🌎 በፀሐይ ባንክ ይቀበሉ! 💵 ከውጭ ሀገራት የሚላክልዎትን ገንዘብ በፀሐይ ባንክ በኩል ሲቀበሉ የተሻለ የውጭ ምንዛሬ ተመን ያገኛሉ፡፡ ደሃብሺል፣ ሪያ እና አልፋናው ፀሐይ ባንክ አብሯቸው የሚሠራ ዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ናቸው፡፡ 👉 የፀሐይ ባንክ ስዊፍት ኮድ:- TSCPETAA ፀሐይ ባንክ ለሁሉ! #TsehayBank #ForAll #Finance #Services #ForexService #Loan #IFB #Fajr
Open in TelegramPosts of Tsehay Bank
🌙 መልካም ጁምዓ! "ወዲዓ ኢድ" ከወለድ ነጻ የበዓል የቁጠባ ሒሳብ በፀሐይ ባንክ ይክፈቱ! ወደሚቀርብዎ የፀሐይ ባንክ ቅርንጫፍ በመሔድ ለእርስዎ የተዘጋጁ ከወለድ ነጻ የቁጠባ እና የፋይናንሲንግ አማራጮች ተጠቃሚ ይሁኑ! ፀሐይ ፈጅር ከዕሴትዎ የተጣጣመ! #TsehayBank #ForAll #IFB #Fajr #JummaMubarak
Open in Telegramየጥንቃቄ መልዕክት! ከባንክ ሒሳብዎ ጋር የተያያዘ ማንኛውም አይነት ማጭበርበር ወይም የማጭበርበር ሙከራ ሲያጋጥምዎ ለባንካችን ወዲያውኑ ያሳውቁን! አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የፀሐይ ባንክ ቅርንጫፍ ጎራ በማለት፣ በነጻ የጥሪ መስመራችን 921 በመደወል ወይም የባንካችን ይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች በመጠቀም ጥቆማዎን ያድርሱን፡፡ ፀሐይ ባንክ ለሁሉ!
Open in Telegramየጨረታ ማስታወቂያ! ፀሐይ ባንክ አ.ማ. ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ለማስታወቂያ አገልግሎት የተጠቀማቸውን ብዛት ያላቸውን ያገለገሉ (RHS) ብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ የንብረቶቹ ዝርዝር፦ ◆ የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ብረቶች ◆ የተለያዩ መጠን ያላቸው ቁርጥራጭ ማይካዎች ጨረታው በባንኩ የግዥ መመሪያ በተገለጸው የውስን ጨረታ ሒደት መሰረት የሚከናወን ሲሆን፣ ጨረታው ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት 9፡00 ተዘግቶ፣ በዛው ቀን ከሰዓት 9፡15 በባንኩ ዋና መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ፋሲሊቲ መምሪያ ውስጥ ይከፈታል፡፡ የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽሞ ንብረቶቹን መረከብ ይኖርበታል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ 👇 ስልክ ቁ. 0114706157 / 0114706033 (ሙሉ የጨረታው ማስታወቂያ ከላይ ተያይዟል፡፡) ፀሐይ ባንክ ለሁሉ!
Open in Telegramየቃል ፈተና ጥሪ! ፀሐይ ባንክ ለአዲስ አበባ ቅርንጫፎቹ በትሬኒ ባንከር የሥራ ዘርፍ ባወጣው ማስታወቂያ አመልክታችሁ፣ ሁሉንም መመዘኛዎች አሟልታችሁና ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መልቀቂያ ፈተና (National Exit Exam) ውጤታችሁ ከ85% በላይ የሆነ ከዚህ በታች ስማችሁ የተዘረዘረ አመልካቾች፤ ከስማችሁ ትይዩ ባለው ቀን እና ሰዓት በቅሎ ቤት አካባቢ መዓዛ ደሳለኝ ሕንጻ ላይ በሚገኘው የፀሐይ ባንክ ዋናው መሥሪያ ቤት በሚሰጥው የቃል ፈተና (Interview) ላይ እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡ በተጨማሪም የትውልድ ዓመታችሁን የሚገልፅ የልደት ካርድ ወይም የ8ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ የምስክር ወረቀት፣ የዲግሪ ሰርተፊኬት፣ የዲግሪ ውጤት (CGPA) እና የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውን ኮፒውን ይዛችሁ እንድትገኙ እናሳስበለን፡፡ ፀሐይ ባንክ ለሁሉ!
