Account

Posts of የቅዱሳን ታሪክ

newest first

#4858Photo
Views260−70%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#4848Photo

Forwarded from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ

No text

Open in Telegram
Views476−46%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#4846Text

Forwarded from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ

#ኅዳር_12_ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁን ገናናው መልአክ የቅዱስ ሚካኤል በዓልን ስለ አራት ምክንያት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች ፡፡ የመጀመሪያው ሳጥናኤል ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ክብር ትቶ አምላክነትን በትዕቢቱ በመሻቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ተገፍፎ ወደ ምድር ተጥሎ በቦታውም ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበትን ዕለትን አስባ በታላቅ ድምቀት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታከብረዋለች ፡፡ ሁለተኛው እስራኤላውያን በግብፅ በባርነት ቀንበር ተይዘው በስቃይ መከራ ፀንቶባቸው ሲኖሩ ሳለ ዕንባቸው መንበረ ጸባዖት ደርሶ እግዚአብሔር ሊቀ ነቢያት ሙሴን አሥነስቶ ባሕረ ኤርትራን ከፍሎ ካሻገራቸው በኋላ በሲና በርሐ ለዐርባ ዘመናት ሲጓዙ ቀን በደመና ሌሊቱን በብርሃን እየመራ ያደረሳቸው ቅዱስ ሚካኤል በመሆኑ ይሄንን ዕለት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስባ በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች ፡፡ ሦስተኛው ዱራታዎስንና ሚስቱ ቴዎብስታ የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ነበር ነገር ግን ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉበትን እስኪያጡ ድረስ በቸገራቸው ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በታላቅ መኮንን አምሳል ተገልጾ የታደገበትን ዕለት ቅድስት ቤተ ክርስቲያ በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች ። አራተኛው እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረው ወደ ተስፋይቱ ምድር ከገቡ በኋላ የኢያሪኮን ከተማ ለመውረስ በተዘጋጁበት ወቅት ቅዱስ ሚካኤል የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ ለኢያሱ ወልደ ነዌ በሰው አምሳል በተገለጠ ጊዜ ኢያሱ “ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? ” አለው ፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም “ እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ አሁንም ወደ አንተ መጥቻለሁ ” አለ ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደ እግዚአብሔር የቅዱስ ሚካኤልን ክብር ገልጧል፡፡ ( ኢያ. 5፥13-14 ) ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ እነዚህን በዓላት በማሰብ ኅዳር 12 ቀን በታልቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ ከመላእክት አለቃ ከቅዱስ ሚካኤል ከበዓሉ በረከት ረድኤት ይክፈለን፤ ጥበቃውና አማላጅነቱ አይለየን አሜን ፡፡

Open in Telegram
Views884+1%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#4845Photo

Forwarded from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ

No text

Open in Telegram
Views711−19%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#4843Photo
Views1,290+47%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#4842Text

