ብርድ ላይ ማደር ከጀመርን 5 ዓመት ሆኖናል ከአምስቱ ውስጥ ሦስቱ ዓመት በጣም የከፋ ነው ይኸው አሁን የጅምላ ጭፍጨፋው ላይ ደረስን፣ ድንጋይ ሲፈናቀል ከስሩ ያሉ ሚጢዎች(ጉንዳን) እንደሚታራመሱ ሁሉ ቁጥራቸው የማይታወቅ ገዳዮች በተኛንበት ሰፈሩብን
Open in Telegram"አምስት ሴቶች ነበርን እኔ ብቻ በሕይወት ተረፍኩኝ" ጥቅምት 14/2019ዓ.ም በሽርካ ወረዳ ጮሌ ቀበሌ ከተፈጸመው ጭፍጨፋ ተርፋ በ አሰላ ከተማ ህክምና እየተከታተለች ያለች ኦርቶዶክሳዊት ሴት @Mktv
Open in Telegramየኦርቶዶክሳውያን ቤቶች በእሳት ወድመዋል በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ በሶሌ ዲገሉ ቀበሌ ሌሊቱን ማለትም ኅዳር 15 ለ16/2019ዓ.ም በርካታ የኦርቶዶክሳውያን ቤቶች በእሳት ወድመዋል። አክራሪዎቹ አሁን ከነጋ የሶሌ የዲገሉ ና የሄላ ኮኔ ቀበሌዎች መገናኛ በሆነ ስፍራ ላይ እንደሚገኙ ከቦታው የደረሱኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ።እነዚህ ኀይሎች ያሉት ከወረዳው መቀመጫ ከጎቤሣ ከተማ ከ7ኪ.ሚ ርቀት ላይ ነው። ይኽን ኦርቶዶክስን የማጽዳት ሥራ ማስቆም ሲገባቸው ለአክራሪዎቹ ስልታዊ ድጋፍ የሚያደርጉ የወረዳው ባለሥልጣናት ስም ዝርዝር፦ ፩ አባስ አብዱሮ ~የወረዳው አስተዲዳሪ ፪ አወል~ የወረዳው ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ። ይኽ ሰው ከወረዳው ፓሊስ አዛዥ (በቅርቡ ተቀይሮ ሄዷል) ጋር በመሆን ባለፈው ለምን የሞቱትን አንስታችሁ ቀበራችሁ? ለምን ሚዲያ ላይ አወጣችሁ? ለምንስ አለቀሳችሁ ? በማለት በየቤቱ እየዞረ ኦርቶዶክሳውያንን ሲያስር የነበረ ሰው ነው ፎቶ፦ጥቅምት 14/2019ዓ.ም እዚያው ሽርካ ወረዳ ጮሌ ላይ የተቃጠሉ የኦርቶዶክሳውያን ቤቶች
Open in Telegramከአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የቀረበ የሰብአዊ ድጋፍ ጥሪ ሕዳር 13 ቀን 2019 ዓ. ም የወገን ጩኸት ይሰማን! የርኅራኄ እጃችንን እንዘርጋ! አፉብን በአሜሪካና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የአማራ ዲያስፖራ አባላትና የሰብዓዊነት ወዳጆች የአስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ጥሪ ያቀርባል! እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 28–29፣ 2026 | የCAAA አገር አቀፍ የኦንላይን የገንዘብ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፉብን) በአሜሪካ የአማራ ማህበራት ትብብር (CAAA) በኖቬምበር 28 እና 29፣ 2026 የሚያካሂደውን የሰብዓዊ ድጋፍ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን በሙሉ ድጋፍ በመቀበል፣ በአሜሪካና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የአማራ ዲያስፖራ አባላትን፣ ኢትዮጵያውያንን፣ የአማራ ሕዝብ ወዳጆችንና ሁሉንም ለሰብዓዊነት የቆሙ ወገኖች በዚህ የርኅራኄና የአጋርነት ዘመቻ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ አጥብቆ ጥሪ ያቀርባል። ወገኖቻችን በችግር ላይ ናቸው! የእናንተን የእርዳታ እጅ መዘርጋት