Account

Posts of የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

newest first

#10202Text

በቢድዓዎች መካከል ልዩነት አለማድረግና ሁሉንም እኩል ማየት የሰለፍን መንሀጅ ይቃረናል፤ ከነርሱም ጋር ሊኖረን የሚገባ ሙዓመላ (አያያዝ) እንደ ደረጃው መሆን አለበት። የቢድዓ ባለቤቶች በቢድዓቸው ልዩነት እንዲሁም ከሐቅ ባላቸው ቅርበት ወይም ርቀት ይለያያሉ፤ በዚህም ምክንያት ከእነሱ ጋር ያሉ አቋሞች እና ከእነሱ ጋር የሚደረግ መስተጋብር(ሙዓመላህ) እንደ ቢድዓቸው መጠን መለያየት ይገባል። ኩፍር ደረጃ የሚደርሱ ቢድዓዎችን እና ኩፍር ያልሆኑ ቢድዓዎችን እኩል ስታደርግ፣ ሙዓመላቸውንም(አያያዛቸውንም) እኩል ስታደርግ ይህ በደል (ዙልም) ነው። ​ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ — አላህ ይዘንላቸውና — እንዲህ ብለዋል፦ «ከእነዚህ ቢድዓዎች አንዳንዶቹ ከሌሎቹ ይበልጥ ከባድ ናቸው፤ ከሙብተዲዖችም አንዳንዶቹ ሌሎቹ ጋር የሌለ እምነት ይኖራቸዋል» 📚[መጅሙዑ አር-ረሳኢል ወል-መሳኢል፡ [3/16] ደግመውም እንዲህ ብለዋል፦ «በዲን መሠረቶች እና በከላም ጉዳይ ወደ ተከታይ የሚጠጉ ቡድኖች በደረጃዎች መሆናቸውም ሊታወቅ ይገባል፦ ከእነሱ መካከል በታላላቅ(ኡሱሎች) መሠረቶች ሱንናን የተቃረነ አለ። ከእነሱም መካከል ሱንናን የተቃረነው በጥቃቅን ጉዳዮች ብቻ የሆነ አለ»። [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 3/348]።

Open in Telegram
Views389−81%vs avg
Forwards—
Reactions2
Comments—
#10200Audio
Views888−56%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#10199Photo
Views886−56%vs avg
Forwards—
Reactions16
Comments—
#10196Photo
Views1,730−15%vs avg
Forwards—
Reactions5
Comments—
#10194Text
Views2,060+1%vs avg
Forwards—
Reactions19
Comments—
#10192Text
Views2,350+16%vs avg
Forwards—
Reactions43
Comments—
#10190Photo
Views3,380+66%vs avg
Forwards—
Reactions57
Comments—
#10188Text