Open in Telegramትልቁ ይገባዎታል! "ዳይመንድ የቁጠባ ሒሳብ" በፀሐይ ባንክ ይክፈቱ! 💎 ከ 9.5% እስከ 10% የወለድ መጠን የሚያስገኝ ልዩ የቁጠባ ሒሳብ! አሁኑኑ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የፀሐይ ባንክ ቅርንጫፍ በመሔድ ዳይመንድ የቁጠባ ሒሳብ ተጠቃሚ ይሁኑ! ፀሐይ ባንክ ለሁሉ! #TsehayBank #ForAll #IFB #Loan #DiamondSavings
Open in Telegram📱 ለተቀላጠፈ የባንክ ፍላጎትዎ *921# የፀሐይ ሞባይል ባንኪንግ አለልዎ! 👉 ኢንተርኔት ኮኔክሽን አያስፈልገውም፤ 👉 በሁሉም ዓይነት የሞባይል ስልክ ላይ መጠቀም ይችላሉ፤ 👉 ቦታና ጊዜ አይገድብዎትም፤ 👉 ፈጣን እና ደኅንነቱ አስተማማኝ ነው፤ 👌 ለዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ፍላጎትዎ ፀሐይ ባንክ ይሁን ምርጫዎ! ፀሐይ ባንክ ለሁሉ! #TsehayBank #USSDBanking #MobileBanking #EasyBanking #DigitalBanking #BankingAtYourFingertips
Open in Telegram✝️ መልካም ሰንበት ይሁንልዎ! 💵 አስራት በኩራት የቁጠባ ሒሳብ በፀሐይ ባንክ ይክፈቱ! ከገቢዎ የሚፈልጉትን ያህል መጠን ለሚፈልጉት ቤተክርስቲያን ወይም ለማንኛውም ኃይማኖታዊ ዓላማ የሚለግሱበት የቁጠባ ሒሳብ አመቻችተናል! ፀሐይ ባንክ ለሁሉ! #TsehayBank #ForAll #SundayVibe #SeamlessBanking
Open in Telegramየአገልግሎት እና የግብይት ክፍያዎን በቀላሉ በፀሐይ QR ይፈጽሙ! Scan. Pay. Go! ከሁሉም ባንኮች ክፍያን ይቀበሉ፣ ወዲያው ክፍያዎን ይውሰዱ! የመክፈያ QR ኮዶችን ስካን በማድረግ ክፍያዎን በቀላሉ ይፈፅሙ! ፀሐይ ባንክ ለሁሉ!
Open in Telegram🌙 መልካም ጁምዓ! የሐጅ ጉዞዎን ዕውን ያድርጉ! "ወዲዓ ሐጅ" ከወለድ ነጻ የቁጠባ ሒሳብ በፀሐይ ባንክ ይክፈቱ! ወደሚቀርብዎ የፀሐይ ባንክ ቅርንጫፍ በመሔድ ለእርስዎ የተዘጋጁ ከወለድ ነጻ የቁጠባ እና የፋይናንሲንግ አማራጮች ተጠቃሚ ይሁኑ! ፀሐይ ፈጅር ከዕሴትዎ የተጣጣመ! #TsehayBank #ForAll #IFB #Fajr #JummaMubarak
Open in Telegramከፀሐይ ባንክ ጋር ይስሩ! ዘርፈ-ብዙ ጥቅም ያግኙ! አሁኑኑ ወደሚቀርብዎ የፀሐይ ባንክ ቅርንጫፍ በመሔድ የቁጠባ ሒሳብ ይክፈቱ! "ለሁሉ" በሆነው ፀሐይ ባንክ በመቆጥብ፣ ጠቀም ያለ ወለድ ያግኙ! ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑ ለእርስዎ የሚሆኑ የቁጠባ እና የፋይናንሲንግ አማራጮችን አዘጋጅተናል፡፡ ፀሐይ ባንክ ለሁሉ! #TsehayBank #ForAll #Services #Saving #Loan #IFB #Fajr #MobileBanking
Open in Telegram💎 ትልቁ ይገባዎታል! 💎 "ዳይመንድ የቁጠባ ሒሳብ" በፀሐይ ባንክ ይክፈቱ! ከ 9.5% እስከ 10% የወለድ መጠን የሚያስገኝ ልዩ የቁጠባ ሒሳብ! አሁኑኑ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የፀሐይ ባንክ ቅርንጫፍ በመሔድ ዳይመንድ የቁጠባ ሒሳብ ተጠቃሚ ይሁኑ! ፀሐይ ባንክ ለሁሉ! #TsehayBank #ForAll #IFB #Loan #DiamondSavings