ይፈልጋሉ! በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ሰብዓዊና ማህበራዊ ቀውስ ከማንኛውም ጊዜ በላይ የጋራ ትኩረትን፣ ርኅራኄንና ተግባራዊ ድጋፍን ይጠይቃል። በአፉብን ቁጥጥር ሥር ባሉ አካባቢዎች ጭምር፣ ማህበረሰቡ ከባድ የሰብዓዊና ማህበራዊ ችግሮችን እየተጋፈጠ ይገኛል። የተፈናቀሉ ቤተሰቦች፣ የምግብ እጥረት የሚሰቃዩ እናቶችና አባቶች፣ የመድኃኒትና የሕክምና እርዳታ የሚሹ ሕሙማን፣ ትምህርታቸው የተቋረጠ ሕፃናት፣ መጠለያ ያጡ ወገኖች፣ የኑሮ ምንጫቸውን ያጡ ዜጎችና በተለይም ለችግር ተጋላጭ የሆኑ አረጋውያንና ሕፃናት የእኛን ድጋፍ በእጅጉ ይሻሉ። በመሆኑም:- ሁለት ወሳኝ የሰብዓዊ ድጋፍ ቴሌቶን መርሃ ግብሮች 1. የCAAA አገር አቀፍ የኦንላይን የገንዘብ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን • ቀን፦ ኖቬምበር 28–29፣ 2026 • አካሄድ፦ በኦንላይን፣ በአሜሪካና በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ሊሳተፉበት በሚችሉ የሚዲያ መድረኮች • ዓላማ፦ በአማራ ክልል ለሚገኙ በችግር ላይ ላሉ ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ 2. በአካል የሚካሄድ የሰብዓዊ ድጋፍ ቴሌቶን • ቀን፦ ኖቬምበር 28፣ 2028 • ቦታ፦ አርሊንግተን፣ ቨርጂኒያ፣ አሜሪካ • አካሄድ፦ የአማራ ማህበራት፣ የማህበረሰብ መሪዎች፣ ደጋፊዎችና ሌሎች ተሳታፊዎች በአካል የሚገኙበት የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተዘጋጅተዋል። ወገኖቻችን በችግር ላይ ሲሆኑ እኛ በሩቅ ሀገር በሰላምና በምቾት እየኖርን የእነርሱን ስቃይ በዝምታ ማለፍ የለብንም። የአንድ ሕዝብ አንድነት የሚገለጠው በደስታው ጊዜ ብቻ ሳይሆን በመከራው ወቅት እርስ በርስ በመደጋገፍ ነው። ስለዚህ፣ አፉብን ሁሉም የአማራ ማህበራት፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ ባለሀብቶች፣ ባለሙያዎች፣ ወጣቶች፣ ተማሪዎችና በአሜሪካ የሚኖሩ የአማራ ወገኖች እያንዳንዱ በሚችለው አቅም የዚህ የሰብዓዊ ድጋፍ ዘመቻ አካል እንዲሆኑ ይጠይቃል። • በአቅማችሁ መጠን ድጋፍ አድርጉ። • የሚገኙበትን ማህበረሰብ አስተባብሩ። • ቤተሰብና ወዳጆቻችሁን አሳትፉ። • ቴሌቶኑን በሚዲያና በማህበራዊ ድረ ገጾች አስተዋውቁ። • በጊዜ፣ በእውቀትና በሙያችሁ ድጋፍ አድርጉ። ለዚህ ዘመቻ የምናደርገው አስተዋጽኦ የገንዘብ መጠኑ ብቻ ሳይሆን የወገንነት ስሜታችንና የሰብዓዊነት እሴታችን መገለጫ ነው። እያንዳንዱ ዶላር፣ እያንዳንዱ የድጋፍ መልዕክት፣ እያንዳንዱ የማስተባበር ጥረት ለተቸገሩ ወገኖቻችን ተስፋ ሊሆን ይችላል። እጃችንን በአንድነት እንዘርጋ፤ የምንችለውን ዛሬ እናድርግ። የሰብዓዊነት ጥሪ የሚጠይቀው ተግባር ነው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፉብን)
Open in Telegram📝 የአርሲ ምዕመናን እንባ 👉የአርሲ ሕዝበ ክርስቲያን ግድያ ዛሬም አልቆመም። ይህ ሁሉ እየሆነ ጳጳሱ በግልጽ ነግረውናል ፣ የሲኖዶሱ አባላት እየቻሉ መንግሥትን ፈርተው ዝምታ መርጠዋል አሉን ። እኛስ በውጭ ያለን ፣ ለምን አንድነት መፍጠር አቃተን ? 