Account

Posts of Techtonic Tribe

newest first

#1466Photo

Forwarded from DBU Daily News

5ኛው ዙር የሳይበር ታለንት የሰመር ካምፕ ስልጠና ምረቃ ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል። በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀው 5ኛው ዙር የሳይበር ታለንት የሰመር ካምፕ (Cyber Talent Summer Camp) የምረቃ ስነ-ስርዓት በአዲስ አበባ በድምቀት  እየተካሄደ ይገኛል። በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ፕሮፌሰሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ «መመረቅ ማለት የትምህርት ማብቂያ ሳይሆን የላቀ ጥረት መጀመሪያ ነው» በማለት፤ ተመራቂዎች አለማችን ያለችበትን እጅግ ፈጣን የቴክኖሎጂ ሽግግርና ለውጥ ከግምት ውስጥ በማስገባት ራሳቸውን በየጊዜው በዕውቀትና በክህሎት ማብቃት እንዳለባቸው አሳስበዋል። ስልጠናው በሀገራችን በሚገኙ 6 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፦ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ስልጠናቸውን በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቁ 1,140 ሰልጣኞች ዛሬ ተመርቀዋል። በፕሮግራሙ ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ሌሎችም የእውቅና ሰርትፍኬት ተበርክቶላቸዋል። @DBU11 @DBU111

Open in Telegram
Views189−49%vs avg
Forwards—
Reactions1
Comments—
#1464Photo
Views264−28%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#1457Photo
Views524+42%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—