ጁምዓህን በምን ታጠናቅቃለህ? የጁምዓ ቀን ፀሐይ ወደ መጥለቅ ስትቃረብ፣ አንዳንዶች በዱንያ ጉዳዮች ተጠምደው እጅግ ታላቅ የሆነ ሰዓት ይዘነጋሉ፤ ይህች ሰዓት ደግሞ ከሁሉ በላይ ዱዓ ተቀባይነት ከሚያገኝባቸው አጋጣሚዎች አንዱ ልትሆን ይችላል። የአላህ መልክተኛ ﷺ፦ « ከዐስር በኋላ ባለችው የመጨረሻ ሰዓት ላይ ፈልጓት።» ብለዋል። ሰለፎች የዚህን ሰዓት ዋጋ አውቀውት ነበርና በንቃት ለመጠቀም ይተጉ ነበር። ከሰዒድ ኢብኑ ጁበይር (ረሂመሁላህ) እንደተዘገበው፣ የጁምዓን ዐስር ከሰገዱ በኋላ እስከ ፀሐይ መጥለቅ ድረስ ከቶ አያወሩም ነበር። ታዲያ እነዚህ ሰዎች እነዚህን ሰዓታት እንዴት ከፍ አድርገው እንደሚመለከቱት ተመልከት! አንተስ መሳካት የምትመኘው ስንት ሃጃዎች አሉ? መወገዱን የምትመኘው ስንት ሃዘን አሉ? ማስማር የምትመኘውስ ስንት ወንጀል አለ? እንግዲህ ለምን የጁምዓህን የመጨረሻ ሰዓት ከጌታህ ጋር የምትነጋገርበት ወቅት አታደርገውም? ሂዳያን፣ጤናን የልብ ሰላምንና የጥፋቶች መማሪያን የሀዘኖች መፈረጅን (እፎይታን) ከእርሱ ለምን አትጠይቅም? ለወላጆችህ፣ ቤተሰቦችህ እና ለምትወዳቸው ሰዎች ሁሉ ዱዓ አድርግ። በዱዓህ ላይ አጥብቅ፤ በጌታህም ላይ መልካም ግምት ይኑርህ፤ ምላሽ ለማግኘትም አትቸኩል፤ ምናልባት በጁምዓ ማብቂያ ላይ የምትደረግ አንዲት እውነተኛ ዱዓ ፈጽሞ የማትጠብቀው ታላቅ የእርሱ ችሮታ ምክንያት ሊሆን ይችላል(ይሆናልም) እርግጠኛ ሁኑ።

Open in Telegram
Views3,310+63%vs avg
Forwards—
Reactions27
Comments—
#10185Photo
Views3,110+53%vs avg
Forwards—
Reactions16
Comments—
#10184Photo

እኛ በአላህ ﷻ ጸጋዎች ውስጥ ከጧት እስከ ማታ፣ ከማታም እስከ ጧት የምንገለባበጥ ፍጡሮች ነን። ከእኛም መካከል አንዱ ጤናማ ሆኖ ይነሳል፣ ፍርሃት ሳይሰማው ይመገባል፣ ልቡ በሰላም ተሞልቶ ይጠጣል። ልብሱን አስተካክሎ ይለብሳል፣ ወደ ቤቱ በሰላም ይመላለሳል። ከዕለት ኑሮውና ከእረፍቱ አኳያ አንዷን ቀን ቢያጣ ኖሮ እንኳ የዕለቱን ጸጋ መጠን ባወቀ ነበር። ለአላህም ምስጋና ይገባው! እርግጥ ነው፣ ከጸጋዎች ትምህርት አንዱ፦ መብዛታቸውና ዘላቂነታቸው ልባችን እነሱን ማስተዋል ሊጋርደው መቻሉ ነው። በመሆኑም የሰው  ልጅ አላህ የለገሰውን ጸጋ አድርጎ ይላምደውና፤ ልክ የማይወገድ መብቱ እስኪመስለው ድረስ። እውነቱ ግን የጌታችን የችሮታና የውለታ ውጤት መሆኑ ነው። አላህ ﷻ እንዲህ ይላል፦ {በናንተም ያለው እያንዳንዷ ጸጋ ሁሉ ከአላህ ነው።} [አን-ነሕል፡ 53] ሰው ከጤንነቱ፣ ከጸጥታው ወይም ከእከት ጉርሶ አንዷን ነገር ቢያጣ ኖሮ፤ በሺዎች ከሚቆጠሩ ፀጋዎችን ዓመታት ውስጥ ባላወቀው መልኩ በዚያች የጠፋችበት ሰዓት ብቻ የጸጋውን ትልቅነት ባወቀ ነበር። ለዚህም ነው ነቢዩ ﷺ እንዲህ ያሉት፦ «ሁለት ጸጋዎች ብዙ ሰዎች የተሸወዱባቸው (ማይገነዘቡባቸው) ናቸው፦ ጤና እና ነፃ(ክፍት) ጊዜ።.»»

Open in Telegram
Views3,270+61%vs avg
Forwards—
Reactions29
Comments—