Forwarded from መርከዙል ሁዳ
የጋዛ ሰርጎች… ከሥቃይ መካከል የሚወለድ ደስታ! 🤍 በጋዛ የሠርግ ደስታ የተለየ ታሪክ አለው። እልልታ ከሐዘን ድምፅ ጋር ተቀላቅሎ፣ የድንኳኖችና የፈራረሱ ሕንፃዎች ጥላ እንኳን በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውን የደስታ ብርሃን ሊያጠፋው ባልቻለበት ምድር፣ ሠርጎች የተለየ ትርጉም አላቸው። የሚወዷቸውን ቢያጡም ይጋባሉ፤ ቁስላቸው ባይድንም ፈገግ ይላሉ፤ በትንሽ አቅምና በቀላል ዝግጅት ደስታቸውን ያከብራሉ። ይህም ለዓለም የሚነግሩት መልእክት አለ፦ እኛ ሕይወትን የምንወድ ሕዝቦች ነን፤ ሐዘንም ቢሆን ከልባችን ውስጥ ተስፋን ሊነጥቅ አይችልም!ኀ በጋዛ ምናልባት ሙሽሮቹ ያጌጠ የሠርግ አዳራሽ፣ ውድ ልብስና እንደተለመደው በቂ ድግስ ላያገኙ ይችላሉ፤ ነገር ግን ሕይወት አሁንም ዋጋ እንዳላት፣ ተስፋም ፈጽሞ እንደማይሞት የሚያምኑ ልቦችን ያገኛሉ። يا رب، كما أتممت فرحتهم وسط الألم، أتمم فرحة غزة بالنصر والسكينة والأمان، واجعل أيامها القادمة أفراحًا لا يعقبها حزن، وبيوتًا لا يسكنها إلا السلام. https://t.me/al_gaziyah
Open in Telegram