Account

Posts of THIKVAH-ETHIOPIA ᴘᴀɪᴅ.ᴠᴇʀsɪᴏɴ

newest first

#22232Photo
Views69−86%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h25
3 h69
  1. After 1 hour25
  2. Total to date69
#22226Photo
Views75−84%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
1 h33
3 h75
  1. After 1 hour33
  2. Total to date75
#22225Poll
Views116−76%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
2 h83
4 h116
  1. After 6 hours116
  2. Total to date116
#22223Photo

ከሚኒስቴሩ ወይም ከክልል ትምህርት ቢሮ የጽሑፍ ፈቃድ ውጭ ማንኛውንም የመማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍ ማተምና ለንግድ ዓላማ ማዋል የሚከለክል መመሪያ ወጥቷል። (ቲክቫህ ኢትዮጵያ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በመማሪያና ማስተማሪያ መጽሐፍት ዝግጅት፣ ሕትመት፣ ስርጭትና አጠቃቀም ላይ ወጥ አሠራር ለመዘርጋት ያወጣው አዲስ አስገዳጅ መመሪያ ቁጥር 1163/2019 ይፋ ሆነ። በትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ የወጣው ይህ መመሪያ፣ በፌዴራልና በክልል የመንግሥትና የግል ትምህርት ተቋማት እንዲሁም በውጭ ሀገር በሚገኙ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል። በመመሪያው መሠረት ማንኛውም ተማሪ የተረከበውን የመማሪያ መጽሐፍ ቢያጣ ወይም ለመማር በማይችል ደረጃ ቢያበላሽ፣ ተመሳሳይ ይዘትና ጥራት ያለው አዲስ መጽሐፍ በምትክነት የማቅረብ አሊያም መጽሐፉ በወቅቱ የሚሸጥበትን የገበያ ዋጋ ከተጨማሪ 20 በመቶ አስተዳደራዊ መቀጫ ጋር የመክፈል ግዴታ ተጥሎበታል። ተማሪው የተጣለበትን ይህን ክፍያ ሳይፈጽም ወደ ሌላ ትምህርት ቤት ለመዛወር ቢፈልግ የዝውውር ሰነድ እንደማይሰጠው በመመሪያው በግልጽ ተቀምጧል። የአንድ የመማሪያ ወይም የማስተማሪያ መጽሐፍ መደበኛ የአገልግሎት ዘመን ቢያንስ ሦስት የትምህርት ዘመናት መሆኑን የሚደነግገው ይህ ሰነድ፤ በትምህርት ቤቶች አስተዳደር ቸልተኝነት ወይም አግባብ ባልሆነ አያያዝ ምክንያት ከአገልግሎት ዘመናቸው በፊት ከጥቅም ውጭ የሚሆኑ መጽሐፍት ተገቢውን አስተዳደራዊና ሕጋዊ ተጠያቂነት እንደሚያስከትሉ ያስጠነቅቃል። ትምህርት ቤቶች መጽሐፍቱን ለእያንዳንዱ ተማሪ በውልና በፊርማ በማስረከብ በዓመቱ መጨረሻ የመሰብሰብ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሲሆን፣ ወላጆችም ልጆቻቸው መጽሐፉን በአግባቡ መያዛቸውንና በዓመቱ መጨረሻ መመለሳቸውን የመከታተል ግዴታ አለባቸው። መመሪያው ለመደበኛ የትምህርት ዓይነቶች የመጽሐፍ እና የተማሪ ጥመርታ 1 ለ 1 (አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ) እንዲሆን የሚያስገድድ ሲሆን፣ ሚኒስቴሩ ከኅትመት መጽሐፍት ጎን ለጎን የተረጋገጡ መጽሐፍትን በዲጂታል ፎርማት (e-Book/PDF) በኦፊሴላዊ ድረ-ገጹ ላይ ለሕዝብ ክፍት እንደሚያደርግ አመላክቷል። በመንግሥት ትምህርት ቤቶች በነጻ እንዲሰራጩ የታተሙ መጽሐፍትን በገበያ ላይ መሸጥም ሆነ ከፈቃድ ውጭ ማባዛትና ዲጂታል ቅጂውን ለንግድ ዓላማ ማዋል በሕግ የሚያስጠይቅ ክልክል ተግባር መሆኑ ተደንግጓል። በዝግጅትና ሕትመት ረገድም ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የመማሪያ መጽሐፍ አዘጋጆች ቢያንስ ሁለተኛ ዲግሪና የአምስት ዓመት የሥራ ልምድ ሊኖራቸው እንደሚገባ ይጠይቃል። በተጨማሪም ከተቀመጠው የወረቀትና የጥረዛ ስታንዳርድ ውጭ የታተመ ማንኛውም የመጽሐፍ ስብስብ በሕትመት ድርጅቱ ወጪ ሙሉ በሙሉ እንዲደገም የሚደረግ መሆኑን መመሪያው ያስረዳል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ህዳር 19 ቀን 2019 ዓ/ም @thikvahethiopia.paid