👉ከአርሲ የሚደርሱን መረጃዎች የግድያውን መቀጠል ያሳያሉ። የሚገደሉት ወገኖቻችን ናቸው። ከሞት የተረፉቱም ዛሬም በስጋት እና በጭንቀት ነገ ይገሉናል ብለው በሰቀቀን ሌሊት እና ቀኑን ያሳልፋሉ። ይህን እያወቁ፣ ዛሬ በውጭ የሚገኙ አገልጋዮች «መንግሥት ቅር ይለዋል፤ ወደ ሀገሬ መግባት አልችልም፤ ኢትዮጵያ ያፈራሁት ሀብትና ንብረት አለኝ» በሚል ስጋት ጥጋቸውን የያዙትን ቤት ይቁጠራቸው። የወገናችንን ሕይወት ከንብረታችንና ከጉዞ ስጋታችን በታች የምናስቀምጥ ከሆነ፣ ወገንነታችን ብሎም አገልጋይነታችን መቼ ይታያል? 👉 ግንባር ቀደም መቆም የሚገባን እኛ፣ የሃይማኖት መሪዎችና የመቅደሱ አገልጋዮች ነበርን። ይሁንና የምናየው ሌላ ነው። በሚያምር ስም የተለያዩ ማኅበራት ይመሠረታሉ። ጥቂት ቆይተው ይፈርሳል፣ አልያም ደብዛቸው ይጠፋል። አንድነት የለም። ኅብረት የለም። በውጭ ሀገር ተቀምጠን ለወገን በጋራ መቆም ሲገባን፣ የወገንን መከራ የግል ፉክክር አድርገው ዋንጫውን ብቻቸውን ለማንሳት የሚደክሙ አሉ። በወገን ሞት ለመነገድ የሚሯሯጡ፣ የአዞ እንባ እያነቡ በሐዘን ሰዓት ድንገት ብቅ ብለው የመድረኩ ዋና ተዋናይና ብቸኛ ተቆርቋሪ ለመምሰል የሚጥሩም አሉ። የወገን ደም የንግድ ሸቀጥ ሆኖ፣ የወገኖቻችን እንባ የዝና መወጣጫ ሆኖ መታየት የለበትም። 👉 መልክና ስም እየቀያየሩ ያንኑ አሠራር መድገም ችግሩን ማድበስበስ ነው። ሀቁ እና እውነታው ከመጀመሪያ ጀምረው ዓላማቸውን ሳይስቱ፣ አቋማቸውን ሳያዛቡ፣ ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን ድምፃቸውን ሲያሰሙ የቆዩ ግለሰቦችና ሚዲያዎች ተሰባስበው። ለሁሉም ቦታ የሚሰጥ ኅብረት ተፈጥሮ፣ በጋራ ምክክር፣ በግልጽ ዕቅድና በጸና መርሕ በየሀገሩ ወደ ሥራ መግባት ነው የሚገባው ። አልያ መሪው በማይታወቅበት፣ ውሳኔው በእጅ አዙር የሚተላለፍበት ስብስብ ረጅም መንገድ ሊያስኬደን አይችልም። ከሰልፍም አይዘልም ።።። 👉ያየነውን፣ የሰማነውን እንናገራለን። በአቋማችን ጸንተን፣ ዛሬም ለወገኖቻችን ድምፅ ሆነን እናገለግላለን። ፍትሕ ዛሬም ለአርሲ ሕዝበ ክርስቲያን 🙏 📍 ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ
Open in Telegramበደቡብ ወሎ ዞን በጃሪ ተፈናቃይ መጠሊያ ጣቢያ ላይ በደረሰው የድሮን ጥቃት የተፈናቀሉ ተፈናቃዮች በመካነ ኢየሱስ ተፈናቃይ ካምፕ ተደርበው እየኖሩ መሆኑ ተገለጸ፤ ከ1,600 በላይ ተፈናቃዮች ለከፋ ሰብዓዊ ችግር መጋለጣቸውንም ለአዲስ ማለዳ ገለጹ ሰኞ፣ ህዳር 14 ቀን 2019 ዓ.ም (#አዲስ_ማለዳ) በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ በጃሪ ተፈናቃይ ጣቢያ ተጠልለው የነበሩ እና ከሳምንታት በፊት የድሮን ጥቃት ተፈጽሞባቸው፣ በሀይቅ መካነ ኢየሱስ ተፈናቃይ ካምፕ ከሚገኙት ጋር ተደርበው የሚኖሩ ተፈናቃዮች የመጠለያ ጣቢያ አለመኖር ለተለያዩ ችግሮች እንደዳረጋቸው እና ሰብዓዊ ድጋፉ አነስተኛ መሆኑን አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው ነዋሪዎች ገለጹ። ቀደም ሲል በነበሩበት መጠለያ ጣቢያ በደረሰባቸው የድሮን ጥቃት ከ16 ሰዎች በላይ ሕይወታቸውን ሲያጡ ወደ 39 የሚጠጉት ደግሞ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የገለጹት ተፈናቃዮቹ፣ አደጋው የደረሰበትን ቦታ “ሙሉ ለሙሉ” ለቅቀው በመውጣት በሀይቅ ዙሪያ በሚገኘው መካነ ኢየሱስ ካምፕ ከነባር ተፈናቃዮች ጋር ተደርበው ለመኖር መገደዳቸውን ተናግረዋል። በዚህ የድሮን ጥቃት በርካቶች ተደናግጠው አካባቢውን ለቅቀው እየወጡ እንደነበር