በዚህ ቪዲዮ ላይ እንደምትመለከቱ ኤፍሬም የተናገረውን ነገር መካድ ብቻ ሳይሆን ከዚያም አልፎ እውነታውን የተናገረውን ሰው “ውሸታም” እንደሆነ አስመስሎ ይናገራል.. እናም እንዲህ ካሉ ለቃላቸው ከማይታመኑ ሰዎች ጋር ዲቤት ማድረጉ መልካም መስሎ ስላልተሰማኝ ከዚህ ወንድም ጋር በልሳን ላይ ላደርገው የነበረውን ዲቤት ሰርዤዋለሁ.. ገስት ላይ መጥቶ የመጠየቅ መብቱ ግን የተጠበቀ ነው..
Open in TelegramPosts of ቄርሎሳውያን
ሰዎች “ኃጢአተኛ ነህ” ብለው ቢጠቋቁሙባችሁ ያለፈ ታሪካችሁን እያነሱ በኃጢአት ዓይን ቢመለከቷችሁ እንደ እናንተ የታደለ ሰው የለም ምን ያህል መታደል እንደሆነ ጌታ ያውቃል። ሰዎች እንዲህ ቢያደርጉባችሁ ይህ መገፋት እናንተን ያበረታችኋል ጽድቃችሁ ከፍ ይላል እምነታችሁም ይጨምራል ትሑት ትሆናላችሁ የተደረገላችሁንም ምሕረት ታስባላችሁ ይህን ወደ ጎን ትታችሁ “ሰዎች ገፉኝ” ብላችሁ ብታማርሩ ግን የመጣችሁት ስለ ክርስቶስ ሳይሆን ለሰዎች እንደሆነ ያሳያል
Open in Telegramየዕለቱ ንባባችን ማቴዎስ 25 31-46(ፍፃሜ) “እነሆ ምድሪቱን ባድማ ሊያደርግ …. ጨካኝ ሆኖ በመዓትና በጽኑ ቍጣ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል የሰማይም ከዋክብትና ሠራዊቱ ብርሃናቸውን አይሰጡም ፀሐይም በወጣች ጊዜ ትጨልማለች ጨረቃም በብርሃኑ አያበራም…… በእግዚአብሔር መዓት በጽኑ ቍጣ ቀንም ሰማያትን አ ነ ቃ ን ቃ ለ ሁ : ምድርም ከስፍራዋ ት ና ወ ጣ ለ ች። @stcyril1 ኢሳ 13:9-13
Open in Telegramእነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፤ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች…ሚል 4:2 @stcyril1
Open in Telegram👉 ለሠው ሁሉ ቃሉ ብርሃን ነውና ልባችሁን ለቅዱስ ነንባብ ክፈቱ የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን ማቴዎስ 25 1- 30 @stcyril1
Open in Telegram👉 ለሠው ሁሉ ቃሉ ብርሃን ነውና ልባችሁን ለቅዱስ ነንባብ ክፈቱ የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን ማቴዎስ 24 29 - 51 @stcyril1
Open in Telegram👉 ለሠው ሁሉ ቃሉ ብርሃን ነውና ልባችሁን ለቅዱስ ነንባብ ክፈቱ የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን ማቴዎስ 24 1-28 @stcyril1
Open in Telegramእኸ ሰዎች ትላንትናና ዛሬ ቮይስ ያላደረኩት ስላልተመቸኝ ነው ለዚህም በክርስቶስ ስም ይቅርታ እጠይቃለው እናንተ ምርጦች ነገ ግን ቢፈቅድና ብንኖር አስቀምጣለው 😀
Open in Telegramዛሬ በጌታ ቀን በቅዳሴ 2ኛ ቆሮ 8:1-17 ጳውሎስ የመቄዶንያ አብያተ ክርስቲያናትን ምሳሌ አድርጎ እነርሱ በታላቅ መከራና ድህነት ውስጥ ሆነው እንኳ አስቀድመው ራሳቸውን ለጌታ ሰጥተው በደስታና ከአቅማቸው በላይ ሰጥተዋል ከዚያም እኛም ኦርቶዶክሶች በእምነት፣ በእውቀትና በፍቅር እንደምንበዛ ሁሉ በመስጠትም እንድንበዛ ይመክረናል ለዚህም ምሳሌያችን ክርስቶስ ነው እርሱ ሀብታም ሆኖ ሳለ እኛ በድህነቱ እንድንበለጽግ ለእኛ ሲል ድሃ ሆኗልና ስለዚህም መስጠትም በግዴታ ሳይሆን በፈቃደኝነትና ባለን መጠን መሆን አለበት ዓላማውም ያለው ለሌለው በመስጠት እርስ በርስ እንዲተጋገዙና ክርስቶስ እንዲከብር ነው ይቆየን ዲ/ን ናታኔም
Open in Telegramእኔ እንደግል በዚ ምድር ላይ እናንተን የመሰለ እህት ወንድም ተሰቶኛል እናንተም እንድታስቡ የምፈልገው የኛ አባት ኢየሱስ ትልቅ ስጦታ ሰጥቶናል በምድር እርሱም ቤ/ን ናት እኔ እና እናንተ፣ እርስ በእርስ ብንዋደድ ከሁሉ በላይ ነን፣ ወርቅ የተቀበረበት መሬት ያለው ነገር ግን ስለ ወርቁ ምንም የማያውቅ አንድ ገበሬ ነበር። ያን መሬት በ1000 ብር ለሌላ ሰው ሸጠው….እኛም እንደዚያ ገበሬ የያዝነውን ውድ ስጦታ ሳናውቅ እንዳንተወው እርሱ ይጠብቀን።
Open in Telegramበቲክቶክ አንዳንድ ቪድዮ አየሁ የሀይማኖት ነገር ስንሰራ ድርጅቶች አይፈልጉንም የሚል ጋይስ እንዴት ነው ነገሩ ጭራሽ ሀይማኖትን ይዘን በተመሳሳይ አለም እንድትወደን መፈለግ ምን ማለት ነው ቆም ብለን እናስብ እንጂ እኛ በሀይማኖት ብንፀና እኮ የሚያስፈልገንን የሚያዘጋጅ ጌታ አለን እኮ። በእርሱ ላይ እምነት ቢኖረን ምንም በክርስቶስ እንችላለን እኮ አደራ ሳናስበው ለ2 ጌታ እንዳንገዛ እንጠንቀቅ አለም ክፋቷ ከክርስቶስ ጋር ስንሆን አትወድም ለዛ ነው ዮሐንስ 15:19 ከዓለምስ ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን ይወድ ነበር፤ ነገር ግን እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ እንጂ ከዓለም ስለ አይደላችሁ ስለዚህ ዓለም ይጠላችኋል።
Open in Telegramተወዳጁ ክፍል ነው የዛሬው ይህ ያመለጠው እንደው የተበደለ ነው ማጋነን አይሆንም ሎል 😆 😂 ማቴዎስ 22 1-46 ( ፍፃሜ) @stcyril1
Open in Telegram