Open in Telegram
Views191−60%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
3 h162
5 h191
  1. After 6 hours191
  2. Total to date191
#22222Photo
Views220−54%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h94
3 h220
  1. After 1 hour94
  2. Total to date220
#22220Photo
Views424−12%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
2 h323
4 h400
6 h424
  1. After 1 hour323
  2. After 6 hours424
  3. Total to date424
#22218Photo

" ከሀዋሳ ወደ ዳዬ በንሳ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተገልብጦ የ3 ሰዎች ሕይወት አልፏል " - ኢ/ር መለሠ ቡኑራ ‎ ‎በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በቦና ወረዳ ኦሎንሶ ሆሬ ቀበሌ ከሀዋሳ ወደ ወደ በንሳ መስመር በመጓዝ ላይ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 02166 የሆነ ኤፍኤስአር የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የ3 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የመንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር መለሠ ቡኑራ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ‎ ‎አደጋው የተከሰተው ከቀኑ 11 ሰዓት ገደማ ሲሆን በአደጋው የሁለት ሴቶችና የአንድ ወንድ ህይወት ማለፉን ገልጸዋል። ኢንስፔክተር መለሠ ጉዳት የደረሰባቸውን የተጎጂዎች ቁጥር ለመለየት ጥረት እየተደረገ ያለ መሆኑን አመልክተዋል። ጉዳት የደረሰባቸው በቦና አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ‎ ‎የአደጋው ትክክለኛ መንስኤ ያልተለየ ሲሆን የሞቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችልም መምሪያ ኃላፊው ገልፀዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ህዳር 19 ቀን 2019 ዓ/ም @thikvahethiopia.paid

Open in Telegram
Views453−6%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
2 h377
5 h431
7 h453
  1. After 6 hours453
  2. Total to date453
#22216Photo