Forwarded from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ

"በመከራ ውስጥ ለሚጸኑ ሰማዕታት መጠጊያቸው በደሙ ለዋጃት ቤተ ክርስቲያን ክብሯ... እርሱ መድኃኔ ዓለም ነው!" #ጥቅምት_፳፯ ቀን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ነው። ታድያ በዚህች በተቀደሰች ዕለት ማኅሌታውያኑ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ ያሬድ ዜማ "እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን፤ መድኃኒቶሙ ለጻድቃን፤ አሠርገዋ ለምድር በጽጌ ሮማን፤ ስብሐተ ዋሕድ ዘምስለ ምሕረት፤ በመስቀሉ ወበቃሉ፤ አዕበዮሙ ለአበዊነ" እያሉ በምሥጢር ሲዘምሩና ሲያመሰግኑ ያድራሉ። ሊቃውንቱ ሌሊቱን በዜማ ሲቆሙት ያደሩት ይኽ ምስጋና ድንቅ ምሥጢር ያለዉ እና ቤተ ክርስቲያን ለአማንያን ልጆቿ የምታስተላልፋቸዉ ብዙ መልእክቶችን የያዘ ሆኖ እናገኘዋለን። እስኪ ጥቂቶቹን በስሱ እንዳስሳቸዉ፡ ፩, ታሪካዊ አመጣጥና የአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ሥርዓት ይህ በጥቅምት ፳፯ ቀን የሚከበረው የመድኃኔ ዓለም በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ትልቅ ሥፍራ አለው። በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሡት ታላቁ ሊቅና ንጉሥ አፄ ዘርዐ ያዕቆብ መጽሐፈ ሥርዓትንና መጽሐፈ ሚላድን በመድረስ የቤተክርስቲያንን ሥርዓተ አምልኮና ዶግማ አጽንተዋል። ንጉሡ ጌታችን ለዓለም የከፈለውን መሥዋዕትነትና የሰማዕታትን ክብር በማስበብ እንዲሁም ጥንተ ዕለቱ መጋቢት ፳፯ ቀን በጾመ ዐቢይ ይውላልና እንደሚታወቀዉ የዐቢይ ጾም ወቅት ደግሞ የኀዘን እና የልቅሶ እንጂ የደስታ ዘመን ባለመሆኑ በዓል ማክበርንም ስለማይፈቀድ ይህ ዕለት በጥቅምት ወር በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀትና ሥርዓት እንዲከበር የደነገጉበት በመሆኑ በዓሉ ታሪካዊ መሠረቱን ከሊቃውንት አባቶቻችን ትዕዛዛትና ቀኖና ጋር በጥብቅ ያገናኛል። ፪, "ስብሐተ ዋሕድ ዘምስለ ምሕረት" ምስጢረ ሥላሴና መለኮታዊ ቸርነት ሊቃውንቱ "የአንድ ልጅ ክብር ከምሕረት ጋር" ሲሉ የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስን አንድነትና ሦስትነት (ምስጢረ ሥላሴን) እና የሰውን ልጅ የማዳን መለኮታዊ ፈቃድ ይገልጣሉ። ዓለምን ለማዳን አንድያ ልጁን የላከው የአብ ቸርነት፣ በፈቃዱ ሰው ሆኖ ደሙን ያፈሰሰው የወልድ ፍቅር፣ እና ያንን መሥዋዕትነት ለሰው ልጅ የሚያጸናው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በአንድነት ተገልጠዋል። ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በቅዳሴው ላይ "አብ መረጠ፣ ወልድ ሥጋ ሆነ፣ መንፈስ ቅዱስም መጣ (አደረ)" እንዳለ፣ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በመስቀል ላይ የፈጸመው የማዳን ሥራ የሥላሴን ዘላለማዊ የምሕረት ቃልኪዳን ለፍጥረት ሁሉ ያበሠረበት ነው። ይህ ቸርነት በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ላይ፡- "ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ... እንደ ምሕረቱ መጠን አዳነን" ቲቶ፡ ፫፥፬-፭ ተብሎ እንደተጻፈው ያለ እኛ ጽድቅ በነፃ የተሰጠን መለኮታዊ ስጦታ ነው። ፫, የሮማን አበባ ምስጢርና ከዘመነ ጽጌ ጋር ያለው ትስስር በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስቲያናችን የምትገኘው በዘመነ ጽጌ (የአበባ ወራት) ውስጥ በመሆኑ የሊቃውንቱ "ምድርን በሮማን አበባ አስጌጣት" የሚለው ምስክርነት ጥልቅ ትርጉም ይኖረዋል። ሮማን ውጫዊ ቅርፊቱ ሻካራና እሾሃማ (የመከራና የስደት ምሳሌ) ቢሆንም ውስጡ ግን በብዙ ቀይና ጣፋጭ ፍሬዎች የተሞላ ነው። ይህ በዘመነ ጽጌ ስደቷንና መከራዋን የምናስባት የድንግል ማርያም (የጽጌ ማርያም) እና የልጇ የመድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ጌታችን በመስቀል ላይ የተቀበለው መከራና የፈሰሰው ደሙ ውጫዊ እይታው አሰቃቂ ቢሆንም ውስጣዊ ምስጢሩ ግን ለዓለም ሕይወትንና ድኅነትን ያስገኘ መለኮታዊ ፍቅር ነው። ቅዱስ ጳውሎስ "በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ..." ሐዋ፡ ፳፥፳፰ በማለት እንደገለጠው ክርስቲያኖች የተከፈለላቸውን ይህንን ታላቅ የደም ዋጋ ሊረዱና ሕይወታቸውን በቅድስና ሊጠብቁ ይገባል። የዳንበትን ዋጋ ማቃለል ሳይሆን በመስቀሉ የተሰጠንን ነፃነት በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ መታተም መገንዘብ ክርስትናችንን መጠበቅ ማለት ነው። ፬, ስለ ሃይማኖታቸው መከራ ለሚቀበሉት የታላቅ ቃልኪዳን በዓል ይህ በዓል ዛሬ ላይ ሆነን ስንመለከተው ለስሙ አጠራርና ለቀናች ሃይማኖታቸው ሲሉ መከራ ለሚቀበሉ፣ ከቀያቸው ለሚሰደዱና በሰማዕትነት ለሚታረዱ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ትልቅ መጽናኛና ትርጉም አለው። ሊቃውንቱ "እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን፤ መድኃኒቶሙ ለጻድቃን" ይላሉ። ቅዱሳንና ሰማዕታት በመከራ ውስጥ ሆነው ለሃይማኖታቸው የጸኑት መድኃኔዓለም ክብራቸውና አዳኛቸው ስለሆነ ነው። ጌታችን በወንጌል፡- "ስለ ስሜ በሰው ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል" ማቴ፡ ፲፥፳፪ እንዳለ ዛሬም ስለ ሃይማኖታቸው ዋጋ ለሚከፍሉ ቅዱሳን ሁሉ መድኃኔ ዓለም መጠጊያቸውና የሰማዕትነት አክሊላቸው ነው። ይህ ዕለት የእነርሱን መከራና ስደት የሚወክል በመጨረሻም በመስቀሉ ድል አድራጊነት የሚያሻግር ታላቅ የተስፋ በዓል ነው። ፭, "በመስቀሉ ወበቃሉ..." የቅዱሳን አባቶቻችን ታላቅነትና ክብር የተመሠረተው በሁለት ምሰሶዎች ላይ ነው፤ እነርሱም፡- የእግዚአብሔር ሕይወት ሰጪ የሆነዉ "ቃል" እና መሥዋዕትነት የተከፈለበት "መስቀል" ናቸው። ሊቁ ቅዱስ አትናቴዎስ፡- "እግዚአብሔር ሰው የሆነው እኛን አምላክ ያደርገን (የጸጋ አማልክት ያደርገን) ዘንድ ነው" እንዳለው አባቶቻችን በቃሉና በመስቀሉ ከፍ ከፍ ያሉበትን ይህንን አሰር እኛም ልንከተለው ይገባል። ክርስቲያን መሆን ማለት መከራን አለመፍራት፣ የተከፈለልንን ዋጋ ማወቅና በቅድስና መኖር ማለት ነው። መድኃኔ ዓለም አምላካችን ስለ ስሙ መከራ ለሚቀበሉ ወገኖቻችን ጽናቱንና መጽናናቱን ይስጥልን፤ ሀገራችንን በደሙ ዋጋ ይጠብቅልን። የመድኃኔ ዓለም ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎትና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን!🤲 ክቡራን እንኳን ለታላቁ የመዳናችን ቀን በሰላም አደረሳችሁ መልካም በዓል ይሁንልን🙏