Open in Telegramፀሐይ ባንክ አ.ማ. ከግዙፉ ፊቤላ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር ጋር የመግባቢያ ስምምነት ውል ህዳር 7 ቀን 2019 ዓ.ም ተፈራረመ፡፡ የመግባቢያ ስምምነቱ የሁለቱን ተቋማት የጋራ እድገት የሚያረጋግጥ እና ዘላቂና አስተማማኝ የባንክ አገልግሎት አጋርነት የሚመሰርት እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በስምምነቱ መሰረት ፀሐይ ባንክ ለፊቤላ ኢንዱስትሪ የምግብ ዘይት ፋብሪካ እና የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ማከፋፈያ የሽያጭ ማዕከላት አጠቃላይ የባንክ፣ የዲጂታል ክፍያ፣ የገንዘብ መሰብሰቢያ እና የደመወዝ አስተዳደር አገልግሎቶችን በከፍተኛ ብቃት የሚያቀርብ ይሆናል። ፀሐይ ባንክ ለፊቤላ ኢንዱስትሪ የተቀናጀ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት፣ የኮርፖሬት ኢንተርኔት ባንኪንግ እና የQR ክፍያ መፍትሔዎችን የሚያቀርብ ሲሆን፣ ይህም የፊቤላ ኢንዱስትሪ የዕለት ተዕለት የገንዘብ እንቅስቃሴዎቹን በቀጥታ (Real-time) እንዲከታተል የሚስችለው ነው፡፡ ስምምነቱ ፊቤላ ኢንዱስትሪ እና ፀሐይ ባንክ አ.ማ. ከዚህ ቀደም የጀመሩትን መልካም ግንኙነት ወደላቀ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የሚያሸጋግር መሆኑ ተገልጿል፡፡ ፀሐይ ባንክ ለሁሉ!
Open in Telegramየፀሐይ ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ተካሔደ፡፡ በጉባኤው ላይ የባንኩ የ2025/26 ሒሳብ ዓመት የሒሳብ ሪፖርት ለባለአክሲዮኖች የቀረበ ሲሆን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫም ተከናውኗል፡፡ ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ በዋና ዋና የአፈጻጸም መለኪያዎች እና በላቀ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ስኬታማ እንደነበር የቀረበው ሪፖርት ያሳያል። ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ አበረታች ትርፍ ያስመዘገበ መሆኑም ተገልጿል፡፡ በተጠናቀቀው ሒሳብ ዓመት የባንኩ አጠቃላይ ደንበኞች፣ የፈጅር ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ደንበኞች እንዲሁም የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ደንበኞች ቁጥር መጨመሩ ተመላክቷል፡፡ በሒሳብ ዓመቱ የባንኩ የተጣራ ብድርና ከወለድ ነጻ የፋይናንሲንግ አቅርቦት እድገት ማሳየቱ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡ የባንኩ አጠቃላይ ገቢ እድገት የታየበት ሲሆን በአጠቃላይ ወጪ አስተዳደር የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡም ተመላክቷል። ተለዋዋጭ በሆነው የሀገሪቱ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውጤታማ ለመሆን ከአዳዲስ መመሪያዎች ጋር አሠራሩን በማጣጣም በርካታ ጥረቶችን እያደረገ እንደሚገኝ የባንኩ የዳሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ አየነው ገልጸዋል። በዚህም ባንኩ አዲስ የሦስት ዓመት ኮርፖሬት ስትራቴጂ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረ ሲሆን ስድስት የትኩረት አቅጣጫዎችን በመለየት እየሠራ ይገኛል ብለዋል። ዘላቂ የቢዝነስ እድገት፣ ደንበኛ ተኮር አገልግሎት፣ ዲጂታላይዜሽን፣ የአሠራር ቅልጥፍና፣ ሪስክ አስተዳደር እና የሰው ሃብት ልማትና ተቋማዊ ባህል ባንኩ በትኩረት የሚሠራባቸው ጉዳዮች መሆናቸው ተገልጿል። ባንኩ የተከፈሉ አክሲዮኖችን በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለማስመዝገብ በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። ፀሐይ ባንክ ለሁሉ!
Open in Telegram