" ችግሩ በሰላም አማራጭ እንዲፈታ ነው የምፈልገው፤ ግን በኔ ፍላጎት ብቻ አይሆንም። ምቹ ሁኔታ የለም " - የጎርካ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ⚠️" ሌላ ቦታ 40 ብር የሚሸጠው ሳሙና እንኳ በ3 እጥፍ ጨምሯል። ጉዳዩ ኑሮ እንዲቃወስ አድርጓል ! " በቀድሞ አደረጃጀት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ሶሮ ባርጉዳና ገላና ወረዳዎች የሚንቀሳቀሱ የ "ኦነግ ሸኔ" ታጣቂዎች ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ፣ ጎርካ ወረዳ ዘልቀው በመግባት ሰዎችን ይገድላሉ፣ ንብረት ይዘርፋሉ፣ ጥቃቱ አልቆመም ሲል ጥቃት የተደጋገመበት ወረዳው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል። ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት ! የወረዳው ዋና አስተዳዳሪው አቶ መልካሙ አስፋው እንደነገሩን፣ ከጥቅምት 1 እስከ ህዳር 16/2019 ዓ/ም ብቻ 11 ንጹሐን ሲገደሉ፣ 23 ተጎድተዋል፤ ከ200 በላይ እንስሳት ተዘርፈዋል፤ ለምርት የደረሰ በቆሎ፣ አደንጓሬ፣ የሙዝ እና የቡና ተክሎች ወድመዋል። 5,909 ወንዶች፣ 6,273 ሴቶች በድምሩ 12 ሺሕ 182 ሰዎች ከወረዳው ጀሎና ዶርባዴ ቀበሌዎች ተፈናቅለው ሸራ ላይ ተጠልለው እንደሚገኙም አክለዋል። ህዳር 16 እና 17 በጀሎ፣ ዳኖ፣ ጎልቤ ቀበሌዎች ህፃንን ጨምሮ ንጹሐን ላይ ሞትና የአካል ጉዳት መድረሱን፣ የአድማ ብተና አባላት ጥቃት ሲከላከሉ መሰዋታቸውን ገልጸው፣ የፌዴራል የጸጥታ አካላት ትኩረት አለመስጠት ችግሩ "እንዲባባስ እያደረገ" ነው፤ ታጣቂዎቹን "ሃይ የሚላቸው አካል የለም"፤ "ትላልቅ የቡድን መሳሪያ" የታጠቁ ናቸው ብለዋል። ለዓመታት የተዘጋው መንገድ ያስከተለው ችግር ! ህዝቡ ለንግድ እንቅስቃሴ የሚጠቀምበት ከኮሬ ዞን በምዕራብ ጉጂ አድርጎ ወደ ዲላ የሚወስደው የፌዴራል መንገድ በጸጥታ ችግር ለ11 ዓመት መዘጋቱን፣ እንዲከፈት ለበላይ የመንግስት አካላት በተደጋጋሚ አቤት ቢባልም መፍትሄ አለመገኘቱን አስተዳዳሪው ነግረውናል። የኮሬ ነጋዴ በትራንስፖርት ጭማሪ ከገበያ ለመውጣት መገደዱን፣ የተወሰኑ የበረቱ የሚያስገቧቸው የፍጆታ ምርቶችም ከዲላ አንፃር ዋጋቸው በ3 እጥፍ መጨመሩን አክለዋል። ነጋዴዎች ዲላ የሚጓዙት፣ ቡርጂን፣ ኮንሶን፣ ጋርዱላን፣ ጋሞን፣ ወላይታን ዞረው በመሆኑ ከተዘጋው መንገድ ጋር ሲነጻጸር ትራንስፖርቱ በሺሕ ብር የሚቆጠር ጭማሪ እንዳለው አስረድተዋል። የምርት ዋጋ ጭማሪ መኖሩን ገልጸው፣ ለአብነትም ሌላ ቦታ 40 ብር የሚሸጠው ሳሙና እነርሱ ጋር በሦስት እጥፍ መጨመሩን፣ የጸጥታው ችግር ኑሮው እንዲቃወስ ማድረጉን ተናግረዋል። ችግሩ በውይይት እንዳይፈታ ያደረገው ጉዳይ ! የጎርካ ወረዳ አስዳዳሪ፣ "እንደ ወረዳ አስተዳዳሪ ችግሩ በሰላም አማራጭ እንዲፈታ ነው የምፈልገው፤ ነገር ግን የሰላም አማራጩ በኔ ፍላጎት ብቻ አይሆንም። ለሰላም አማራጭ ምቹ ሁኔታ የለም" ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ችግሩ ከ10 ዓመታት በላይ መዝለቁን፣ በተለይ ዘንድሮ ግን እየተወሳሰበ እንደመጣ፣ በሁለቱ የጉጂ ወረዳ ባሉ ቀበሌዎች "የፈለገውን እያደረገ ያለው ሸኔ" በመሆኑ፣ ከስፍራው የመንግስት አመራሮች ጋር ተወያይቶ ችግሩን መፍታት እንዳልተቻለ አስረድተዋል። የ"ሸኔ" እንቅስቃሴ ባይኖር የአመራሮች ኮሚቴ በማቋቋም ችግሩን መፍታት እንደሚቻል አስገንዝበው፣ "በኦሮሚያ ክልል በኩል በህዝቡ ውስጥ እየኖረ ያለው ታጣቂ ቡድን ቀጠናውን እንዲለቅ ከማድረግ አንጻር አይቶ መተው ሁኔታ በተጨባጭ ይተስተዋላል" ብለዋል። የፌዴራል መንግስት ጣልቃ ገብቶ ጥቃቱን እንዲያስቆም አሳስበዋል። የክልሉ ምክር ቤት አባል ምን አሉ? የኮሬ ህዝብን ወክለው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዴያሞ ዳሌ በሰጡን ቃል፥ በጎርካ ወረዳ ከትናንትና በስቲያ ጥቃት ተከፍቶ የሰው ህይወት ማለፉን፥ በዛው ዕለት ምሽት ላይ ተኩስ እንደነበር ገልጸው፣ "አርሶ አደሩ የግብርና ስራ መስራት አልቻለም። አካባቢው የጦር ግንባር ነው የሆነው" ሲሉ ተናግረዋል። ጥቃቱም የሚያቆስም ወጥ መፍትሄ ላይ እንዳልተሰራ፥ እርቅ ቢደረግም በፖለቲከኞች መካከል እንጅ ተጎጂዎችን ያካተተ ባለመሆኑ ጥቃቱ እንደሚያገረሽ ተናግረው፥ ጥቃቱ የሚከፈተው በአንድ በኩል፥ በሁለቱም ወገኖች ባለ "የወሰን ይገባኛል" ጥያቄ፤ በሌላ በኩል በ "የሸኔ" እንቅስቃሴ ሆኖ እንደሚስተዋል አስረድተዋል። የድንበር ጭቅጭቅ እንዴት እና የት ነው የሚፈታው ? የሚል ነገር መወሰን፤ በፍርድ ቤት የሚፈታበት ስርዓት መፍጠር፣ የተጎጂ ቤተሰቦችን አቀራርቦ ይቅር ማባባልና እንዲካካሱ ማድረግ፥ ተጎጂዎችን መልሶ ማቋቋም መፍትሄ ሊያመጣ እንደሚችል ጠቁመዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ህዳር 19 ቀን 2019 ዓ/ም @thikvahethiopia.paid