Open in Telegram
Views1,470+67%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#4841Photo

Forwarded from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ

No text

Open in Telegram
Views898+2%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#4840Text

Forwarded from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ

መ ድ ኃ ኔ ዓ ለ ም #ጥቅምት_27 ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የመድኃኔ ዓለምን በዓል በደማቁ ታከብራለች ይህም የለውጥ በዓል ነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ሥጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ነው። ነገር ግን እንደዛሬዉ በግለሰቦች ፈቃድ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሳይጣስ በፊት ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች መጋቢት 27 ቀን ዐቢይ ጾም ላይ ስለሚውል በዐቢይ ጾም ደግሞ ኀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ በዓል ማክበርም ስለማይፈቀድ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን ከድሆች ጋር እንድናከብረው በቤተ ክርስቲያን ሥርዓትን ሠርተውልን ነበር። በሞቱ ሞታችንን ያስወገደ፣ በኀዘኑ ኀዘናችንን ያራቀ በለቅሶው ዕንባችንን ያበሰ፣ ከወደቅንበት ያነሳን፣ ጠላታችንን ከመንገዳችን በመስቀሉ ጠርቆ ያስወገደ፣ በደሙ የቀደሰን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በአይሁድ ተንኮልና ክፋት በሐሰት ተወንጅሎ 6666 ጊዜ ተገርፎ 41 ጊዜ በብረት ዘንግ አናቱን ተመቷል። በምራቁ ዕውር የሚያበራ ምራቅ ተተፋበት ሥጋው አልቆ ደሙ ፈሶ አጥንቱ ይቆጠር ነበር ስለ ሁላችንም እርሱ ታመመ ስለሁላችን እርሱ ሞተ መስቀል ተሸክሞ በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ወድቆ ተነሳ። አይሁድ በወንጀለኛው በርባን ፋንታ ክርስቶስ ይሰቀል በርባን ይፈታ በማለት መድኃኒታቸውን ሰቀሉት ይሆን ዘንድ ግድ ነውና በቀራኒዮ አደባባይ በማዕከለ ምድር የዓለም መድኃኒት ተሰቀለ። አይሁድ በውስጣቸው ባደረ ጠላት ዲያቢሎስ ምክንያት ክፋት ጭካኔያቸው የበዛ ሆነ አዳኝ መድኃኒት ህይወት ፍቅር ተስፋ የሆነውን ክርስቶስ በክፋት ተነሳስተው ቢሰቅሉትም ለእኛ ግን መዳን ሆነልን ሥጋውን በልተን ደሙን ጠጥተን የምንድን ሆንን። በክርስቶስ ሞት ሞታችን ተወግዶ ህይወት አገኘን በነፃነት እንኖር ዘንድ ነፃ አወጣን ተስፋችን መታመኛችን ኃይላችን እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር የሆነ በመስቀል ሞት ነፃነታችንን አውጆ የዲያቢሎስ ክፋትና ተንኮል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አስወግዶ #ተፈፀመ በማለት ነፍሱን ሰጠ ዛሬ በቀደመው ክብሩ በዙፋኑ አለ ለማማለድ ሳይሆን ለመፍረድ አማላጅነት የአገልጋዮቹ የቅዱሳን ተግባር ነውና። ጌታ : ሆይ : ወሰን : ስለሌለው : ፍቅርህ : እናመሰግንሃለን። እንኳን አደረሳችሁ ክቡራን🙏

Open in Telegram
Views1,090+24%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—
#4839Photo

Forwarded from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ

No text

Open in Telegram
Views906+3%vs avg
Forwards—
Reactions—
Comments—