ያልሄድንባቸዉ መንገዶች ያላወቅናቸዉ እዉነቶች መኖር ስንጀምር ያላየችን እናት ደርሰንለት ያልመረቀን አባት ከኛ አልፈን የምናተርፋቸዉ ነፍሶች ሳቃችንን ማየት ያለባቸዉ ምቀኛዎች……… ገና አሉ……….. በኛ ፈጣሪ ሲመሰገን ድንቅ እኮነዉ ቆመዉ ሲሉ እንዴት ሆነላት ሲባባሉ እግዚአብሔር የሚጠራበት ስሙ የሚከብርበት ጐጆ ቀልሰን እኔ ና አንተ የምንኖረዉ የምናየዉ ህይወት አለን……….. ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ትዝታ ወልዴ✍️ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems
Open in TelegramPosts of የትዝታ ወልዴ ግጥሞች
አስሬ ሰአቴን እያየዉ እረፍዶብኝ ስጠዳደፍ እግሮቹን ወደኃላ አመሳቅሎ ፍልስስ ብሎ መሀል ቦሌ አስፓልቱ ላይ ሽር ብትን የሚሉትን መኪኖች ወይ ደሞ ህይወቱን ያያል (ልጅነት በራሱ ሙሉነት ነዉ አደል?) የኔ ልዑል ነፃነቱ ኡፍ🥹🥹🥹 ለዚ ፎቶ ወይ ግጥም ወይ ስም ስጡት ❤️ @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems
Open in Telegramጥርስ አለኝ ተብሎ ሲሳቅ አይዋልም አይን እንባ ስላለዉ አይዘረገፍም ለሚሳቅለት ሰዉ ለእንባም ቦታ አለዉ ለመዉቀስም ጊዜ ለመልስም ቀን አለዉ አንዳንዴም…………. ፈገግ ተብሎ በጥርስ ይለቀሳል እንባ እያወጡ በአይንም ይሳቃል የሚያዉቁትን ሁሉ ……. የታዘቡት ሁሉ………. አፍ ስላለ ብቻ አይዘከዘክም የጭንቅ የምጥ ቀን ዘላለም አይዘልቅም አንዳንዴም………. በዝምታ ብቻ የልብ ይተረካል አዉቀነዋል ያልነዉ ስንተነፍሰዉ ቀን ቀንን ሲወርሰዉ እድሜያችን ሲያበስለዉ ሚዛን ላይ ሲቀመጥ ከገለባ ይቀላል ያለወቅቱ ሲሆን ያስተዛዝበናል። ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ትዝታ ወልዴ✍️ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems
Open in Telegramየናቴ መቀነት አደናቅፎኝ የአስቴር ዘፈኗ አሳስቶኝ እንጂ እሮጬ የመጣሁ ናፍቀሀኝ አደለም ስርህ የተገኘዉ ሀጥያቴነህ አንተ ሳግኝ ሳቅፍህ ሳይህ ሀሴት አደርጋለሁ ትንሽ እቆይና ደሞ እፀፀታለሁ መጥፎ ሱስ……. ናፍቆት ሀጥያተኛ ደሞ ፅድቄ እኮነህ …… ጭልምልም ያለብኝ ዙርያዉ ገደል ሆኖ ሀጥያት አደል ታዲያ መጨላለም ደምኖ ሲያጡህ መኮስመን ሲያግኙህ መግነን ናፍቆት ፃድቅ…….. ለክፋም ለደጉም ፅድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም ሳያዩ ከመዋል ሳይሻል አይቀርም የት ነህ? ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ትዝታ ወልዴ✍️ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems
Open in Telegramትዝታ ወልዴ✍️ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
Open in Telegramአንተና እኔ የአሁን እድሜ ላይ ኗሪዎች ዛሬን አጥተን አሁን ነጥተን ለነገ አሳ አስጋሪዎች በደጉ ቀን ሳሉ ለክፉ ቀን ብሎ ስንቅን መለቃቀም ፍቅርን መጠርቀም። ደሞ………. ተፈቃቅረን ተፈላልገን ተብሰልስለን ………ደሞ ተፈራርተን ምናባቱን ፍርሀት ከሞት መቼ ይበልጣል አሁን ላይ ተዋዶ አሁን እንደሚ’ኖር እራሱስ መች ያዉቃል እዚሁ ላይ ተፋቅረን …………. አሁን እንደሚሞት ለነገ ሳናስቀር ……………ትእቢታችን ሰብረን ና እንታረቅና ነገ በኛ ይቅና ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ትዝታ ወልዴ✍️ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems
Open in Telegramከልቤ ላይ አንተን ማዉጣት ማለት…… ገቢዎች ሰምተዉኝ ያላመንኩበትን ጉዳዬን መቀልበስ ቀበሌ ገብቼ በደስታ መመለስ መርጌታ ከሚል ቻናሎች ላይ መዉጣት የተበደርኩትን ስመልስ በብቃት ከ crash ኤ ጋራ እራት እንደመዉጣት ለእናቴ በአደራ ሚስጢር እንደማዉራት አንተን መርሳት ለኔ…… አለቃዬን መዉደድ እብድ ሰዉ ማሳበድ ዛፍና ፓል መግጨት ተምሬ በድፍረት ያልፍልኛል ማለት እርሺኝ ብሎ ማሰብ……… ወፍ በእግሯ ስትሳብ ተኩላ በዉበት ሲሳብ ቴሌ በትክክል ሲያመጣልኝ ሂሳብ እኒህ ሁሉ ተቀይረዉ ምድር ቀዉጢ እስካልሆነች- አንተን መርሳት ዉዴ የሚቻል አደለም። ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ትዝታ ወልዴ✍️ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems
Open in Telegram''ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም'' ''ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ'' እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ። @tizitawolde_poems
Open in Telegramግጥሞቼን አሐዱ የሬዲዮ ጣቢያ (94.3) ላይ ወይም የራሳቸዉ YouTube ላይ በቀጥታ ይተላለፋል ከ 2 ሰአት ጀምሮ አቀርባለሁ ጠብቁኝ
Open in Telegramሰዉ ሰዉን ቢበድል ለአምላክ ይከሱታል የአምላክን መበ’ደል ለማን ይነግሩታል? @Tizitawolde_poems @Tizitawolde_poems
Open in Telegramድስት ግጣሙን ካላጣ እኔ ጭልፋ ነኝ ወይ? ሁሌ የምቀናዉ February ሲመጣ🤯 ❤️ ከቁም ነገር እንዳትቆጥሩት😄 ነገ 3:30 የመፅሀፋን ምርቃት እንዳትቀሩ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ @Tizitawolde_poems
Open in Telegram