Open in Telegram
Views411−15%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
2 h346
5 h391
7 h411
  1. After 6 hours411
  2. Total to date411
#22212Photo

በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በዚህ ዓመት በዲጂታል ቴክኖሎጂ እንደሚተሳሰሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) 5ኛውን ዙር ብሔራዊ የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም 1,140 ታዳጊዎችንና ወጣቶችን በማስመረቅ አጠናቋል። ተመራቂዎቹ ለአንድ ወር ያክል በስድስት የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የተሰጠውን የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠና በመከታተል ያጠናቀቁ ናቸው። በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በዚህ ዓመት በኢንተርኔት (ሳይበር) ተሳስረው የዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት እና የዲጂታል ላቦራቶሪ ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችል መርሐ-ግብር መያዙን አስታውቀዋል። ፕሮፌሰር ብርሃኑ አክለውም የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን በተወሰኑ የከተማ ትምህርት ቤቶች ብቻ ከመገደብ ይልቅ በመላው አገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች እኩል የቴክኖሎጂ ዕድል እና ተደራሽነት እንዲያገኙ ማድረግ የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ መሆኑን ገልጸዋል። ቴክኖሎጂ እያስከተለ የሚመጣውን አደጋ ለመከላከልና አገራዊ ህልውናን ለማስጠበቅ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል በፍጥነትና በብዛት ማፍራት ወሳኝ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል። በመርሐ-ግብሩ ላይ የኢመደአ የሳይበር ልሕቀት ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ቢሻው በየነ ባቀረቡት ሪፖርት የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ የሀገሪቱን የሳይበር ደህንነት አቅምና ዲጂታል ሉዓላዊነት ለማጠናከር ብቁ የሰው ኃይልን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማፍራት የተቀረጸ ሀገራዊ የተሰጥኦ ልማት መርሐ-ግብር መሆኑን አብራርተዋል። በ5ኛው ዙር ፕሮግራም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገቡ 14,646 ታዳጊዎችና ወጣቶች መካከል በተለያዩ የብቃት ምዘናዎች የተሻለ ውጤት ያመጡ ሰልጣኞች ተመርጠው በስድስት ዩኒቨርሲቲዎች ለአንድ ወር ያህል የንድፈ ሐሳብና የተግባር ስልጠና መውሰዳቸው ተገልጿል። ስልጠናው በሳይበር ደህንነት፣ በሶፍትዌር ልማት፣ በኢምቤዲድ ሲስተም እና በኤሮስፔስ ቴክኖሎጂዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ ሰልጣኞችን በቴክኒካዊ ክህሎት፣ ራስን በማወቅና በሥነ-ምግባር በማነጽ ሁለንተናዊ ብቃትና ሀገራዊ ስብዕና እንዲላበሱ ማድረጉ ተመላክቷል። በመጨረሻም አቶ ቢሻው ተመራቂዎቹ በካምፑ ያገኙትን እውቀትና የፈጠራ ፕሮጀክቶች ወደ ሀገር በቀል ምርትና አገልግሎት በመቀየር ለሀገራቸው ልማትና ዲጂታል ሉዓላዊነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ህዳር 19 ቀን 2019 ዓ/ም @thikvahethiopia.paid