አዲስ ማለዳ መዘገቧ የሚታወስ ነው። አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻው ተፈናቃዮች የሚኖሩበት ሁኔታ ለሚዲያ መናገራቸው ለደኀንነታቸው እና ሊያገኙት የሚችሉት ጥቅማጥቅም ካለ እንዳይስተጓጎሉ በመፍራት ማንነታቸው እንዳይገለጽ በመጠየቃቸው ስማቸው አልተገለጸም። በአሁኑ ወቅት 1,600 በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮች በስፍራው እንደሚገኙ የገለጹት ነዋሪው ነባር ተፈናቃዮች መጠለያ ቢያገኙም አዲስ የገቡት ግን መጠለያና ቦታ ባለማግኘታቸው በባህር ዛፍ ስር ተጠልለው “በውርጭና በብርድ” እየኖሩ መሆኑን ተናግረዋል። ከጃሪ ተፈናቃዮች መካከል ለ250 ሰዎች በቀይ መስቀል በኩል ሸራ ቢሰጥም ቀሪው እና አብዛኛው ተፈናቃይ፣ አካል ጉዳተኞችንና ቁስለኞችን ጨምሮ፣ ኬንዳ(ሸራ) እየለበሱ ሜዳ ላይ ለመተኛት መገደዳቸውን ገልጸዋል። አክለውም ከመንግሥት የሚቀርብ ሰብዓዊ ረድኤት ባለመኖሩ፣ በቀን አንድ ጊዜ በምሳ ሰዓት ብቻ በበጎ አድራጊዎች የሚዘጋጅ ሩዝ፣ ዳቦ ወይም እንጀራ ብቻ እንደሚያገኙና “ቁርስም ሆነ እራት” እንደሌላቸው ተናግረዋል። ከቀድሞ መጠለያቸው ሲወጡ ንብረታቸው አንድም በመቃጠሉ በሌላ በኩል ደግሞ ትተው በመውጣታቸው ምክንያት በአሁኑ ወቅት አልባሳትም ሆነ ፍራሽ እንደሌላቸው ገልጸዋል። ተፈናቃዩ አክለውም “በብርድና በተጨናነቀ አኗኗር ሳቢያ” ተፈናቃዮቹ “ለጉንፋንና ለሳል” መጋለጣቸውን እንዲሁም አካባቢው በተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች የተሞላና ለኑሮ አስቸጋሪ መሆኑን አመልክተዋል። የአካባቢው ንፅህና መጓደልም ለጤና እክል እንደዳረጋቸው አንስተዋል። የተፈናቃዮች ኮሚቴ ችግሩን በተመለከተ እስከ ዞን ድረስ በመሄድ መጠለያና ቦታ እንዲሰጣቸው ቢያመለክትም እስካሁን ምላሽ አለማግኘቱንም የአዲስ ማለዳ ምንጮች ገልጸዋል። የሚመለከታቸው የወረዳና የዞን አመራሮች ወደ ክልል ስብሰባ መሄዳቸውንና ሲመለሱ መፍትሔ እንደሚሰጡ ቃል እንደገቡላቸው የሚጠቅሱት ነዋሪዎቹ፣ ችግራቸው እስኪፈታ ድረስ የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል። በሌላ በኩል በመጠሊያው ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርታቸው እንዳይስተጓጎል በሀይቅ ዙሪያ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንዲመቻችላቸው ተደርጎ የተወሰኑት ትምህርታቸውን መከታተል መጀመራቸው ታውቋል። አዲስ ማለዳ ከደቡብ ወሎ ዞን የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሙኒኬሽን መረጃ ለማግኘት ስልክ ደውላ መረጃውን ለመስጠት “አመራሩ ስብሰባ ላይ ነው እንጠይቅ” የሚል ምላሽ ሰጥዋት የነበረ ሲሆን፣ አመራሩን ከጠየቁት በኋላ “መረጃ በአካል እንጂ በስልክ መስጠት አንችልም” በማለታቸው ከመንግስት በኩል ያለውን ምላሽ ማካተት አልቻለችም። ኃላፊዎቹ ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ በሆኑበት አፍታ አዲስ ማለዳ ታስተናግዳለች፡፡ ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦ YouTube ➲ t.ly/vSgS Telegram ➲ t.ly/SOXU Facebook ➲ t.ly/flx8 Twitter ➲t.ly/mxA
Open in Telegram