Open in Telegram
Views400−17%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
2 h331
5 h381
7 h400
  1. After 6 hours400
  2. Total to date400
#22209Video
Views356−26%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#22207Photo

🇨🇳 ሙሰኞችን እስከ #ሞት የምትቀጣው ቻይና ! በሙስና የተከሰሱት የቀድሞ የቻይና ባለስልጣን የሁለት ዓመት ገደብ ያለበት የሞት ፍርድ ተፈረደባቸው። • ያላቸው ንብረት ሁሉ ይወረሳል። የቀድሞው የቻይና ጓንግዚ ግዛት አስተዳዳሪ ላን ቲያንሊ፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ጉቦ በመቀበል ወንጀል በሁናን ግዛት በሚገኝ ቻንግዴ የህዝብ ፍርድ ቤት የሁለት ዓመት እገዳ ያለበት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸዋል። የ64 ዓመቱ ባለስልጣን ከ2008 እስከ 2025 ባሉት ዓመታት ውስጥ ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀም ለግለሰቦችና ለድርጅቶች ፦ - የንግድ ስራዎችን፣ - የፕሮጀክት ኮንትራቶችን - የሹመት ዕድሎችን በማመቻቸት ከ587 ሚሊዮን ዩዋን በላይ የሚያወጣ ገንዘብና ውድ ስጦታዎችን በጉቦ መልክ ተቀብለዋል። ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ የፈጸሙት ሙስና በሀገርና በህዝብ ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ የሞት ቅጣት የሚያስከትል ቢሆንም ፍርዱ ወዲያውኑ እንዳይፈጸም ወስኗል። ለዚህ ምክንያት የሆነው ላን ቲያንሊ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ወንጀላቸውን በግልጽ በማመናቸው፣ መርማሪዎች ያልደረሱባቸውን ሌሎች የሙስና ጉዳዮች በፈቃደኝነት በማጋለጣቸው እና በህገ-ወጥ መንገድ ያገኙትን አብዛኛውን ገንዘብና ንብረት በጸጸት በመመለሳቸው ነው። በሁለት አመቱ ጊዜ ውስጥ ሌላ አዲስ ወንጀል ካልፈጸሙ ወይም የእስር ቤትን ህግ በከፍተኛ ሁኔታ ካልጣሱ የሞት ፍርዱ ቀርቶ እድሜ ልክ ይታሰራሉ ፤ ነገር ግን ወደፊት ምንም ዓይነት ይቅርታም ሆነ በአመክሮ የመፈታት ዕድል አይኖራቸውም። በእርስ ቤት አንዲት ወንጀል ከፈጸሙ ግን በቀጥታ ወዲያው የሞት ፍርዱ ይፈጸምባቸዋል። ከዚህ ባለፈ ያላቸው ንብረት ሁሉ ይወረስባቸዋል። ላን ቲያንሊ ረጅም የስልጣን ዘመናቸውን በጓንግዚ ክልል በተለያዩ ከፍተኛ የአመራር እርከኖች ያሳለፉ ሲሆን ከ2021 ጀምሮ ደግሞ የክልሉ ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ሆኖም ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ በሙስና ተጠርጥረው ምርመራ ከተጀመረባቸው በኋላ ከፓርቲ አባልነታቸውና ከመንግስት ስልጣናቸው ተባረው ክስ ተከፍቶባቸው አሁን የሁለት ዓመት እገዳ ያለበት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸዋል። ቻይና፣ ከፍተኛ ባለስልጣናትንም ሆነ ዝቅተኛ ሰራተኞችን በእኩል የመምታት ጥብቅ የፀረ-ሙስና ዘመቻ አካሄድን ትከተላለች። በሙስና የተዘፈቁ አመራሮችን ከስልጣን ከማባረር ጀምሮ እስከ ዕድሜ ልክ እስራትና የሞት ቅጣት የሚደርስ ምህረት የለሽ እርምጃ ነው ሀገሪቱ የምትወስደው። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ህዳር 18 ቀን 2019 ዓ/ም @thikvahethiopia.paid

Open in Telegram
Views209−57%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#22202Photo

የ200 ዓመት እስራት የተፈረደበት ራሱን " ፓስተር " ብሎ የሚጠራው ፖል ማኬንዚ በሌሎች 123 ሰዎች ሞት ዳግም ጥፋተኛ ተባለ። የኬንያ ፍ/ቤት የሃይማኖት መሪውን ፖል ማኬንዚን (ራሱን ፓስተር ብሎ ይጠራል) በተጨማሪ 123 አዋቂ ተከታዮቹ ሞት ዛሬ ዓርብ ጥፋተኛ ብሎታል። የሞምባሳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፖል ማኬንዚን " የዓለም ፍጻሜ ደርሷልና ጹሙ መንግሥተ ሰማያት ትገባላችሁ ፤ ከኢየሱስም ጋር ትገናኛላችሁ " በሚል 123 አዋቂ ተከታዮቹን በረሃብ እንዲሞቱ በማድረግ ጥፋተኛ ብሎታል። ከማኬንዚ በተጨማሪ ባለቤቱን ሮዳ ማዌውን ጨምሮ ሌሎች 29 ተከሳሾች በዚሁ ወንጀል ጥፋተኛ ሲባሉ፣ 60 ተከሳሾች ደግሞ በነፃ ተሰናብተዋል። ይህ በሻካሆላ ጉዳይ በማኬንዚ ላይ የተላለፈ የመጨረሻው የጥፋተኝነት ውሳኔ ሲሆን ለዚህኛው ወንጀል የሚጣልበት ተጨማሪ ቅጣት ወደፊት ይወሰናል ተብሏል። ከሳምንታት በፊት190 ሕፃናትን እና አንድ አዋቂን " ሆን ብሎ በመግደል " ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ የ200 ዓመት እስራት ተፈርዶበታል። ከ2021 እስከ 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ በኬንያ የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ በሚገኘው የሻካሆላ ጫካ ውስጥ በተፈጸመው በዚህ ድርጊት ከ400 በላይ አስከሬኖች ተገኝተዋል። ፍርድ ቤቱ እንዳረጋገጠው፣ ማኬንዚ ተከታዮቹ በረሃብ የሚሞቱበትን ቅደም ተከተል አውጥቶ ነበር። በዚህም መሠረት በመጀመሪያ ሕፃናት፣ ቀጥሎ ሴቶች፣ በመጨረሻም ወንዶች እንዲሞቱና እሱ ራሱ ከሁሉም በኋላ ሕይወቱን ለማጣት አቅዶ ነበር። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ህዳር 18 ቀን 2019 ዓ/ም @thikvahethiopia.paid

Open in Telegram
Views900+86%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
8 h355
24 h900
  1. After 24 hours900
  2. Total to date900
#22200Photo

" ... መታወቂያቸውን ጠይቁ መታወቂያው ላይ ያለውን ባርኮድ በስልክ ስካን በማድረግ ትክክለኛ ማንነታቸውን አረጋግጡ " - ገቢዎች ቢሮ " የገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች ነን " በሚል ስም የንግድ ተቋማትን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ በቱሉ ዲምቱ ወረዳ በንግድ ቤቶች በመዞር " ያለደረሰኝ ግብይት ፈጽማችኋል " በሚል 100 ሺህ ብር ቅጣት እንደሚጣልባቸው በመግለጽ፣ ቅጣቱን ለመንግስት ከመክፈል ይልቅ ለእነሱ 50 ሺህ ብር እንዲከፍሉ በመጠየቅ ሲያጭበረብሩ ነበር። ግለሰቦቹ እውነተኛ ማንነታቸውን በመደበቅና ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት ወንጀሉን ሲፈጽሙ መቆየታቸው ተገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ አቶ ምትኩ ጋዲሰ በሐሰተኛ ስም አየለ ጥላሁን፣ እንዲሁም አቶ ጌታሁን ደቻሳ በሐሰተኛ ስም አድማሱ ከበደ በሚል ማንነታቸውን በመቀየር የሐሰት መታወቂያ ተጠቅመው ሲያጭበረብሩ በንግዱ ማህበረሰብ ጥቆማ ነው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት። በተጠርጣሪዎቹ እጅ የገቢዎች ቢሮ ሰራተኛ መሆናቸውን የሚያሳይ ሐሰተኛ መታወቂያ ብቻ ሳይሆን የመሬት ባለሙያ መሆናቸውን የሚገልጽ ሌላ ሐሰተኛ መታወቂያም መገኘቱን ተገልጿል። ከዩኒፎርም ውጪ ቁጥጥር የሚያካሂዱ የገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች ባርኮድ ያለው መታወቂያ የሚይዙ በመሆኑ፣ ግብር ከፋዮች መታወቂያቸውን በመጠየቅና ባርኮዱን በስልክ ስካን በማድረግ ትክክለኛ ማንነታቸውን እንዲያረጋግጡ ከገቢዎች ቢሮ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። የንግዱ ማህበረሰብ በገቢዎች ቢሮ ስም የሚፈጸሙ ማጭበርበሮች ሲያጋጥሙት ለፀጥታ አካላት ወይም ለቢሮው በተዘጋጀው 7075 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ መስጠት ይችላል ተብሏል። ህዳር 18 ቀን 2019 ዓ/ም @thikvahethiopia.paid

Open in Telegram
Views976+102%vs avg
Forwards—
Reactions3
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
14 h805
26 h976
  1. After 24 hours976
  2. Total to date976
#22196Photo
Views880+82%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
14 h732
26 h880
  1. After 24 hours880
  2. Total to date880
#22195Photo
Views864+79%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
15 h716
26 h864
  1. After 24 hours864
  2. Total to date864
#22193Photo
Views899+86%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
Views growthHide views growth

Views growth

Hours after publication

Show as table
Hours after publicationViews
0 h0
15 h757
24 h899
  1. After 24 hours899
  2. Total to date899
#22191Photo

10 ሚሊዮን ዶላር የተበጀተለት "ካማ" (KAMA) ፕሮጀክት እንዴት ይሰራል ? (ቲክቫህ ኢትዮጵያ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) በስምንት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ለተለዩ 21 ችግሮች መፍትሔ የሚያመጡ ሥራ ፈጣሪዎችን የሚያሳትፍና 10 ሚሊዮን ዶላር የተበጀተለት "ካማ" (KAMA) ፕሮጀክት ይፋ አደረገ። የሆልዲንጉ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ታዬ በሰጡት መግለጫ፣ ፕሮግራሙ የተነደፈው የልማት ድርጅቶቹ "ይህ ተግዳሮት አለኝ፤ በስታርታፖች፣ በሥራ ፈጣሪዎችና በወጣቶች እንዲፈታልኝ እፈልጋለሁ" በሚል ባቀረቡት የችግር ማብራሪያ ላይ ተመሥርቶ መሆኑን አስረድተዋል። እነማን መሳተፍ ይችላሉ ? ጥሪው በየትኛው ደረጃ ላሉ ሥራ ፈጣሪዎች ነው ? ዶ/ር ብሩክ ፕሮጀክቱ ስታርታፖችን በመጠን እንደማይከፋፍል ገልጸው፣ "ትንሽ እና ትልቅ ብለን አይደለም ስታርታፖቹን ዲፋይን ያደረግናቸው። ለኛ ማንኛውም አይዲያ ትልቅ ነው" ብለዋል። አክለውም፥ "ማንኛውም ሰው ብሪፉን (የተለዩትን ችግሮች) ሲመለከት የሚጠይቀው 'ይህንን መፍታት እችላለሁ ወይስ አልችልም፤ ከቻልኩስ በምን መንገድ?' የሚለውን ነው። የስታርታፑ ትልቅ መሆን ወይም ትንሽ መሆን አይደለም ዲተርሚን የሚያደርገው። ስለዚህ ለሁሉም እኩል ክፍት ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ሂደቱ ምን ይመስላል ? ለመጀመሪያው ዙር ለተለዩት 21 ችግሮች የመፍትሔ ሐሳብ ያላቸው ሥራ ፈጣሪዎች፣ የተሟላ ፕሮቶታይፕ ወይም የተጠናቀቀ መፍትሔ ማቅረብ አይጠበቅባቸውም። ማመልከቻቸውን አሟልተው የተመረጡት በድርጅቶቹ ውስጥ ሦስት ደረጃዎችን የሚያልፉ ሲሆን እነዚህም፥ የ4 ሳምንት የልምድ ልውውጥና ትውውቅ፣ የ12 ሳምንት የጋራ ልማት (Co-development) እና የ3 ወር ወደ ንግድ ሥራ የማሸጋገር (Commercialisation) ሂደት ያካትታል። ዶ/ር ብሩክ እንዳሉት፥ የፕሮጀክቱ ግብ፣ በአንድ ዓመት ውስጥ ሐሳቡን ኢንኪዩቤት አድርጎ፣ አነስተኛ አዋጭ ምርት (MVP) ፈትሾ፣ ለኢንቨስትመንት ዝግጁ ምርት ማውጣት ነው። ኤ.ኤል.ኤክስ (ALX) በፋይናንስ፣ በስትራቴጂና በገበያ ክፍተት ያለባቸውን ስታርታፖች በቅርበት ለመደገፍ የፕሮጀክቱ አጋር ሆኖ ተመርጧል። ለሥራ ፈጣሪዎቹ የሚሰጠው ገንዘብ ብድር ነው ? ዶ/ር ብሩክ ገንዘቡ እርዳታም ሆነ ብድር እንዳልሆነ በመግለጫቸው አስምረውበታል። "ድጋፍ አይደለም፣ እርዳታ አይደለም፣ ብድር አይደለም። እኛ ያዋጣል ብለን ካመንንበት ኢንቨስት የምናደርገው ነው፤ ለዚያም ሪተርን እንጠብቃለን" ብለዋል። "ይህን ያህል ፐርሰንት ኢኩቲ እንፈልጋለን" የሚለው በየሐሳቡ እንደሚወሰን በመጥቀስም፣ ሆልዲንጉ በመፍትሔዎቹ ውስጥ ድርሻ እንደሚኖረው አመልክተዋል። 10 ሚሊዮን ዶላሩ እስከመቼ ነው ? 10 ሚሊዮን ዶላሩ ለዚህ ዓመት ብቻ የተመደበና የEIH መዋጮ ብቻ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ብሩክ፤ ለቀጣይ ዓመት እንደ ሁኔታው እንደሚጨምርና ሌሎች ኢንቨስተሮችም ፍላጎት ማሳየታቸውን ነው የጠቆሙት። ፈንዱ በስታርታፕ አዋጁ ከተቀመጠው የስታርታፕ ፈንድ ጋር እንደማይገናኝ፣ እሱ ራሱን የቻለ ማዕቀፍ መሆኑንና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚተገብርበትን መንገድ እየሠራ እንደሆነ አስረድተዋል። እንዴት ማመልከት ይቻላል ? ከዛሬ ጀምሮ አመልካቾች እስከ ታኅሣሥ 29 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በፕሮጀክቱ ድረ-ገጽ kama.et በኩል ማመልከት ይቻላል ተብሏል። የምርጫ መስፈርቶቹ፣ ማለትም ምን ዓይነት ሰነዶች፣ ልምድና ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ በማመልከቻው ላይ በግልጽ መቀመጡን በመግለጬቸው ተጠቅሷል። አመልካቾችን የሚመዘኑት ለዚሁ ፕሮጀክት በተቋቋመው የEIH ፓናል ሲሆን፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችም በሂደቱ ይሳተፋሉ ተብሏል። ሥራ ፈጣሪዎች በዋናነት ምን ያስፈልጋቸዋል ? ለዚህ ጥያቄ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ የሰጡት ዶ/ር ብሩክ "ትልቅ ድራይቨር የሚሆነው ችግሩን የመፍታት አቅም ነው። እኔ ይህ ችግር ኤክስ ነው ብዬህ አንተ ዋይ የሚሆን ሶሉሽን ብትሰጠኝ አይሆንልኝም። ኤክስን የምትፈታ ከሆነ ሳልወድ በግድ ካንተ ጋር መሥራት እገደዳለሁ"  ብለዋል። ስለዚህ አመልካቾች ድርጅቶቹ "የተቸገርነው በዚህ ነው" ብለው ባስቀመጡት ችግር ላይ በማተኮር፣ በፈጠራ መንገድ እንዴት እንደሚፈቱት ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል። 📷 ሙሉ መግለጫው https://youtu.be/SRgheitewoc @thikvahethiopia.paid

Open in Telegram
Views1,020+111%vs avg
Forwards—
Reactions6
Comments—